Sunday, 10 April 2016

Hiber Radio : ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ኤርትራን ለመውረር መዘጋጀታቸውን ነግረውኛል ሲሉ የአውሮፓ ህብረት ሹሙ ጅያኒ ፒቲላ ገለጹ


አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ጅያኒ ፒቲላ እና አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ
በታምሩ ገዳ (ህብር ሬዲዮ -ላስ ቬጋስ)
የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስታቸው በጎረቤት አገር በኤርትራ ላይ የወረራ ዘመቻ ሊያደርግ መዘጋጀቱን እና የአውሮፓ ህብረት ለኤርትራ ያለውን ቀና አመለካከት ካልለወጠ /ሁኔታዎች ግፍተው ከመጡ ኢትዮጵያ የአወሮፓ ጎዳናዎችን በሰደተኞች እንደምታጨናንቃቸው አቶ ሃይለማሪያም ለአንድ የአውሮፓ ህብረት ከፈተኛ የፓርላማ አባል ሰሞኑን ማስጠንቀቃቸው ተገለጸ።
ይህ “የማሰጠንቀቂያ” እና የማስፈራሪያ” ገለጻ የተደረገላቸው ሰሞኑን ከ አውሮፓ ህብረት መናገሻ ከተማ ቤልጂዩም/ ብራስለስ ወደ አዲስ አበባ ለሰራ ጉብኘት ያቀኑት በህብረቱ የሶሻሊስት እና የዲሞክራት ፓርቲ አባልት ጥምረት ፕሬዜዳንት የሆኑት ጅያኒ ፒቲላ ሲሆኑ የፓርላማው አባል እና የፓርቲው መሪ በአ/አ ቆይታቸው ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳልኝ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው የጠቀሰው ዘ ሁፊንግ ቶን ፖስት ድህረ ገጽ በእሮብ ሚያዚያ 6 / 2016 እኤአ እትሙ ሲያብራራው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካክል ባለፈው 1998 -2000 እኤአ ከተካሔደው ደም አፋስሽ የድንበር ይገባኛል ግጭት በሁዋላ የዘለቀው የውጥረት ደመና ዛሬም ማንጃበቡን የተናገሩት ሚስተር ጅያኒ “የተባበሩት መንግስትታት ያስተላለፈው ወሳኔን አሻፈረኝ ያለቸው አዲስ አበባ የመፍትሄ ሃሳቦች እንድታቀርብ ስትጠየቅ በአስመራ ያለው መንግስት አምባ ገነን በመሆኑ ለዚህም መፍትሄው የኤርትራ መንግስትን ማስወገድ እና ይህንንም ለማድረግ/ኤርትራን ለመውረር ተዘጋጅተናል። በለውናል ሲሉ የአውሮፓው ህብረት የሕዝብ እንደራሴው ፣የሶሻሊስት እና የዲሞክራሲ ፓርቲ ሹሙ ለዜናው ዘገባው በሰልክ ገልጸውለታል።
ሚስተር ጅያኒ ለጀርመን ራዲዮ የአማሪኛው ክፍለ ጊዜ የብራስልሱ ወኪል ይህንኑ ሁኔታ በተመለከተ ሲናገሩ ” የአወሮፓ ህብረት ለ ኤርትራ የሚያደረገው እርዳታን አቁሟል ።እርዳታው ከቀጠለ ግን ኢትዮጵያ በኤርትራ መንግስት ላይ ወረራ ለማድረግ መዘጋጀቷን እና በግዛቷ (በኢትዮጵያ ) ውስጥ የሚገኙ በ 10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኤርትራዊያን ሰደተኞችን ወደ ጣሊያን እና ወደ አውሮፓ አባል አገራት እንዲጎርፉ እንደምታደርጋቸው ዝተዋል። “ሲሉ ሚስተር ጅያኒ ለዘጋቢው ተናግረዋል ። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ዛሬ ድርስ ያላቆመው “የገደብ የለሹ” ወታደራዊ ስልጠና የሚያደርገው “ኢትዮጵያ ልትወረን ሰለምትችል እራሳችንን በቅድሚያ ማዘጋጀት አለብን።” የሚል አቋም እንዳለው በሆፊንግተን ፖስት ላይ ተገልጿል። ከዚሁ ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ወደ ስልጠና ማእከል ሊወስዱ ከነበሩ ወጣት ኤርትራዊያኖች መካከል ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያለታወቀ ምልምሎች ከ መኪና ላይ በመወረድ ለመጥፋት ሲሞክሩ አደጋ እንደደረሰባቸው የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ መገናኛ ብዙሃናትን ዋቢ ያደረገው የእንግሊዙ (ቢቢሲ )በሚያዚያ 6/2016 እኤአ ዘግቦታል። የኤርትራው የማስታወቂያ ሚ/ር አቶ የማነ ገ/መስቀል በበኩላቸው በወዳጆች መገናኛው ቲውተር አካውንታቸው”ለብሔራዊ አገልግሎት ወደ ስልጠና ማእከል በወታደራዊ ካሚዮን ሲጓዙ ከነበሩ መካከል ሁለት ምልምሎች አስመራ ከተማ ውስጥ ከመኪና ላይ ለመዝለል ሲሞክሩ ከደረሰባቸው ጉዳት ሳቢያ ሞተዋል።” በማለት የወጣቶቹ አሟሟት በራሳቸው ውስኔ እንደሆነ እና የሻቢያ መንግስት ታጣቂዎች ገደለዋች ዋል ተብሎ በአንዳንድ ሚዲያች የቀረበው ዘገባን አቶ የማነ ለማስተባበል ሞክረዋል።
የአቶ ሃይለማሪያም ሰሞነኛ “ኤርትራን ለመውረር ተዘጋጅተናል “ ዛቻ አንዳንድ ወገኖች በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተከሰተውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት/ሕዝባዊ ቁጣን አቅጣጫን ለማስቀየር ፣አሊያም ከኤርትራ ጋር የዘለቀው “ጦርነት የለም፣ ሰላም የለም / No war , No peace “የሚለው አቀራረብን ለማጥበቅ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይገምታሉ። “የኤርትራ ሰደተኞችን ወደ አውሮፓ እንጎርፋለን ” የሚለው የአቶ ሃይለማሪያም ሰሞነኛ ዛቻን በተመለከተ የቀደሞው የሊቢያው አምባገነን መሪ ኮ/ሌ መሃመድ ጋዳፊ በምእራባዊያን በተለይ ደግሞ አውሮፓዎች ባደረጉት ልግስና ሳቢያ ተቃዋሚዎችን በማስታጠቅ ሲዋጓቸው ጋዳፊ ”አርዳታችሁን ካላቆማችሁ በግዛቴ የሚገኙት በ10ሽዎች የሚቆጠሩ ህገ ዋጥ ሰደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዲ ጎርፉ አደርጋለሁ።” በማለት መዛታቸው ይታወሳል። ጋዳፊም ተዋርደው ከስልጣን መውረዳቸው አይዘነጋም ፣የአውሮፓ ከተሞችም ዛሬ በመጠነ ሰፊ የስድተኞች ጎርፍ እየተጥለቀለቁ ይገኛሉ። የኤርትራ መንግስት ከ ኢትዮጵያ በኩል ሰለ ቀረበበት ሰሞነኛው “የጦርነት ነጋሪት” ዙሪያ በተመለከተ አስከ አሁን ድረስ የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።
ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች እና ኤርትራዊያኖች በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የተገነባው “የጥላቻ ግንብን” ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመናድ እና በምትኩ ዘለቂታዊ ሰላም እና መረጋጋት ለመፍጠር ከተፈለገ ሁለቱ አምባገነኖች ( የ አ/አው ሕዋት/ኢሕ አዲግ እና የአስመራው አቻው ሻቢያን) ማስወገድ ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉ ይደመጣሉ።
የአውሮፓ የፓርላማ አባላቱ በአዲስ አበባ ቆይታቸው የኢሕ አዲግ መንግስት በዜጎቹ በተለይ በኦሮሚያ ወስጥ እየፈጸመ ያለውን የሰበዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ያሳደረደርባችው ስጋትን እና ሕብርቱም በቅርቡ በኢሕ አዲግ መንግስት ላይ ሰለ ወሰድው እርምጃ ሳይገልጹ አላለፉም
ህብር ሬድዮን በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Friday, 8 April 2016

ብቸኛው የትግራይ ወያኔ አገዛዝ ተግባር በኢትዮጵያ ላይ (ዶ/ር ደጀኔ አለማየሁ)

በዶ/ር ደጀኔ አለማየሁ ላቀው*
አንድ ነገር ከተለያዩ ነገሮች የዉህደት ዉጤት መሆኑን የምናዉቀው እነዚያ በቀመሩ ላይ የተቀመጡት የተለያዩ ነገሮች በተፈጥሮአዊ ባህሪያቸው በውህደቱ ዉስጥ ተግባራዊ የሆነ መንስኤአዊና ክትትልነት ያለው ከዉጭ ከምናየው መጠናዊ የቅምር መሰረት ስራ ሲሰሩ ነው፣ ያ ካልሆነ ግን ዉህደቱ ትክክለኛ ጥምረት ሳይሆን ለይስሙላ ብቻ ያሉ ግን በተግባር የሌሉና ስብስቡም የአንድ ነገር ስብስብ ብቻ ነው። ለምሳሌ የምንጠጣው ዉሃ የ 2 እጅ ሃይድሮጅን እና 1 እጅ ኦክስጅን ዉህደት ዉጤት ነው እነዚህ ሁለት ነገሮች ተፈላጊዉን የንጥረ ነገር ስራ ይሰራሉ፣ ከሁለቱ ነገሮች ትንሽም የሆነ ክፍል ከጎደለ ዉሃ የለም፣ ስለዚህ ነገሩ ኦክሲጅን ነው ወይም ሃይድሮጅን።Ethiopia, TPLF officials
በኢትዮጵያ ዉስጥ ላለፉት 25 አመታት የትግራይ ወያኔ ቡድን ከደደቢት ዋሻ እንደ አዉሬ በርግጎ ወጥቶ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተከሰተው ታሪካዊ አደጋና አጋጣሚ ስልጣን ላይ ወጥቶ ሃገራችን ኢትዮጵያን አንቆ ይዞ ምንም አይነት ኢትዮጵያዊ ይሉኝታ በሌለውና ከቦኒቶ ሞሶሎኒ በበለጠ ሁኔታ መሰረቷን በማናጋትና ማንነቷን እያፈረሰ፣ ህዝቦቿን እጅግ በጣም ኋላ ቀር በሆነና የአለም ህዝቦች ጥለዉት በሄዱት አሳፋሪ የጎሳ ድሪቶ እርስ በርሳቸው እያናቆረና እያገዳደለ ብቸኛው ተጠቃሚ አውሬ ሆኖ ለመኖር በየመንደሩ ለቃቅሞ ለሱ የሚያገለግሉ እንስሳዊ ፍላጎት ብቻ ያላቸዉን ግለሰቦች የጥቃቱ ሰለባ በሆነበት ህዝብ ዉስጥ መልምሎ የስልጣን ተጋሪ ድርጅቶች ናቸው ብሎ ለይስሙላ፣ በተግባር ግን ወያኔ ብቻ የሚመራውን አገር አቀፍ የዝርፊያ ድርጅቱን በየቦታው መሰረተ።
እነዚህ ግለሰቦች ያንተ ተወካዮች ናቸው እከሌ የሚባል ያንተን ጎሳ ስም የያዘ ቡድን ታርጋ ተሰጥቷቸዋል የናንተን አባልነት ይጠይቃሉ፣እናንተም ችግራችሁን ለነዚህ ተወካዮቻችሁ ታቀርባላችሁ በዚያም መሰረት መፍትሄወች ይፈለጋሉ እያለ፣ ለዚህ ሃገራዊ ወንጀል ተባባሪ እንዲሆኑ የሰበሰባቸዉን ግለሰቦችም የፈለጉትን ነገር እንዲዘርፉ ማስቻል፣በዚህም እጅግ መጠን ያጣ ሃገራዊ ስሜት በሌለው መልኩ የህገወጥነትና ዘራፊነት ስርአት ተመስርቶና ተንደላቆ ለመኖር የወያኔን ወንጀል በመደበቅና በፊርማቸውም ተባባሪ በመሆን እስካሁን ድረስ አሉ።
ከነዚህ የወያኔ የይስሙላ ድርጅቶች ዉስጥ አንደኛው የእንስሳ ስብስብ አማራዉን እንዲወክል ብአዴን የሚል ታርጋ ተሰጥቶት የአማራ ህዝብ በብዛት በሚኖርበት አካባቢ ቢሮ ይዞ ያለው ቡድን ነው። ይህ ቡድን ለአማራ ህዝቦች ተወካይና ተቆርቋሪ ሳይሆነ የአማራን ህዝብ ቤቱ ዉስጥ ሆኖ ለማሸበር፣ በጎጥ ለማበጣበጥና ባልና ሚስትን ለማገዳደል፣ ለማፈን፣ ለማሰርና ለመግደል፣ የወያኔን ወንጀል ህዝቡ እንዳያይ፣ አይንህን ጨፍን ዝም ብለህ ኑር እንዲል ተልኮ የተሰጠው የትግራይ ወያኔ የመዋጊያ ድሪቶ ነው ። በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል በጎንደር አማራው በጎሳው ብቻ ይህ ነው የሚባል ታይቶ የማይታወቅ ሰብአዊና ማህበራዊ ጥቃት ሲፈጸምበት አንድም ነገር ተናግሮ የማያውቅ ግን ለዚያ ወንጀል ተባባሪ ሆኖ ከወያኔ ጋር የሚጨፍርና ይባስም ብሎ የሚሳደብ ድርጅት ፣ የጎንደር አካል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ህገወጥ በሆነ መልኩ ማንነቱ ተጨፍልቆ፣ መሬቱም ከጎንደር ተለይቶ ወደ ትግራይ ተወስዶ ለሁልት አስርተ አመአታት በበደል፣ በስቃይ፣ በመገደልና በመሰደድ ፣ ከዚአም የተረፉት ቋንቋቸውን አትናገሩ ትግርኛ ቋንቋ ተማሩ እየተባሉ ኢሰብአዊ በሆነ አያያዝ እየኖሩ ከነሱ ጋር እየኖረ ምንም ያላለ ድርጅት ነው።
ይህ የድሪቶ ድርጅት ከጎናቸው እያለ የናንተ ተወካይ ነኝ እያለ ፣ የትግራይ ወያኔ የተከዜን ወንዝ እያቋረጠ በየቀኑ ጎንደር ዉስጥ ጎንደርን የማፍረስ ስብሰባ እያካሄደ፣ ምንም አይነት የአማራዉን ህዝብ ተወካይነንት የያዘ ስሜት ሳያስይና ተግባር ሳይፈጽም ግን ለወያኔ የተቀጠረ የደህንነትና የጥበቃ ስራ ብቻ ለመስራት እንደሚኖር ህዝቡ አይቷል አውቋልም።አንድም ጊዜ የትግራይን ወያኔ ለምንድነው ይህ ህዝብ አማራ ነኝ እያለ ነው፣ እኛም እናውቃለን፣ ይህ ህዝብ በታሪክም በስነ ልቦናም ሁልጊዜ የጎንደር አካል እንጅ የትግራይ ሆኖ አያዉቅምና ትክክለኛ የሆነ መፍትሄ መፈለግ አለብን፣ ማንነታቸው መመለስ አለበት፣ መሬቱም ወደጎንደር መመለስ አለበት እንደማለት ፋንታ፤ አይ ዝም በሉ፣ እኛ የምንወያየው ስለምትኖሩባት መንደርና አካባቢ ብቻ ነው፣ ስለወልቃይት ጠገዴ አታንሱ መልስም የለንም እያለ (እዉነት ነው መልስም የላቸዉም ምክንያቱም የወያኔ የቁጭበሉ የጎሳ ታርጋ ያዞች ናቸዋ) የህዝቡን ቁጭትና ብሶት በማፈን ስራ ላይ ተሰማርቶ ያለ የወያኔ ተወካይ መሆኑን ነው። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ይህን የረጅም ጊዜ በደሉን ለማሰማት በየቦታው ቢጮህም ሰሚ አጥቶ አሁን በመጨረሻ ብቸኛው አዲስ አበባ ላይ ያለው የትግራይ ወያኔ (ግን ብሄራዊ) ሸንጎ ጥያቄአችሁን የትግራይ ቡድን ነው የሚመለከተው ብሎ ወደመንደሩ ተመልሳችሁ ሂዱ ብሎ ወሰነባቸው፣ ማለትም እናተ የትግራይ አካል ናችሁ፣ ችግራችሁንም እኔ ለማስተዳድረው ለክልላዊ መንግስታችሁ ጠይቁ እዚህ የናንተን ችግር የምናይበት(የማይበት) ምክንያት የለም ነው።
ይህ ፍርድ የሚያረጋግጠው አንድ ነገር ብቻ ነው አዲስ አበባ ያለው ሸንጎ የትግራይ ወያኔ ያቋቋመው የሌሎች ጎሳወች ውክልና በታርጋ ብቻ የሆነበት ወያኔ ብቻ የሚቆጣጠረውና የሚያዘው የሌባ ሸንጎ መሆኑን ነው። እዚህም እኔ ነኝ እዚያም እኔ ነኝ ስለዚህ ወደዚያ እኔ በስሜና በተግባሬ በግልጽ በምታወቅበት ቦታ ሂዱ ነው ያለው። ማንም ሰው ያውቀዋል ከሌባ ምንም ፍትህ አይጠበቅም፤ ፍትህ መስረቅን ማጭበረበርን እንደዋነኛ የመተዳደሪያ ባህሪ አድርጎ ከያዘ ሰው ወይም ድርጅት መጠበቅ የዋህነት ነው፣ ፍትህ የእዉነተኛ ሰው ወይም ድርጅት የእዉነታዊ ባህሪ ተግባራዊ ነጸብራቅ ነችና።
ጀግናው የጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ ግን ማንነታችን፣ ርስታችን ፣ የተወለድንበትን, ያደግንበትን, አያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችን ጠብቀው ያቆዩልንን ክልል በዚህ የወያኔ ቁጭ በሉ ሸንጎ ድለላ ሳንዘናጋ ለማስከበርና ለማስመለስ ትግሉን በበለጠና ዉስብስብ በሆነ ስልታዊ መልኩ መቀጠል አለብን። የትግራይ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ የነበሩት መንገሻ ስዩም እንኳን በቅርቡ የትግራይ ወሰን ተከዜ እንደሆነ እራሳቸዉም እንደሚያውቁ ፣ ከአባታቸውም ከዚያ በፊትም ከቅድመ አያቶቻቸውና በታሪክም የሚያውቁት ይህንኑ እንደሆነ ተናግረዋል ፣ ወያኔ በቅሌት የሰዉን እርስት ሰርቆ፣ አይነጋም መስሏት ከምትተኛበት ላይ … እንደሚባለው የሰረቀዉን መሬት ይዞ ለመቅረትና ለማወናበድ የፈለገዉን አፈር ቢቆፍር ታሪክንና እዉነትን ማዳፈን አልቻለም፣ አይችልምም ። የኢትዮጵያ ታሪክ በጽሁፍ ላይ መስፈር ከጀመረበት፣ የሰው ልጅ የመሬትን ገጸ ባህሪ ካርታ ላይ በመዛግብት ማዋል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የምናዉቀውና ሁሉም የአለም ህዝብ ከታሪካዊ ሙዚየማቸው የሚያዩት ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የጎንደር አካል እንደነበረና፣ ጎንደርና ትግራይ አዋሳኝ የሆኑ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደነበሩ፣ ወሰናቸዉም አንጋፋው የተፈጥሮው ወንዝ ተከዜ መሆኑን ብቻ ነው።
የትግራይ ወያኔ ቡድን ይሀንን ዘላለማዊ ማህበራዊና ታሪካዊ እዉነታን ነው በጉልበትና በማን አለብኝነት አፍርሶ አሁንም ጥፋቱን ከማመንና ይቅርታ ከመጠይቅ ይልቅ በጉልበት የሰዉን ንብረት እንደሰረቁ ልኑር የሚለው፤ አንድ ሰው ወንጀል ፈጽሞ ጤነኛ የሆነ ዘላቂነት ያለው ግኑኙነት, ወንጀል ከተፈጸመበት አካል ጋር ሊመሰርት አይችልም ፤ ያ የሚሆነው መጀመሪያ ወንጀል መፈጸሙን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ ሲችልና ተበዳዩ ክፍል ይቅርታዉን አምኖበት ሲቀበለው፣ ከዚያም የፈጸመዉን ወንጀል አምኖ መመለስ፣ ካልሆነ ደግም ካሳ መክፈል ሲችል ነው። ወያኔ ግን የፈለጉትን ወንጀል እየሰራሁ ከማንም የኢትዮጵያ ህዝብ ጎረቤት ሆኘ መኖር እችላለሁ ስለሆነ የኑሮው ፍልስፍና፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ፍጹም ማሰብ የተሳነውን የእንስሳ ቡድን በተናጠል ሳይሆን በተባበረ መልኩ ማጥፋት አማራጭ የሌለው ተግባሩ መሆን አለበት። ዘመናዊ ለሆነ ሰው የአንድ አመት ነጻነት ከእድሜ ልክ ባርነት እጅግ እጅግ ይሻላል። አሜሪካ ዉስጥ የሰዉን ማንነትና የመኖርን ትርጉም ዋጋ የሚያሰጠው ፣ እንደ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና የምንወደው አንድ አባባል አለ ” ነጻነቴን ስጠኝ ወይም ሞቴን” ነጻነት ከሁሉም በላይ እንደሆነና ፣ ዝም ብሎ ህሊናን ሽጦ ግኡዛዊ ህይዎትን ለመግፋትና ሆድን ለመሙላት ብቻ መኖር ግን የእንስሳ ብቸኛው ፍላጎትም ችሎታም ነው።
ጸሃፊው በጆን ታይለር ኮሙኒቲ ኮለጅ ቨርጅኒያ ሀገረግዛት አሜሪካ የሂሳብ አድጃንክት ፕሮፌሰር ናቸው                                                         Posted by: ecadforum

ሰበር ዜና — ወያኔ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 29 በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ በዳንሻ ከተማ የጦርነት አዋጅ መርዙን ሲረጭ አምሽቷል

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር ኢትዮጵያ
መጋቢት 29 /2008 አ/ም
በዛሬው  ቀን ወያኔ የዳንሻን ወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በነገው ቀን ስብሰባ ካልወጡ ከባድ እርምጃ  እንደሚወስድ  አስጠነቀቀ። ነገ  መጋቢት 30  ሱቆች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣብያና ክሊኒኮችና ሁሉም  የሲቪል  ሰርቪስ  ቢሮዎች  ካላንደር  ሳይዘጋቸው በእነርሱ  ፈቃድ ብቻ  ነገ  እንዲዘጉ  ትእዛዝ  ካስተላለፉ  ብሗላ  በያንዳንድዋ  የዳንሻ  ከተማ ጥግ ልዩ  ልዩ የስድብና  ማስፈራሪያ  የተሞሉበት ትምክህታዊና ውዳቂ  መፈክሮች  የተጻፈባቸው  ጨርቆችና  አርቴፊሻል ላይቶች ዲኮር  አድርጎ “አንድም  የዳንሻ  ሰው  በነገው  ቀን በተዘጋጀው ስብሰባእንዳይቀር!”  በማለት  በተለየ  ሁኔታ ደግሞ  አንድም  በዳንሻ  የሚገኙትን   የወልቃይት  ጠገዴ ወጣቶች ሞባይሎቻችሁ ከቤቶቻችሁ  ጥላችሁ በስብሰባው  ባትገኙ ውርድ ከራሴ!!!”  በማለት በሶስት  መኪኖች  ሞንታርቦዎቹ  እስኪቀደዱ  ድረስ  እያስጠነቀቀ  እስከዚህችው  እስከ ምሽቱ 4:45 ከተማዋን እያመሳት ይገኛል። ውድ ወገኖቻችን እየደረሰብን ያለውን መከራና ስቃይ እባካችሁ ተረዱልን።
በሶስት  ሞንታርቦዎች  ጀሮአችንን  የሚያደነቁሩን  አንሷቸው  ፖሊሶችና ካድሬዎች  በአካል መስጊድ ድረስ ሄደው ሙስሊሞች እየሰገዱ ሳለ ምንም ኣይነት ስቅታ ሳይሰማቸው አጨብጭበው ካስቆሟቸው ብሗላ ነገ ከበሯቸውናየበአል ልብሳቸው ለብሰው እንዲወጡ እያስፈራሩ ሲናገሩዋቸው የመስጊዱን  በር  ከሚዘጋ  ከአንዱ ሙስሊም  ወገናችን ውጭ ሁሉም  በመስጊድ ሲሰግዱ የነበሩት  ሙስሊም  ወገኖቻችን  በንዴት ስግደታቸውን ሳይጨርሱ ፖሊሶቹንና ካድሬዎቹን ሳያናግሩዋቸው እዛው የመስጊዱ  ግቢ  ውስጥ ጥለዋቸው ሄደዋል።
ለህዝበ-ክርስቲያኑ ደግሞ  በከተማ  በሚዞሩት ሞንታርቦ  ሀፍረት ሳይሰማቸው የቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ  አቡነአረጋዊ የቤተ ክርስቲያን ሁሉም አገልጋዮች ደግሞ የቤተ- ክህነት ልብሳቸውን  ለብሰውና  ታቦቱን  ተሸክመው የዝማሬ  መሳሪውያዎች  ሁሉ  ይዘው  እንዲወጡ  በእብሪት  ከከባድ  ማስጠንቀቂያ  ጭምር ጥሪ  አቅርበዋል።  ይህ  በእንዲህ  እንዳለ ተማሪዎቹ  ዩንፎርማቸውን  ለብሰውና  ደብተሮቻቸውን  ይዘው  በአንድ  በኩል፣ ህዝቡ ደግሞ በሌላ በኩል ሆነው በአራት ቡድን  ሆነው  ለሰላማዊ ሰልፍ መውጣት እንዳለባቸው በማሳወቅ በሞንታርቦ  እየተናገሩት እናለ ከሆነ በባለፈው በዳንሻ  ከተማ  የተፈጠረው  ረብሻ  የጸረሰላም  ሃይሎች  በመሀላችንተገኝተው የሰሩት ተንኮል ነው እንጂ  እኛን  የዳንሻን  ህዝብ  አይወክልም!  የእኛ  ድምጽ  አይደለም!!  የጸረሰላምሃይሎች ለፍርድ ይቅረቡልን!  መንግስት  ከኣማራ  ክልል የተላኩ ትምክህተኞችን  ልክ ያስገባልን! መንግስትትዕግስቱ  በዝቶ  በትምክህተኛ  ሃይሎች  ትግሬነታችን ተነጥቆ  ያልጠየቅነውን  አማራነት በግድ  ሲጫንብን  ለምን ዝም ይላል? እያላችሁ ቀሳውስት በአንድ በኩል፣ ሼኮች በሌላ በኩል፣ ተማሪዎችና መላው ህዝብም እንዲሁነገ ጧት ይፋ በሚሆንላችሁ  ቡድን ሆናቹህ በየራሳችሁ ቡድን መናገር አለባችሁ” ብለዋል። ይህ ሳያደርግ የሚቀር ጥሪየተደረገለት አካል ቢኖር ግን የጸረሰላም ሃይሎች ተባባሪ እንደመሆኑ መጠን ከነገ ጀምሮ ለሚደርስበትበህልውናው ያነጣጠረ ጥቃት ሃላፊነቱ በራሱ ይወስዳል ብለዋል። “ይህን  የማያደርግ  ሰው የትግራይ  ህዝብ  ጠላት ብቻ ሳይሆን  እንዲሁም  የኢትዮጵያ  የመለስ  ራእይ የሚያደናቅፍ  የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት እንደመሆኑ መጠን ለዚህም መንግስት ሃላፊነት አይወስድም” በማለት ስጋታችንን ከፍ እንዲል በማድረግ ከባድ ጫና በህዝባችን ላይ ሲፈጥሩ ውለው ኣሁንም ይሔን ጽሑፍ እያዘጋጀን እስካለንበት ድረስ ጫናውን በመፍጠር ላይ ናቸው።
የትግራይ መንግስት ከአሁን በፊት ያደረሰብንን ሰቆቃ እንዳይበቃው ጭራሽ በዚህ መልክ እኛን እያፈነና እያሸማቀቀ  ልዩ ልዩ የውሸት ቀረጻ በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝብ በውሸት በቀረጻው በማደናገር እውነተኛ የአማራ ማንነታችንን በሃይልና  በአፈና  ነጥቆ በግድ ያልሆነውን  የትግሬ ማንነት  ለመጫን ሲል እንዲህ  በአስጨናቂና  አጣብቂኝ ሁኔታ እንድንገኝ አድርጎናል።
“ውሽትና  ስንቅ  እያደር ይቀላል”  እንዲሉ በግዜ ሂደት እውነታው እንደሚወጣና እኛም የአማራነት ማንነታችን እንደሚከበር በልበ ሙሉነት ብናምንም ይሄን ያወቀ የትግራይ መንግስትና ካድሬዎቹ  ግን  ‘በውሸት  ህጋዊነት’  ከባድ የሞት ድግስ እየደገሰልን ስለሆነ የተወደድከውና  የተከበርከው  መላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  ሆይ በእኛ በወገኖችህ ላይ እየደረሰ ያለውን  መጠነ-ሰፊ ጭፍጨፋ በማውገዝ ከጎናችን እንድትቆም አደራ እንላለን።
የግዜ  ጉዳይ ሆኖብን ነው እንጂ እኛ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ  እንኳን አሸባሪ ልንሆን ጣልያንና  ድርቡሽ  እንዲሁም  በየግዜው የተነሱ በሱዳን በኩል የመጡብንን ጠላቶች እንኳን የመከትን  ለኢትዮጵያ  ሰላምና  አንድነት የምንተጋ ሰላማዊ  የአማራ ህዝብ  መሆናችን ታሪክ የሚመሰክረው ሃቅ ነው። እኛ የጎንደር አማራ ህዝብ አሸባሪዎች የሚል ስም በፍጹም አይመለከትንም  የሰማነውም  በወያኔና  ካድሬዎቹ  ነው፤ ማንነት መጠየቅ  አሸባሪነት ከሆነ ግን  ከዛሬ  ጀምሮ  አሸባሪዎቹ  እኛ  የወልቃይት  ጠገዴ አማራ ህዝብ ሳንሆን ኣሸባሪዎቹ   ወያኔና ካድሬዎ  እንደሆኑና  ይልቁንስ  በማህበረሰባችን  ህጋዊ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማድረግ  ሲል የለጠፈብን የውሸት ማንነት መሆኑን መላው የኢትዮጵያ  ህዝብና መላው አለም ኣውቆልን ከዚህ የጥፋት ዘመቻ እንዲጠብቀን በጥብቅ እናሳስባለን ።
አዎ አሸባሪነትማ ምንም ወንጀል ያልሰራነውን እኛን የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ ማፈን፤በመኪና  እየገጩ  መግደል፤ ያለ በዳላችን በሃሰት ፍርድ  ማሰቃየትና ደብዛችንን ማጥፋት፣ የእኛን የአማራ ማነንት  ከህግ በላይ ሆኖ መጨፍለቅና ህልውናችንን በመካድ በግድ ያልሆነውን የትግሬ ማንነት ማከናነብ ነው!!! እነዚህና ሌሎች ያልጠቀስናቸው በደሎች የሚያደርስ  ህግ የማይገዛው የትግራይ መንግስትና ካደሬዎቹ  ናቸው አሸባሪ  ተብለው መኮነን ያለባቸው። እንደዚህ ኣይነት የኣምባገነን  ውዳቂ ኣስተሳሰብ በ21ኛው መ.ክ.ዘ  ልእልና ኣግኝቶ የኣንድ ማህበረሰብ ማጥፊያ መንገድ ሊሆኑ ኣይገባቸውም ይህ ሳይሆን ቀርቶ ቢደረግ ግን ለተከበረችው ኣገራችን በእውነቱ በጣም ኣሳፋሪ ታሪኳ ይሆናል ማለት ነው።
ስለዚህ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ በወልቃይት ጠገዴ ወገኖችህ  በወያኔ እየደረሰብን ያለውን ፍጹም የሆነ አፈና፣ የዘር መጥፋት፣ የኣማራ ማንነት መጨፍለቅና የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም ድጋፋችሁን በሰላማዊ ሰልፍ እንድትገልጹልን በሞት አፋፍ ላይ ሆነን ይህንን ጥሪ አቅርበናል።
መላው የአማራ ህዝብም በፍትነት  ሊደርስልን  ይገባል።  እኛ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶችና ህዝብ  ግን  እኛም  በግድ  ካስወጡን  ውርድ  ከራሳችን”  ብለን ተማምለናል። ውድ የአማራ ህዝብ ሆይ ጉዳዩን ራሳህን ለማንኛውም ኣይነት ኣስፈላጊ ዝግጅት እያደረክ  ጉዳያችንን  በአንክሮ እንድትከታተል  እኛ  የመከራው ተካፋይ የሆንን  የዳንሻ  ህዝብ ጥሪ  አቅርበንልሃል። እባካችሁ ድረሱልን በላያችን ላይ በያንዳንድዋ ደቂቃ ወያኔ ብዙ ግፍ እየፈጸመብን ነው፤ ብአዴን ባይደርስልን እንኳ የምንወደው ወገናችን ሊደርስልን ይገባል!!! እኛ ይህ ሁሉ ሰቆቃ  የምንቀበለው ስለ አማራነታችን ብለን ነውና እባካችሁ ድረሱልን።
ተጻፈ በወልቃይት ጠገዴ
ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር ፤ጎንደር  ኢትዮጵያ   Posted by: ecadforum  

Sunday, 3 April 2016

በመፍሰስ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያዊያን ደምን እና እምባን የሚያደርቀው ሃይል ማን ነው ?

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ አገራችን ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎች አብዛኞቹን ለማየት፣ለመሰማት እና ለማማን ይከብዳል። “እውን በዚህ ዘመን ይህ አይነቱ ድርጊት ለምን እና እንዴትስ ይፈጸማል? ብሎ መጠየቅ ደግሞ ተገቢ እና ወቅታዊ መጠይቅ ጭምር ነው። ለዚህ መጣጥፌ መንደረደሪያ ሃሳብ የጫረብኝ ደግሞ የአልጃዚራው ጋዜጠኛ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ለማለት የባለሰልጣናቱን ይሁንታን አግኝቶ(በ አገሪቱ ውስጥ ጋዜጠኞች እንደልባቸው ተንቀሳቅስው የመዘገባቸው መብት ውሱን መሆኑ ይታወቃል ) በምእራብ የአገሪቱ ክፍል ኦሎንኮሚ አካባቢ ሰለ አለው ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ያጠናቀረው አንሰተኛ ነገር ግን ሰለ ወቅቱ በደል እና ጭቆና የሚያውቅ የማንኛውንም የሰብዊ ፍጡር ልብን የሚያደማው ዘገባው ነበር ። 

cry ethiopia
ታሪኩ ባጭሩ ሲቃኝ በቅርቡ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በ ወልቃት እና ጠገዲ እንዲሁም በኮንሶ የማንነት ጥያቄ ዙሪያ በተለይ በ ኢሕ አዲግ አጠራር በኦሮሚያ ክልልዊ መንግስት ውስጥ የተለያዩ የማህበረስቡ ክፍሎች የቀሰቀሱት ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ተከተሎ በ አገዛዙ ታጣቂዎች በጥይት አንገታቸው ላይ የተመቱት አንዲት እናት ሁለት ልጆች የእናታቸው ባለፈው የካቲት ወር መቁሰል እና አሟሟትን እንዴት እንደተቀበሉት ይዘግባል። የ 9 አመቱ ደረጀ ቱሪ ወላጅ እናቱ በታጣቂዎች በተመቱ ሰሞን ሰቃያቸውን እያየ መሪር የሃዘ እንባውን ከማፈሰሱ በተጨማሪ ወላጅ እናታችው በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ባላፈው መጋቢት ወር የሚወዳኡቸው ሁለቱ ጨቅላ ልጆቻቸውን እና ይህቺን አለም በሞት ሲሰናበቱ ደረጀ ዳግም አንብቷል ።ቁርጡንም አውቋል ።አንደ ወንድ አያታቸው አቶ ቀና ገለጻ መሆኑ ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የ6 አመት ታናሸ እህቱ አቤ “እናቴ የት ሄደች?፣ከሄደችበትስ ቦታ መቼ ትመጣለች?”የሚለው ተደጋጋሚ ጥያቄ የወንድ አያታቸውን የአቶ ቀና እና የመላው ቤተሰባቸው ልብን ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም ሰብ አዊ ፍጥረት ሁሉ ልብን የሚነካ ፣እንቅልፍ የሚነሳ ቁሰል እና አፋጣኝ ምላሸ የሚሻ ጉዳይ ነው ።ይህ አይነቱ የንጹሃን ደም በከንቱ መፈሰስ ፣ ህይወት እንደዋዛ መቀጠፍ እና ከሚወዱት ቤተሰቦቻቸው በታጣቂዎች መነጠቅ የተከሰተው በታዳጊዎቹ በእነ ደረጀ ቱሪ እና በእህቱ በአቤ ቱሪ ቤት ብቻ ሳይሆን በመቶዎች አሊያም በሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦች ውስጥ ሲስማ ታዲያ ሕዝቡ አፉን አውጥቶ ይሆን በልቡ እና በ አይምሮው አንድ ጥያቄ ማቅረቡ አይቀረም። እርሱም” በመፈሰስ ላይ ያለውን የወገኖቻቸን ደምን እና እምባን ማን ያብሰለናል/ያስቆምልናል?’ የሚለውን መሰረታዊ ፣ሞራላዊ እና ሰብ አዊ መጠይቅን ነው ። በሰሞነኛው በኦሮሚያ ፡ በአማራ፣ በደቡብ እና በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በታየው ያለመረጋጋት አደጋ ሳቢያ በቁጥሩ ላይ ልዩነቶች ቢኖሩም በመቶዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን እንዳጡ፡ አካለ ሰንኩል እንደሆኑ፣ በሺዎች ለእስራት እና ለግዞት እንደተዳርጉ የአገዛዙ ሹማማንቶች ሆኑ በተቃዋሚ ዎች ጎራ የተሰለፉ ወገኖች ይናገራሉ ። የተለያዩ አገራዊ እና አለማቀፋዊ ተደራሽነት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃናትም ዘግበውታል ።

ለችግሩም መፍትሔ በተመለከተ እንደዚሁ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ሰነባብተዋል።በመሰንዘርም ላይ ይገናሉ። እንደብዙዎች እምነት የችግሩ ምክንያትን በቅጡ ያልመረመሩት ወይም በምንቸገረን እሳቤ ተኝተው የሰነበቱት የአገዛዙ ጠ/ሚ/ር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና ፓርቲያቸው “በአገር ቤት እና በውጪ የሚገኙ ተቃዋሚዎች እና የኤርትራ እጆች አሉበት “ በማለት ሲወነጅሉ ከርመው በሰተመጨረሻ ላይ “ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንደማይሞኝ ተረድተናል ፣ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ማንንም ተጠያቂ አናደርግም ፣ዋንኛ ተጠያቁዎቹ እኛው ነን ። ይቅርታም አደርጉልን ፣ ቤታችንንም እናጸዳለን” ሲሉ ተደምጠዋል። ምንም እንኳን በሰለጠነው አለም እና በዚህ ዘመን የቅርታ መጠየቅ እና ለተፈጸመ ስህተት ሃላፊነትን መውሰድ ግጭትን በማስወገድ (ኮንፍሊክት ሪዞሊሽን) ረገድ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ሲሆኑ “ባዶ ይቅርታ ምን ሊፈይድልን ነው?፣ ይቅርታውም በ አሮጊ ጨርቅ ላይ አዲስ እራፊ ጨረቅ የመለበጥ ያህል ነው “ ያሉ እና ከይቅርታው ለጥቆ ወንጀል የፈጸሙ ሃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የሞራል እና የአካል ጉዳት ሰለባዎች በተገቢው መንገድ እንዲ ካሱ፣ ያለ አግባብ ወደ እስር ቤት የተወረውሩ ወገኖች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጠየቁ እና በመጠየቅ ላይ ያሉ ወገኖች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።

ከዚሁ ከጠ/ሚ/ሩ ሰሞነኛ “ይቅርታ አድርጉልን “ ተማጽኖ ጋር በተያያዘ የወቅቱ የአገሪቱን የፖለቲካ ትኩሳት ፣የህዝቡን ስጋት እና ምሬትን የተገነዘቡ በአገር ቤት በሰላማዊ ትግል ከሚነቀሳቀሱት የፖለቲካ ሃይሎች መካከል የአንዱ ፓርቲ ሃላፊ ሰሞኑን “ችግሩን ለማስወገድ የሃዝቡን እልቂት እና ዋይታ ለመግታት ሲባል የሃይማኖት አባቶች በአገዛዙ ላይ ተጽኖ ያሳርፉልን “ በማለት በዚህ በቀውጢ ወቅት የመለኮታዊ ሃይል አሰፈላጊነትን በአማሪኛ ቋንቋ ለሚሰራጭ ለአንድ አለማቀፋዊ ተደራሽነት ባለው ራዲዮ አማካኝነት በግል የምልጃ መል እክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው የግፍ በትር ለጊዜውም ቢሆን ያለነካቸው አንዳንድ የዋህ ወገኖች ” ከዚህ የባሰ አታምጣ” በማለት ተደላድለው መቀመጣቸው እንዳለ ሁሉ በሌላ ወገን ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ እየደረሰ ባለው የፍትህ እና የሰብ አዊ መብት ጥሰት ሳቢያ ዱር ቤቴ ብለው አገዛዙን በትጥቅ ትግል ለመፋለም እንቅሰቃሴ መጀመራቸውን የሚናገሩት ሃይሎችንም በተመለከተ “ምን እየሰራችሁ ነው ያላችሁት ?፣ ከዚህ የከፋ ምን እስኪመጣ ነው የምተጠብቁት?” በማለት የሚጠይቁ በጭንቀት እና በምሬት ወጀብ የሚናጡ ወገኖች መኖራቸው የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ውሎ አድሯል።

አገሪቱ እና ሕዝቧ በዚህ እና በመሰል ችግሮች በተወጠሩበት በአሁኑ ወቅት ፣ በተለያዩ ጎራዎች የተሰለፉ ፓለቲከኞች” ብቸኛው መንገድ እና መፍትሔ የእኛ ጎዳና ብቻ ነው “ በሚሉን በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ የተከሰተው የድርቅ አደጋ የፖለቲካ ምንነትን እና የፖለቲከኞች ማንነትን በጭራሽ የማያውቁ ከ400 ሺህ በላይ ጨቅላ ህጻናትን ጨምሮ በ ስድስት ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሕዝባችን ላይ የ ረሃብ እና የሞት ደመና ባንጃበበት ፣ የለጋሽ አገራት እና ተቋማት የእርዳታ እጆች ከመቼውም ጊዜ በላይ ባጠሩበት በዚህ በአሳዛኙ እና አሳሳቢው ወቅት ላይ የመኖራችን ጉዳይ ሳይዘነጋ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወገኖቻችን እየፈሰሰ ላለው የንጹሃኖች ደምን እና እንባን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በፍጥነት የሚያደርቀው ሃይል/ወገን ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ በንጹህ አይምሮ ፣ በሰከነ ልቦና መጠየቅ ፣ለጋራ ችግር የጋራ ውይይት እና ምክክር ማድረግ ብዙዎች ወደ ሚያልሙት ወደ ዘላቂው እና ሰላማዊው ምእራፍ ያደርሳል። አገርንም ሆነ ሕዝቧን ከተደቀነባቸው ከመበታተን እና ከእልቂት አደጋ ያድናል                                                by