Friday, 26 August 2016

በአማራው ክልል ያለው መለስተኛ ጦርነት ሳይባባስ መፍትሄ ይፈለግ



ግርማ ካሳ

በአማራው ክልል ያለው መለስተኛ ጦርነት ሳይባባስ መፍትሄ ይፈለግ –  ግርማ ካሳ
– በሰሜን ጎንደር ዞን 145 ወታደሮች ተገድለዋል
– ከአዘዞ ካምፕብቻ 143 ወታደሮች ካምፑን ጥለው እስከነ ትጥቃችው ጠፍተዋል
ህወሃት ለሰላም በሮቹን በሙሉ ስለዘጋ፣ በሰላም የሚታገሉ፣ እንደ አንድነት ያሉ ፓርቲዎችን አግዶ፣ እንደ አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን ኦልባና ለሌሳ …ያሉ ሰላማዊ የፖለቲካ መሪዎችን አስሮ፣ ምርጫ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ፣ ዜጎች ወደ ማይፈለጉት መስመር ፊታቸውን እንዲያዞሩ ገፋፍቷቸዋል።የሰላም በር ሲዘጋ የአመጽ በር ተከፍቷል። በአሁኑ ወቅት ምንም መሸፋፈን አያስፈለግም፤ በተለይም በአማራው ክልል በአሁኑ ጊዜ መለስተኛ ጦርነት ነው ያለው።
አንዳንዶች የሕዝቡን ተቃዉሞ እንደ ቀላል ይቆጥሩታል። ከሚገባውም በላይ ሕወሃትን አጎዝፈው ይመለከታሉ። ምናልባት ሕወሃቶችም ራሳችው፣ ለብሄራዊ እርቅ እስከ አሁን ድረስ በራቸውን የዘጉት፣ ለራሳቸው ከፍተኛ ግምት ስለሰጡና ህዝቡንም ስለናቁት ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
እርግጥ ነው የህወሃት ሰራዊት መሳሪያ የታጠቀ ሃይል ነው። ያኔ ደርግ እንደነበረው ማለት ነው። ግን የመሳሪያ ብዛት በራሱ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። መሳሪያና ትጥቅ አስፈላጊነቱ እንደተጠበቀ፣ ጦርነት የሚደረግበት አካባቢ ሁኔታ፣ የወታደሮች ሞራልና ስሜት፣ የስለላ መረጃ የመሳሰሉትን የየራሳችው ትልቅ አስተዋጾ አላቸው። እንደ ደርግ በአፍሪካ የታጠቀ ሰራዊት አልነበረም። ወደ 500 ሺህ የሚሆን ወታደር ነበር። በመሳሪያና በወታደር ብዛት ቢሆን ደርግ አይሸነፍም ነበር። ያ ጦር ግን የተሸነፈው አንደኛ ወታደሩ ስለተሰላቸና ሻእቢያና ወያኔም በቀጥታ ቅድመ መረጃዎች ያገኙ ስለነበረ ነው። ወያኔና ሻእቢያ ደርግን ያሽነፉት ተዋግተው ሳይሆን በሳቦታጅ ነበር። አሁን ያለው የሕወሃት ሰራዊትም ከደርግ ሰራዊት በምንም አይለየም፡
ሕወሃቶች አንደኛ በአማራው ክልል የታጠቁ ሃይላት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴዎች የማወቅ እድል የላቸዉም። ያ ብቻ አይደለም፡ እነማን እንደሆኑም አያውቅም።
ሁለተኛ በኮንቮይ ከአዲስ አበባ ይሁን ከመቀሌ ወታደሮች መንቀሳቀስ ሲጀምሩ በቀላሉ መረጃዎች ይወጣሉ። የአማራው ክልል መሬቶችም አስቸጋሪ እንደመሆናቸው በወታደራዊ ኮንቮዩ ላይ ጥቃቶችን በመፈጸም ወይንም መንገዶችን በመዝጋት የጦሩን እንቅስቃሴ መግታት ወይንም ማጓተት ቀላል ነው የሚሆነው።
ሶስተኛ መሬቱን የማያውቅ ወታደር፣ ከባባድ መሳሪያ ቢሸከምም ፣ ጉድጓድ ሸንተረሩን ከሚያውቅ የአካባቢው ታጣቂ ጋር መፋለሙ ለርሱ አስቸጋሪ ነው። ባዙቃዉን ተሸክሞ ወደ ላይ ሲመለከት፣ በስር ከዋሻ ብቅ ብሎ አንዱ ይጠለዋል።
አራተኛ አሁን ያለው ሰራዊት በስሜት የሚዋጋ ሰራዊት አይደለም። የሚለግም፣ በሕዝቡ ላይ መተኮስ የማይፈለግ፣ እያጉረመረመ ያለ ሰራዊት ነው። በአለቆቹ እየተሰደበ፣ የዘር ልዩነት እየተደረገበት፣ እድገትና የዉጭ ስልጠና ለአንድ ብሄረሰብ ተወላጆች ብቻ ስለሚሰጠት የተማረረ ሰራዊት ነው። እንዲህ አይነት ሰራዊት ተዋግቶ ድል ማድረግ አይደለም፣ አንድ እርምጃ መራመድ አይችልም።
አምስተኛ ቀውስና አለመረጋጋት የተፈጠረባቸው ቦታዎች አድማሳቸው በጣም የሰፋ ነው። ድፍን ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ( ጎንደር ከተማ፣ ዳባት፣ ደባርቅ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ አዘዞ፣ ማክስኚት፣ ጎርጎራ፣ አርማጭሆ፣ ዳንሻ፣ ደብረ ታቦር፣ ጋይንት፣ አዲስ ዘመን፣ አዘዞ፣ ጭዋሂት፣ ሐሙሲት፣ ሳቆጥራ፣ አለፋ፣ አይንጋ፣ ሳንጃ፣ ሙሴ ባንድ፣ ቆላ ደባ….) በምእራብ ጎጃም ዞን ( ፍኖት ሰላም፣ ማንኩሳ፣ ቡሬ፣ ጅጋና እንዳለ የዳሞት አወራጃ )፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን ( ደብረ ማርቆስ፣ አባይ በረሃ ፣ በደጀን አርጎ ወደ ሞጣ ከዚያ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ በአይንጋ) ፣ በባህር ዳር ከተማ እና በጢስ አባይ ከተማ፣ በሰሜን ወሎ ሸዋ (መቄት፣ ቆቦ፣ ማጀቴ ….)፣ በአጠቃላይ በመላው የአማራ ክልል ማለት ይቻላል እንቅስቃሴና ተቃዉሞ አለ። በስንቱ ቦታ ወታደር፣ ከዚህ እዚያ እያመላለሱ ይችላሉ ? እንደ ደሴ ፣ ደብረ ብርሃን፣ ወልዲያ፣ ኮምቦልቻ፣ ሸዋ ሮቢት ባሉ ቦታዎች ህዝቡ ተቃዉሞ ለማሰማት ተዘጋጅቷል። በነዚህ ከተሞች ከፍተኛ የወታደር ክምችት አለ። ህዝቡ እንዳይወጣ ለማፈን እየተጠባበቀ ያለ። ወታደሮቹ ወደ ሌላ ቦታ ከተንቀሳቀሱ ሸዋና ወሎ እንደ ፍም እሳት መቀጣጠሉ አይቀሬ ነው።
እስከ አሁን በተደረገው መለስተኛ ጦርነት፣ ሕወሃቶች ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱን አፍነው ለመወሰድ ብዙ ጊዜ ሞክረው አልተሳካላቸውም። ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጀመሮ እስከ አሁን በሰሜን ጎንደር ዞን ብቻ (ጎጃምን እና ደቡብ ጎንደር ዞንን ሳይጨምር) ቢያንስ 145 ወታደሮች ሕይወታቸው ጠፍቷል።
በጎንደር ከተማ አሥራ ስድስት የፌዴራል ፖሊስ፣ አንድ የመከላከያ ሰራዊት፣ አንድ ሚሊሺያ፣ ስምንት ልዩ ኃይል የተገደሉ ሲሆን በአዘዞ ሶስት፣ በአይንጋ አሥራ ሶስት፣ በአምባ ጊዮርጊስ ሶስት ፣ ቆላድባና አዘዞ መሃል ላይ (ከገበሬ ማህበር ጋር በተደረገ ጦርነት) ዘጠኝ ፣ በሙሴ ባንድ ዘጠና አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ተገድለዋል።
በአጠቃላይ 143 ወታደሮች። (ይህ መረጃ የተገኘው በሰሜን ጎንደር በጸጥታና ደህነነት እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አመራር አባላትን ባካተተ ስብስባ ከቀረበ ሪፖርት ነው)
አንድ መቶ አርባ አምስት ወታደሮች መገደላቸው፣ የሕወሃት ጦር ያለበትን ከፍተኛ አጣብቂኝ አንዱን ገጸታ ብቻ ነው የሚያሳየው። ትጥቃቸውን እየያዙ ሰራዊቱን ትተው፣ ህዝቡን ከቀድሞ አለቆቻቸው ለመጠበቅ የሕዝቡን ትግል የተቀላቀሉም ጥቂት አይደሉም። አዘዞ ከሚገኘው የጦር ካምፕ ብቻ ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም ጀመሮ፣ ትላንት 13 የሰራዊቱን አባል ያካተተ አንድ ጋንታን ጨመሮ፣ አንድ መቶ አርባ አንድ ወታደሮች ካምፑን ጥለው ሄደዋል። ጠፍተዋል።
የህዝብን መብት በሃይልና በጠመንጃ ማፈን አይቻልም። ህዝብ ቆርጧል። የሕወሃትን መንግስት በፊትም አልመረጥኩም፣ አሁንም እኔን አይወክልም። ይሄን መንግስት የምሸከምበት ትከሻ ከአሁን በኋላ የለኝም ብሏል።ይህ ህዝብ አንገቱን ከዚህ በኋላ አይደፋም። የዚህን ህዝብ ጥያቄ ከመስማትና ከማክበር ዉጭ ሌላ አማራጭ የለም። የዚህ ሕዝብ ጥያቄ ፍትህ፣ ሰላም፣ ልማት፣ እኩልነት፣ አንድነት ፣ ዲሞክራሲ ነው።
በመሆኑ የሕወሃት መንግስት ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት በማስገባት፣ ነገሮች የበለጠ ወደ ከፋ ደረጃ ከመድረሳቸው በፊት፣ ነገሮችን በማርገብ፣ ራሱን ለብሄራዊ እርቅ እንዲያዘጋጅ አሳስባለሁ። በአፋጣኝ የሚከተሉት ቢደረጉም ይጠቅማሉ ብዬ አስባለሁ፡
1. የሕሊና እስረኞች በሙሉ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ
2. የሽግግር መንግስት ወይንም ካቢኔው አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎችን ያካተተ( መድረክ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ. የቀድሞ አንድነትና ኢዴፓ) የአንድነት መንግስት ይቋቋም (ጦርነት ወይንም ችግር ሲፈጠር ብዙ ጊዜ እስራኤሎች የፓርቲ ልዩነቶቻቸው ወደ ጎን አድርገው ለአገራቸው ደህነንት ሲሉ የአንድነት መንግስት ይመሰርታሉ) ከ እስራኤሎች ትምህርት ይወሰድ። ከፓርቲ ይልቅ የአገር ሰላምና ደህንነት ይቅደም።
3. አሁን ያለውን የፌዴራል አወቃቀር የሚመረመር ገለልተኛ ኮሚሽን ይቋቋም። ይሄ በዘር ላይ የተመሰረተው ፌዴራል አወቃቀር ነዉና አሁን ወዳለነብት ቀዉስ ዉስጥ የከተተን።
4. ፖሊሲ፣ ፍርድ ቤት፣ ምርጫ ቦርድ፣ የህዝብ ቆጠራ ጽ/ቤት፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ ሜዲያው ነጻና ገለልተኛ የሚሆንበት ሁኔታ እንዲፈጠር የሚረዳ ተቃዋሚዎችና ባለሞያተኞችን ያካተተ ኮሚሽን ይቋቋም።
5. ለሁለት አመት በኋላ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይደረግ።

Wednesday, 24 August 2016

የፍኖተ ሰላም ዐማሮች የተሳካ የዐማራ ተጋድሎ አካሔዱ • ኮሎኔል ደመቀን ለመውሰድ መከላከያ ሠራዊት ሙከራ አደረገ • በጎንደር የቤት ውስጥ አድማ ዳግመኛ ተጀመረ

• ኮሎኔል ደመቀን ለመውሰድ መከላከያ ሠራዊት ሙከራ አደረገ
• በጎንደር የቤት ውስጥ አድማ ዳግመኛ ተጀመረ
• በአርማጭሆ የዐማራ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከሕዝብ ጋር መሆናቸውን አሳዩ
• በደብረ ታቦር ከነሃሴ 22 እስከ 25 የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ ይደረጋል
ፍኖተ ሰላም፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ የዐማራ ተጋድሎ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል

ከሙሉቀን ተስፋው
በዳሞቷ ፈርጥ ፍኖተ ሰላም ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ ነበር እቅዱ፡፡ ግን ይህ ከቤት ውስጥ የመቆየት የተጋድሎ አድማ በወያኔዎችና በቅጥረኞቹ እንዲከሽፍ በጠዋት ወደ ሥራ የተሰማሩ ቡድኖችና ግለሰቦች መኖራቸው ታወቀ፡፡ የቆላ ደጋ ዳሞት ዐማራ ከቀናት በፊት ለገጠር ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት መልእክት አስተላልፎ ነበር፡፡ ገበሬው በንቃት ጉዳዩን ተከታተለ፡፡
ዛሬ ገበያ ቦታ ላይ አድማውን ትተው ከሕዝብ የተነጠሉትን ሆድ አደር ነጋዴዎች ወጣቶች ሒደው ተነሱ ወደ ቤታችሁ ግቡ አሏቸው፡፡ አልሰሙም፡፡ ተጋድሎው ተጀመረ፡፡ የቤት ውስጥ አድማው ወደ አደባባይ ዞረ፡፡ ከዚያ በኋላማ ለዳሞት ዐማራ ምን ይነገረዋል? ሀምሌ 30 ቀን ተጀምሮ እንዲኮላሽ የተደረገው የተጋድሎ እንቅስቃሴ ቁጭት አለ፡፡ የሰላሟ ከተማ በቆራጥ የዐማራ ጀግኖች ቁጥጥር ሥር ለመዋል ጠዋት ሦስት ሰአት ብቻ ነው የጠበቀችው፡፡
demeke z - satenaw
በ3፡00 የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ ሥራ የጀመሩ የንብ፣ የዓባይ፣ የንግድና የዳሸን ባንኮችን ቶሎ በራቸውን እንዲዘጉ በዐማራ ባሕል ነገሯቸው፡፡ አልሰሙም፡፡ በግዴታ ነበልባሎቹ ወጣቶች ሁሉንም እንዲጠረቀም አደረጉ፡፡ የዐማራ ወጣቶች ወደ ማረሚያ ቤት በመሔድ የመኪና መንገድ ዘጉ፡፡ ከወደ ጅጋ በኩል የሚመጣውንም የመኪና መንገድ ጥርቅም አደረጉት፡፡ ወደ አደባባይ ሲሔዱ ‹‹መጪው ጊዜ ከኢሕአዴግ ጋር ብሩህ ነው›› የሚል ፌዘኛ ቢል ቦርድ አገኙ፤ ይህ ቀልድ ዳግም በጎጃም ምድር መኖር የለበትም ሲሉ አጋዩት፡፡
አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የሚመካበትን የብአዴን ጽ/ቤት ጋ ሔዱ፡፡ ማንም የሚያቆማቸው አልነበረም፡፡ የብአዴንን ዓርማ አቃጠሉት፡፡ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ በፍኖተ ሰላም ከ25 ዓመታት በኋላ ተውለበለበ፡፡ አደባባይ ላይም ሰቀሉት፤ የቆላ ደጋ ዳሞት ዐማሮች በደስታ እልል አሉ፡፡
የዐማራ ፖሊስ ከእኛ ጋር እንደሆነ ከሕዝብ ጋር ቆመ፡፡ አንድም እንኳ የዐማራ ፖሊስ በዐማራ ሕዝብ ላይ የተኮሰ የለም፤ እንዲያውም ሰልፈኞችን አበረታተዋል፡፡ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ የንግድ ቤቶችና ንብረቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በኋላ በአንበሳ ባንክ የሚጠቀም ዐማራ የለም፡፡
ወያኔ ከብር ሸለቆ መከላከያ ሲያንቀሳቅስ መንገድ ተዘጋበት፡፡ በእግር ብዛት ያለው መኪና ከብር ሸለቆ እየሔደ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ የዳሞት ዐማራ ለቋሪትና ለሰከላ፣ ለእንጅባራና ለጃግኒ መልእክት ልኳል፤ ‹‹የዐማራ ተጋድሎ እስከ ነጻነት ይቀጥላል›› በማለት፡፡
በፍኖተ ሰለም ከተማ ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ጊዜ ድረስ ተጋድሎው እንደቀጠለ ነበር፡፡ ብዙ ወጣቶች ምሳና ቁርስ ሳይበሉ ተጋድሎአቸውን መቀጠላቸው ታውቋል፡፡ ከደብረ ማርቆስ በኩል የመጣ የፌደራል ፖሊስ መንገድ ተዘግቶበት እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ወደ ማረሚያ ቤት በመሔድ መንገድ ዘግቶ ከዚያ የፓርቲው ሰንደቅ አላማ ተቃጥሏል፡፡ አደባባይ ቀይ ቢጫ አረንጓው ሰንደቅ አለማ ተሰቅሏል፡፡ የኢሕአዴግ ደጋፊ ድርጅቶች ሙሉ ጥቃት ደርሷል፡፡ ፖሊስ ከእኛ ጋር ነው፡፡
ግልገል በለስ፤ በግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ ሁለት የአገዛዙ ቅጥረኞች የእጅ ቦንብ ይዘው ግቢው ውስጥ እንዲያዙ ከተደረገ በኋላ ዐማሮች ጉምዞችን ለመጨረስ ሲሉ ተያዙ እያሉ በማስወራት በመተከል ዞን ሁሉም አመራር የዐማራን ጉዳይ ለማየት ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል፡፡ ይህ ዓይነት ምክንያት ዐማራን ለመጨፍጨፍ በየጊዜው የሚፈበረክ ወሬ በመሆኑ ሁሉም በአካባቢው የሚኖሩ ዐማሮች እንዲጠነቀቁ መልእክት እንዲተላለፍ መረጃውን የሰጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ጃግኒ፤ የጃግኒ ከተማ ገበሬው ወደ ገበያ ሲመጣ በመከላከያ ኃይል እንዲመለስ እየተደረገ ነው፡፡ ገበሬዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የዐማራውን ተጋድሎ ይቀላቀላሉ በሚል ስጋት ወደ ከተማ እንዳይገቡ እየተመለሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ባሕር ዳር፤ የባሕር ዳር ዐማሮች ቤታቸው ውስጥ ከተቀመጡ ዛሬ አራተኛ ቀናቸውን ይዘዋል፡፡ አንዳንድ የባጃጅ ሾፌሮችና የንግድ ቤቶች በግዴታ እንዲከፈቱ የተደረገ ቢሆንም በከተማው ብዙ እንቅስቃሴ እንደሌለው ነው የሚነገረው፡፡ በባሕር ዳርም የዐማራ ፖሊስ ከሕዝብ ጋር መቆሙን አረጋግጧል፡፡ ደብረ ታቦር፤ የደብረ ታቦር ዐማሮች ከነሃሴ 22 እስከ 25 ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ ይደረጋል፡፡ የደብረ ታቦር ከተማ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ጭር ብላ ትሰነብታለች፡፡ ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ገበታ ባለመሔድ ትብብር እንዲያደርግ የደብረታቦር ከተማ የተጋድሎው አስተባባሪዎች ጠይቀዋል፡፡ የዐማራውን ተጋድሎ ትቶ የሚሔድ ሰው ቢገኝ ግን ዝምድናው ከወያኔ ጋር እንደሆነ ይቆጠርበታልም ብለዋል፡፡ ማንኛውም የንግድ ቤትና የመንግሥት መሥሪያ ቤት ዝግ ሆኖ ይሠነብታል፡፡ ደብረ ታቦርን በእነዚያ ቀናት ታቦር ተራራ ላይ ሆኖ ለሚያያት በውስጧ ሕይወት ያለባትም አትመስል ይሆናል፡፡
ጎንደር፤ ኮሎኔል ደመቀን ለመውሰድ የትግሬ መከላከያ ሙከራ እያደረገ እንደሆነ ዛሬ ከመሸ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡ ከሰአት በኋላ ሁለት ፓትሮል ስናይፐር የያዘ የመከላከያ ሠራዊት ወደ አንገረብ ማረሚያ ቤት ሒደው ነበር፡፡ ለምን እንደሆነ ሲጠየቁም በቂ መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡ የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ የመከላከያ ሠራዊቱን ጉድብ በመያዝ የጠበቃቸው ሲሆን ምንም ሳያደርጉ እንደገና ተመልሰዋል፡፡ የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ ላደረገው ቁርጠኝነት መረጃውን የሠጡን ሰዎች ገልጸው ሕዝቡም በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ለአምስት ቀናት ሊዘልቅ የሚችል የቤት ውስጥ አድማ በጎንደር ከተማ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ የጎንደር ከተማ ዐማሮች ትግሉን ከፍ አድርገው ሰቅለውታል፡፡ ዳቦ ቤቶች፣ ክሊኒክና ፋርማሲዎች እንዲሠሩ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ከዚያ ውጭ ያለ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ጸጥ አረጭ ያለ ነው ዛሬ በጎንደር፡፡ በቀን ሥራ የተሠማሩና ሕይወታቸውን በእየለቱ እየሠሩ ለሚመገቡ ዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ዐማሮችም መፍትሔ መኖሩን ነው ያነጋገርናቸው ሰዎች የገለጹት፡፡
ኮሌኑ ጋ መከላከያ ዛሬ ሒደው ነበር፤ ሰውየውን ለመውሰድ እየሞከሩ ነው፡፡ መከላከያዎች ስናይፐር ይዘው በሁለት ፓትሮል ሲሔዱ የክልሉ ልዩ ኃይል ጉድብ ይዘው የጠበቁት፡፡ ሰልፉን እንዴትና በማን እየተመራ ነው ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹አንተ ዐማራው በአንድ ልብ ነው የሚተነፍሰው፤ በጣም ተግባብቷል፡፡ ከወያኔወች ሁሉ ቀድሞ ሒዷል፡፡ ምን ቢከሰት ምን እንደሚያደርግ ራሱ ያውቃል›› ሲሉ በመደነቅ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የዐማራው ሕዝብ ተጋድሎውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እያቀጣጠለው ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል ሐምሌ 06 ቀን 2008 ዓ.ም በአጋዚ የተመታው አቶ አዳነ አየነው ከ40 ቀን በኋላ ዛሬ ማረፉን በሐዘን ውስጥ ሆነን ሰምተናል፡፡ የሰማእቱ ወንድማችን ቀብር በቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የፈጸማል፡፡
ምእራብ አርማጭሆ፤ በምዕራብ አርማጭሆዋ የኩር ዑመር (ጠፈረ ወርቅ) ከተማ ነሃሴ 16 ቀን የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እስካሁን እንደቀጠለ ነው፡፡ የሥርዓቱ አጋፋሪዎች ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ የወያኔ ደጋፊዎችም አካባቢውን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡
በሌላ ዜና የዐማራ ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአርማጭሆ አገዛዙን እየተው ወደ ሕዝብ መቀላቀላቸውን ሰምተናል፡፡ ትናንት አንድ የመቶ አለቃ ሦስት የበታች አባሎቹን ይዞ ከሕዝቡ ጋር ገብቷል፡፡ ወደ አርማጭሆ የተላኩት የመከላከያ ሠራዊት አባለት በቂ ካምፕ ሳይዘጋጅ ወደ ቦታው በመንቀሳቀሳቸው ምክንያትም ወደ ሕዝቡ እንጀራ እንደሚለምኑ ተሰምቷል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ደግሞ ምንም እንኳ እንግዳ ተቀባይ ቢሆንም የወያኔ መከላከያ ሠራዊት አባላትን ማየት እንደማይፈልግ እየነገራቸው ነው፡፡
ወልቃይት፤ ባለፈው ሳምንት ከዩንቨርሲቲ ተመርቀው ሥራ ያልያዙና 12ኛ ክፍል የጨረሱ የወልቃይት ዐማሮችን መቀሌ በቀን 500 ብር አበል ለስብሰባ ተጠርተው ነበር፡፡ ሆኖም የወልቃይት ዐማሮችን ዐማራ ነን ማለታችሁን ተው በመባላቸው ምክንያት ስብሰባውን አቋርጠው ተመለሰዋል፡፡ እስካሁን ድረስ በዳንሻ፣ አዲረመጥና ኹመራ አካባቢዎች የትግራይ ተወላጆች ሀብት ንብረታቸውን እያሸሹ እንደሆነ ነው የሚሠማው፡፡(Posted by: )

Wednesday, 17 August 2016

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስሤራ – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ማክሰኞ ነሐሴ ፲ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.             ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፪
Moresh-901.jpgላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል እንደሆነ፣ በተከታታይ በተደረጉት የሕዝባዊ እንቢተኝነት ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽ ታይቷል።
ይህ የሕዝብ አመጽ ያርበደበደው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን በማጣቱ፣ የእርሱ ምርኮኛ የሆነውንና በጥቅማጥቅም የገዛውን የትግራይ ትውልድ በነቂስ አስታጥቆ፣ በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ ለመዝመት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስተማማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ። የትግሬ-ወያኔ ከሚያደርገው ሠፊ የጥፋት ዝግጅቶች ውስጥ፣ የትግራይን ትውልድ «በትግልህ ያገኘኸውን ልዩ መብትና ነፃነት፣ ትምክተኞች፣ ነፍጠኞች፣ የድሮው ሥርዓት አራማጆችና ዐማሮች ሊነጥቁህ ነውና ዐማራን ለማጥፋት ዝመት፣ ተንቀሳቀስ» በማለት፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በአርማጭሆ ነዋሪዎች ላይ ክተት አውጇል። በአጠቃላይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም ሰሞኑን በጎጃምና በጎንደር የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ቡድኖችን በማሰማራት ሌሊት ሌሊት ወጣቱን እየፈነ ወደ ማሰቃያ እስር ቤቶቹ እያስገባ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ድርጊቱ ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ሊሳካለት እንደማይችል በመረዳት፣ በመላ ኢትዮጵያ የሚያካሂደው ሌላም ሠፊ የጥፋት ዕቅድ አቅዶ ለተግባራዊነቱ በጥድፊያ እየሠራ መሆኑ እየተሰማ ነው። ይህም መጠነ ሠፊ የሆነ ጥፋት ያነጣጠረው በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ እንደሆነ ታውቋል። የትግሬ-ወያኔ በእነዚህ ነገዶች ሕዝብ ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመወጣት ያቀደው ዕቅድ፣ «በዐረብ ኢሚሪቶችና በሻዕቢያ የሚታገዙ አሸባሪዎች፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ እየተንቀሳቀሱ ነው» የሚለውን ሀሳብ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ፣ በተለይም ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ሸሪክ የሆነውን የምዕራቡን ዓለምና የአሜሪካንን ልብ ለማማለል እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ረገድ በቅርብ ቀናት ውስጥ የትግሬ-ወያኔ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳርና መሰል ከተሞች፣ የሕዝብ ክምችት በሚበዛባቸው ቦታዎች፣ በመንግሥታዊ ተቋሞች፣ በመገናኛ አውታሮች ወዘተርፈ ፈንጅ በማፈንዳት እኩይ ዓላማውን በተግባር እንደሚያውል ውስጥ አዋቂዎች አስጠንቅቀዋል። ፈንጂዎችን ራሱ አፈንድቶ፣ «የዐማራ እና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንዲህ አደረጉ» በማለት ለደጋፊዎቹ  የተቀነባበረ የሤራ መረጃ በማቅረብ፣ «ሕገ-መንግሥት» ተብየውን አግዶ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አገዛዝ በማወጅ፣ በሁሉም ቦታዎች ለወያኔ ጄኔራሎች የመግደልና የማሰር ሥልጣን በመስጠት በዐማራውና በኦሮሞው ነገዶች ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊና አሰቃቂ ዕልቂት ለመፈጸም ቁርጠኛ አቋም መያዙ ታውቋል።
በሰኔ 1980 ዓ.ም. «ነፃ ላወጣህ መጣሁ» ባለውና በራሱ ነገድ በሆነው የሀውዜን ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ላይ ያን የመሰለ የተቀነባበረ ሤራ ሠርቶ ሕዝብ ያስጨረሰ ድርጅት፣ «ጠላቶቼ ናቸው» ባላቸው የዐማራና የኦሮሞ ነገድ ሕዝብ ላይ ይህን ዓይነቱን ድርጊት አያቅድም፣ አይፈጽምም፣ አያደርጉትም፣ አይሆንም የሚያሰኝ አመክንዮ አይኖርም። ኢትዮጵያዊ የሆኑትንና «ለትግሬ-ወያኔ ዓላማ አንገዝም፣ አባልም አንሆንም» ያሉትን የትግራይ ልጆች፣ «አባሎቼ ናቸው» የሚል የተቀነባበረ የሐሰት መረጃ፣ ለደርግ የመረጃ አካላት እያቀበለ ወገኖቹን ያስጨፈጨፈ ድርጅት ይህን አያስብም አይባልም። በሂደት እንዳስተዋልነው፣ ወያኔ «አደርገዋለሁ፣ አጠፋዋለሁ» ብሎ ያቀደውንና ያለው በተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ ያለበት አንድም አጋጣሚ አላየንም። ይህንም እኩይ ድርጊት አያደርገውም ለማለት የሚያስችል ምክንያት ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው።
የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጠፋለሁ ብሎ አቅዶ መነሳቱ ይታወቃል። በዕቅዱ መሠረትም 5 ሚሊዮን ዐማራ አጠፋ። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመራርን ከሦሥት ከፈለ፥ የአገር ቤትና ስደተኛ ሲኖዶሶች እንዲሁም ገለልተኛ በሚል። የሃይማኖቱ ነባር ተቋሞችን፣ ለምሣሌ ያህል፥ የዋልድባን፣ የዝቋላ አቦን እና የማኅበረሥላሴን ገዳማትን አቃጠለ፤ ቅጥረ ግቢያቸውን መነጠረ። የሃይማኖት አባቶችን አሰደደ። ቱባ ባለሥልጣኖቹ ዐባይ ፀሐየ፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሣሞራ የኑስ ሌሎችም በአደባባይ፣ «ዐማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል፣» «ገድለን ቀብረነዋል» ማለታቸውን አንዘነጋም። እናም ባለፉት 25 ዓመታት ገድለው ካልጨረሱት ውስጥ የቀረውን የዐማራና የኦሮሞን ነገዶች ሕዝብ «አስቸኳይ ወታደራዊ» አገዛዝ በማወጅ ሊጨርሱት ቁርጥ ሀሳብ ማድረጋቸውን የዐማራውና የኦሮሞው ነገድ አባሎች ለአፍታም መጠራጠር አይኖርባቸውም። ስለሆነም፣ የትግሬ-ወያኔ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ጥፋት ተልዕኮው ሳይገባ፣ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዕቅዱን ለማክሸፍ መተባበር ይጠበቅባቸዋል።
ከሁሉም በላይ «ሺህ ጋን ቢታለብ ወይ በገሌ» እንዳለችው ድመት፣ ዐማራው በብሔርተኞቹ ድርጅቶች በቀና ስለማይታይ፣ ልጆቹ በመካከላቸው አለን የሚሏቸውን ጥቃቅን ልዩነቶች በማርገብ፣ በአንድነት በመቆም ለወገናችን መከታ መሆን ይጠበቅብናል። የዐማራው ምሁራንና ፖለቲካኞች በአንድነት መቆም፣ የአንድነት ኃይሉን ለተፈላጊው አጠቃላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት ጽኑ መሠረት ስለሚሆን፣ የዐማራው ምሁራን በቅድሚያ የነገዳቸውን አንድነት ዕውን በማድረግ፣ በሌሎች አቻ ቡድኖችና ድርጅቶች ላይ መልካም ተጽዕኖ ማሳደር ይጠበቅባቸዋል። ይህን ለማድረግ ስበቦችን መደርደር አስፈላጊ አይደለም። በወገናችን አንገት ላይ ሳንጃ ተጥሏል፤ በግንባርና ደረቱ ላይ አፈሙዝ ተደግኗል። ስለዚህ ይህ ጊዜ አይሰጥምና በዐማራ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች ከያላችሁበት «አለን» ብላችሁ በጋራ የምትሠሩበት መንገድ ካሁኑ ካልጀመራችሁ፣ ይህንም ለወገናችሁ በግልጽ ካላሳያችሁ፣ የጥፋቱ አካል እንጂ፣ የመፍትሔው አካል ናችሁ ብሎ ማኅበረሰቡም ሆነ ታሪክ  ሊያወሳችሁ እንደማይችል በእርግጠኝነት መናገር ድፍረት አይሆንም። ስለሆነም ሁላችንም ለዐማራው ኅብረትና አንድነት ኅሊናችን ከፍተን በቅንነት እንነሳ! በዚህ የመከራ ጊዜ የዐማራው ልሂቅ በአንድነት ቆሞ፣ ለወገኖቹ ቤዛ ካልሆነ ምንጊዜም ዐማራው አንድ ይሆናል ለማለት ያስቸግራል። እንኳን የአንድ ታላቅና ታሪካዊ ነገድ ልጆች ቀርቶ፣ በክረምት እባብና ጓጉንቼር በአንድ ጉድጓድ ይኖራሉ። ይህ ክፉ የወያኔ ዘመን ዐማራውን ቀርቶ፣ ዐማራና ኦሮሞውን በአንድ ካላሰላለፈ የኢትዮጵያ አንድነት ርቆ የተሰቀለ ባዶ ተስፋ ከመሆን አያልፍም። by: 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ዐማራነት ነፃነት፣ ዕኩልነት አንድነት ነው!
ኢትዮጵያ በቆራጥና ጀግና ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

Thursday, 4 August 2016

ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና! (አንዱዓለም ተፈራ) – የእስከመቼ አዘጋጅ

ረቡዕ ሐምሌ ፳ ፯ ቀን ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት ( 08/03/2016 )

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግሌ አላውቀውም፤ ነገር ግን እስከሚበቃኝ ድረስ አውቀዋለሁ። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እኔን አያውቀኝም፤ ነገር ግን እኔና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ጠበቆቹ እንዳለን ያውቃል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደር ውስጥ አንገረብ እስር ቤት ባሁኗ ሰዓት – ምሽት፣ ረቡዕ ሐምሌ ፳ ፯ ቀን ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት – ለጊዜው አለ። እዚያ እንዲቆይ ያደረገው ወገኑ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፤ በእስር ቤት ያለ ግለሰብ፤ በትክክል ይሁን በድፍረት በመታሰሩ ብቻ፤ ጠበቃ ያስፈልገዋል። እናም ጠበቃው ነኝ።
የጠበቃ ሀ፣ ሁ ው፤ ሠርተሃል ከተባለበት ወንጀል በፊት፤ ፍርድ ቤቱን መመዘን ነው። እናም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የሚቀርብበትን ፍርድ ቤት እንመርምር። እንደማንኛውም ፍርድ ቤት ቆጥረን ይሄን ፍርድ ቤት ብንመለከተው፤ ሕግ አለ፣ ፖሊስ አለ፣ ዳኛ አለ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ፤ ፍርድ ቤቱን ያቋቋመው መንግሥት አለ። ፍርድ ቤቱን ስንመረምር፤ ያቋቋመውን መንግሥትም ማጤን አለብን። ከላይ ያነጠብኳቸውን እያንዳንዳቸውን ነጣጥሎ መመልከቱ ችግር ይፈጥራልና፤ እስኪ ጠቅለል አድርጌ በአንድነት ላቅርበው። በርግጥ አንድነት ባሁኑ ዘመን አስቸጋሪ ከመሆኑ በላይ፤ ራሱ አንድነት የሚለው ቃል ወንጀል ሆኗል። ነገር ግን፤ የማያመልጡትን መረብ፤ በተስፋ ቃኝተው፤ መውጪያ በመፈለግ መጣር ያለ ነውና፤ በዚያው ላምራ።
ፍርድ ቤቱን ያቋቋመው መንግሥት፤ የኅብረተሰብን ብሶት አንገብኩ ብሎ፤ ትጥቅ አንስቶ፤ በጉልበቱ ሥልጣን ላይ የወጣ አካል ነው። እናም ከተፈጥሮው ምንነት የተነሳ፤ ማንንም የኅብረተሰብ ብሶት አንስቶ የሚታገልን ግልሰብ ሆነ ቡድን፤ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ፤ ሕጋዊ ፈቃድም ሆነ የሞራል ብቃት የለውም። የዚህ አካል መሪዎች፤ የሥልጣን ንጥቂያ ግብግባቸው ባይሳካላቸው ኖሮ፤ ራሳቸው ፀረ-ሕዝብ፣ ፀረ-ሀገር፣ ፀረ-መንግሥት ተብለው በዚሁ ፍርድ ቤት ይቀርቡ ነበርና!
በሌላ በኩል ደግሞ፤ አሁን በሀገራችን ሕግ የለም። አሁን በሀገራችን ደንብ የለም። አሁን በሀገራችን የአስተዳደር መመሪያ የለም። ያለው የጉልበት ግዛት ነው። ያለው፤ ባለጉልበቱ የሚፈልገው፣ በፈለገው መንገድ፣ በፈለገው ጊዜና በፈለገው ቦታ፤ ባሻው መንገድ መፈጸሙ ብቻ ነው። ቋሚ የሆነ ሕግ የለም። እንዲያውም እንደ ዕውነቱ ከሆነ፤ ሕግ ቦታ የለውም። ቦታ ያለው፤ ገዥው የሚፈልገው ጉዳይ ብቻ ነው። ከዚህ ተነስተን፤ ዳኛው፣ ፖሊሱ፣ ሕጉ፣ ጠበቃዎቹ፣ ሁሉ የገዥውን ፍላጎት አስፈጻሚ አካል ለመሆናቸው ጥርጣሬ ሊኖረን አይገባም። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በመከላከል ሊቀርብ የሚፈልግ ጠበቃ ሁሉ፤ ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የበለጠ ወንጀለኛ ሆኖ እስር ቤት ይገባል። ለዚህ ነው፤ አንድ ብቻዬን ሳልሆን፤ በሚሊዮን የምንቆጠር ኢትዮጵያዊያን ለሱ ጥብቅና የቆምነው፤ አንዳችን ስንታሰር ሌላችን በየተራ ለመታሰር ተዘጋጅተን።
ቀረብ ብለን ስንመለከት፤ ፍርድ ቤቱ በተግባር የገዥው ክፍል መሣሪያ ከመሆኑ አልፎ፤ ከላይ እስከታች የተሰገሰጉት፤ የዚሁ ገዥ ፓርቲ አባላት ናቸው። የገዥው ፓርቲ አባላት ሙሉ በሙሉ ትግሬዎችና ትግሬዎች ብቻ ናቸው። በወሳኝነት ያሉት የዚሁ ፍርድ ቤት አባላት ደግሞ፤ ሁሉም በአባልነታቸው ትግሬዎች ናቸው። እና አንድ አማራ ወልቃይቴን፤ ለዚያውም በጥቅማቸው በወልቃይት ላይ ለመጣ ወኪል፤ በደሉን ሆነ ወንጀሉን ያዳምጣሉ ማለት፤ ከሰማይ መና ይወርዳል ብሎ ነጠላ መዘርጋት ይሆናል። ወልቃይት እኮ የታሪክ ወይንም የሕግ ጉዳይ ሳይሆን፤ የትግሬዎች ክልል የጥቅም ጉዳይ ነው! እናም የወልቃይትን ጉዳይ የትግሬዎች መንግሥትና ክልል መዋቅርና ዳኞች ይመልከቱት ማለት፤ ወይንም በዚያ ቀርቦ ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት መሞከር፤ ትርጉም የማይሠጥ ሂደት ነው። በጎንደሩ ሰላማዊ ሰልፍ አንድ መፈክር ከሁሉ ደምቆ ታይቶኛል፤ “ትግሬ እንጂ ትግራይ ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም!” የሚለው።
በመጀመሪያ ነገር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የመጀመሪያው ወይንም የመጨረሻው እስረኛ አይደለም። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ታስረው፤ በዚያው ዕድሜያቸውን ጨርሰዋል። እስክንድር ነጋ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ የእስልምና ተከታይ አቤቱታ አቅራቢዎች፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች፤ አሁንም በስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተቋማትና መሪዎቻቸው በሙሉ ተባረዋል፣ ተደምስሰዋል፣ ተገድለዋል፤ – የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበር፣ ወ. ዘ. ተ. ።
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለምንድን ነው ለእስር የተዳረገው? ተመልከቱ፤ በሌሊት ሊያፍኑት የመጡትን የትግራይ መሪ የአባይ ወልዱ ታጣቂዎች፤ “በሕግ የምትፈልጉኝ ከሆነ፤ ሲነጋ፤ መጥታችሁ ልትወስዱኝ ትችላላችሁ። እኔ በሕግ የሰፈረልኝን መብት ጠንቅቄ የማውቅ ግለሰብ ነኝ።” ቢላቸው፤ በግድ ገብተው እጁን ሊይዙት ሞከሩ፡ ራሱን እንደሚከላከል ሲገልጽላቸው፤ ተኩሰው ዘው ብለው ገብተው ሊያፈኑት ጣሩ።  ራሱን ለመከላከል እሱም ሞከረ። በዚህ የተኩስ ልውውጥ አመለጠ። ሕዝቡ ከጎኑ ቆመ። ለሕዝቡና ለሕዝቡ ድምጽ ደንታ የማይሠጠው የትግራይ ክልል ገዥና የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ዋና መሪ ብሎም የኢትዮጵያ መሪ፤ ጉልበት እንጂ ራሱ ያወጣውን ሕግም ስለማያከብር፤ ሕዝቡን ጥሶ ሰዎችን ገደለ። ቀደም ብሎ አፍኖ የያዛቸውን የወልቃይት ሕዝብ አቤቱታ ወኪሊችን ሰወረ። አሁንም የውሸት ውርጅብኝ በማከታተል፤ ሕዝቡን ወንጀለኛ ራሱ ግን ሕግን አክባሪ አድርጎ አስቀመጠ። መቼም ማን ሕግን አክባሪ፤ ማን ሕግን ጣሽ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀዋል።
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ወልቃይትን ለዘለዓለም ታድጓታል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደርን በሕይወቱ ጠመንጃውን አንስቶ ታድጓታል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አማራውን በማንነቱ እንዲኮራ ታድጎታል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ኢትዮጵያን ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነፃ እንድትሆን ክንፉን ዘርግቶ ታድጓታል። ነገ ዛሬ የተጫረው እሳት ምን ሊያስከትል እንደሚችልና ምን መሆን እንዳለበት በጃችን ነው። አሁን በዚች ሰዓት ግዴታችን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን መታደግ ነው። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በዚህ ሕገ-ወጥ በሆነ መንግሥት ፍርድ ቤት ትክክለኛ ፍርድ አያገኝም። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነፃ የሚሆነው በቆመለት ሕዝብ ብቻ ነው። ምንም ያጠፋው ነገር እንደሌለ ሁላችን እናውቃለን። ያደረገው ቢኖር፤ አማራ ነኝ እንጂ ትግሬ አይደለሁም። በጎንደሬነቴ የመጣ ሕይወቴን እሠጣለሁ። ነፃነቴን እፈልጋለሁ፤ ማለቱ ብቻ ነው። ነፃነቱን ለሚሻ አብረን መቆም አለብን። በአንድነት እንሰለፍ።
ከታላቅ አክብሮታ ጋር
አክባሪያችሁ አንዱዓለም ተፈራ

አንድ ሰሞን ከሙኒኮች ጋር – በኤፍሬም ማዴቦ

ኤፍሬም ማዴቦ
አባባ . . .  አባባ . . . . ስማ አባባ ረሳህ እንዴ አለኝ ያ ባለፈዉ ነኃሴ ወር ስንለያይ ያስለቀሰኝ ልጄ።  ምኑን አልኩት።  ቅድም ምሳ ላይ የነገርኩህን . . . እንዴ!  እሱንማ እንዴት እረሳለሁ። Please don’t አባባ! …… I will not! ሲረጋጋና ደስ ሲለዉ ታየኝና ልቤን ደስ አለው። ልጄ ኮሌጅ የሚገባበት ቀን እኔ ደግሞ ከትግል ጓደኞቼ ጋር የምንገናኝበት ቀን ናፍቆናል። አባባ Good luck አለኝ። እኔም ይቅናህ አልኩት። Good luck እና ይቅናህ የተባባልነው እኔ እሱ የሚመኘዉ ኮሌጅ እንዲገባ እሱ ደግሞ እኔ በድል ኢትዮጵያ እንድገባ ነበር። ሁለታችንም ይቅናን . . . አሜን!!!

አዉሮፕላን ዉስጥ ገብቼ ከተረጋጋሁ በኋላ ኢር ፎኑን ጆሮዬ ውስጥ ሰክቼ አይፎኔ ላይ “Play” የሚለዉን ስጫነዉ ጥላሁን ገሰሰ “አራዊቱ ሁሉ መጥቶ ቢከበኝ” እያለ ጀመረኝ። የምወደው ዘፈን ነበርና ደጋገምኩት። ጥላሁንኮ ድምጻዊ ብቻ አይደለም ነቢይም ነዉ፤ የዛሬ ስንትና ስንት አመት በአራዊቶች እንደምንከበብ ተንብዮ ነበር። የሚቀጥለው ዘፈን ገና ሲጀምር ምን መሆኑ ታወቀኝና. . . . . ኧረ በፍጹም. . . እንዴት ተደርጎ አልኩና አይፎኔን ዘግቼዉ ኪሴ ዉስጥ ከተትኩት። “መለያየት ሞት ነዉ” የሚለዉን የጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃ ብወደዉም የጠነከረዉ ሆዴ እንዲባባ በፍጹም አልፈለኩም። አይፓዴን አወጣሁና የአስናቀች ወርቁን ሰዉነት እየሰረሰር ገብቶ አንጀት የሚያርስ ክራር መኮምኮም ጀመርኩ። አስናቀች ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ቦታ ወሰደችኝ፤ ደግነቱ ዬትም ትዉሰደኝ ዬት መልሳ መላልሳ እዚያዉ አዉሮፕላኑ ውስጥ ታመጣኝ ነበር . . .  አለዚያማ!

አዉሮፕላኑ ወንበር ላይ አንደተኛሁ ከአንድ ጎኔ ወደ ሌላዉ ጎኔ ስገላበጥ ሁለት የተለያዩ ድምጾች ተራ በተራ ጆሮዬ ዉስጥ ገቡ። ከአይፓዴ የሚወጣዉ ድምፅ “እልም አለ ባቡሩ” ይላል፥ የአዉሮፕላኑ ድምጽ ማጉያ ደግሞ “Welcome to Munich” ይላል። እንቅልፋም አይደለሁም፥ እንቅልፌን ሳልጨርስ የሚቀሰቅሰኝ ሰዉም ሆነ ምንም አይነት ድምጽ ግን ጠላቴ ነዉ። ደግሞም የእንቅልፍ ነገር ሆኖብኝ ነዉ እንጂ ሙኒክ መድረሴን ወድጄዋለሁኮ።

እኔንና ሌሎች ከ180 በላይ መንገደኞችን የጫነዉ ዩናይትድ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 106 አዉሮፕላን ጎማዎች ከሙኒክ አዉሮፕላን ማረፊያ ወለል ጋር ሲላተሙ ያ ለካሳ ተሰማ ዘፈን አልበገር ያለዉ እንቅልፌ ዳግም አይመጣ ይመስል እልም ብሎ ጠፋ። እኔም የምን እንቅልፍ አልኩና ሙኒክን ለማየት ቸኮልኩ። ሙኒክ ሲባል ከልጅነቴ ጀምሮ እሰማለሁ እንጂ እቺን ዉብ የባቫሪያ ከተማ ሳያት የመጀመሪያዬ ነበር። አይፎኔን አወጣሁና ከአስመራ አሜሪካ ከገባሁ ጀምሮ ስልክ እየደወለ ሙኒክ ካልመጣህ እያለ ለሚጨቀጭቀኝ የአገሬ ሰዉ ስልክ ደወልኩ. . . .  ጋሼ ደረስክ እንዴ አለኝ። አዎ እናንተን እየጠበኩ ነዉ አልኩት። ጋሼ እኛ መግባት አንችልም ስትወጣ ታየናለህ አለኝ። ሁለት ተንጠልጣይ ሻንጣዎቼን ግራና ቀኝ ትከሻዬ ላይ አንጠልጥዬ ሻንጣ የጫንኩበትን ጋሪ እየገፋሁ ወደ መዉጫዉ አመራሁ። የሁለቱ ሻንጣዎች ክብደት ትከሻዬን ሲያጎብጠዉ ግዜ ሁለተኛ ለማንም ሰዉ ዕቃ አላደርስም ብዬ ማልኩ። ሁሌም እየማልኩ የምረሳዉ መኃላ ቢኖር ይህ ብቻ ነዉ። ወደ መዉጫዉ ስጠጋ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተ። ታክሲዉና አዉቶቡሱ፤ ሸኚዉ፤ እንግዳ ተቀባዩ፤ እኔን መሰሉ ወደ ሙኒክ የሚመጣዉና ሙኒክን የሚለቀዉ መንገደኛ እዚህም እዛም ይተራመሳል። ከዚህ ሁሉ የሰዉና የመኪና ትርምስ ዉስጥ አይኔ ተሽቀዳድሞ ያረፈዉ በዚያ በዉበቱና በድምቀቱ የባንዲራዎች አዉራ በሆነዉ የአገሬ ባንዲራ ላይ ነበር። ሊቀበሉኝ የመጡ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ያንን በትንሽነቴ “ደሙን ያፈሰሰ” ብዬ የሰቀልኩትንና ማታ “ተጣማጅ አርበኛ” ብዬ ያወረድኩትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘዉ ሲመጡ አየሁና ተጠጋኋቸዉ። ሰንደቅ አላማዉ “አምባሻ” ስለሌለበት አመንኳቸዉ። አለዚያማ ፊቴን አዙሬ ጉዞዬን ወደ አስመራ እቀጥል ነበር እንጂ አምኜ አልጠጋቸዉም ነበር። ወይ ጉድ …… ዘመን አያመጣዉ ነገር የለም. . . . . .  የምንተነፍሰዉንም አየር መጠርጠር ጀመርንኮ!

ሙኒክ የገባሁት ሐሙስ ጧት አስር ሰአት ተኩል ላይ ነበር። እሁድ ጧት ለስራ ጉዳይ ሲዊዘርላንድ እስክሄድ ድረስ ከሁለት ቀን ተኩል በላይ ሙኒክ ዉስጥ ቆይቻለሁ። ግን እንኳን ሁለት ቀን ተኩል ግማሽ ቀንም የቆየሁ አልመሰለኝም። ነገሩ ምንድነዉ ብዬ ተገረምኩ። ሚስጢሩ የገባኝ አስመራ ገብቼ ከእንቅልፌ ስነቃና የቀረብኝን ሳዉቀዉ ነዉ። ሙኒኮች በልቼ የምጠግብ፥ ጠጥቼ የምረካ አይመስላቸዉም። ያገኙኝ ሰዎች ሁሉ ብላ፤ጠጣ፤ እንሂድ፤ እንዉጣ፤ ምን እንግዛ፤ ምን እናምጣ፤ ምን ትፈልጋለህ፤ ምን አነሰ ነዉ ጥያቄያቸው። የሙኒክ ወገኖቼ ከኑሯቸዉ በላይ ሲያስቡልኝና ከራሳቸዉ በላይ ሲሳሱልኝ አይቼ እንደ ዐለት የማይነቃነቅ ደጀን አለኝ ብዬ ተመክቼባቸዋለሁ። በተለይ ሙኒክ ውስጥ ያየኋቸዉ ሴቶች እህቶቼ መጥተን እንቀላቀላችሁ እንጂ ከተማ ዉስጥማ ምን እናደርጋለን ነበር ጥያቄያቸዉ። የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ የቀረዉን የመጨረሻ የፍርሃት ጠብታ ጠራርገዉ ሲወስዱት ታወቀኝና ድፍረቴ ከአናቴ አልፎ ሲያንሳፍፈኝ ተሰማኝ። እቴጌ ተዋበች ለቋራዉ አንበሳ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ ለዳግማዊ ምንሊክ ጉልበት፤ ብርታትና ጽናት እንደሆኗቸው ሁሉ ለኔም የሙኒክ ሴቶች ደሜ ዉስጥ ገብተዉ ብርታት፤ ልቤ ዉስጥ ገብተዉ ጽናት ሆኑኝ። አደራ. . . .  ሴት የላካዉ ሞት አይፈራም ብላችሁ ለቆራጥ እህቶቼ የምሰጠዉን ምስክርነት እንዳታሳንሱብኝ። የሙኒክ ሴቶች የልብ ልብ የሰጡኝ ዕቃችንን ጠቅልለን ካልተከተልንህ እያሉ ነዉ እንጂ አይዞህ በርታ አለንልህ እያሉ ብቻ አልነበረም።

ቀኑን እንደ ደዋሪ ከወዲህ ማዶ ወዲያ ማዶ ስሽከረከር ዉዬ ስለደከመኝ አርብ ዬካቲት 26 ቀን (Feb 26) አልጋዬ ዉስጥ የገባሁት በግዜ ነዉ። ከሆቴሉ ሰራተኛ ቁልፍ ተቀብዬ መኝታ ክፍሌ ስደርስ አልጋዋ እንኳን ሙሉዉን ኤፍሬም አንድ እግሩንም ተሸክማ የምታድር አልመሰለችኝም። ትንሽዬ አልጋ ናት። ሽንት ቤቱና መታጠቢያ ቤቱም እንደዚሁ። ብቻ ምን አለፋችሁ አዉሮፓ ዉስጥ ትልቅ ነገር ያለም አይመስል። መንገዱ፤ መኪናዉ፤ ሀንጻዉና መኖሪያ ቤቱ ሁሉም ነገር ትንሽ ነው። አዉሮፓዉያን አንድ ነገራቸዉ ግን ትልቅ ከትልቅም ትልቅ ነዉ። ለሀይል ቁጠባና (Energy Conservation) ለአካባቢ ጥበቃ የሚሰጡት ቦታ እጅግ በጣም ትልቅ ነው። አዉሮፓ ስሄድ ሁለት ጉዳዮች ነበሩኝ። አንደኛዉ የሙኒክ ኢሳት ቤተሰቦች ባዘጋጁት የገንዘብ ማሰባሰብ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የትግል ጓደኛዬን የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ለማክበር ነዉ።

አርብ ማታ በግዜ ቆጤ ላይ ስለተሰቀልኩ ቅዳሜ ዬካቲት 27 ቀን ከእንቅልፌ ስነቃ እንደልማዴ እየደጋገመ አላዛጋኝም ወይም ተኛ ተኛ አላሰኘኝም። ፈጣን ሻወር ወስጄ ልብሴን ለባበስኩና ያደርኩበት ሆቴል በነጻ ብላ ያለኝን ቁርስ መቆርጠም ጀመርኩ። ከቁርሱ ይልቅ የጣመኝ ቡናዉ ነበርና አንዴ ደግሜ ሶስተኛዉን ይዤ ጠረቤዛ ቀየርኩና አይፓዴን ከፍቼ ዜና መቃረም ጀመርኩ። ኦሮሚያ ዉስጥ ከሦስት ወራት በፊት የተቀሰቀሰዉ ሀዘባዊ ቁጣ አለመብረዱ፤ የአዲስ አበባዉ ታክሲ ሾፌሮች አድማና ጎንደር ዉስጥ በየቦታዉ የሚፈነዳዉ ህዝባዊ አመጽ ትኩረቴን ከሳቡ ዜናዎች ዉስጥ ዋና ዋናዎቹ ነበሩ። ዜና ማንበቡን ጨርሼ ቀና ስል ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞና ጓደኛዉ መጡና . . . ጋሼ ምሳ እንብላ እንጂ ብለዉኝ ተያይዘን ወጣን።

ፉጨቱ፤ ሆታዉ፤ መዝሙሩና አዳራሹ ዉስጥ በየማዕዘኑ የሚዉለበለበዉ ሰንደቅ አላማችን ገና ስብሰባው አዳራሽ ዉስጥ ሳልገባ በሩቁ የአዳራሹን ስሜት ነገረኝ። አዳራሹ ዉስጥ ያሉት ኢትዮጵያዉያን አላማቸዉ አላማዬ ምኞታቸዉ ምኞቴ እንደሆነ ካውቅኩ ቆይቷል። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ስሜታቸዉን ሳይ ግን ልባቸዉ ከልቤ ተገናኘና ደሜ ደማቸዉ፤ ሞቴ ሞታቸዉ መሆኑ ዉስጤ ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ። ከሰዉነቴና ከሰዉነታቸዉ የአካል ፍላጭ ወጥቶ አዲስ አካል ሲፈጠር ታወቀኝ። አዎ. . . ዜግነት መሰረቱ፤ እኩልነት ማዕዘኑ፤ ነጻነት ጣራዉ፤ ፍትህ ወለሉ፤ አንድነትና ዲሞከራሲ ድርና ማጉ የሆነ ፍጹም አዲስ አካል ሲፈጠር ተሰማኝ። ፍጹም ልዩ ስሜት ነበርና ወደድኩት። አዳራሹ ዉስጥ ገብቼ ብዙም ሳልቀመጥ እኛ በህይወት እንድንኖር የሞት መስዋዕትነት ለከፈሉልን ጀግኖች የሂሊና ጸሎት እናድርስ ሲባል አዳራሹ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ በሙሉ ከመቀመጫዉ ተነሳ። አዳራሹ ላንዳፍታ ሰዉ የሌለበት ኦና ቤት መሰለ። ያንን ሰው የሞላበት የስብሰባ አዳራሽ የዝምታ ጽላሎት ዋጠዉ። ሁላችንም በአንድ አፍንጫ እንተነፍስ ይመስል ትንፋሻችን እራሱ አንድ ሆነ።

ሁለቱ የኢሳት ጋዜጠኞች አፈወርቅ አግደዉና ሀይሉ ማሞ ማይክሮፎናቸዉን ጨብጠዉ መድረኩ ላይ ቦታ ቦታቸዉን ይዘዋል። አዳራሹን የሞላዉ ህዝብ እነሱን እነሱ ደግሞ ህዝቡን ያዩታል። ጋዜጠኛ ሀይሉ ማሞ ለእለቱ ጨረታ የቀረበዉን ዉብ የኢሳት አርማ ለተሰበሰበዉ ህዝብ ሲያሳይ ያ የሂሊና ፀሎት ሲደረግ ዝምታ የዋጠዉ አዳራሽ በጭብጨባ ጩኸት የፈረሰ መሰለ። ጨረታዉ በአንድ ሺ ዩሮ ተጀመረ። አፈወርቅ አግደዉ መድረክ ላይ ወጣና በዚያ ጀት ድምጹ ንግግሩን ሲጀምር አዳራሹ ዉስጥ ኢሳት ቴሌቭዥን የተከፈተ መሰለኝ። ከጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ አፍ እንደ አብሪ ጥይት እየተወረወሩ የሚወጡት ቃላት አድራሻቸዉ ጆሮ ሳይሆን የተሰበሰበዉ ሰዉ ኪስ ዉስጥ ይመስል ሁሉም እየተነሳ ያለዉን ይለግስ ጀመር። በአንድ ሺ ዩሮ የተጀመረው ጨረታ ብዙም ሳይቆይ አምስት ሺ ዩሮ ደረሰ። አዳራሹ ዉስጥ የነበርኩት ብቸኛ የበረሃ ሰዉ ጨረታዉ አምስት ሺ ዩሮ ላይ የሚቆም መስሎኝ ነበር። ምን ላድርግ እዉነቴን ነዉ። በረሃ ዉስጥ ብቸኛዉ የገንዘብ ቋንቋ ናቅፋ ብቻ ነው።  አምስት ሺ ዩሮ ደግሞ እጅግ በጣም ብዙ ናቅፋ ነዉ። ለሁሉም ጨረታዉ እኔ እንዳሰብኩት አልቆመም፤ እንዲያዉም የማሸነፍ እልህ ዉስጥ በገቡ ከተሞችና ግለሰቦች መካከል ፉክክር ፈጠረና 6 ሺ፤ 7 ሺ፤ እና 8 ሺ እያለ ቀጠለ።

የሙኒክ ጨረታ ትዉስታቸዉ በበጋው ፀሐይና በክረምቱ ዝናብ የማይደበዝዝ ሶስት ትዝታዎች ጥሎብኝ አልፏል። ለወትሮዉ እኔ ጨረታ የማዉቀዉ ግለሰቦች በቡድን ወይም በግል ሲጫረቱ ነዉ። የሙኒኩን ጨረታ ለየት ያደረገብኝ አንዱ ነገር የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ሙኒክ፥ በርሊን፥ ፍራንክፈርትና ኑረምበርግ. . .  ወዘተ እያሉ በከተማ ጭምር ያደረጉት ጨረታ ነዉ። እንግዲህ ይታያችሁ አዉሮፓ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ጨረታ በተካሄድ ቁጥር የሚጫረቱት በግል፥ በቡድንና በከተማ ጭምር ከሆነ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን ለፍትህና ለነጻነት ለሚደረገዉ ትግል የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከሌሎቻችን ይበልጣል ማለት ነው። ሌላዉ የሙኒክ ትዝታዬ የጀርመን ኢትዮጵያዉያን ወያኔን ለማጥፋት በሚደረገዉ ትግል ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባደረጉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን በነ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ርእዮት አለሙ፤ እስክንድር ነጋ፤ ኡስታዝ አቡበከር፤ በቀለ ገርባና አንዱአለም አራጌ . . . ወዘተ ስም መጫረታቸዉ ነዉ። በእነዚህ ጀግኖች ስም የተደረገዉ ጨረታ የጀግኖቹ ስምና ህያዉ ስራቸዉ ከልባችን እንዳይጠፋ ማድረጉ ብቻ ሳይሆን የእነሱን ፈለግ እንድንከተል የሚገፋፋ ነበርና ለሙኒኮች ያለኝ አድናቆት ከፍተኛ ነው። Dank u München!

ሶስተኛዉ ትዝታዬ ሙኒክን ለቅቄ አስመራ ከገባሁ ከሶስት ሳምንታት በኋላ አሁንም ፊቴ ላይ አለ። ካሁን በኋላም ቢሆን እየረሳሁ ብዉልና ባድር ሶስተኛዉን ትዝታዬን የምረሳ አይመስለኝም። ይህ እንደ አፍላ ፍቅር ልቤ ዉስጥ ተተክሎ የቀረዉ ትዝታ የሶስት ሰዎች ትዝታ ነዉ። በአንድ በኩል ፊት ለፊት የመጀመሪያዉ ረድፍ ላይ ተቀምጦ ከተሸነፍኩ ሞቼ እገኛለሁ የሚል ዶክተር አለ። በሌላ በኩል ደግሞ አዳራሹ ኋላ ሆነዉ አንሸነፍም ብለዉ የመሸጉ ባልና ሚስት አሉ። እነዚህ ሶስት ሰዎች ኋላና ፊት ተቀምጠዉ ያካሄዱት ለሰአታት የዘለቀ ፉክክር ተሰብሳቢዉን እንደ ልብ ሰቃይ ድራማ ከፍና ዝቅ ያደረገ ልዩ ትርዕት ነበር።

ዶክተሩ የህክምና ዶክተር ነዉ። ታላቄ ነዉ ሆኖም በቁመት እንጂ በዕድሜ ብዙ አንበላለጥም። የምፈልገዉን ነገር አድርግልኝ ስለዉ ያደርጋል፤ ና ስለዉ ይመጣል። ከሙኒክ ሲዊዘርላንድ እንሂድ ስለዉ ሳያቅማማ ስራዉን ጥሎ ነዉ የተከተለኝ። ቀልዱ፥ጨዋታዉና ቁምነገሩ አይጠገብም፥ በተለይ ከአፈወርቅ አግደዉ ጋር ሲተራረቡ የአራት ሰአቱ የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ እንኳን ያለቀ የተጀመረም አይመስልም ነበር። ብቻ ምን ልበላችሁ ዶ/ሩ ለኔ የነበረዉ አክብሮትና ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ ያለው ፍቅር በኔ ደካማ ብዕር የሚገለጽ አይደለም።

ባልና ሚስት ናቸዉ፥ የተቀመጡት አዳራሹ የመጨረሻ ረድፍ ላይ ነዉ። አይቸኩሉም ደግሞም አይዘገዩም። ፈጣሪ ያደላቸዉ ስጦታ ነዉ መሰለኝ ትክክለኛዉን ግዜ ያዉቁታል። ሲማከሩ ጆሮና አፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ። ሲስማሙ ስምምነታቸዉን የሚናገረዉ ባልየዉ ነዉ። የእነዚህ ባልና ሚስት ፍላጎት ጨረታዉን ማሸነፍ ሳይሆን ኢሳትን መርዳት መሆኑን የሁለቱም ፊት በግልጽ ይናገራል። ከላይ ባስተዋወቅኳችሁ ዶክተርና በእነዚህ ባልና ሚስት መካከል የተደረገዉ የጨረታ ፉክክር አዳራሹ ዉስጥ የተሰበሰበዉን ኢትዮጵያዊ ልብ ሰቅዞ የያዘ ፍጹም ልዩ ድራማ ነበር። ፉክክሩ ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና እኛነት የታየበት እንዲሁም የማይቀረዉን ብሩህ የአገራችንን ተስፋ ከወዲሁ በናሙና መልክ ፈንጥቆ ያሳየ ዉብ መድረክ ነበር። በገንዘብ አስተዋጽኦ መልኩም ቢታይ ባልና ሚስትና ዶክተሩ ያደረጉት ፉክክር የጨረታዉን ጣሪያ ከሃያ ሺ ዩሮ በላይ አድርሶታል። በነገራችን ላይ እዚህ መጣጥፍ ዉስጥ ስማቸዉን ጠቅሼ ብጽፍ ደስ የሚለኝ ብዙ ኢትዮጵያዉያን አሉ። የማላደርገዉ ክፉ ብቻ ሳይሆን ጭራሽ ደንቆሮ የሆነ ጠላት ስላለን ነዉ። ይህ ጠላት የደደብነቱ ብዛት የሥልጣን ክልል ያለዉም አይመስለዉም፤ አዉሮፓና አሜሪካ ዉስጥ የጻፈ፥ የተናገረና ሀሳቡን የገለፀ ኢትዮጰያዊ ላይ እድሜ ልክ እስራት ይፈርዳል። ደሞስ ጭንቅላታቸዉ በንፍጥ ብቻ የተሞላና ሰዉነታቸዉ በተዘረፈ ሀብት የደለበ ሰዎች ከዚህ የተለየ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

ከሙኒክ የሲዊዟ መናገሻ ቤርን ድረስ የአራት ሰአት መንገድ ነዉ። በረጂም በረራና በቅዳሜዉ የአዳራሽ ዉስጥ ቆይታ የተዝለፈለፈዉ ሰዉነቴ እየከዳኝ ቢሆንም የግድ ሲዊዘርላንድ መሄድ ነበረብኝና ተንገዳግጄ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ የአራት ሰአቱን መንገድ ተያያዝኩት። የሙኒከ ሲዊዘርላንድ መንገድ የሚያልፈዉ በኦስትሪያ በኩል ነዉ። ከጀርመን ወጥቼ ኦስትሪያ መግባቴን ያውቅኩት ሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ የቆሙትን ፖሊሶች ስመለከት ነዉ፤ ለዚያዉም ባይነገረኝ ኖሮ አላዉቅም ነበር። መኪናዉ ዉስጥ እንቅልፍ ብጤ ሞካክሮኝ ነበር ግን የጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉና የዚያ ደግ ዶክተር ጨዋታ እንኳን እንቅልፍ ሌላም ነገር የሚያስረሳ ነበርና ጨዋታቸዉ እንቅልፌን አባረረዉ። የመኪናዉ ዉስጥ ቀልድ፥ ተረብና ጆክ ከአካባቢዉ የተፈጥሮ ዉበት ጋር ሆነዉ መንፈሴን እያደሱት ድካሜን አስረሱኝ። አፈወርቅን የምትወዱት በቴሌቭዥን መስኮት ዉስጥ ብቻ አይታችሁት ከሆነ ብዙ ገና ብዙ ይቀራችኋል . . . ምኑን አያችሁና። አፈወርቅ ሲቀርቡት ጨዋታዉ፤ ቀልዱና ቁም ነገሩ አይጠገበም። ስለምንም ነገር ሲናገር የራሱ የሆነ ልዩ ዜማና ቃና አለዉ። ታሪክ ሲናገር በታሪኩ ዉስጥ ይዟችሁ ያልፋል። የታሪኩን መቸትና የተዋንያኑን ስም ከአባት ስም ጋር ሲናገር መጽሐፍ የሚያነብ እንጂ በቃሉ የሚናገር አይመስልም። የአማርኛ ቋንቋ በተለይ የቅኔ ችሎታዉ ይኸ ሰዉ ዋልድባ ነዉ ጋሙጎፋ ተወልዶ ያደገዉ ያሰኛል።

ከሙኒክ ተወጥቶ ኦስትሪያ እስኪገባ ድረስ ከመንገዱ ግራና ቀኝ የሚታየዉ ዘመናዊ እርሻ ከሳንሆዜ ሳንታክላራ ሲኬድ የሚታየዉን ሜካናይዝድ እርሻ አስታወሰኝ። የአዉሮፓና የአሜሪካ መመሳሰል ገረመኝ። በሃሳቤ ረጂም ርቀት ወደኋላ ተጓዝኩና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስማር ከአዋሳ አዲስ አበባ በአዉቶቡስ ስጓዝ አዉቶቡሱ ቆቃን እንዳለፈ አርሲ ነጌሌ እስኪደርስ ድረስ አልፎ አልፎ  የማያቸዉ ትናንሽ እርሻዎች ፊቴ ላይ መጡ። አስናቀች ወርቁ “እንደ መቀነቴ ዞሬ ዞሬ እዚያዉ” ብላ የተጫወተችዉ ዘፈን ትዝ አለኝና ሆዴ በቁጭት ተሞላ። አዎ የኛ ነገር ዞሮ ዞሮ እዚያዉ ነዉ። እርሻው እዚያዉ፤ ገበሬዉ እዚያዉ፤ ፋብሪካዉ እዚያዉ ባጠቃላይ የኑሮ ደረጃዉ እዚያዉ ነዉ። እዚያዉ ድሮ የነበረበት ቦታ። ወደፊት እናያለን እንጂ ወደፊት አንሄድም። ይህንን ሳስብ ተቆጨሁ . . . ተናደድኩ።  ለምን አልናደድ ለምንስ አልቆጭ . . .  እኛና ድህነት፤ እኛና ኋላቀርነት፤ እኛና እየረገጡ ከሚገዙን ጋር መሞዳሞድ ሞት ካልለየን በቀር ላንለያይ የቆረብን ይመስላልኮ!

እኛ ኢትዮጵያውያን ከአዉሮፓና ከአሜሪካ ለምንድነዉ ይህን ያህል የምናንሰው ብዬ እራሴን ጠየኩና መልሳ ሳጣ የአዉሮፓን ዉበት ማድነቄን ቀጠልኩ። እዉነቱን ለመናገር የኋላ ቀርነታችን ምክንያት ጠፍቶኝ አይደለም። ለምን መናጢ ደሃዎች እንደሆንም ጠፍቶኝ አይደለም።  ችግሩ. . .  የኋላ ቀርነታቸንን ምክንያት ባሰብኩ ቁጥር ከዚህ አሳፋሪ ኋላ ቀርነት ለመላቀቅ የምናደርገዉ ጥረት እምብዛም መሆኑን ስለማዉቅ ማሰቤን አቆምና ንዴትና ቁጭት ዉስጥ እገባለሁ። የኔ ነገር ደግሞ ጉድ ከጉድም ጉድ ነው፤ አራሴን ስጠይቅ የማገኘዉ መልስ ቁጭትና ንዴት ነዉ። ቁጭትና ንዴት ደግሞ እንደገና ጥያቄ ያጭሩብኛል። ይገርማል .…  አገሬ ከድህነት ኡደት እኔ ከጥያቄ ኡደት ላንላቀቅ የተማማልን ይመስላል። የራሱ ፊደል፥ ስነጽሁፍና የራሱ የሆነ የዘመን መቁጠሪያ ቀመር ያለዉ ሀዝብ እንዴት ያልሰለጠነ ህዝብ ተበሎ ይጠራል? አባይን፤ አዋሽን፤ ሸበሌን፤ዴዴሳን . . . ወዘተ ይዞ አገር እንዴት ይራባል? አክሱምን፤ ላሊበላንና ፈሲለደስን የገነባ ህዝብ ለምን ከኋላ ቀሮች ተርታ ስሙ ይጻፋል? ለምን? ለምን? ለምን?

ኦስትሪያ ስደርስ እርሻዉ፤ መኪናዉ፤ ከተማዉ፤ የሰዉ መልክና ቋንቋዉ ምንም አልተለየብኝም። ልዩነት አለ ቢባል ጀርመንን ለቅቄ ኦስትሪያ የሚባል አገር መድረሴ ብቻ ነዉ። ኦስትሪያን ለቅቄ ሲዊዘርላንድ ስገባም ፊት ለፊቴ ላይ ጉብ ጉብ ብለዉ ከሩቁ ከሚታዩኝ  ተራራዎች ዉጭ ከተማዉ የጀርመንን ከተሞች ይመስላል፤ ብዙዎቹ መኪናዎች ጀርመን ዉስጥ የተሰሩ መኪናዎች ናቸው፤ ቋንቋዉም ጀርመንኛ ነዉ። ከአሜሪካ ተነስቼ ሲዊዘርላንድ እስክደርስ ድረስ በአራት አገሮች ዉስጥ አልፍያለሁ (አሜሪካ፥ ጀርመን፥ ኦስትሪያና ሲዊዘርላንድ) – ማነህ ተብዬ ፓስፖርት የተጠየኩት አሜሪካንን ስለቅና ሙኒክ ስገባ ብቻ ነው።

ሽፍታዉ ልቤ መሸፈት አይታክተዉ ነገር አሁንም ሸፈተ። ደግሞስ ይሸፍት አንጂ. . . . ለምን አይሸፍት?  የተወለድኩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉኮ! እኛ ሰዎች እግዚአብሄር በአምሳያዉ እኩል አድርጎ ፈጥሮን አንዱ መሪዉን መርጦ ሲሾም ሌላዉ በገዛ መሪዉ ሲጎሸም፤ አንዱ በልቶ ጠግቦ ሲያምርበት ሌላዉ የሚበላዉ አጥቶ ህይወት ሲከዳዉ፤ አንዱ ሁሌም አሳሪ ሌላዉ ሁሌ ታሳሪ፤ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች ሲሆን እንኳን የሰዉ ልብ ከሳር ዉጭ ሌላ የማያዉቀዉ በሬም ይሸፍታል። ጀርመንን፤ ኦስትሪያንና ሲዊዘርላንድን ሳይ በገዛ አገራቸዉ ማናችሁ እየተባሉ በየኬላዉ የሚጉላሉት ምስኪን ወገኖቼ ትዝ አሉኝ። ቤንች ማጂ ዉስጥ ወደ ክልልህ ተመለስ ተብሎ የተገፋዉ ወገኔ በርቀት ታየኝ። ቤኒሻንጉል ዉስጥ አለክልልህ ምን ታደርጋለህ ተብሎ ንብረቱን ተቀምቶ እየተረገጠ የተባረረዉ ኢትዮጵያዊ ወገኔ ትዝ አለኝና ሆዴን አመመኝ። ጋምቤላ ዉስጥ የአያት ቅድም አያቶቹ መሬት ጠመንጃ ባነገቱ ጉልበተኞች ተቀምቶ ሲታርስ እሱ ተመልካች የሆነው አኝዋክ ወገኔ ትዝ አለኝ።

ከጀርመን ሲዊዘርላንድ ስንጓዝ መኪናዉ ዉስጥ የነበርነዉ አምስት ሰዎች ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ነን። አዉሮፓ ዉስጥ አገሮችን በሚያሳስብ ደረጃ ከፍተኛ የስደተኛ ቀዉስ አለ። ሆኖም ከጀርመን ወጥተን በኦስትሪያ በኩል ሲዊዘርላንድ እስክንደርስ ድረስ አንድም ግዜ ማናችሁ የሚል ጥያቄ አልቀረበልንም። ተመልሰን ጀርመን ስንገባም እንደዚሁ። እትብቴ በተቀበረባትና የዚህ አለም ጉዞዬን ስጨርስ የመጨረሻ ማረፊያዬ እንድትሆን በምፈልግባት ምድር እንደ ቆሻሻ ነገር የሚረገጠዉ መብቴ በባዕድ አገር ሲከበር አየሁና  “ኢትዮጵያዊነት” ምን ያደርጋል ብዬ አማረርኩ። ችግሩ ኢትዮጵያዊነት ላይ ሳይሆን ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ቆርጠዉ በተነሱ ከሃዲዎች ላይ መሆኑ ገባኝኛ እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ አለኩ። አዎ!  እነዚህን ከሃዲዎች ማጥፋት አለብኝ ። “ማጥፋት” አለብኝ ሲባል አባባሉ በተግባር ካልተተረጎመ የባዶ ቃላት ጫጫታ ወይም የሞተ ሰዉ ዛቻ ነዉ። አንተ/አንቺ አንባቢ አስተዉል/አስተዉይ። ነፃነትና ፍትህ የሌሉበት አገር ሁሉ የአጥፊዎችና የጠፊዎች መድረክ ነዉ። ጠፊና አጥፊ ባሉበት ቦታ ደግሞ ሁለቱም ያጠፋሉ። አጥፊ ስራዉ ማጥፋት ነዉና ያጠፋል። ጠፊ ደግሞ ላለመጥፋት የሚያደርገዉ ምንም ነገር ስለሌለ እራሱን በማጥፋት ከአጥፊዉ ጋር ይተባበራል። የኛ የኢትዮጵያዉያን ችግርም ይኼዉ ነዉ. . .  ጠፊዉም አጥፊዉም እኛዉ እራሳችን ነን። ከዛሬ በኋላ ግን እኛ አጥፊዎች ጠላታችን ጠፊ መሆን አለበት። ተፈላሲፌባችሁ ከሆነ ይቅርታ . . . እንደዚህ የሚያንበለብለኝ ዉስጤ ያለዉ ላለመጥፋት የማጥፋት ፍላጎት ነዉ። ሲዊዘርላንድ መናገሻ ቤርን መድረሴን ያወቅኩት መኪናዋ ቆማ . . . ጋሼ እንዉረድ ስባል ነው።

የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጅ የአንዳርጋቸዉ ጽጌን 61ኛ አመት የልደት በዐል ለማክበር ሲዊዘርላንድ ዉስጥ የሚኖረዉ ኢትዮጰያዊ ከያለበት ተሰባስቧል። አዳራሹ ከመሙላቱ የተነሳ መቀመጫ ያጣዉ ሰዉ ያዳራሹን ዳር ዳር አጨናንቆታል። በየማዕዘኑ የሚወዛወዘዉ የኢትዮጰያ ሰንደቅ አላማ ለአዳራሹ ልዩ ዉበት ሰጥቶታል። የእንኳን ደህና መጣህ ጩኸቱ፥ ጭብጨባዉና ፉጨቱ አዳራሹ የእግር ኳስ ስታድዩም እስኪመስል ድረስ ቀለጠ። አጠገቤ የቆመው ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደዉ ጭብጨባዉ ለኔ ነዉ ላንተ ብሎ ጠየቀኝ . . . ለኛ ነዉ አልኩት። ሳቅ አለና ሁለት እጆቹን ዘርግቶ ተሰብሳቢዉ እንዲቀመጥ ተማፀነ። እኔም እጆቼን ዘርግቼ አብሬዉ ተማፀንኩ። ከእግራቸዉ ጣት እስከ ጸጉራቸዉ ጫፍ ድረስ ፍቅር በፍቅር የሆኑት የሲዊዝ ኢትዮጵያዉያን የምን መቀመጥ አሉና ሆታዉና ጭብጨባዉ ቀጠለ። ጧት ሙኒከን ስለቅ ድካም በድካም የነበረዉ ሰዉነቴ ዉስጥ አዲስ ሀይል እየገባ ሲያጠነክረኝ ተሰማኝ። ለካስ እኛ ሰዎች ምናብ ለምናብ ስንናበብ ዉጤቱ ፍቅር፥ ሀይልና ብርታት ነዉ። ብቻ ምን አለፋችሁ የሲዊዘርላንድ ኢትዮጵያዉያን እንደ ሲዊዝ ቸኮለት የሚጣፍጥ የአገር ልጅነት ፍቅር አቀመሱኝና በወገን ፍቅር ሰከርኩ። ሲዊዞች፥ ቸኮለታቸዉና ፍቅራቸዉ በጣም ተመቸኝ…….. ግን ብዙ ስራ ስላለብኝ የአንዲን ልደት ሻማ አብርተንና ኬኩን ቆርሰን “መልካንም ልደት” አንዲ ብለን ከዘመርን በኋላ ተለያየን። ጉዞ እነሱ ወደ ቤታቸዉ እኔ ወደ ሙኒክ ሆነ።

ረቡዕ መጋቢት 2 (March 2) ቀን በጧት ተነስቼ ቁርስ ከበላሁ በኋላ ከአዲሶቹ የሙኒክ ጓደኞቼ ጋር ተያይዘን ጉዞ ወደ ኦሎምፒክ መንደር ሆነ። ሙኒክ ኦሎምፒክ ልጅነቴን ይዞ የሚመጣ ብዙ ትዝታ አለዉ። የሜክሲኮዉ ኦሎምፒክ ጀግና ሻምበል ማሞ ወልዴ የመጨረሻዉን የኦሎምፒክ ማራቶን፤ ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ደግሞ የመጀመሪያዉን የኦሎምፒክ ሩጫ የሮጡት ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነዉ። ምሩዕ ይፍጠር ሙኒክ የሄደዉ ለ10ሺና ለ5ሺ ሜትር ዉድድሮች ሲሆን በ10ሺ ሜትር ሦስተኛ ከወጣ በኋላ የ5ሺ ሜትር የመጨረሻዉ ዉድድር ከተጀመረ በኋላ በመድረሱ ያሸንፋል ተብሎ በጉጉት ይጠበቅ በነበረዉ ዉድድር ላይ ሳይሳተፍ ቀርቷል። ሙኒክ ኦሎምፒክ አሳዛኝ ታሪክም አለዉ። ጨለማዉ መስከረም (Black September) በመባል የሚታወቀዉ የፍልስጥኤማዉያን አክራሪ ቡድን ኦሎምፒክ መንደር ዉስጥ አሸምቆ ገብቶ በእስራኤል አትሌቶች ላይ አደጋ ያደረሰዉ በዚሁ እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1964 ዓም በተካሄደዉ ሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ ነበር። በነገራችን ላይ ሙኒክ ኦሎምፒክ የተካሄደዉ ጥቁር አሜሪካዊዉ ጆዜ ኦዉንስ በርሊን ኦሎምፒክ ላይ የወርቅ ሜዳሊያዎች አሸንፎ የናዚ ሂትለር መሪዎች ጥቁር ስለሆንክ ከኛ እጅ ሜዳሊያ አትቀበልም ካሉት ከ36 አመታት በኋላ ነበር።

ሙኒክ ዉስጥ በመጨረሻ የጎበኘሁት ከከተማዋ 19 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የሚገኘዉንና በ1944 ዓም የተሰራዉን የዳሁ ናዚ ማጎሪያ (Concentration Camp) ነበር። ዳሁን ጎብኝቶ ለመጨረስ ወደ ሦስት ሰአት አካባቢ ፈጅቶብኛል። እነዚህ ሦስት ሰአቶች ወደፊትም ወደኋላም እየወሰዱኝ ዳሁ የጭካኔና የእልቂት ቦታ የመሆኗን ያክል የይቅርታና የመማማሪያ ቦታም እንደሆነ አሳይተዉኛል። ዳሁ ለሰዉ ልጅ ቁስሉም መድኃኒቱም ሰዉ መሆኑ የታየበትና የሰዉ ልጆች ጭካኔ መድረስ የሚችልበት የመጨረሻዉ ከፍታ ላይ የደረሰበት ቦታ ነዉ። ዳሁ አሁንም ድረስ ሲያዩት ጣረ ሞትን የሚጣራ የጨለማና የብርህን፤ የሞትና የህይወት፤ የጭካኔና የምህረት ቦታ ነዉ። ዳሁ የናዚ ግፍና ጭካኔ እማኝ ነዉ። ዳሁ የዘግናኝ ታሪክ ቅርፊት፡ የብሩህ ዘመን ትዉፊት፥ ቂምና ጥላቻን አብናኝ ይቅር ብሎ ይቅርታ ለማኝ ቦታ ነዉ። ዳሁ አይዋሽም . . . እንኳን ሊዋሽ  ጭራሽ ዉሸት የሚባል አያዉቅም። ዳሁ ከአንዱ ክፍል ወጥተን ወደ ሌላዉ ክፍል በገባን ቁጥር የሚነግረን እዉነት ግን እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ያሰኛል። ያቆስላል፤ ያደማል፤ ልብ ይሰብራል፤ ሆድ ይቆርጣል። እስረኞች ከመኝታ ቤታቸዉ እየተነዱ ገላችሁን ስለምትታጠቡ ልብሳችሁን አዉልቁ ተብለዉ ወደ ሌላ ክፍል ይወሰዳሉ። የሚቀጥለዉ ክፍል ዉስጥ የሚጠብቃቸዉ የመታጠቢያ ገንዳ ሳይሆን የመርዝ ጋዝ ገንዳ ነዉ። እስረኞቹ በመርዝ ጋዝ ከተገደሉ በኋላ እሬሳቸዉ ወደሚቀጥለዉ ክፍል ይወሰድና አገር የሚያክል ምድጃ ዉስጥ እየተጣለ ይቃጠላል። ይህ ግፍና ጭካኔ የተፈፀመዉ በሰዉ ልጆች ላይ ነዉ፤ ይህንን ግፍና ጭካኔ የፈፀሙትም የሰዉ ልጆች ናቸዉ። ጀርመንና ፖላንድ ዉስጥ ስላሉ የናዚ ጀርመን ማጎሪያ ካምፖች ከሰማሁ ቆይቷል። ይህንን በተለያዩ መጽሐፍት ላይ ያነበብኩትን ታሪክ ታሪኩ የተፈጸመበት ቦታ ላይ ቆሜ ስመለከት ግን አእምሮዬ ማሰብ አቆመና በድን ሆኜ ቀረሁ። ሁለት እጆቼን ዘርግቼ አማተብኩና . . . . . እንዲህ አይነት ክፉ ጭካኔ ዬትም ቦታ መደገም የለበትም ብዬ የዳሁ ጉብኝቴን ጨረስኩ።

ጀርመን፥ ኦስትሪያ፥ ሲዊዘርላንድና ዳሁ ስለ አሁኗና ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ በየራሳቸዉ መንገድ የሚነግሩን ብዙ ነገር አለ። ዳሁ በሚባለዉ የናዚ ሂትለር ማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ የተፈጸመዉን ግፍና ጭካኔ የፈጸሙት እኛን የመሰሉ የሰዉ ልጆች ናቸዉ እንጂ ከጥልቅ ባህር ዉስጥ የወጣ ዲያብሎስ አይደለም። ጀርመን፥ ኦስትሪያና አራት የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባት ሲዊዘርላንድ ድንበር፤ ቋንቋ፤ባህልና ሐይማኖት ሳያግዳቸዉ ከአንዱ አገር ወደ ሌላዉ እንዳሰኛቸዉ እየተዘዋወሩ በኤኮኖሚ ተሳስረዉ በሰላም የሚኖሩት አርቆ አስተዋይ መሪዎቻቸዉ በወሰዱት መልካም እርምጃ ነዉ እንጂ እግዚአብሄር ከሰማይ ወርዶ የልዩነት ግድግዳቸዉን አፍርሶላቸዉ አይደለም። ክፉዉም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ፥ መልካሙም ስራ የሰዉ ልጆች ስራ ነዉ።እኛ ኢትዮጵያዉያን ምርጫችን ምንድነው? አዉሮፓ ዉስጥ ሰዉ ከአባቱ ገዳይ ጋር ተስማምቶ ሲኖር እያየን እኛ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር በሠላም ጎን ለጎን መኖር ለምን አቃተን? አዉሮፓዉያን በየአገሮቻቸዉ መካክል ያለዉን ድንበር አፍርሰዉ በአንድ ገንዘብ ሲገበያዩ እኛ በአንድ አገር ዉስጥ ለዘመናት አብሮ በኖረ ህዝብ መካከል አጥር የምንሰራዉ ለምንድነዉ?

ሙኒክ ከመሄዴ በፊት አሜሪካ ሜሪላንድ ዉስጥ አንድ ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር። እዚህ ስብሰባ ላይ የእምነት አባቶች፤ የሲቪክና የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች፤ አባቶች፤ እናቶችና ወጣቶች ተገኝተዉ ነበር። የሁሉም ፍላጎት አንድ፤ አንድና አንድ ብቻ ነበር። እሱም ፍትህ፤ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። አዉሮፓ መጥቼ ጀርመንና ሲዊዘርላንድ ዉስጥ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ጋር ስገናኝ የተሰማኝ ስሜት አሜሪካ ዉስጥ ከተሰማኝ ስሜት ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ነበር። እርግጠኛ ነኝ ኢትዮጵያዉያን በሚኖሩበት የአለም አካባቢ ሁሉ ፍላጎታቸዉ ፍትህ፥ ነጻነትና ዲሞክራሲ ነዉ። ግን ፍትህና ነጻነትን ስለፈለግናቸዉ ብቻ አናገኛቸዉም። የተናጠል ትግል ደግሞ ተራ በተራ የወያኔ ምሳና ቁርስ ያደርገናል እንጂ ነጻነታችንን አያስገኝልንም።  በእርግጥ ነጻነት ስንደሰትበት ደስታዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ፤ ሆኖም ነጻነታችንን ጠላት እንዳይቀማን የምንጠብቀዉና ከተቀማንም ታግለን የምናስመልሰዉ በጋራ ነዉ። ስለዚህ ጽኑ የሆነዉ የፍትህና የነጻነት ፍላጎታችን ጽናት ባለዉ የጋራ ትግል ካልተደገፈ ያለን አማራጭ እየተረገጥን መኖር ብቻ ነዉ።
ወያኔ የበላይ በሆነባት በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደዳሁ አይነት በሰዉ ዘር ላይ የተፈጸመ ወንጀል ሊፈጸም አይችልም የምንል ሰዎች ካለን ወደ ኋላ ዞር ብለን አኝዋክንና ኦጋዴንን ልንመለከት ይገባል። ዛሬ ወያኔ ኦሮሚያ ዉስጥ መብቴ ይከበር ብሎ በጮኸ ኢትዮጵያዊ ላይ የሚወስደዉ ፍጹም አረመኔያዊ የሆነ እርምጃም የሚያሳየን ወያኔ የስልጣን ገመዱ ባጠረ ቁጥር የማያደርገዉ ምንም ነገር እንደሌለ ነዉ። የወደፊቷ መልካም ኢትዮጵያ የምትናፍቀን ኢትዮጵያዉያን ከጀርመን፥ ከኦስትሪያ፥ ከሲዊዘርላንድና ከዳሁ የምንማረዉ ጠቃሚ ትምህርት አለ። ዛሬ በማድረግ ወይም ባለማድረግ የምንፈጽማቸዉ ብዙ ስህተቶች አሉ። እነዚህ ስህተቶች የጠላታችንን የወያኔን የሥልጣን ዘመን ማራዘማቸዉ ብቻ ሳይሆን ወያኔ ከተወገደ በኋላም ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በምናደርገዉ ጥረት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያደርጋል። ለምሳሌ ኦሮሚያ ዉስጥ ለወራት የዘለቀዉ ህዝባዊ ቁጣና እምቢተኝነት በሌላ አገር የሚካሄድ ይመስል ብዙዎቻችን ከጎን ቆመን ተመልክተናል። ይህ አጉልና የማያዋጣ ቸልተኝነት ነገ በአማራ፤ በሲዳማ፤ በሃዲያና በኮንሶ … ወዘተ አካባቢዎች የሚነሱ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ኦሮሞዉ በቸልተኝነት እንዲመለከት ያደርገዋል። ኢትዮጵያ ዉስጥ አማራዉ ለኦሮሞ ካልጮኸና ኦሮሞዉ ከአማራዉ ጋር አብሮ ካልታገለ አማራዉ፤ ኦሮሞዉ ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ባርነት ነፃ አይወጣም። ወደድንም ጠላን ታሪክ ኢትዮጵያ ዉስጥ ሲዳማን በወላይታ፤ ጉጂን በጌዲኦ፤ ትግሬን በአማራ፤ አማራን በኦሮሞ . .  ወዘተ አዉድ ዉስጥ ጠቅልሎ አስቀምጦናል። ከዚህ ጥቅልል ዉስጥ በተናጠል አንዱ ብቻዉን ነፃ መሆን አይችልም። ወያኔ ጨፍልቆ የሚረግጠን አንድ ላይ ነዉ፤ ነፃ የምንወጣዉም አንድ ላይ ነዉ። ኢትዮጵያና አንድነቷ አደጋ ላይ ወድቀዋል። ኢትዮጵያዊነት የምንለዉ ክቡር ማንነትም ከፍተኛ አደጋ ላይ ነዉ። እነዚህን ጣምራ አደጋዎች  ማቆም የዚህ ትዉልድ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነዉ። የወደፊቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዳሁን የመሰለ የመታሰቢያ ቦታ እንዲኖራት በፍጹም መፍቀድ የለብንም። ይህ እዉን የሚሆነዉ ግን እኛ ኢትዮጵያዉያን እጅ ለእጅ ተያይዘንና ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የዛሬዋን ኢትዮጵያ ከእልቂት አድነን የነገዋን ኢትዮጵያ በፍትህ፤ በነጻትና በዲሞክራሲ መሰረት ላይ መገንባት ከቻልን ብቻ ነዉ። ሌላ ምንም መንገድ የለመልኩም። ቸር ይግጠመን።by: 



አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር – ebini23@yahoo.com