Wednesday, 20 July 2016

“ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም” ታሪክ

"የአማራ ተወላጆች ወልቃይት ጠገዴ ሄደው መኖር ይችላሉ" ቴድሮስ

welkait tsegede

የወልቃይት ጉዳይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ ደም እያፋሰሰ ባለበት በሁኑ ወቅት ቴድሮስ አድሃኖም ወልቃይትን የትግራይ ግዛት አድርገው በመቁጠር “የአማራ ብሔር ተወላጆች ወልቃይት መጥተው መኖር ከፈለጉ የትግራይ ሕዝብ በደስታ ይቀበላቸዋል” በማልተ የትግራይ ሕዝብ ወክለው ስለ ወልቃይት የትግራይ ክልልነት በድፍረት በፌስቡክ ላይ ይህንን ብለዋል – ሙሉው ቃል ከዚህ በታች ይገኛል:-
በጎንደር የተከሰተውን የማንነት ጥያቄ ሰበብ በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦች ብጥብጥ ለማስነሣት ቢሞክሩም መንግሥታችን በሰከነ ዘዴ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሥር አውሎታል:: የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከአማራ ተወላጆች ጋር በመወያየትና በማሳመን የወልቃይትን መሬት የትግራይም ሆኑ የአማራ ተወላጆች በጋራ እንዲኖሩበት በማግባባት ላይ ይገኛል፡፡ ወልቃይት የአማራ ነው በማለት የሚነዛው ፕሮፓጋንዳም የሐሰት መሆኑና ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የታለመ በመሆኑ ሊወገዝ ይገባዋል:: የትግራይ ሕዝብና የአማራ ሕዝብ ለረዥም ጊዜያት በመቻቻልና በመከባበር አብረው የኖሩ በመሆናቸው በጥቂት ግለሰቦች ፍላጎት የሚጣሉ አይደሉም:: የትኛውም ብሔር በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል በመሄድ የመኖር መብት ያለው በመሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ወልቃይት ጠገዴ ሄደው ቢኖሩ አንድም የትግራይ ተወላጅ ቅሬታ እንደማይሰማው ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ:: በዚህ አጋጣሚ የትግራይ ሕዝብ አማራ ወንድሞቹን በፍቅር በማየት የተለመደ እንግዳ ተቀባይነቱን በተግባር ማሳየት እንዳለበት ለማሳሰብ እወዳለሁ::ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ለመሆኑ ወልቃይት የማን ነው? Horn Affairs ላይ Ze Addis በሚል መጠሪያ የተጻፈው ከታሪክ ማስረጃ አንጻር ይህንን ይተነትናል

ወልቃይት ላለፉት ሺህ ዓመታት በትግራይ ስር ተዳድራ አታውቅም – የታሪክ ማስረጃዎች

የኢትዮጵያ መንግስት (ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ) አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ከወሰዳቸው ዓብይ ኩነታት አንዱ፤ የሀገሪቱን የፖለቲካን የአስተዳደር ካርታን መቀየሩ እንደሆነ ይታወቃል:: የኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት ካርታ እ.ኤ.አ. በ1994 ቢቀየርም፤ አዲሱ ካርታ ብዙ የማንነት ጥያቄዎችን አስነስቷል:: ይህ የዳግም መካለል ጥያቄ ከሚነሳባቸው ቦታዎች ውስጥ ወልቃይት አንዱ ነው።
እንዲህ አይነት የማንነትና የመካለል ጥያቄ ሲቀርብ ዋና መፍትሄ የሚሆኑት የታሪክ ሰነዶች ናቸው:: የታሪክ ሰነዶች ስለ ወልቃይት ግን ምን ይላሉ? ላለፉት ብዙ መቶ ዓመታት የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች ምን እንደሚሉ እንመርምር::
1/ ወልቃይት ጠገዴና አላማጣ ኮረም በአጼ ዮሓንስ ዘመን በትግራይ ሥር አልነበሩም የታሪክ ሰነድ ማስረጃ
አጼ ዮሓንስ ከ 1871 ዓ.ም እስከ 1889ዓ.ም (እ.ኤ.ኣ) ኢትዮጵያን የመሩ ንጉስ ናቸው:: ንጉሰ በንግሥና ዘመናቸው የራሳቸው ጠንካራና ደካማ ጎን ቢኖራቸውም፣ ከጠላት ደርቡሽ ጋር በመፋለም ለሀገራቸው ክቡር ሕይወታቸውን የሰጡ ንጉሰ ናቸው:: ጥቂት የማይባሉ የሕወሀት ሰዎች፣ ከወልቃይትና ጠገዴ ጋር በተያያዘም የሚጠቅሱት እሳቸውን ነው:: ወልቃይት እናጠገዴ ፣ ጥንት በአጼ ዮሓንስ ዘመነ መንስግት በትግራይ ስር ነበረች”በማለት እንደ ዋና መከራከርያ ሲያቀርቡት ይደመጣል:: እውነታውን የዘገቡት የታሪክ ሰነዶች ናቸውና የታሪክ ሰነዶችን እንመርምር::
በአጼ ዮሓንስ ዘመን የነበረው የትግራይ ግዛትና፣ አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ግዛት ምን እንደሚመስል በዝርዝር በሀገር ውስጥና በውጭ ሊቃውንት ተጽፏል:: ስለ ወልቃይትም አስተዳደር በማን ስር እንደነበረ በዝርዝር ጽፈውታል:: ለዚህም የእውቁን የፈረንሳዊ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር ኤሊስ ሬክለስ መጽሓፍን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል::
በዩንቨርሲቲ ኦፍ ብረስልስ የኮምፓራቲቭ ጂኦግራፊ (University of Brussels, Professor of Comparative Geography) ፕሮፌሰርና የዴፓርትመንቱ ሀላፊ የነበረው ይሄው ፕሮፌሰር ፤ በ1880 ጀምሮ በርካታ መጽሓፎችን በዓለም ጂኦግራፊ ላይ ጽፏል:: እነዚህም መጽሓፍቱ ከለንደንና ፓሪስ ጆኦግራፊካል ሶሳይቲ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርገውታል::
ከነዚህ መጻሕፍት አንዱ በ 1880 የተጻፈው The Earth and its Inhabitants የሚለው ሲሆን፤ ዘጠኝ ተከታታይ ክፍሎች አሉት። የዚሁ መጽሓፍ ክፍል አራት በገጽ 443 ላይ የሰሜን እና ምስራቅ አፍሪካን የወቅቱን ጂኦግራፊ በዝርዝር ይተነትናል:: በአጼ ዮሓንስ ዘመን የነበረውንም የኢትዮጵያን ክፍላተ ሀገራት በዝርዝር ቁልጭ አድርጎ እንዲህ ጽፎታል::
“The Amhara government provinces are: Dembia, Chelga, Yantangera, Dagossa, Kuarra, Begemidir, Guna, Saint, Wadla, Delanta, Woggera, Simen, Tselemt, Armachiho,Tsegede, Kolla Wogerra፣ Waldiba and Wolkait”
Table - Tigray territories from the book - The Earth and its Inhabitants
Table – Tigray territories from the book – The Earth and its Inhabitants
ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ይህ ጽሁፍ የተጻፈው በ1880ዎቹ አጼ ዮሃንስ የሀገሪቱ ንጉስ በነበሩበት ዘመንና የተጻፈውም በግዜው ከነበሩ ከተለያዩ የጂኦግራፊካል ሶሳይቲዎች የወርቅ ሜዳይ ተሸላሚ በሆነ ባለሙያ ፕሮፌሰር ነው:: ይህ በ1880ዎቹ የተጻፈው መጽሓፍ እንደሚያስረዳው በአጼ ዮሓንስ ዘመን ወልቃይት: ጠለምት : ዋልድባ : አላማጣ : በሙሉ በትግራይ ስር አልነበሩም:: እነዚህን ቦታዎች በስም ጠቅሶ እንደሚነግረን በትግራይ ስር ሳይሆን በጎንደር ስር ነበሩ::
“በአጼ ዮሓንስ ዘመን ወልቃይትና ጠግዴ በትግራይ ስር ስለነበሩ ነው አሁን ወደ ትግራይ የጠቀለልናቸው ” የሚለው መሰረት የሌለው መሆኑን ይሄ መረጃ ያሳየናል:: ከአጼ ዮሓንስ በፊትስ እነዚህ ቦታዎች ይተዳደሩ የነበሩት በማን ነው? የሚለውን እንመልከት። ወደ አጼ ቴዎድሮስ ዘመን እንጓዝ፡፡
2/ በኣጼ ቴዎድሮስም ዘመን ወልቃይት ጠገዴ በትግራይ ስር አልነበሩም – የታሪክ ማስረጃ ሰነዶች
በኣጼ ቴዎድሮስ (1818 – 1868 እ.ኤ.አ) የነበሩ ስመ ገናና ኢትዮጵያዊ ንጉስ ነበሩ:: በየቦታው የነበሩ መሳፍንትን አሸንፈው፣ ማዕላዊ መንግስት ከመሰረቱ በኋላ፣ ቀጣይ ራዕያቸው የምዕራብያውያንን ቴክኖሎጂ እዚሁ ኢትዮጵያ እንዲመረት ማድረግ ነበር:: ለዚህም ከበርካታ አውሮፓ ሀገራት ጋር ግንኙነት መስርተው ነበር:: የአውሮፓውያን ጥበበኞችን ኢትዮጵያ ለማስቀረት እና ጥብቅ ግንኑነት ለመመስረት፣ አጼ ቴዎድሮስ ልጃቸውን ለአንድ ስዊስ ኢንጂነር እስከመዳር ደርሰው ነበር:: በዚህም ምክንያት በርካታ አውሮፓውያን ጠቢባን በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ኢትዮጵያ መጥተዋል:: እነዚህም ባለሙያዎች ኢትዮጵያ መጥተው ስለ ሀገሪቱ በዝርዝር ጽፈዋአል:: የእንግሊዝ መንግስትና የኢትዮጵያ ግንኑነት መሻከር ሲጀምር፣ እንግሊዞች ስለኢትዮጵያ ይበልጥ የማወቅ ፍላጎታቸው ጨመረ::
የእንግሊዝ መንግስት የintelligence ሰዎችም የእንግሊዝ መንግስት ፓርላማና የጸጥታው ኃይል ኢትዮጵያን በሚገባ ያውቃት ዘንድ ትዕዛዝ ወጣ:: የእንግሊዙ Topographical and Statistical Department of The War Office ኤ . ሲ ኩክ (A. C. Cook) በተባለ እንግሊዛዊ ኮሎነል አማኻኝነት ስለ ኢትዮጵያ ከ15ኛው ክፍለ ዘመን ጀመሮ በተለያዩ እውሮፓውያን ተጻፉ መጻሕፍት ባንድ ላይ እንዲጠርዘ ተደረገ:: የሚደንቀው ይሄ መጽሓፍ በ 1867 ዓ.ም እ.ኤ.ኣ የታተመው በግስቲቷ ጥያቄ ለእንግሊዝ ሀውስ ኦፍ ኮመን ሎወር ሀውስ ግብአት (House of Common lower House) ይውል ዘንድ መሆኑ ነው:: በዚሁ መጽሓፍ ውስጥ፤ የወቅቱ የኢትዮጵያ ዝርዝር ጉዳይ ተጽፏል:: ይሄውም መጽሓፍ ስለ ወልቃይትና ጠገዴም በኣጼ ቴዎድሮስም ይሁን ከሳቸው በፊት በማን ስር ይተዳደሩ እንደነበር በዝርዝር ያትታል::
“The Provinces of Amhara are : Simen, Waldibba, Wolkait,Wogera,Chilga, Kuara, Belesa, Fogerra, Damot, Gojjam, Begemidir, Beshilo ….. Waldiba situated to the NW of Semein between the Tekeze and the Angereb, extends as far as the junction of the two rivers. Welkait is to the west Of Waldiba it is intersected through its whole length by the two river tekuar and guang. It is more wooded than waldiba..” (Routes in Abyssinia (printed in 1867 G.C) page 188)
ይሄው ታሪካዊ መጽሓፍ በወቅቱ የነበረውንም የትግራይ ክፍለሀገር ድንበር እና ግዛት እነማን እንደነበሩ በማያሻማ ቋንቋ እንዲህ ይነግረናል፡፡
“The territory of Tigre whose capital is Adwa, is bounded on the West by Shire, on the Southwest by Temben and Adet on the South by Geralta on the South –East by Haramat, on the East by Agame, and on the North by the rivers of Mereb and Belessa”
የትግራይ ግዛትስ? ብሎ ለሚጠይቅ ወገን ፤ ይሄው መጽሓፍ በወቅቱ የነበርቸው ትግራይ ምን እንደምትመስል እንዲህ ሲል አስፍሮታል በዚሁ መጽሓፍ ላይ ገጽ 187 – 188 የትግራይን ግዛት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል
“The territory of Tigray whose capital is Adwa is bounded on the west by Shire, on the south west by Temben and Adet, on the south by Geralta, on the South East by Haramat, on the East by Agamae, and on the North by the Rivers Mereb and Belessa”
Map - northern Ethiopia areas
Map – northern Ethiopia areas
እዚህ ላይ በ 18ተኛው ክፍለ ዘመን የትግራይን ወሰኖች በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ አስቀምጦታል:: የትግራይ ወሰን በምዕራብ – ሽሬ ፤ በምዕራብ ደቡብ – ተምቤን እና አዴት ፤ በደቡብ – ገር አልታ ፤ በምስራቅ – አጋሜ ፤በሰሜን – መረብና በለሳ ናቸው:: የታሪክ ሰነዶች በአጼ ቴዎድሮስም ዘመን እንደሚነግረን ፤ ወልቃይትና ጠገዴ በትግራይ ስር አልነበሩም::
ከዛስ በፊት ወልቃይትና ጠገዴ በትግራይ ስር ነበሩን? አሁንም የታሪክ ሰነድ እንመርምር::
3/ በዘመነ መሳፍንት ዘመንም ወልቃይትጠገዴ በትግራይ ስር አልነበሩም – የታሪክ ማስረጃ ሰነዶች
እንደሚታወቀው ከአጼ ኢዮአስ ሞት ጀምሮ ፤ አጼ ቴዎድሮስ እስኪነሱ የነበረው ዘመን ዘመነ መሳፍንት ይባላል:: በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት አልነበራትም:: መሳፍንቶች የገነኑበትና በሀገሪቱ ማዕከላዊ አስተዳደር የጠፋበት ዘመን ነበር:: በዚህ ማዕከላዊ የመንግስት ሕግ በሌለበት ወቅት እንኳን ወልቃይት፥ጠገዴ፥ ዋልድባ ፥ አላማጣ፥ ኮረም እና የመሳሰሉ ቦታዎች በትግራይ ስር አልነበሩም:: አሁንም ማስረጃ እነሆ!
ጀምስ ብሩስ የተባለው ስኮትላንዳዊ ፥ በዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያ መጥቶ ኢትዮጵያ በዘመነ መሳፍንት ምን ትመስል እንደበረ፥ ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል:: እያንዳንዱ መስፍን ግዛቱ የት ድረስ እንደነበረ፥ የትኛው መስፍን ማንን ይገዛ እንደነበረ በሰፊው ተንትኖታል:: በዚህም መሰረት ስለ ትግራይ ግዛትና እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ይሰጣል :: Travel to discover source of the Nile Volume 3 page 582 ላይ
“Tigre is bounded by the territory of the Bahirenegash that is by the river Mereb on the East and Taccazze upon the west. It is about one hundred and twenty miles broad from E. to W. and two hundred from N. to S. “
ጀምስ ብሩስ በዚሁ መጽሓፉ Chapter 10 ላይ Geographical division of Abyssinia into province በሚለው አንቀጹ ላይ በይበልጥ ቁልጭ አድርጎ እንዲህ ያስቀምጠዋል
The first division is called Tigre, between Red Sea and the river Tekeze. Between that River (Tekeze) and the Nile Westwards where it bounds the Oromo, it is called Amhara.
ካለ በኋላ ወረድ ብሎ ይበልጥ ጉዳዩን ሲያስረዳ “Tekezze is the natural boundary between Tigre and Amhara”
ከላይ ለአብነት ያስቀመጥኳቸው ሊቃውንት በግዜ፣ በቦታና በዜግነት አይገናኙም:: ለምሳሌ በአጼ ዮሓንስ ዘመን የነበረው አሊስ ሬክለስ ፈረንሳዊ (French) ነው:: በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን የነበረውን የኢትዮጵያ ግዛት የጻፈው ደግሞ እንግሊዛዊ ነው (British):: ጀምስ ብሩስ ደግሞ ስኮትሽ (Scottish)ነው:: ግን ሁሉም በተለያየ ግዜ መጥተው ያዩትና የተገነዘቡትን ጽፈዋል:: የሚናገሩት አንድ ና ተመሳሳይ ነው:: እውነት ምን ግዜም አንድ ናትና!
4/ ወልቃይት በ1630ዎቹስ በማን ስር ነበረች?
በ16ኛው መቶ አጋማሽ ላይ ያሉ ያታሪክ መዛግብትም የሚናገሩት ተመሳሳይ ነገር ነው:: በተለያዩ ወገኖች ተደጋግሞ የሚጠቀሰው የ ማኑኤል በሬዳም መጽሓፍ የሚተነትነው ያንኑ ነው:: ይሄ መጽሓፍ የተጻፈው በ1634 ሲሆን ጸሓፊውም ኢማኑኤል በሬዳ ይባላል:: በወቅቱ የነበረውን የትግራይ ግዛት በዝርዝር አስቀምጧል:: እሱም እንደሌሎቹ ጸሓፍት የትግራይ ድንበር ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠገዴ ናቸው አይልም::
«Tractatus tres historico-geographici (1634): A seventeenth century historical and geographical account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen) 1634» መጽሀፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስለ ትግራይ ግዛት እንዲህ ይላል::
“Among all the kingdoms that the Emperor of Ethiopia possesses today one of the greatest if not the greatest and the most important is the kingdom Tigre. From north to south, that is from the limits of the Hamasen to Enderta, it covers an areas of from ninety to one hundred leagues (3.2 miles); and from the east, which is besides Dancali, located at the entrance to the Red sea to the southern end of the Red Sea, to the west bounded by the Tekezze River beside the Semen, it covers an area of similar size, so that the Kingdom has a nearly circular shape.”
አሁንም ወደኋላ እየራቅን እንሂድና ወልቃይት ጠገዴ በነ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በማን ስር ነበርች? የሚለውን እንመልከት
5/ በኣጼ ዘርዓ ያዕቆብ ( 14ኛው ክፍለ ዘመን) ዘመንም ወልቃይትጠገዴ በትግራይ ስር አልነበሩም – የታሪክ ማስረጃ ሰነዶች
አጼ ዘርዓ ያዕቆብ በኢትዮጵያ ታሪክ ከተነሱ ሃያልና ሊቅ ነገስታት ውስጥ አንዱ ነበሩ:: በቀድሞ ስሙ ፈጠጋር በአሁን ስሙ ኦሮሚያ አዋሽ ወንዝ አካባቢ የተወለዱት አጼ ዘርዓ ያዕቆብ፥ የሀድያ ሲዳሞ ንጉስ ልጅ የሆነችውን እሌኒን አግብተው፥ በ37 ዓመታቸው ከነገሱ ጀምሮ በርካታ ዓበይት ስራዎችን አከናውነው አልፈዋል:: እኒሁ ንጉስ ከፍተኛ የጥበብ ፍቅር የነበራቸውና ከመሆናቸው ባሻገር፥ ራሳቸው ብዙ መጻሕፍትን ጽፈዋል:: በሳቸው ዘመንም ብዙ መጻሕፍት እንዲጻፉ ድጋፍ በመስጠታቸው አያሌ መጻሕፍት በሳቸው ዘመን ተጽፈዋል:: ከነዚህ መጻሓፍት አንዱ በአክሱም ንቡረ ዕድ የተጻፈው ዜና አክሱም መጽሃፍ አንዱ ነው:: ዜና አክሱም ከሃይማኖያትዊ ሐተታው ባለፈ ስለ 14ኛዋ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ በዝርዝር ጽፎታል:: ይህ መጽሓፍ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ወሰንና ታሪክ ብቻ ሳይሆን የክፍላተ ሀገራቱንም ድንበር ጥንቅቅ አድርጎ ዘግቦታል:: የትግራይንም ክልል በካርታና በጽሁፍ ከዚህ እንደሚከተለው ይገልጸዋል::
Chart - List of Tigrai areas on Zena Axum book
Chart – List of Tigrai areas on Zena Axum book
ይህም መጽሓፍ በተመሳሳይ መልኩ የሚነግረን፣ ወልቃይትና ጠገዴ በፍጹም ፣ የትግራይ አካል አንዳልነበሩ ነው::
ዮሓንስ መኮንን Ethiopia: the land, its people , History and Culture በሚለው መጽሓፉ Page 351 በአጼ ዘርዓ ያ ዕቆብ ዘመነ መንግስት የነበረውንና በመጽሓፍ አክሱም የተተነተውን የትግራይን ካርታ እንዲህ ያቀርበዋል
“The Book of Axum.. Shows a traditional schematic map of Tigray with its city Axum at its center surrounded by the thirteen principal provinces: Tembein, Shire, Seraye, Hamasen, Bur, Sama, Agame, Amba Senait, Geralta, enderta, Sahart and Abergele”
በተመሳሳይ ሁኔታም The World through Maps: A History of Cartography (ገጽ 352 ይመልከቱ)፡፡ በJohn R. Short የተጻፈው የዓለም ጂኦግራፊን የሚተርከው መጽሓፍ በ15ኛው ክፍለዘመን የነበሩ የትግራይ ግዛቶች ከላይ የተጠቀሱት መሆናቸውን መጽሓፈ አክሱምን በመጥቀስ ያስረዳል:: ይህም መጽሓፍ በተመሳሳይ መልኩ የሚነግረን፣ ወልቃይትና ጠገዴ በፍጹም የትግራይ አካል አንዳልነበሩ ነው::
6/ ቋንቋን መሰረት ወዳደረገ ክለላን አንመልከት
የኢትዮጵያውያን ወጣቶችና አርበኞች ቁጣ ያሳሰበው ጣልያን፣ ኢትዮጵያን በቋንቋና በዘር በትኖ ለመግዛት ያቀደውን መርዝ ይፋ አወጣ:: የዚህ እቅድ ፊታውራሪ ከሆኑት አንዱ ፋሺስቱ Baron Roman Prochàzka አቢሲንያ ዘ ፓውደር ባረል (Abyssinia: the Powder barrel) በሚል መጽሓፉ ላይ እንዳስቀመጠው፣ ኢትዮጵያውያንን ለመግዛት በዘር መከፋፈልና በመሀከላቸውም ጥላቻን በመዝራት እርስ በርስ ለማናከስ፣ ሀገራቸውን በዘር መከለል የሚለውን እቅድ መተግበር ጀመረ:: በዚሁም መሰረት፣ ዘርንና ቋንቋን መሰረት ባደረገ ሽንሸና ኢትዮጵያን አምስት ቦታ ከፈላት::
እነዚሁም ክልሎች አማራ: ኤርትራ(ትግሬ); ሐረር: ኦሮሞ-ሲዳማ: ሸዋና ሶማሌ ናቸው:: ጣልያን ይሄንን የግዛት ሽንሸና ሲያካሂድ መሰረት ያደርገው ዘርና ቋንቋን ነበር:: የሚከተለውም ሰማንያ በሃያ የሚለውን መርህ ነበር:: ከሰማንያ በመቶ በላይ ሕዝቡ የሚናገረውን ቋንቋ መሰረት በማድረግ ወደየ ክልሉ ይደለደላል:: ሸዋን ግን ለብቻው ለይቶ መቆጣጠር ይገባል ብሎ በማመኑ ሸዋን ና ሀረርን ለብቻ ለይቶታል:: ወደ ነጥባችን ስንመጣ በዚህ የቋንቋ ሽንሸና መሰረት ወልቃትና ጠገዴና ጠለምት ወደ ትግራይና ኤርትራ አልተካተቱም:: በጎንደር ስር ነበሩ::
እዚህ የጣልያን ቋንቋንና ዘርን መሰረት ያደረገ ካርታ ላይ በግልጽ እንደሚታየው ፣ የትግራይ ድንበት ተከዜ እንጂ – ከተከዜ ተሻግሮ አይደለም:: ላልፉት 25 ዓመታት ተቃዎሞ ሲካሄድባቸው የከረሙት ወልቃይት – ጠገዴ – አላማጣ ኮረም በፍጹም በትግራይ ስር እንዳልነበሩ በግልጽ ያሳየናል::
Map - Tigray during Fascist Italy
Map – Tigray during Fascist Italy
7/ አንዳንድ ሚድያዎች ደጋግመው የሚያነሱት ነጥብ አለ:: ይሄውም ወልቃይት ጸገዴና ሌሎች ወደ ትግራይ የተካለሉ ቦታዎች ጥንት የትግራይ እንደነበሩና አጼ ኃይለ ሥላሴ የምስራቃዊ ትግራይ ገዥ ከነበሩት ከደጃዝማች ኃይለሥላሴ ጉግሳ አርዓያ ጋር በመጣላታቸው – ወልቃይትና ጠገዴን ወደ ጎንደር ወሰዱት የሚል ነው:: ሌላው የማያስማማው ነጥብ ደግሞ – የቀዳማይ ወያኔን አመጽ ምክንያት በማድረግ ትግራይን ለመቅጣት – ወልቃይትንና ጠገዴን ወደ ጎንደር ከለሉት የሚል ነው::
እስካሁን ከላይ የገለጽኳቸው ሰነዶች ለዚህ ነጥብ በቂ ማስረጃ ቢሆኑም : ካርታን መሰረት ያደረገ መረጃ ለሚጠይቅ ሰው – እነሆ:: ይህ ካርታ በጣልያኖች በ1928 ዓ.ም የተሰራ ነው:: ኢትዮጵያን በደምብ ካጠኑ በኋላ ለያንዳንዱ ክፍለሀግር ካርታ ሰርተዋል:: ያኔ ገና ኃይለሥላሴ ጉግሳ አልከዳም:: ያኔ የቀዳማይ እንቅስቃሴ አልነበረም:: የቀዳማይ እንቅስቃሴ በ1943 ነበር፡፡ ይህ ካርታ ግን ከዛ ብዙ ዓመታት በፊት የተሰራ ነው:: አንባቢው አይቶ ይፍረድ:: ወልቃይት ጠገዴን ነጥለን ስንመለት ካርታው ይሄንን ይመስላል::
Map - north west Ethiopia in 1928
Map – north west Ethiopia in 1928
8/ በዘመነ መንግስቱ ኃይለማርያም ወልቃይትና ጠገዴ
በካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ይበልጡንም በኢትዮጵያ ታሪክና ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ምርምር ካደሩት ሰዎች ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሱት ፕሮፌሰር ክሪስቶፈር ክላፓም: እንደ ኤሮፓ አቆጣጠር 1990 ( ህወሀት አዲስ አበባብ ከመያዙ አንድ አመት በፊት) ድንቅ የሆነ መጽሓፍ አሳትመው ነበር:: በዚሁ መጽሓፋቸው ላይም ስለ ወልቃይትና ጠግዴ እንዲህ ሲሉ ይተርኩታል
“the area concerned (welkait -Tsegede) separated from Tigray by impressive natural barrier of Setit Tekezze river has never been governed as part of Tigray at any period in the past, but has come under Gonder and Semein.” (Christopher Clapham: Transformation and continuity in revolutionary Ethiopia (Cambridge: Cambridge university press 1988 pp 259)
ስናጠቃልለው
1. 1420ዎቹ እንደተጻፈ የሚታመነው መጽሓፈ አክሱም በግልጽ እንደሚያሰረዳን የትግራይ ግዛቶችና ወሰኖች 13 ነበሩ:: እነርሱም Tembein, Shire, Seraye, Hamasen, Bur, Sama, Agame, Amba Senait, Geralta, enderta, Sahart and Abergele ናቸው::
ማስረጃ : መጽሓፈ አክሱም , Ethiopia: the Land, Its People, History and Culture By Yohannes Mekonnen. The World through Maps: A History of Cartography (ገጽ 352 ይመልከቱ) By John R. Short
2. 1634 ዓ.ም የተጻፈው የ እማኑኤል በሬዳ መጽሓፍ Tractatus tres historico-geographici (1634): A seventeenth century historical and geographical account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen) 1634» እንደሚያስረዳው የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠገዴ አይደሉም
3. በዘመነ መሳፍንት ኢትዮጵያን ጎብኝቶ የነበረው የጀምስ ብሩስ መጽሓፍም በግልጽ የሚናገረው የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠገዴ አይደሉም፡፡ Travel to discover source of the Nile Volume 3 page 582
4. በአጼ ዮሓንስ ዘመንም የታሪክ ማስረጃዎች የሚያስረግጡት ያንኑ ነው:: የትግራይ ደንበር ተከዜ ነው:; ወልቃይትና ጠገዴ በጎንደር ስር እንደነበሩ በግልጽ ፈረንሳዊው ፕሮፌሰረ ሬክለስ ጽፎታል
5. በአጼ ቴዎድሮስ ዘመንም ወልቃይትም ይህን ጠግዴ በትግራይ ስር አልነበሩም::
6. በጣልያን ግዜም የትግራይ ወሰን በደቡብ እንዳምሆኒ, በደቡብ ምስራቅ አበርገሌ ;በም ዕራብ ሽሬና አዲያቦ ነበሩ እንጂ ወልቃይት ጠግዴ ዋጃ ኮረም እና መሰል ቦታዎች በትግራይ ስር አልነበሩም
7. ወልቃይትንና ጠገዴን ወደ ትግራይ የከለሉት አጼ ኃይለሥላሴ ናቸው:; ይህም በ1943 ዓ.ም የተካሄደውን የቀዳማይ ወያኔን አብዮት ለመበቀልና ሕዝቡንም ለመቅጣት ነው የሚለው: መሰረት እንደሌለው እነሆ ይህ ማስረጃ:: ጣልያን ይሄን ካርታ የሰራው በ1928 ዓ.ም ነበር:: ያኔም በአጼው ግዜም የትግራይ ወሰን ያው ነበር
8. የህዝብ ቁጥርና በሚነገሩት ቋንቋ ነው ወልቃይትንና ጠግዴን ወደ ትግራይ የከለልነው ለሚለውም – የዘርና የቋንቋ ክልልን ለመጀመርያ ግዜ ኢትዮጵያ ላይ የመሰረተው ጣልያን ነው:: ጣልያን ይህን ካርታ ሲሰራ የራሱን የዘርና የቋንቋ ጥናት አድርጎ ነበር:: በዚህም መሰረት ወልቃይትና ጠግዴን ወደ ትግራይ ሳይሆን ያካለላቸው ወደ ጎንደር ነበር:: ይሄ ከሆነ አንድ ትውልድ እንኳን አላለፈው:: ታድያ ያኔ አብላጫ የነበረው ቋንቋና ሕዝብ አሁን ወዴት ገባ?
9. በዚህ ዘመን ያሉ እውቅ የኢይዮጵያ ነክ ፕሮፌሰሮችም ምስክርነታቸው ያው ነው:: የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲው ክሪስቶፈር ክላፕማን እንዳጠቃለሉት
“the area concerned ( welkait -Tsegede) separated from Tigray by impressive natural barrier of Setit Tekezze river has never been governed as part of Tigray at any period in the past, but has come under Gonder and Semein.
10. የአጼ ዮሓንስ የልጅ ልጅ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩምም እንዳረጋገጡት ” የትግራይ ወሰን ተከዜ እንጂ ተከዜን ተሻግረው ያሉት ወልቃይትና ጠግዴ አይደሉም”
አሁንም ቢሆን የወልቃይት የማንነት ጠያቂዎች የ ሃምሳ ሺህ ሰው ፊርማ አሰባስበው ነው ፌዴሬሽን ምክር ቤት ድረስ የሄዱት:: እንግዲህ ይሄ ሁሉ ጫና: ወከባና ግድያ ባለበት በዚህ ወቅት ሃምሳ ሺህ ሰው ፊርማ ማሰባሰብ ከቻሉ ነጻነት አግኝተው ሁሉም ቦታ ቢንቀስቀሱ የምን ያህል ሰው ፊርማ ማሰባሰብ እንደሚችሉ መገመቱ ቀላል ነው:: ያለው እውነታ ይሄው ነው::
ማጠቃለያ
አሁንም ከላይ የጠቀስኳቸውን የፕሮፌሰር ክላፕማንን ቋንቋ ልጠቀምና “ወልቃይትና ጠግዴ በኢትዮጵያ ታሪክ በትግራይ ስር ሆነው አያውቁም”:: ለመጀመርያ ግዜ በትግራይ ስር : እንዲካተቱ የተደረገው በ1994 ነው::
እኔን የሚያሳሰበኝ ግን ሌላ ነው:: በአንድ ሀገር ውስጥ ሆነን ስለ ድንበር እያወራን ነው:: ከዚህ የማንነት ጥያቄም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የሰባዊ መብቶች ጉባኤ አሳውቋል:: ወዴት እየሄድን ይሆን?
(ይቀጥላል)
———–
ዋቤ መጻሕፍትና ሊንኮች
2. The Earth and its Inhabitants, Africa: South and east Africa, by Elisée Reclus 1890
5. Tractatus tres historico-geographici (1634): A seventeenth century historical and geographical account of Tigray, Ethiopia (Aethiopistische Forschungen) 1634
7. Christopher Clapham: Transformation and continuity in revolutionary Ethiopia (Cambridge: Cambridge university press 1988 pp 259
8. The World through Maps: A History of Cartography : John R Short
9. https://archive.org/details/liberaxumae00pari (the Book of Axum part one)

Saturday, 16 July 2016

ከእልቂት እንዲድኑ ትግሬ ሁሉ ወያኔ አለመሆኑን ያሳዩን (አብርሃም ታዬ)

የእናንተ ቤት እየተመረጠ ሲቃጠል፥ የእናንተ ድርጅት እየተነጠለ ጉዳት ሲደርስበት፥ የሰላም ባሳችሁ በየወቅቱ  ሲቃጠል ምንም አይሰማችሁም ትግሬ ወያኔዎች? ኢትዮጵያ ውስጥ ግርግር በተነሳ ቁጥር ለምን የሁሉም ጣት እኛ ላይ ያነጣጥራል ብላቹ ለምን አትገመግሙም። ምርጫ ዘጠና ስባትን ተከትሎ በተነሳው ነውጥ ሆነ የአሁኑ የጎንደር ህዝብ ጥያቄ ላይ የትግሬ  ሆቴል እና ንብረት ኢላማ መሆናቸው ሌላውም ሲነሳ ያንገበግባችኋል።መጽሃፍ እንደሚል በእርጥቡ እንዲህ ከሆነማ በደረቁ እንዴት እንደምትነዱ አስቡት። ዘላለም ስለማትነግሱ የለውጥ አብዮቱ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ለመግባት ገና ግማሽ ሃገር ሲቀረው ሙሉ በሙሉ የዘረኝነት ጄኖሳይድ ሰለባ እንደምትሆኑ ግልጽ ነው። ከኢትዮጵያ ህዝብ  አምስት ከመቶ የማይሞላ የቁጥራችሁን ማነስን የባሰ የሚገዳደር ዕልቂት ተጋርጦባችኋል።በየጊዜው ቂም የያዘባቹ  ከዘጠና ፐርሰንት በላይ  የሚሆን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የግፍ ጽዋው ሲሞላ ይበቀላችኋል። ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በሰላም በፍቅር በመከባበር ለመኖር የሚያስችል የእርቅ ድልድይ  መፍጠር ካለባቹ ጊዜው አሁን ነው።

የተገላቢጦሽ  እናንተ ግን  የአናሳ አምባገነን (minority dictatorship )ነታቹ ብሶባችኋል።ከናዚ ጀርመን  የበለጠ የሚዘገንን ሰይጣናዊ በሆነው ዘረኝነት ታውራቹ ዛሬም  አማራ እና ኦሮሞን በማናቆር  በዳኝነት  ስልጣን ለመክረም የማትፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ይልቁንም ተጋሩ የተሰኘው ማህበራችሁ ሳይቀር ያባሳጨው የወደመው ንብረት እንጂ ከሁለቱም ወገን የተቀጠፈው የሰው ህይወት አይደለም በመግለጫቹ  እንዳሳሰባችሁት።

በአገዛዙ ተማረው ተሰደው  በግፈኛው  አይሲስ እና በሜዲትራንያን ባህር ያለቁት ኢትዮጵያውያን   መሆናቸውን የአለም ሚዲያዎች እየዘገቡት እየነገሯችሁ  ዜግነታቸውን ሳናጣራ እንደርስላቸውም በማለታችሁ ስንቶች መንግስት የሌላቸው አስከሬን ሆኑ? ለህወሃቱ ዘፋኝ ኢያሱ በርሄ ወይም ለመለስ ዜናዊ በድን ግን መንገድ ተዘግቶ ከሁለት ሳምንት በላይ ብሄራዊ የ ሃዘን ቀን ታውጆ ነበር። እነዚህ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሊወክሉ የሚችሉ  ከመቶ በላይ የወገኖች  ደም ከዘረኛው መለስ ዜናዊ ወይ ካንዱ  ዘረኝነትን ሊተክል ከተሰዋ ትግራዋይ ደም በብዙ እጥፍ መከበር ነበረበት።  በጋምቤላ የአኙዋክና የኑዌርን ጎሳ በማጋጨት ለፈጸማችሁት የዘር ጅምላ ጭፍጨፋ የብዙ ሺ ሰዎች  ፍርድ ሳታገኙ የሩዋንዳን ሁቱ እና ቱት ሲን  ኢንተርሃሞይ ዕልቂት ትዘክራላቹ። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላልች ማለት ህወሃት ናት። ጀኖሳይድ ዋች የተባለ ድርጅት እንደዘገበው ኢትዮጵያ ውስጥ በወያኔ ሁሉም አይነት  ድርጊት በዘር ከመከፋፈል classification እስከ ጅምላ ጭፍጨፋ ያሉት ሰባት እርከኖች ተፈጽሞብናል። “Genocide Watch considers Ethiopia to have already reached Stage 7 of the 8 stages of, genocidal massacres, against many of its peoples, including the Anuak, Ogadeni, Oromo, and Omo tribes.”

በደኖ በሃረር በቁማቸው ለተቀበሩት የአማራ ወገኖች እልቂት መንስኤ መፍትሄ ሳታበጁ ከሃያ አምስት  አመት በላይ ተጎልታቹ በፌደራሊዝም ስም ትነግዳላችሁ።

አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው ብሎ ህወሃት እንደተነሳ ሁሉ አማራው እናንተ ላይ የአጸፋ እርምጃ ቢወስድ አይደንቅም። ሆን ተብሎ በሰሜን ጎንደር ያሉ ሴቶች እንዳይወልዱ የሚያመክን መርፌ ለምን ተወጉ? ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ እንዳረጋገጠው የአማራ ህዝብ ብዛት መሆን ካለበት በሶስት ሚሊዮን ያነሰው በዘመናዊ ጀኖሳይድ ሂሳብ ብትገድሉ ኣይደል እንዴ? በጀቱን ለመቀነስ?

በታሪክ ድንበሩ ከተከዜ ወንዝ  አልፎ ያማያውቀውን የትግራይ ክልል ከሱዳን ጋር ለማዋሰን ስትሉ ብሎም በአፋርም በወሎም በኩል ያልነበራችሁን ይዞታ የመውረር አባዜ ግጭት የፈጠራችሁት እናንተ አይደላችሁ እንዴ? በጎንደር ወልቃት ጠገዴ  አማራነት ላይ ያልነበረ ማንነት ባትፈጥሩ ኖሮ ይኼ ሁሉ  ቀውስ ባልመጣ ነበር።

ለመሆኑ የትኛው የኦሮሚያ ክልል ወይ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ነው በህወሃት ከተሰጠው ሃላፊነት ውጭ ራስ ገዝ የሆነው?  ለጠቅላይ ሚንስትር አማካሪ በትግሬው  መለስ ጊዜ ሳይኖር ከደቡብ ለመጣው ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆን ግን አራት አማካሪ በአናቱ ማስቀመጥ ስድብ አይሆንም? ተጠቅላይ ምኒስትርነቱን ለማጉላት ለዛውም አለቆቹ ሁሉ ትግሬ። እራሳቹ  እንደምትናገሩት ኦሮሞዎችን የምታስፈራሩበት የምትገለገሉበት ድርጅት  ኦህዴዶች ልባቸው ቢፋቅ ኦነግ ናቸው። በቅርቡ ግምገማቹ   ስጋታችሁን እንደገለጻችሁት  የአማራው ብአዴን ወይ የደቡቡ አሻንጉሊት ድርጅት  ደኢህዴን ውስጥ ግንቦት ሰባቶች  አሉ። እነዚህ ህወሃትን ያዘሉ አንቀልባ ድርጅቶች ማዘል ደክሞአቸው በቃ ሲሉ ማንም የሚያዝንላቹ የለም።  እስካሁንም ያላችሁት በነዚህ ተላላኪ ካድሬዎች ብቻ ነው። አንዳንድ የኦህዴድ፥ የብአዴን ወይም የደቡብ ህዝብ ደኢህዴን  አመራሮች ከአለቃቸው ህወሃት የበለጠ ዘረኝነቱንስ ሲያስፈጽሙ ወገናቸው ላይ የመጨከናቸውን ያህል ትግሬ ሆኖ ህወሃትን ጨክኖ አንቅሮ የሚተፋ አርአያ ሰብ ያስፈልጋል።

በየድርጅቱ ፥በየሰራዊቱ ፥በየህዋሱ ጠርናፊው ህወሃት ብቻ ሲሆን አንድ ቀን በቃኝ የማይሉ ይመስላችኋል? እስቲ አስቡት ከስልሳ የጦር ጄነራሎች 57 ትግሬ፥ ብሎም የቴሌ እና ሌሎች ሲቪክ መስሪያ ቤቶች ጠርናፊ አለቃ ትግሬ ሲሆን አይሰቀጥጣችሁም?  ንግዱንማ ሙሉ በሙሉ  በድፍረት ተቆጣጥራሁታል።

ኢፈርት በተባለ የህወሃት ክንዳቹ  የሃገሪቱ ሃብትን ስትቀራመቱ ያልመሰላችሁን ከገበያ ስታባርሩ ከርማችሁ  በቅርቡ የሆላንድ ካር(Holland car ) ድርጅትን  ከአዲስ አበባ በቀይ ካርድ አባራችሁ  የፈረንሳዩ ፔጆ መኪና በመስፍን ኢንደስትሪያል ስር እንዲመረት ፋብሪካውን መቀሌ ላይ ገነባችሁ። ትግራይ ልትለማ ሌላው የሚደማ ለምንድነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ቲቪ  ከፍተን ስናይ ማስታወቂያው ሁሉ ሲሚንቶ፣ መድሃኒት ፋብሪካ፥ ምግብ እና የተለያዩ ሸቀጦች ወዘተ የተገነቡት ወይ አድራሻቸው ትግራይ ላይ ነው። ብቻውን የበላ ብቻውን እንደሚሞት ማን በነገራችሁ? የሃገሪቱ ሃብት ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለሁሉም ተደራሽ ይሁን የሚል እንዴት አንድ ቅን አሳቢ ከመሃላችሁ ይጥፋ?

ለኮሎኔል አታክልቲ ገብረሚካኤል  ልጅ ህክምና ከኢፌዲሪ የብረታብረት ኮርፖሬሽን ኤጀንሲ 14 ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች  ሶስት ሚሊዮን ብር አዋጥተው ባንኮክ ታይላንድ አሳከሙት። ብቸኛው የህዝብ ልጅ ሃብታሙ አያሌው ግን በከፍተኛ ኪንታሮት ታሞም ከሃገር ወጥቶ እንዳይታከም ተከልክሏል። ኢፍትሃዊነት በየፈርጁ ማለት ይኸ ነው። ህወሃት ማለት ኢፍት ሃዊነት ነው።

በእርግጥ ትግሬ ሁሉ አልፎለታል ወይም ትግሬ ሁሉ ወያኔ ነው ባይባልም ትግሬ ሆኖ ተቃዋሚ የሆነ አስር አይሞሉም። እንዘርዝር ሲባል ወያኔ አስሮ ከሚፈታቸው አብርሃ ደስታ ፤ አሰግድ ገብረስላሴ ወይም በስደት ካሉት ገብረመድህን እና አረጋሽ ይጠቀሳሉ።በቃ። ከነዚህ  ውጭ ሰው የለም እንዴ? ህወሃት እየገነባ ካለው ራሱን አጥፊ ዘረኝነት አንጻር ቅን ትግሬዎች ተሰባስባቹ ትግራይን እናድን የሚል ማህበር ወይ ፓርቲ ብትመሰርቱ ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በጉልህ ከሚጠቀስላችሁ የጣልያን ጊዜ ባንዳነታቹ (የመለስ ዜናዊ አባትንም የጣልያን ተላላኪ እንደነበሩ በመጥቀስም) ወይም ወይም ሞላ አስገዶም ትህዴንን  ስለካደ    አይደለም ካሳ የምትከፍሉት። ይልቅ ከትግራይ ማሕጸን ተወልደው መሰዋዕት የሆኑት የራስ አሉላ አጽም ብሎም ለጣልያን ያደሩ መስለው ለአጼ ምኒልክ መረጃ በማቀበል ለአደዋው ድል  አስተዋጾ ያበረከቱት የባሻ አውአሎም አጽም እንዳይወቅሳችሁ  ነው።ለወያኔ ተብሎ  የተተኮሰ ጥይት ወይ ፍንጣሪ  እናንተንም በማወቅም ይሁን ባለማውቅ   ስለሚመታችሁ አስቡበት።ነግ በኔ በሉ። ለወያኔ የተወረወረ እሳት ትግሬዎችን በሙሉ እንዳያቃጥል መፍትሄውን ራሳቸው አሁኑኑ ይጠቁሙን ትግሬ ሁሉ ወያኔ ላለመሆኑ በተናጥል ወይ በማህበር  አሳዩን።  ጀግኖች በአንድነት የተዋደቁላትን ሃገር እንዳትፈራርስ ማደረግ  የሁሉም ሃላፊነት ነው።

አብርሃም ታዬ  zeabraham@gmail.com

Friday, 15 July 2016

የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ! ነፃነትህ በደጅህ ቆማለችና እነሆ ግቢ በላት ! – ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

ጎንደር ስለፍቅር ሞትን ይታገሳል! ስለሰላም እልፍ ይጓዛል!
gmder 5 - Copy - Copy (2) - Copy
የጎንደር ህዝብ ለአለፉት 25 ዓመታት በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን የዘር ማጽዳት ወንጀልና የጎንደር ታሪካዊና ለም መሬቶችን ወደ ትግራይ በመከለል በትግራይ ሰፋሪዎች የማጥለቅለቁን የእብሪትና የግፍ ጉዞ በሰላማዊ መንገድ እንዲቀለበስና ችግሩንም በህግ አግባብ ብቻ ለመፍታት ሲል ብቻ ትግስት አስጨራሹንና የተንዛዛውን የህወሃት የህግ ተቋማት ሂደት በትእግስት በመከታተል እስከ መጨረሻው ሰአት ድረስ ለሰላምና ለፍቅር ያለውን የሚደነቅ ፅኑ አቋም አሳይቷል።
ይሁን እንጂ ዛሬም ድረስ በጫካ ህግ የሚመራው ፋሽስቱ የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ሃገራችን ኢትዮጵያንና ህዝቧን በዘር ከፋፍሎ እያባላ፣ ሃብቷን እየዘረፈ፣ በልጆቿ ላይ ግፍንና መከራን እያፈራረቀ፣ መሬቷን በንፁሃን ደም እያጨቀየ፣ ድንበሯን እያፈረሰና፣ ታሪኳን እያጎደፈ የተጓዘበትን የእብሪትና የዘረኝነት መንገድ በማጠናከር በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ፍትህ የጠየቀውን የጎንደር ህዝብ አግባብነት ባለው መንገድ መልስ ከመስጠት ይልቅ እንደ ተራ ሽፍታ አፋኝ ቡድኖቹን በሌሊት በማዝመት “የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ” አቅራቢ ኮሚቴ አባላትን ሐምሌ 5, 2008 ዓ.ም ሌሊት ላይ በማፈን ህዝብን ለማሸበርና ለማሸማቀቅ የሄደበት መንግስታዊ የውንብድና መንገድና በዚህም ምክንያት የፈሰሰው የንጽሃን ወገኖቻችን ደምና የደረሰው ጉዳት እጅግ አስቆጥቶናል።
ጀግናው ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ለህዋሃት አፋኝ ጦር እጄን አልሰጥም በማለት ባደረገው አኩሪ ተጋድሎ የኮራነውን ያህል፤ ከዚህ አፋኝ ቡድን ጋር ለህዝባቸው ክብርና ለነፃነታቸው መከበር ባደረጉት ታላቅ ተጋድሎ ውድ ህይወታቸውን የገበሩትን አርበኛ ሰጠኝ ባብል፣ አርበኛ ሲሳይ ታከለና፣ ሌሎችም መስዋዕትነት የከፈሉ ውድ ወገኖቻችን በጎንደር ህዝብና በትውልዱ የነፃነት ታሪክ ውስጥ ስማቸውን በወርቅ ቀለም ፅፈው አልፈዋል።
ለህወሃት ማስፈራሪያና ዛቻ ሳይንበረከኩ የህዝባቸውን የነፃነት ጥያቄ በማንገብ የጎንደርን ህዝብ ከፊት ሆነው በመምራት ወደዚህ ታሪካዊ የተጋድሎ ምዕራፍ ያሸጋገሩትና አሁንም ትግሉን እዳር ለማድረስ በፅናት የቆሙትን ውድ የቁርጥ ቀን ለጆቻችንን አንገታችንን በኩራትና በክብር ቀና አድርገን እንድንሄድ አብቅታችሁናልና ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።
ጀግናው የጎንደር ህዝብ ሆይ!
ከዚህ የህወሃት ርካሽና ወራዳ ተግባር ባሻገር ነጥሮና ገዝፎ የወጣው የጎንደር ህዝብ ለሰላምና አብሮ ለመኖር ያለውን ታላቅ ትእግስትና በአንፃሩ ደግሞ ግፍን መሸከም ሲበቃውና ጀግኖቹ ሲነኩ በአንድነት እንደ አራስ ነብር በቁጣ መነሳቱና ጠላቶቹን በቁጣው እሳት የማንደዱ እውነታ ነው!
ወደ ነፃነትህና ልዕልናህ ከፊት ሆነው እንዲመሩህ ያስቀደምካቸውን ውድ ልጆችህን ለማፈንና ለማረድ በሌሊት ወረራ የፈፀመውን መንግስት ነኝ ባይና በህግና በሕገመንግሥት እመራለሁ እያለ ሌት ከቀን ከሚለፍፍ በተግባር ግን ከተራ የሰፈር ሽፍታ በማይጠበቅ ውንብድና የሚዳክረውን የህወሃት አፍኝ ቡድን እኩይና የንቀት ተግባር ለማስቆም ከአርማጭሆ እስከ ደባርቅ፣ ከወልቃይት እስከ ሰሜን፣ ከበለሳ እስከ ጭልጋ በሁሉም አቅጣጫ መሪህንና ወገንህን ለመታደግ ቀፎው እንደተነካ ተናዳፊ የንብ መንጋ በአንድነት መዝመትህና ለድል መብቃትህ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያኮራና በህወሃት አምባገነናዊ አገዛዝ ላይ በአንድነት እንዲነሳና እንዲያምፅ መነቃቃትን ፈጥረሃልና እንኳን ደስ ያለህ!
ከህወሃት መዋዋል አጋንንትን እንደማማለድ ያለ ነው!
ኢትዮጵያን ለአለፉት 25 ዓመታት በሃይልና በጭካኔ እየገዛ የሚገኝው ዘራፊና ተስፋፊ ቡድን ዛሬም እንደ ተራ ሽፍታ “የትግራይን ህዝብ ነፃ አወጣለሁ” እያለ ሲፎልልና ከበሮ ሲደልቅ ማየት እጅግ አሳፋሪና መዳረሻውም የት ሊሆን እንደሚችል ማወቅ በልጆች የድብብቆሽ ጨዋታ አዋቂዎችን ለማታለል እንደ መድከም ይቆጠራል።
ስለሆነም ከዚህ ስግብግብና ዘራፊ ቡድን ጋር ስለሰላምም ሆነ ተከባብሮ በጉርብትና ስለመኖር ማሰብም ሆነ መነጋገር ከፋሽስቱ የኢጣሊያ ወራሪ ሃይልና ከአራጁ ድርቡሽ ጋር እንደ መመቻመች የሚቆጠር ሲሆን፤ ህወሃትን “ንፁሃን መግደልህን አቁም” ወይም “ለህግ ተገዛ” ወዘተ እያሉ መማፀን ኩርንችትን ቄጤማ ሁንልኝና ልተኛብህ ብሎ እንደ መማፀን ያለ የቂልነት ሃሳብን ይመስላል።
ስለሆነ ማንኛውም ከህወሃት ጋር የሚደረግ ውይይትም ሆነ ተማፅኖ ምንም አይነት መፍተሄ አያመጣምና ህዝባችን ህወሃትን አስወግዶና በሃይሉ የእራሱንና የመላው ወገኑን ሰላም አስከብሮ መጓዝ የሚችልበትን መንገድ አጥብቆ መፈለግ ይኖርበታል። በሰላም ስም የሚደረግ ማንኛውም ያልተመጣጠነ ድርድር ደማቸው በግፍ የፈሰሰውን ወገኖች መስዋዕትነት ያለዋጋ ማስቀረትና መጭውንም ጊዜ የከፋ ያደርገዋልና ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል እንላለን።

የቆሰለ አውሬ አድብቶ እንዲመጣ እናውቃለንና!
የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ዛሬ በህዝባችን ታላቅ ተጋድሎ ተዋርዶና አፍሮ ወደ መጣበት ቢመለስም እንኳ የደረሰበትን ውርደት ለመበቀል ሃይሉን አሰባስቦና አጠናክሮ እንደሚመለስ ምንም ጥርጥር የለንም።
ይልቁንም ይህን መግለጫ በምናዘጋጅበት ሰአት ከፍተኛ ቁጥር ያለውና በትግሬ ተወላጆች ብቻ የተዋቀረው አውሬው የአግዓዚ ጦር ወደ ጎንደር በገፍ እየተጓጓዘ ስለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ አግኝተናል።
ስለሆነም መላው የጎንደር ህዝብ ከህወሃት እብሪተኛ ቡድን ሊሰነዘርብህ ከሚችል ማንኛውም የበቀል ጥቃት እራስህን እንድትከላከል ከወዲሁ ተዘጋጅ። እኛም በመላው ዓለም የምንገኝ ልጆችህ በሙሉ አቅማችንና ሃይላችን ከጎንህ መቆማችንን ስናረጋግጥልህ በታላቅ ኩራት ነው።
ከህወሃት አገዛዝ ነፃ የሆነች ጎንደር!
ዛሬ በደባርቅ፣ በዳባት፣ በጋይንትና በሌሎችም የጎንደር አካባቢዎች የተቀጣጠለው የነፃነትና የአልገዛም ባይነት ትግል በሁሉም የጎንደር አውራጃዎችና ወረዳዎች ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት ሊንቦገቦግ ይገባዋል።
ሁሉም የጎንደር ግዛት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከህወሃት አገዛዝ እራሱን ነፃ ማውጣት ይኖርብታል። በተለመደው የመናበብ ጥበብ በመጠቀም ሁሉም ጎንደሬ ነፃነቱን ማወጅ አለበት።
ይድረስ ለአማራ ህዝብ!
ፋሽስቱ የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን በጎንደር ህዝብ ላይ ሊያደርስ የሞከረውን አፈና እና ከህዝባችን የተሰጠውን የጀግንነት ምላሽ በንቃት እየተከታተልክና ድጋፍህንም ለማድረግ በደጀንነት መሰለፍህና በቋፍ ላይ መገኘትህ በእጅጉ አኩርቶናል።
ይህ ፋሽስታዊ ስርአት እስካልተወገደና በሃገራችንም ህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እስካልተገነባ ድረስ ሃገሪቷም ሃገር አልሆነች ህዝቧም ከእልቂት፣ ከስደት፣ ከርሃብ፣ ከውርደት፣ ብሎም ከዜግነት ክብር ወርዶ ከመኖር መዳን አልተቻለውም።
ይልቁንም እነዚህ ዘረኛ፣ ዘራፊና፣ ተስፋፊ ቡድኖች በስልጣን ላይ እንዲቆዩና ዳግም ልጆችህን እንዲያርዱና ዘርህን እንዲያጠፉ ከምትፋቅድላቸው ይልቅ ከውስጥህ በመረጥካቸው የጎበዝ አለቆችህ መመራትና መዳኘት እጅጉን ይልቃል።
ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳትል የጎበዝ አለቃህን በመምረጥ እራስህን አደራጅተህ በምትወዳቸውና በምታምናቸው ልጆችህ ተመራ፣ ከወንድምህ የጎንደር ህዝብ ጋር አንድነትህን በማጠናከር ወደ አካባቢህ የሚገባውን የህወሃት ጦር አልፎ እንዳይሄድ አስቁመው። በሰላም እጁን የሚሰጠውን ትጥቁን ተቀብለህ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት አስተናግደው። አብሮህ አንተን መስሎ ሊኖርና ከአንተ ጋር ሊታገል ከወደደ አትከልከለው። መሄድን የሚሻ ከሆነ ወደ ሚፈልግበት ሸኘው። ትጥቄን አልፈታም የሚለውን ተላላኪ ግን በወጣበት አስቀረው።
በዚህም ክፉ ጊዜ የጎንደር ህዝብ አጋርነትህን ይሻልና በተግባር ታረጋግጥለት ዘንድ በህዝባችን ስም ወንድማዊ የትግል ጥሪ አቅርበንልሃል!
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ነፃነትህ በደጅህ ቆማለችና እነሆ ግቢ በላት !
እነሆ ጎንደር አምርሯል። ለዘመናት በትዕግስት የተሸከመው ግፍና በደል ከልኩ አለፈና እነሆ ተሸክሞት የኖረውን ደምመላሽ ወደ ጠላቶቹ አዙሯል። ጎንደር ከአምባገነኑና ከአናሳው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ጋር ላይታረቅ ደም ተቃብቷል። በሌሊት ልጆቹን ሊያፍንና ሊያርድ የመጣውን የሽፋታ ቡድን ለመርዶ ነጋሪ እንዳይተርፉ አድርጎ አስቀርቷቸዋል። በዚህም ከህዋሃት ጭቆና ነፃ የሆነች ጎንደርን የማረጋገጥ የነፃነት ጉዞ ተጀምሯል።
እነሆ ዛሬ ተራው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። አናሳው የህወሃት ሽፋታና ዘራፊ ቡድን የሚንበረከከው በአንድነት ስትነሳ ነውና በያለህበት በአንድነት ተንሳ። ነፃነትህ በደጅህ ቆማለችና ዛሬ ነገ ሳትል ወደ ቤትህ ግቢ በላት። እኛም ዛሬ በትግል ላይ ለሚገኘው ህዝባችን አጋር በመሆን ፋሽስቱን የህወሃት ቡድን በየአካባቢህ በመፋለም ሃይሉን ታዳክመው ዘንድ በመላው የጎንደር ህዝብ ስም የትግል ጥሪ አቅርበንልሃል።

 በመጨረሻም
ጎንደር ውስጥ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የንግድ ተቋማትና፣ ከፍተኛ ንብረት እንደወደመ ይታወቃል። ይህ ውድመት የተፈፀመው በትግራይ ተወላጆች ላይ እንደሆነ በማስመሰል ቀጣፊው የህወሃት መገናኛ ዘዴ ለህዝብ ሲለፍ ይደመጣል። በአንዳንድ የመገናኛ ዘዴዎችም እንዲሁ በህወሃት ካድሬዎች አማካኝነት ሲራገብ ለማየት ችለናል።
የደረሰው ውድመት በህወሃትና የህወሃት ተላላኪና ሰላይ በመሆን ከህዝብ በተዘረፈ ሃብት ላይ በመሆኑ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ እንወዳለን። ጥቃት ከተፈፀመባቸው ድርጅቶች መካከል ንብረትነታቸው ለህወሃት ባደሩ የወልቃይት ተወላጆች የተያዙ እንደሚገኝበት ማረጋገጥ እንወዳልን። የትግራይ ተወላጆች የጥቃት ኢላማ ናቸው የሚባለው ጉንጭ አልፋ ጩሃት የህወሃትና የህወሃቶች ብቻ ነው።
በዚህ አጋጣሚ ለትግራይ ህዝብ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ካስተላለፍናቸው መልዕክቶች የተለየ የምናስተላልፈው ቁምነገር ስለሌለን በእጅጉ እናዝናለን። “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም” እንዲል አማራ!by: 
ድል ነፃነት ለተጠማው ህዝባችን!
ልሳነ ግፉዓን ድርጅት

Wednesday, 13 July 2016

የቅማንት ጥያቄ፤ የአፈታቱ ፈተናና ከጥያቄው ጀርባ የተደበቁ ሰዎች ማንነት – አለሙ ይግለጤ

Alemu.yigletie@gmail.com
እንደ መቅድም
tplf_PAFDየኢህአዴግ መንግስት አገራችንን በዘጠኝ ብሄር ተኮር ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እንዲዋቀር የሚደነግግ ሕገመንግስት በ1987 ዓ.ም አጸደቀ። በዚህ ሕገመንግስት መሰረት ከተቋቋሙት የብሄር ብሄረሰብ ክልሎች መካከል አንዱ የአማራ ብሔራዊ ክልል ነው። የአማራ ብሔራዊ ክልል በዋነኛነት የአማራ ህዝብ የሚኖርበት ክልል ሲሆን በውስጡ የአዊ፣ ህምራ፣ ኦሮሞ፣ አርጎባ፣ ቅማንትና የሌሎችም ብሄረሰቦች ተወላጆች የሚኖሩበት ክልል ነው። የአዊ፣ ህምራና ኦሮሞ ብሄረሰቦች የክልሉ መስተዳድር ሲመሰረት ጀምሮ በክልሉ ህገመንግስት መሰረት በዞን ደረጃ የብሄረሰብ ም/ቤት እንዲያቋቁሙና የራሳቸው የሆነ አስተዳደር እንዲመሰርቱ ተደርጓል። የአርጎባ ብሄረሰብም በሂደት የብሄረሰቡ ልዩ ወረዳ እንዲቋቋም በክልሉ ም/ቤት በአዋጅ ከጸደቀለት በኋላ የብሄረሰቡን ም/ቤት መስርቶ እርሱን በራሱ እያስተዳደረ ይገኛል። የቅማንት ብሄረሰብ የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄም ከብዙ ውጣውረድ በኋላ ሐምሌ 2007 ዓ.ም በክልሉ ም/ቤትና መንግስት ይሁንታን አግኝቶ የብሄረሰቡ የልዩ ወረዳ ማቋቋሚያ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ እንደወጣለትና የፌደሬሽን ም/ቤትም የክልሉን ም/ቤት ወሳኔ እንደተቀበለው ይታወቃል። ይሁንና በክልሉ ም/ቤትና በፌደሬሽን ም/ቢት የጸደቀው የቅማንት ብሄረሰባዊ ም/ቤትን በልዩ ወረዳ ደረጃ የማቋቋም ስራው መሬት ላይ እስካሁን አልተጠናቀቀም።
የጥያቄው አነሳስና አካሄዱ ስለመጠለፉ
ብሄረሰባዊ ም/ቤቱን የማቋቋም ስራው እንዳይከናወን ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው እራሱን በራሱ የቅማንት ህዝብ ተወካይ አድርጎ የሰየመ ስልጣንና ጥቅም ናፋቂ የሆነ ጠባብና አክራሪ ኮሚቴ አባላት በየደረጃው የሚያሰራጩት አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ተጠቃሽ ነው። እነዚህ ጠባብ ሀይሎች ቅማንቱን ከቅማንቱ እንዲሁም ቅማንቱን ከአማራው ለመለያየትና ለማዳማት ቀን ከሌት ይጥራሉ። ባለፈው በተካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ ክንዉን የቅማንት ብሄረሰብ በክልሉ እንደሌለ መደረጉ ሁሉንም እኩል ያስቆጣ ድርጊት ነበር። በዚህ ቆጠራ ወቅት ሁለት ሚልዮን የአማራ ህዝብም “ባልታወቀ” ምክንያት መጥፋቱን ልብ ይሏል። የብሄረሰቡን ከክልሉ መዝገብ አለመካተት ተከትሎ ብሄረሰባዊ ማንነታችን ይታወቅ፤ የራስ በራስ ማስተዳደር መብታችን ይረጋገጥ የሚል የመብት ጥያቄ ተነሳ። የተነሳውን የመብት ጥያቄ አግባብነት በማመን ቅማንቱም አማራውም በመተባበር በአንድነት ጥያቄው በአግባቡ እንዲመለስ የሚቻለውን ሁሉ አድርጓል። ይሁንና በጥያቄው አቀራረብና አፈታት ሂደት የህዝቡን አግባብ ያለው ጥያቄ ለራሳቸው የግል መበልጸጊያና የስልጣን መወጣጫ ለማድረግ አልመው የሚንቀሳቀሱ የኮሚቴ አባላትና ደጋፊወች አልነበሩም ማለት አይደለም። በወቅቱ አንዳንድ የኮሚቴ አባላት በቅማንት ህዝብ ስም ያካሂዱት የነበረው ዘረኝነት የተሞላበት አካሄድ በተለይ ደግሞ በጋብቻ፣ በሀይማኖት፣ በባህልና አብሮ በማደግ ተሳስሮ በኖረው ወንድም የአማራ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ነበር። አፍራሽ የዘረኝነት ቅስቀሳቸው የሁለቱንም ወንድማማች ህዝብ አብሮነት የሚያደፈርስ፤ ለግጭትና ለግድያ የሚጋብዝ ነበር። ይህን የተገነዘቡና መጭውን አርቀው ማየት የቻሉ የሁሉም ወገኖች የጉዳዩን አሳሳቢነት በመገንዘብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የኮሚቴ አባላት ነን ለሚሉት ወገኖች ቆመው እንዲያስቡበት ያለመታከት ጥሪ አቅርበዋል። አክራሪ የኮሚቲው አባላት ልባቸው በመደፈኑና የሽማግሌዎችን ጥሪ ባለመቀበላቸው በኋላ ላይ የተፈራው ደረሰ። በመተማ፣ በአይከል፣ ማውራ፣ ትክል ድንጋይ ወዘተ በህዝቡ በንብረቱና በህይወቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውድመት ደረሰ። የደረሰውን ውድመትም ተከትሎ የአክራሪው ኮሚቴ አባላትም የተወሰኑት ለእስራት ተዳረጉ፤ የተወሰኑት እራሳቸውን ደበቁ፤ የተወሰኑት ከኮሚቴው ስራ ራሳቸውን አገለሉ። አንዳንድ ዘረኛ የኮሚቴው አባላት ግን ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከለኩ አሁንም ህዝቡን በመካፋፈል ድርጊታቸው እንደቀጠሉበት ይገኛሉ።
የጥያቄው ምላሽ ማግኘት መገለጫዎች
ከላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው በአማራ ክልልም ሆነ በፌደሬሽን ም/ቤቶች (በብአዴንም ሆነ በኢህአዴግ) እነዚህ የኮሚቴ አባላት አለን ያሉትን የቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ መልሰውላቸዋል። በዚህም መሰረት፦
  1. በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ውስጥ የሚገኘው የቅማንት ብሄረሰብ በአገራችን ኢትዮጵያ ከሚገኙት የተለያዩ ብሄረሰቦች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በክልልም በአገርአቀፍ ደረጃም እውቅና አግኝቷል። በመሆኑም በክልሉና በፌደሬሽን ም/ቤት የብሄረሰቡ ተወካይ እንዲኖረው ተደርጓል። በተጨማሪም ዘንድሮ ጋምቤላ ላይ በተካሄደው ዓመታዊ “የብሄር ብሄረሰቦች ቀን” ቅማንት እንደ ብሄረሰብ ተወካዮችን በመላክ ተሳትፏል። ይህ የማንነት ጥያቄው ስለመመለሱ አስረጅ ነው።
  2. የቅማንት ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ም/ቤት እንዲቋቋም የሚደነግግ አዋጅ የአማራ ክልል ም/ቤት በሐምሌ 2007 ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ አጽድቋል። የፌደሬሽን ም/ቤትም የክልሉን ውሳኔ ተቀብሎታል። በአዋጅ እንዲቋቋም በጸደቀው 42 የቅማንት ቀበሌወችን በሚያካተው ልዮ ወረዳ የቅማንት ብሄረሰብ እርሱን በርሱ እንዲያስተዳድር ተደንግጓል፤ የአፈጻጸም ዝርዝር መመርያ ተዘጋጅቶለታል። ይህ ሂደት የራስ አስተዳደር ጥያቄውን ይመልሳል።
ይሁንና አንዳንድ የኮሚቴው አባላት አሁንም የመጀመርያው ጥያቄያቸው እንዳልተፈታ በማስመሰል ህዝብን የሚከፋፍልና ለበለጠ እልቂት የሚዳርግ ቅስቀሳ ከማድረግ አልተቆጠቡም። የቀረበው የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ እንደተመለሰ ከላይ ተገልጿል። የኮሚቴው አባላት ጥያቄያችን አልተመለሰም ማለታቸው የተደበቀ ሌላ አጀንዳ እንዳላቸው የሚያስረዳ ይሆናል።
ከጥያቄው ጀርባ የታሰበው ሴራ
የክልሉንም ሆነ የፌደራል መንግስት ውሳኔ ለመቃወም በጠባብ የኮሚቴው አባላት የሚቀርበው ሽፋን ቅማንት ከወገራ እስከ ቋራ በ8 ወረዳወች በሚገኙ 126 ቀበሌዎች ስለሚኖር ከወገራ ጀምሮ እስከ ቋራ ያለው አገር በሙሉ የቅማንት ክልል ብቻ ሆኖ ሊቋቋም ይገባል የሚል የልምዣት ነው። እነሱ አሳነሱት እንጅ ቅማንትና አማራ በሁሉም የጎንደር ወረዳዎች ሊባል በሚችል ደረጃ ተቀላቅለውና ተዋህደው የሚኖሩ ናቸው። ከዚህም የተነሳ ሁለቱ ህዝብ ይለያይ ቢባል በህዝቡ መካከል የሚያስከትለው ችግር በጣም አሳሳቢ ነው። ምን አልባትም በመተማ፣ በአይከል፣ በማውራና በትክል ድንጋይ ከታየው የበለጠ አደጋ መፈጠሩ አይቀሬ ይሆናል። ለዚህም ይመስላል ከህዝቡ ጋር በየደረጃው ብዙ ውይይት ከተደረገና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ጥናትም ካስጠና በኋላ የክልሉ ም/ቤት ቅማንቶች በተለይ የሚኖሩባቸው በኩታገጠምነት የተያያዙት 42 ቀበሌዎች በልዩ ወረዳ ይደራጁ ወደሚለው ውሳኔ የደረሰው። የመንግስት አካላት በተለያየ ጊዜ ከህዝብ ጋር ባደረጓቸው ውይይቶችም እንደተገለጸው ጥናቱ ወደፊትም የሚቀጥል ሲሆን ከ42 ቀበሌዎች በተጨማሪም ወደፊት መመዘኛውን የሚያሟሉ ቀበሌዎች በህዝብ ይሁንታ ሲያገኙ እየተካተቱ እንደሚሄዱ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ይሁንና በአካባቢው መረጋጋት ሰፍኖ ህዝቡም በሰላም ወደእለት ስራው ከተመለሰ አክራሪው የኮሚቴው አባላት የግል ጥቅማቸውና በተላላኪነት የቆሙለት ዓላማ ግቡን ስለማይመታ ጭቁኑን አርሶአደርና ወጣት ተማሪዎችን መሰላል አድርገው ሊጠቀሙባችው እየሞከሩ ነው።
አክራሪ የኮሚቴ አባላቱ አርሶ አደሩን 126 ቀበሌዎችን በቅማንት ዞን ካደራጀን የቋራንና የመተማን ጥቁር አፈር መሬት ሌላውን (አማራውን ማለታቸው ነው) እያስወጣን እንሰጥሃለን እያሉ በመቀስቀስ ህዝቡን ለበለጠ እልቂት እያዘጋጁት ይገኛሉ። ለወጣት “ምሁራን” እና ተማሪዎችም በ126 ቀበሌዎች የራሳችን ዞን ስንመሰርት ለተለያዪ መምርያዎች ብዙ የተማረ ሰው ስለሚያስፈልግ አሁን ከእኛ ጋር ከተባበራችሁ ዞን ስንመሰርት ደህና ስልጣን ታገኛላችሁ፤ የዞናችን ዋና ከተማ ጎንደር ከተማ ስለሚሆን ለመኖርያና ለንግድ የሚሆን ቦታ ታገኛላችሁ ወዘተ የሚል ማማለያ በማቅረብ የጥፋት ተባባሪ ሊያደርጓቸው እየጣሩ ነው።
በአጠቃላይ ከወገራ እስከ ቋራ ያሉ የ126 ቀበሌዎች የዞን ምስረታ እና ጎንደር ከተማ የቅማንት ዋና ከተማነት ትርክታቸው የአክራሪው ኮሚቴ አባላት ጥያቄ ፊት ለፊት እንደሚሉት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ሳይሆን ህዝቡን የመበታተንና የማጫረስ እንዲሁም ድብቅ ግዛት የማስፋፋት ጥያቄ መሆኑ እየተገለጠ ነው። ይህ ካልሆነ አሁን ባለው የጎንደር ከተማ አስተዳደር በሚሰጠው አገልግሎት ቅማንት ቅማንት በመሆኑ ብቻ ያጣው ምንድን ነው? አማራስ አማራ በመሆኑ ብቻ ያገኘው ምንድን ነው? ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ ብቻ እንኳ የጎንደር አስተዳዳሪ ከነበሩት አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች ስንቶቹ ቅማንት እንዳልነበሩ በድፍረት መናገር የሚችል የኮሚቴ አባል አለ? ታድያ ጎንደር ከተማን የቅማንት መናገሻ እንደርጋለንን ምን አመጣው? ጥድፊያው ገበሬውን ከእርሻ መሬቱ ላይ ለማፈናቀል ከተሜውንም “የአይንህ ቀለም አላማረንም” ከከተማችን ውጣ ለማለት ነው? የጎንደር ህዝብ አስተዳዳሪው አማራም ይሁን ቅማንት መከራውንም ደስታውንም እኩል ሲቀምስ ኑሯል። አሁንም እየኖረ ነው፤ ወደፊትም ይኖራል። ሰላሙን ለማደፍረስና ጎንደርን ለማዳማት በአክራሪ የኮሚቴ አባላት የሚሽረበውን ሴራ እንደእስከዛሬው ሁሉ ህዝቡ በአንድነት በመቆም ያከሽፈዋል።
ከጀርባ ያደፈጠው አካል የሚጠቀምበት የትግል ታክቲክ
አክራሪ የኮሚቴው አባላት አጀንዳቸውን ወደፊት ለመግፋት፣ ከአክራሪነታቸውም ባሻገር በመንግስት ተቀባይነት ለማግኘትና የሁከትና መለያየት ዓላማቸውን ለማሳካት የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ።
  1. ህዝቡን መከፋፈልና ማሸማቀቅ፦ አክራሪዎቹ ቅማንትን ከቅማንት፤ ቅማንትን ከአማራ ይከፋፍላሉ። በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መወያያቸው መድረክ ላይ አማራን ለመግለጽ የሚጠቀሙበት ቋንቋ በጣም አሳፋሪ ነው። ቅማንት መሆናቸው እስከሚያጠራጥር ድረስ። በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የማጥላላት ስራ ያካሄዳሉ። ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛ፣ ቆማጣ፣ ለማኝ፣ ድሃ፣ ፈሪ፣ የራሱ ታሪክ የለለው ወዘተ አማራው ላይ የሚለጥፉት ገለባ-አልባ ጭቃ ነው። እነዚህ ሰዎች የእነርሱ ተቃራኒ ከመሰላቸው የቅማንት ተወላጅም ቢሆን የጭቃ ጅራፋቸውን ማንሳታቸው አልቀረም። ከቅማንትነትም ወረድ ይሉና የጭልጋ ቅማንት፣ የጎንደር ዙሪያ ቅማንት፣ የአርማጭሆ ቅማንት፣ ግማሽ ቅማንት፣ ሩብ ቅማንት፣ 1/8ኛ ቅማንት ወዘተ በማለት ክፍፍሉን ያከፉታል። ከእነርሱ ጋር የሚስማማ ከሆነ 1/8ኛ ቅማንትም ቢሆን የእነርሱ ጀግና ነው፤ ባንፃሩ ደግሞ ሙሉ ቅማንት ሆኖ ከነሱ አስተሳሰብ ጋር ካልተስማማ ወይ ቅማንትነቱን ይሰርዙታል ወይም ባንዳ የሚል ታርጋ ይለጥፉበታል። በዚህ ሁኔታ ሰዎችን እያሸማቀቁ እነርሱ ወደ ሚፈልጉት ግን ለመሄድ ይሞክራሉ። ይህን ጉዳይ በማስረጃ እንመልከተው።
  2. አቶ በየነ አስማረ የተባሉ የብሄረሰቡ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ የቅማንት የማንነትና ራስን የማስተዳዳር ጥያቄ የተነሳበትን አቅጣጫውን የመሳት ምልክቶች መታየት ሲጀምሩ ጉዳዩ ወደ ግጭት ከማምራቱ በፊት በተለያዩ ሚዲያዎች (ቪኦኤን ጨምሮ) ቀርበው የቀረበውን ጥያቄ በእርጋታ በመወያየትና በመደማመጥ መፍታት እንደሚያስፈልግ ተናገሩ። ሁሉንም ህዝብ ባሳተፈ ሰላማዊ መንገድ ችግሩ ካልተፈታ አላስፈላጊ የህዝብ ግጭት ሊያስከትል ይችላል በማለት ምክራቸውን አስቀድመው አቀረቡ። በኋላም እንደታየው ሰሚ በማጣታቸው አቶ በየነ አስቀድመው ያስጠነቀቁት መከራ ደረሰ። አቶ በየነ ሁሉም ነገር በሰላምና በአንድነት እንዲሆን በመመኘታቸው በአክራሪ የኮሚቴው አባላት ዘንድ በየማህበራዊ ሚዲያው ሁሉ የቅማንት ጠላት፣ ባንዳ፣ ከዚያም ወረድ አድርገው እርሱ “የጎንደር ዙርያ ቅማንት ስለሆነ ነው ይህን ያለው” ወዘተ በማለት ልያሽማቋቸው ሞክረዋል፤ አክራሪዎች ባይሳካላቸውም። እነአቶ በየነ አስማረ ግን ለሁለቱም ወንድማማች ህዝብ አንድነት ዛሬም በጽናት የሚቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ።
  3. የአቶ ደሴ ግዛቱን ጉዳይ እንመልከት። አቶ ደሴ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ በጭልጋ ወረዳ አይከል ከተማ የሚገኘው ቬሩት የተሰኘ ዘመናዊ ሆቴል ባለቤት ናቸው። ይህን ሆቴል በመክፈታቸው ለከተማው ልማት አስተዋጽኦ አበርክተዋል፤ ለአካባቢው ነዋሪ ደግሞ የስራ እድል ፈጥረዋል። ይሁንና የአክራሪው ኮሚቴ አባላት አቶ ደሴን በፀረ-ቅማንትነት ፈርጀው በየማህበራዊ ድረ-ገጽ መወያያ መድረኮችና በቴሌኮንፈረሳቸው ከፍተኛ የሆነ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሄደውባቸዋል። ከመንግስት ጋር ለማናከስም የጎንደር ህብረትና የአርበኞች ግንቦት 7 አባል እንደሆኑ ቀስቅሰውባቸዋል። ከዚህም አልፎ ሆቴላቸው እንዲቃጠልና እርሳቸውም በተገኙበት እርምጃ እንዲወሰድባቸው አክራሪዎቹ ለተከታዮቻቸው በፌስቡክ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ይህም የአክራሪ ኮሚቴዎች ሁሉቱን ህዝብ የመከፋፈልና እርስ በእርስ የማጫረስ ቅስቀሳቸው አስረጅ ነው።
  4. ከወረዳ እስከ ፌደራል መንግስት ድረስ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት ተቋማትንና ኃላፊዎችን ለመከፋፈል ያላሰለሰ ሙከራ ማድረግ፦ መጀመሪያ ላይ የቅማንት ጥያቄን በማፈን የክልሉ መንግስት ውሳኔ እንዳይሰጥ የሚያደርጉ በሰሜን ጎንደር አስተዳደር ሊቀመንበርና ምክትላቸው የሚመራው የበለሳና የአለፋ ወረዳወች ቡድን ነው በማለት የዞኑን አስተዳደር ለመከፋፈል ሙከራ አደረጉ። ትንሽ ቆይተው ደግሞ ጋይንቴዎችና ፋርጦች ዋነኛ የቅማንት ጠላቶች ናቸው የሚል ቅስቀሳ ጀመሩ። በዚህ ወቅት ዋነኛ ጠላቶቻችን ናቸው የተባሉት አቶ ግዛት አቡየና አቶ አማረ ሰጤ ነበሩ።ይህ ሁሉ ሲሆን የክልሉን መንግስት የእነርሱ ደጋፊ አድርገው ይቀሰቅሱ ነበር። ከላይ እንደተገለጸው የክልሉ ም/ቤት ሐምሌ 2007 ዓ.ም ላይ ለቀረበለት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ ሰጠ። በዚህ ጊዜ አክራሪዎቹ የጥያቄው መመለስ ሊያስደስታቸው ሲገባ እነርሱ ግን የክልሉ ም/ቤትን በጠላትነት ፈረጁ። በክልሉ መንግስት ከፍተኛ የአመራር አባላት ላይም ከፍተኛ የማጥላላት ዘመቻ በማህበራዊ ሚዲያው ማካሄድ ጀመሩ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አቶ አለምነው መኮንን፣ አቶ ደሴ አሰሜ፣ አቶ አገኘሁ ተሻገርና አቶ ያለው አባተ በአክራሪዎች የማጥላላት ዘመቻ ከተደረገባቸው የክልል አመራሮች ዋናዎቹ ነበሩ። እንደ ዞኑ አስተዳደር ሁሉ የክልሉን መንግስትና አመራሩን በጥላትነት ከፈረጁ በኋላ “የአፄዎች ናፋቂ” የሆነው የአማራ ክልል አመራር ችግራችን ሊፈታው ስላልቻለ ጥያቄያቸውን ለፌደሬሽን ም/ቤት ማቅረባቸውን አወጁ። የፌደሬሽን ም/ቤትም የቀረበለትን ጥያቄ ከመረመረ በኋላ የአማራ ክልል ም/ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ አጸደቀ። አክራሪ የኮሚቴው አባላት ግን እውነታውን ወደጎን በመተው የፌደሬሽንና የክልሉ ም/ቤቶች በቅማንት ጥያቄ አፈታት ላይ የተለያዩ በማስመሰል የክልሉ መንግስት ውሳኔውን እንዲቀይር በፌደሬሽን ም/ቤት ታዟል በማለት ህዝቡን የማደናገር እርምጃቸውን ቀጠሉበት። ቅስቀሳቸውንም ተከትሎ ከፍተኛ ደም መፋሰስና ንብረት መውደም ደረሰ። ከዚያ ሁሉ እልቂትና ውድመት በኋላም አክራሪዎች የፈደራሉ መንግስት ይደግፈናል የክልሉ መንግስት ግን ጥላታችን ነው የሚለውን የመከፋፈል ቅስቀሳ አላቆሙም። ለዚህም ይመስላል በቅርቡ በአቶ ካሳ ተክለብርሐን (የቀድሞው የፌደሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤና የወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር) የተመራ ልኡክ ጎንደር ከተማ ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ በቅማንት ጥያቄ አፈታት ላይ የፌደራል መንግስቱ ከአማራ ክልል መንግስት የተለየ አቋም እንደሌለው ለህዝቡ በይፋ የገለጹት። አቶ ካሳ በስብሰባው ወቅት 42 ቀበሌዎችን ያካተተ የቅማንት ብሄረሰብ የልዩ ወረዳ ም/ቤት እንዲቋቋምና የሚቀሩ ቀበሌዎች አሉ ከተባለም ወደፊት በጥናት እየተረጋገጠ የሚስተካከልበት አግባብ እንደሚኖር በማስገንዘብ የአክራሪ ኮሚቴዎችን በቅማንት ጥያቄ አፈታት የፌደራሉና የክልሉ መንግስት አልተስማሙም የሚለውን አፍራሽና ከፋፋይ ቅስቀሳ በተግባር ሰባብረውታል።
ይሁንና አክራሪ የኮሚቴው አባላት ህዝቡን የማጋጨትና የማተራመስ ቅስቀሳቸውን አሁንም ቀጥለውበታል።
ከጥያቄው ጀርባ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አስተባባሪዎች
አክራሪ የኮሚቴው አባላትን በፕሮፓጋንዳ፣ ፋይናንስና ሎጀስቲክስ የሚያደሯጃቸውና የሚያሰማሯቸው ለራሳቸው የግል ጥቅም መሰረት ለመጣል የሚሯሯጡ በውጭ የሚኖሩ ግለሰቦችም ይገኙበታል። የእነዚህን ሰዎች ማንነትና የሰሩትንም ስራ ማየቱ ለብዙሃኑ አስተማሪ ስለሚሆን ለዛሬ ሦስቱን “የቅማንት ተቆርቋሪዎች” ነን ባዮች ዶሴ እንደሚከተለው እናቀርባለን።
  1. አቶ ጥጋቡ ክብረት ተቀባ፦ ይህ ግለሰብ የተወለደው ጎንደር ክ/ሀገር ጭልጋ ወረዳ ጮንጮቅ ቀበሌ ነው። ወደ 40 ዓመት አካባቢ አሜርካን አገር በሲያትል ዋሽንግተን ነዋሪ ነው። አቶ ጥጋቡ በደርግ ጊዜ ለአይከል ከተማ የኤሌክትሪክ ሀይል መብራት ለማስገባት በሚል ሽፋን ከሌላው የጭልጋ ተወላጅ አቶ እጹብ አሰፋ ገላጋይ ጋር በመተባበር ከአካባቢው ተወላጆች፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያንና አሜርካውያንም ጭምር ከ120ሺ እስከ 140ሺ ዶላር የሚገመት ገንዘብ ካሰባሰቡ በኋላ ገንዘቡን ተከፋፍለው ለግል መጠቀሚያ ካደረጉት ሰዎች ውስጥ ዋነኛው ነው። ከዚህ በተጨማሪም አቶ ጥጋቡ አቶ ደሳለኝ አደመ ከተባለ ግለሰብ ጋር በመሆን በፈረንጅ አቆጣጠር መጋቢት 12 ቀን 2002 ዓ.ም በሚኖርበት ሲያትል ዋሽንግተን የቅማንት ታሪካዊ ህብረተሰብ (Qemant Historical Society) የሚባል ድርጅት በስቴቱ አስመዝግቦ ነበር። በዚህ ድርጅት ስም ከመንግስት የበጀት መደጎሚያ 30ሺ ዶላር በየዓመቱ እየወሰደ አቶ ጥጋቡ ለግል መጠቀሚያ አድርጎታል። በ6ኛው ዓመት የዋሽንግተን መንግስት የአቶ ጥጋቡ ድርጅት የሚወስደውን የበጀት መደጎሚያ ለቅማንት ታሪካዊ ማህበረሰብ በሚገባ አለማዋሉን በኦዲት ስላረጋገጠ የአቶ ጥጋቡን ድርጅት በፈረንጅ አቆጣጠር ሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ከድርጅትነት ተሰርዟል። በዚህም ምክንያት እስከዛሬ ድረስ በአሜርካ በሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ከማህበራዊ ህይዎት የተገለለ ስው ነው። አቶ ጥጋቡ በቅማንት ጥያቄ ሽፋን በጎንደር የተፈጠረውን ሁከትና ደምመፋሰስ ከጀርባ ሆኖ በማቀድ፣ በማደራጀትና በመምራት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ለዚህም በየቀኑ በስልክ፣ በኢሜል እንዲሁም በፊስቡክ በመገናኘት የተፈጠረውን ደምመፋሰስ ያስተባበረ ነው። አሁንም በዚህ አፍራሽ ተግባሩ እንደቀጠለ ይገኛል።
  2. አቶ ታደለ አሰፋ ገላጋይ፦ የተወለደው በጎንደር ክ/ሀገር ጭልጋ ወረዳ አይከል ከተማ ሲሆን አሁን የሚኖረው አሜርካን አገር በፖርትላንድ ኦሪገን ነው። አቶ ታደለ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው የአቶ እጹብ ወንድም ሲሆን ለጭልጋ ወረዳ አይከል 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት ማሳደሻ፣ የሽንት ቤት መስሪያ፣ ላቦራቶሪና ቤተ-መጽሐፍት ማቋቋሚያ የሚሆን በማለት ከአካባቢው ተወላጆችና ከሌሎችም ኢትዮጵያውያን የተሰበሰበውን 65ሺ ዶላር ወስዶ አዲስ አበባ ላይ የግል መኖሪያ ቪላ የሰራ ሰው ነው። አቶ ታደለ የአሜርካውን አስተባባሪ ኮሚቴ በመወከል በየጊዜው አዲስ አበባ በመሄድ እነአቶ ከፋለ ማሞን ከጭልጋ አዲስ አበባ አስመጥቶ አሜርካ በቴሌኮንፈረስ ያሰባሰበውን ገንዘብና የብጥብጥ አጀንዳ ሰጥቶ ይመለሳል። አቶ ታደለ በተለያዩ የፌስቡክ አካውንቶች በመጠቀም በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ ያደረገ ነው። በጎንደር ግጭት በተካሄደባቸው ቦታዎች በሙሉ በተለይ ደግሞ በአይከል፣ በመተማና በማውራ ለተካሄደው ፍጅት ህዝቡን ለእልቂት እንዲነሳሳ ቀስቅሷል። በፎቶው እንደሚታየው አሮጊቶችና ሴቶችን ሳይቀር መሳሪያ እያስያዙ ለጦርነትና ለግድያ እንዲወጡ አስተባብሯል።
  3. ወ/ሮ አበባ ተፈሪ ንጉሴ፦ የተወለደችው ጎንደር ከተማ ነው። ላለፉት 35 ዓመታት አካባቢ ነዋሪነቷ አሜርካን አገር በሲያትል ዋሽንግተን ነው። ወ/ሮ አበባ ለሦስት ጊዜ በቁርባን አግብታ የፈታች ስትሆን አራትኛ ባሏ ይሆናል ተብሎ የነበረው “ጓደኛዋ” በሰላም አብረው አምሽተው ከእርሷ መኖሪያ ቤት ፊት ለፊት በመኪናው ውስጥ “በድንገት” ሞቶ በመገኘቱ በሲያትል የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። ወ/ሮ አበባ በማህበራዊ ሚድያ ፀረ-አማራና ጥላቻ የተሞላበት ቅስቀሳ በየቀኑ ታራምዳለች። ለዚህም የፊስቡክ ገጿ ምስክር ነው። ከዚህ በፊት ከሌሎች የቅማንት ብሄረሰብ ተወላጅ ወንድሞች ጋር ለውይይት በቪኦኤ ቀርባ ሰላምና የቆየው አንድነታችን ይሻላል ያሉትን ወንድሞች (አቶ በየነ አስማረና አቶ አበበ ንጋቱን) በባንዳነት የከሰሰች የሁከት እናት ናት። በሰሜን አሜርካ የሚገኙትን የብጥብጥና መለያየት ደጋፊዎች ለማሰባበስ ከአቶ ጥጋቡና ከአቶ ታደለ ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ቴሌኮንፈረስ ታስተባብራለች፤ ትመራለች። ለአገር ቤቱ አክራሪ የኮሚቴ አባላትም ገንዘብ እያሰባሰበች ትልካለች።
እንደ መደምደሚያ
ከላይ እንደተገለጸው እነዚህ ግለሰቦች ከ35 እስከ 40 ዓመታት በአሜርካ ሲኖሩ ለተወለዱበት አካባቢ ያበረከቱት አንዳች መልካም ነገር የለም። እንዲያውም ለመብራት ማስገቢያ፣ ለት/ቤት ማሳደሻ፣ ለላቦራቶሪና ለቤተመጽሐፍት ማቋቋሚያ ወዘተ እያሉ በአገሩና በህዝቡ ስም የሰበሰቡትን ወደ 200ሺ ዶላር የሚደርስ ገንዘብ ተከፋፍለው ለግል መጠቀሚያ አድርገዋል። ለራሳቸው የሚያከራዩት ቪላ ቤት አዲስ አበባ ላይ ሲሰሩ ተወልደው ላደጉበትና እንቆረቆርለታል ለሚሉት ለቅማንት ህዝብ ግን በስሙ ከመነገድ በስተቀር ያደረጉለት አንዳች ነገር የለም። ይባስ ብለው ለአካባቢው ልማት ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ ያፈሰሱትንና ለወጣቱ የስራ እድል የፈጠሩትን እንደነ አቶ ደሴ ግዛቱ አይነት ሰዎች ባልዋሉበት እየወነጀሉ በፌስቡክ ስማቸውን በማጥፋት ለማሸማቀቅ ሙከራ ያደርጋሉ። ይህ ድርጊታቸው እነዚህ ግለሰቦች ከራሳቸው ፍላጎት ውጭ ለአካባቢ ልማትም ሆነ ለህዝቡ ምንም ደንታ እንደሌላቸው ያሳያል።
በአጠቃላይ እነዚህ ግለሰቦች አገር ቤት በቅማንት ስም እራሱን የሰየመውን አክራሪ የኮሚቴ አባላትን በመጠቀም ባጠቃላይ በጎንደር በተለይ ደግሞ በመተማ፣ በጭልጋና አርማጭሆ በየጊዜው የተከሰተውን ፀረ-ሳላም እንቅስቃሴ በጋራ አቅደዋል፤ አስተባብረዋል፤ መርተዋል። አክራሪ የኮሚቴው አባላትን በገንዘብ በመደለልና በተቃውሞ እንቅስቃሴ መሳተፋቸው ወደ ውጭ አገር ለመሄድ እንደሚረዳ በማማለል አካባቢው እንዲተራመስና ህዝቡ እንዲከፋፈል አድርገዋል። የሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያንን (አማራም ቅማንትም) መልካም ስም ለማጉደፍ ጥረዋል፤ ሰዎች እንዲገደሉ በፊስቡክ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፤ ከፍተኛ ቅስቀሳም አድርገዋል። አሁንም ከአፍራሽ ተግባራቸው አልተቆጠቡም። በመሆኑም የእነዚህ ግለሰቦችንና ተላላኪያቸው የሆኑትን አክራሪ ትቂት የኮሚቴ አባላትን ማንነትና እኩይ ዓላማ በአግባቡ በመረዳት ወንድማማች የሆነው የአማራና ቅማንት ህዝብ በጋራ ቆሞ የጋራ ባህሉንና አገሩን ሊጠብቅ ይገባዋል። ለዚህ አጋዥ ይሆን ዘንድ ሌሎች የችግሩ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችንም በየደረጃው ያለው ህዝብ እንዲያውቃቸው በተከታታይ ማንነትቸውንና ህዝቡን ለመበታተን የሚያደርጉትን ድርጊት በመረጃ እየተደገፈ በተከታታይ መቅረቡ ይቀጥላል። እስከዚያው ቸር እንሰንብት።

Monday, 11 July 2016

ዜጎችን ማፈናቀል መግደልና ማሰደድ የህወሃት አይነተኛ መግለጫዎች ናቸው!!! (አርበኞች ግንቦት 7)

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በአገራችንና በህዝባችን ላይ ሲፈጽም የቆየውና እየፈጸመ ያለው ግፍና ስቃይ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደልም። አፈና ፣ እስር፣ ግድያና ዜጎችን ማፈናቀል አይነተኛ መግለጫዎቹ የሆነው ይህ የህወሃት አገዛዝ፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችንና የከተማ ቦታዎችን በመቸብቸብ ሃብት ለማካበት ባለው ዕቅድ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬና የትውልድ መንደሮቻቸው በግፍ እንዲፈናቀሉ አድርጎአል። አሁንም እያደረገ ነው ።
ሰሞኑን በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ቀርሳና ኮንቶማ በተባሉ ቀበሌዎች ከ30 ሺ በላይ የሚገመት ህዝብ ለአመታት ከኖረበት መኖሪያ ቤቶች በሃይል ተገፍትረው በመውጣት ጎዳና ላይ እንዲበተኑ ተደርጎአል። በዚህም እርምጃ ምክንያት አቅመደካማ የሆኑ አዛውንቶች፤ ነፍሰጡሮችና ከወለዱ ገና ሳምንታት ያልሞላቸው እመጫቶች፤ የሚያጠቡ እናቶች፤ ህጻናትና ለጋ ወጣቶች ለከፋ ችግር ተዳርገው ለቅሶና ዋይታ በማሰማት ላይ ናቸው ። በስንት ልፋትና ድካም ከሰሩዋቸው ቤቶች ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጠን ወይም ካሳ ሳይከፈለን አንወጣም በማለት ለማንገራገር የሞከሩ 10 ሰዎች በፖሊስ ጥይት ተገደለዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ለእስር ተዳርገዋል።
ህወሃት እንዲህ አይነት የጭካኔ እርምጃ እየወሰደ ያለው በክፍለ ከተማው የሰፈሩት ሰዎች “ህገወጦች ናቸው” በሚል ሰበብ ነው። ትናንት ባዶ እግራቸውን ነፍጥ አንግበው ቤተመንግሥቱን የተቆጣጠሩና ጄሌዎቻቸው ከመሃል ከተማው ዜጎችን እያፈናቀሉ ቪላና ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ሲገነቡ ህገወጥ ያልተባሉት ሰዎች፣ አረብ አገር ድረስ ተጉዘው በግርድና ሥራ ሳይቀር በመሥራት ባገኙት ገንዘብ በአገራቸው መሬት ላይ ጎጆ የቀለሱ ለምንድነው ህገወጥ የሚባሉት የሚለውን ለታሪክ ፍርድ እንተወውና እነዚህ ህገወጥ የተባሉ ሰዎች በመንግሥት ይዞታ ሥር ካሉ የአገልግሎት ድርጅቶች ጋር ተዋውለው መብራትና ውሃ አስገብተው ሲጠቀሙ መኖራቸው ፤ ገንዘብ በማዋጣት መንገድ ፤ ጤና ጣቢያዎችንና ትምህርት ቤቶችን በከተማው አስተዳደር ድጋፍ ማስገነባታቸው ፤ የህወሃት የንግድ ድርጅቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠር ትርፍ ለሚዝቁበት የአባይ ግድብ ቦንድ በየመኖሪያቤታቸው ቁጥር ሲሸጥላቸው የነበረና የምዕራቡን አለም ለማደናገር በየአምስት አመቱ የሚደረገውን የምርጫ ድራማ ለማድመቅ በግዳጅ እንዲመዘገቡና ድምጽ እንዲሰጡ ሲደረጉ መቆየታቸው ብቻውን አገዛዙ ሲመቸው እውቅና ሰጪ ሳይመቸው ደግሞ እውቅና ነሺ መሆኑን የሚያሳይ፣ ለፍትህና ለርእትዕ የማይሰራ የዘራፊዎች ቡድን በመሆኑ፣ የድሆችን ቤቶች ለማፍረስ የወሰደው እርምጃ በየትኛውም መስፈረት ተቀባይነት የሌለው ህገወጥ ድርጊት ነው። ለነገሩ ህገወጥ ከሆነ ቡድን ህጋዊነትን መጠበቅ አይቻልምና ወያኔ በህግ ሽፋን የሚወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ህገወጥነታቸውን አይለውጠውም።
አባቶቻችን አገራቸውን ከባዕድ ወረራ ለመከላከል ደማቸውን ያፈሰሱትና አጥንታቸውን የከሰከሱ መጪው ትውልድ በአገሪቱ አንገት ማስገቢያ ጎጆ እንዲኖረው በማሰብ እንጅ፣ በደምና በአጥንት የተገዛው መሬት ለውጭ አገር ዜጎች እንዲቸበቸብ ወይም በመንግስት ስም የተደራጁ ሽፍቶች እንዲዘርፉት አልነበረም።
ሌላው አስገራሚና አሳዛኙ ነገር እንዲህ አይነት ሰቆቃ የተፈጸመባቸውና በዚህ ክረምት ወቅት ቤቶቻቸው ፈርሶና ንብረቶቻቸው ወድሞ ወደ ፍጹም ድህነት እንዲገቡ በተደረጉት ዜጎች መሬት ላይ ፣ ህወሃት ኮንዶሚኒዬሞችን ገንብቶ ለዲያስፖራ ለመቸብቸብ ዕቅድ ያለው መሆኑ ነው ። ዲያስፖራው አገዛዙ በወገኖቹ ላይ የሚፈጽማቸውን ሰቆቃና ግድያ በማጋለጥ ሥራ ላይ በመጠመዱ የህወሃት መሪዎች እረፍት አጥተዋል። በተለይ ከምርጫ 97 ወዲህ አጋዚ የተባለው ሃይል በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል የቀን ጉዳይ ካልሆነ በቀር በአለም አቀፍ ወንጀል እንደሚያስጠይቅ ወያኔ ይረዳል። ይህንን ስጋት ለማስቆም የዲያስፖራን እንቅስቃሴ ማዳከም እንደስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስ የጀመረው የነ ቴዎድሮስ አድሃኖም አገዛዝ፣ ዲያስፖራውን በጥቅም በመከፋፈል ስጋቱ ይቀነሳል ብሎ ያምናል። ከዚህም በተጨማሪ አገር ውስጥ የሚደረገውን አልገዛም ባይነት ትግል ለማጠናከር የዲያስፖራው እምቅ ሃይል የሚፈጥረውን ተአምር ህወሃት አውቆታል። ላፍቶ ክፈለ ከተማ 40 በ60 በተባለው ፕሮጄክት የኮንዶሚኒዬም ባለቤት በመሆን የአገራቸውንና የወገኖቻቸውን ስቃይ ለማራዘም ላኮበኮቡ የዲያስፖራ አባላት እየተመቻቸች ያለ ሰፈር ነው። ከውስጧ እየተሰማ ያለው ለቅሶና ዋይታ የማይቆረቁራቸው ፤ ኮንዶሚኒዬም ቤት የሚያማልላቸው ዲያስፖራዎች አይኖሩም አይባልም።
አርበኞች ግንቦት 7 የህወሃት አገዛዝ ዜጎችን በመግደልና በማሰር ከቀያቸውና ከመኖሪያቤታቸው በሚያፈናቅለው የከተማም ሆነ የገጠር መሬት ላይ ማንም ሰው በህግ ፊት በዘላቂነት የሚጸና መብት ሊያገኝ ይችላል ብሎ አያምንም። ህወሃት በሚወረውርላቸው የጥቅም ፍርፋሪ የወጎኖቻቸውን ስቃይና መከራ ዕድሜ እያራዘሙ ያሉ ከየማህበረሰቡ የተገዙ ስላሉ በተለመደው ርካሽ ዋጋ በንጽጽር ደህና መኖር እየቻለ ካለው የዲያስፖራ ማህበረሰብ ሰዎችን መሸመት እችላለሁ ብሎ ህወሃት እየተንቀሳቀሰ ነው። በቴዎድሮስ አድሃኖም ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ በተግባር እንዲተረጎም በውጪ አገር ባሉ የወያኔ ኤምባሲ ሁሉ የተበተነው የዲያስፖራ ፖሊሲ አላማ ይሄ ነው። ቀርሳና ኮንቶማ በእንዲህ አይነት ርካሽ ጥቅም የሚሸመቱ የዲያስፖራ አባላትን ለማሰባሰብ እየተዘጋጀ ያለ ሰፈር ነው። አርበኞች ግንቦት 7 የሶስት ቀን አራስ በተገደለችበት፤ በርካታ እናቶች ፤ አቅመደካማ አዛውንቶችና ታዳጊ ህጻናት ተፈናቅለው ለጎዳና ተዳዳሪነት በተዳረጉበት ቦታ ላይ የሚገነባውን ኮንዶሚኒዬም፤ ለተለያዩ አገልግሎት የሚሆኑ ህንጻዎች ወይም ሌላ ኢንቬስትመንት ባለቤት ለመሆን በየዋህነት ያሰፈሰፉ ካሉ ውሳኔያቸውን ቆም ብለው እንዲያጠኑት ይመክራል። ከቤታቸው ተፈናቅለው እንባቸውን እያፈሰሱና በየሜዳው ተበትነው የሚንከራተቱ ወገኖቻችን እንባ ሳይደርቅ ህወሃት ወደ መጨረሻው ከርሰመቃብር ይወርዳል። ይህ ምኞት ሳይሆን የቆምንለትና እየሞትንለት ያለው ትግል ውጤት ነው።
ወያኔ ሃብት ለማካበት በሚያጧጡፈው የመሬት ንግድ የሚፈናቀሉ ወገኖቻችን ህይወት ሁላችንንም ይመለከታል። የአገሪቱን ዜጎች ለጎዳና ተዳዳሪነት በመዳረግ የሚገነቡ አዳዲስ ህንጻዎችና መንገዶች ልማት ሳይሆን ማህበራዊ ቀውስ በመፍጠር ህብረተሰቡን ለከፍተኛ ችግር የሚዳርግ አደጋውም ለአገር የሚተርፍ ነው። አልጠግብ ባይ ጥቂት የህወሃት አመራሮች ህዝባችንን ሲያፈናቅሉትና አገር አልባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ መመልከት ችግሩ እንዲባባስና እያንዳንዳችን የጥቃቱ ሰለባ እንዲንሆን መጋበዝ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ይህንን የህወሃት ዜጎችን የማፈናቀል እርምጃ ለማስቆምና በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን በህግ ለመፋረድ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት ጸረ ወያኔ ትግሉን እንዲያፏፉምና ትግሉን እንዲቀላቀል ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።by: ecadforum
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Sunday, 10 July 2016

አብዮታዊ ዲሞክረሲ… የማያቋርጥ ሰቆቃ እንቅስቃሴ (ታሪኩ አባዳማ)

አብዮታዊ ዲሞክረሲ… የማያቋርጥ ሰቆቃ እንቅስቃሴ
ታሪኩ አባዳማ ሐምሌ 2008
TPLFቃላት ይናገራሉ ፣ ተፈጥሮን ይገልፃሉ ፣ የሀሳብን ጥልቀት እና የጉዞን አቅጣጫ ያመለክታሉ — አብዮታዊ ሆኖ ዲሞክረሲያዊ – ሁለት ሸጋ ቃላት ፣ ሁለት ተፃራሪ የፖለቲካ ንግድ ማራመጃ ማድመቂያ ቃላት። ሁለተኛውን ቢጥሉት ሌላው ቀዳሚውን ራቁት ያስቀራል – ስለዚህ አብዮት የሚለውን ቃል ዲሞክረሲ የሚሉት ካባ ያጠልቁለታል – ተኩላን የበግ ለምድ አልብሶ ከበግ መንጋ እንደ መቀላቀል…
አብዮት ሲሉ የነበረውን እንዳልነበር አድርጎ መቀየር ማለት ነው። የነበረው እንዳልነበር የሚሆነው ህብረተሰብ ነው ፣ አገር ነው ፣ ህዝብ ነው… አብዮት በተመሰቃቀለ እና ህገ ወጥ በሆነ እርምጃ ስልጣን መቆጣጠር ማለትም ነው። አብዮት ግርግር ነው ፣ ምስቅልቅል ነው። የታመቀ ብሶት ገንፍሎ ግድቡን በመጣስ በስልጣን ላይ ያለውን አፋኝ ስርአት ሲያጥለቀልቀው ፣ ሲውጠው ፣ ሲሽረው አብዮት ተካሄደ ይባላል። አብዮት እንደ እሳተ ገሞራ ነው…
የታመቀ እሳተ ገሞራ ይፈነዳል ፣ ያካባቢውን መልክአ ምድር ይቀይራል – ሜዳው ኮረብታ ይሆናል ፣ ጫካው በድንጋይ ቋጥኞች ይተካል ፣ ሸንተረር እና ገደል ይፈጠራል… እሳተ ገሞራ የሚፈነዳው አንዴ ነው ፣ እዚያው ከደገመም ጉልበቱ ሀይሉ እንደ መጀመሪያው አይሆንም – ተነፈስ ብሏላ። የታመቀው እቶን ተንፈስ ሲል እሳቱ ይጠፋል ፣ አፈሩ ይቀዘቅዛል – አዲስ የተከሰተው መልካ ምድር የተፈጥሮን ህግ ተከትሎ ኡደቱን ይቀጥላል… የእፅዋት አእዋፍ ዘር ይራባበታል – የሰው ዘር ይሰፍርበታል… ይረጋጋል።
እንደ እሳተ ገሞራው ሁሉ አብዮት የሚፈጥረው ምስቅልቅል ካንድ እርከን ላይ ሲደርስ መገታት አለበት። ህብረተሰቡ ሲመሰቃቀል መኖር ፈልጎ አብዮት አያቀጣጥልም – እርጋታ ይፈልጋል ፣ ህግ ይፈልጋል ፣ ስርአት ባለው እና በረጋ ግንኙነት ህይወቱን መቀጠል ይሻል። የወያኔን አብዮታዊ ዲሞክረሲ ሰነድ በጥሞና ከፈተሻችሁት ግን መሬት ላይ በህዝብ ላይ የሚፈፅመውን ያላቋረጠ ግፍ ስታጤኑ አብዮት ልጓም የሌለው የማይዳፈን የማያቋርጥ ምስቅልቅል መፍጠር ማለት ሆኗል።
ይህ እንዲሆን አስገዳጅ የሆነው ዋንኛው ሰበብ የወያኔ የራሱ ተፈጥሮ ነው። የዘረኝነት ተፈጥሮ ፣ ሌላውን አግልሎ በግል እና ጠባብ አመለካከት ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ብሎም በዚያ ጎዳና ገደብ የለሽ ዘረፋ እና ግድያ ማራመድ። ተፈጥሯቸውን ‘አብዮታዊ’ እናም ደግሞ ለምድ አጥልቀው ‘ዲሞክረሲ’ ብለውታል። ተፈጥሯቸው ዘረኛ ስለሆነ ዘረ ብዙ በሆነቸው አገር ውስጥ ተረጋግተው ስልጣናቸውን ማቆየት አይችሉም። ስለዚህ ሁሌም እንደባነኑ ፣ ሁሌም እንደደነበሩ ፣ ከራሳቸው ዘር በስተቀር ሁሉንም እንደጠረጠሩ ፣ እንደገነፈሉ ይኖራሉ። ተፈጥሯቸው ለተረጋጋ ህይወት ዋስትና አይሆንም – በመደናበር እና በማደናበር በሚያሰፍኑት ምስቅልቅል ውስጥ ዕድሜያቸውን ማራዘም ግባቸው ነው። ያንን ነው አብዮት የሚሉት…
ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ በፈጠሩት የማያቋርጥ የምስቅልቅል እንቅስቃሴ ውስጥ ገደብ የለሽ ሀብት ዘረፋ ያካሂዳሉ። ግርግር ከሌለ ፣ አብዮት ከሌለ ዘረፋ ማካሄድ አይቻልም… አገር ከረጋ ፣ ህግ የበላይ ይሁን ከተባለ ፣ ተጠያቂነት እና ግልፅነት ይረጋጋጥ ከተባለ ዘረፋ (ኪራይ ሰብሳቢነት ይሉታል) ይቆማል። ሰው በዘሩ ሳይሆን በብቃቱ እና ችሎታው ይመዘናል። ይህ መልካም የግርግር ዘመን ከሰከነ ያግበሰበሱት እና የሚያገበሰብሱት ሀብት ብቻ ሳይሆን ህልውናቸውም ፈተና ላይ ይወድቃል። አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ፣ የማያቋርጥ ግርግር ነው… እናም ያገሪቱን ጥሬ የተፈጥሮ ሀብት ላገኙት የባዕድ ቱጃር ይቸበችባሉ – ይጣደፋሉ ፣ ፋታ የላቸውም ሩጫው ከጊዜ ጋር ነው – እንቅስቃሴው ፈጣን ነው…
እስከ አሁን ድረስ ድሀው ህዘብ ላይ የሚዘንበውን የግፍ ውርጅብኝ ፣ ማፈናቀሉን ፣ ወህኒ ማጎሩን ፣ ቶርቸሩን ፣ አሸባሪ ብለው ያገቱትን ዜጋ ጥፍር እየነቀሉ ማሰቃየቱን… አረ ስንቱን… አስተውሉ… በማያቋርጠው አብዮታዊ እንቅስቃሴ የሚለበለው ዜጋ መድረሻ ጠፍቶት መፈጠሩን ከሚረግምበት ደረጃ ደርሷል። ወያኔዎቹ እያመሰቃቀሉ ፣ እያደናገሩ ፣ እያፈናቀሉ ፣ ወህኒ እያጎሩ ፣ እየገደሉ ካልሆነ አንድ ጀምበር ማደር አይቻላቸውም። ያንን የማያቋርጥ ምስቅልቅል ፣ ያንን የማያባራ ግርግር በዲሞክረሲ ለምድ ጀቡነውታል – መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ… አብዮታዊ ዲሞክረሲ ብለውታል። ‘አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ነው…’ የማያቋርጥ ምስቅልቅል …
አብዮታዊ ዲሞክረሲ – ወያኔ ሁለቱንም ቃላት ይወዳቸዋል። እንቅስቃሴውን የሚመሩት ዘረኛ ነብሰ በላዎች የብሔረሰቦች ተቆርቋሪ እና ጠበቃ ያውም አብዮተኞች መሆናቸውን ይሰብካሉ። ለሚፈፅሙት ማናቸውም ወንጀል የሚጠየቁት በህግ ሳይሆን በአብዮታዊ ሂስ ብቻ ነው – አብዮተኞች ስለሆኑ ከህግ በላይ ናቸው። አብዮተኞች ስለሆኑ በፈለጉት ያገሪቱ ክልል ያሻቸውን ዜጋ ማሰር ፣ መግደል ፣ ንብረቱን መቀማት ፣ ከይዞታው ማባረር ማፈናቀል ይችላሉ… ጥፍሩን እየነቀሉ ያልፈፀመውን ሀጢያት ተናዘዝ ይላሉ… ብልቱን እየቀጠቀጡ ‘ዘር ማንዘርህን እናኮላሻለን’ ይላሉ… አረ ስንቱ።
ወቅቱ ስለ ዲሞክረሲ መኖር አለመኖር ሳይሆን ስለ አብዮቱ አለመቋረጥ ፣ ስለ ምስቅልቅሉ አለመገታት ነው። ባንድ ጀምበር ሰላሳ ሺህ ዜጎች ካንድ መንደር ሲፈናቀሉ አብዮቱ አለማቋረጡን ፣ ምስቅልቅሉ መቀጠሉን ፣ መንግስታዊ ህገ ወጥነት በህልውና መስፈኑን ያረጋግጣል —
እንግዲህ አብዮትን ከዲሞክረሲ ባህሪ ጋር አዳቅሎ ማራመድ የሚቻለው እንዴት ነው? ህግ የለም እንዳይባል የሆኑ ሸጋ አንቀፆች የታጨቁበት ሰነድ ያሳያሉ – ህጉን ግን የማያቋርጠው አብዮት እንደ አመቺነቱ ይተረጉመዋል ፣ ይሸረሽረዋል ፣ ይመደምደዋል። አብዮተኞቹ ሁልጊዜም ከዚያ ህግ በላይ ናቸው – ዜጎችም ከህግ ፊት እኩል በመሆን ሳይሆን በአብዮት ፊት ታማኝ በመሆን እና አለመሆን ፤ ለአብዮተኞቹ ቅን ታዛዥ እና ታማኝ ከመሆን አለመሆን አንፃር ይፈረጃሉ። ፀረ-አብዮታዊ ዲሞክረሲ የሆኑ ዜጎች አሸባሪ ተብለው በዚያ አብዮቱ በፃፈው ልዩ ህግ ለፍርድ ይቀርባሉ… ይጋዛሉ ፣ ወህኒ ይወረወራሉ – በአብዮታዊ ዲሞክረሲ ካራ ይቀላሉ…
ህግ አለ መስሏቸው ‘በህገ መንግስቱ እንደተፃፈው’ የሚሉ ቅን ዜጎች በዚያው ለምድ ባጠለቀው ህገ መንግስት ተፈርዶባቸው ወህኒ ይማቅቃሉ…
ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለማምጣት አብዮት ማካሄድ አንድ ነገር ነው – አብዮት የአጭር ጊዜ
ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ከመሆን የሚያልፍ ነገር አይደለም። ዲሞክረሲ ደግሞ ዘላቂ የፖለቲካ ህይወት ነው። የህግ በላይነት ፣ የሰብአዊ መብቶች መረጋገጥ ፣ በነፃ የህዝብ ምርጫ ስልጣን ላይ መቀመጥ የመሳሰሉትን ያመለክታል። የዲሞክረሲ ባህል ግንባታ በአይምሮው የጎለመሰ ፣ በስነ ምግባር የተኮተኮተ ፣ አገሩን እና ህዝቡን የሚወድ እና የሚያከብር – በአስተዳደር ጥበብ ሁነኛ ተሞክሮ ያለው አስተዳደር ይጠይቃል። ከፍየል እረኝነት ወደ ህወሃትነት ብሎም ወደ መንግስት ስልጣን እና ሀላፊነት መሸጋገር
እርግጥ ነው ሌኒን ነበር ‘አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ነው…’ ያለው። መፈክሩን በተግባር የተረጎመው ደግሞ ሌላ ሳይሆን ስልጣኑን ከሌኒን የወረሰው ጆሴፍ ስታሊን ነበር። ስታሊን ስልጣን ላይ በቆየባቸው ሁለት አስርት ከግማሽ ዘመን በማያቋርጠው አብዮት ስም እየተገዘተ ያገሩን ህዝብ የደም እንባ አስለቅሶበታል – ተቀናቃኝ መስለው የታዩትን የራሱን የቦልሼቪክ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ሳይቀር በመረሸን ፣ የደረጁ ገበሬዎችን አፈናቅሎ በቅጣት ወደ ማጎሪያ ሰፈሮች በማጋዝ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አብዮት ‘የማያቋርጥ እንቅስቃሴ’ መሆኑን ሲያስመሰክር ቆይቷል። ይሁንና ስታሊን በአብዮት ስም የአገሩን ዳር ድንበር ለማንም አልሸጠም – ፓርቲው በዘር እና ጎጥ ላይ የተገነባ ባለመሆኑ አገራዊ ብሔራዊ ክብር እንዳይደፈር በጀግንነት ተዋድቋል። በዚህ ረገድ ከወያኔ ፍፁም የተለየ ያደርገዋል። ተፈጥሯቸው ለየቅል በመሆኑ በሁሉም ነገር አይመሳሰሉም።
ወያኔ ከስታሊን የወረሰው መንፈስ ‘አብዮት የማያቋርጥ እንቅስቃሴ’ ፣ የማያቋርጥ ምስቅልቅል መሆኑን ብቻ ነው። ለወያኔ ህልውና የሚጠቅመውም ይህ ብቻ ነው። ይህን የሚጠራጠር ካለ ሀያ አምስት አመታት ወደ ሁዋላ ሄዶ እነ መለስ ዜናዊ ስለ ጆሴፍ ስታሊን አብዮታዊ ተግባራት ይሰብኩ የነበረውን ማንበብ ይችላል። አዎ ሀያ አምስት አመታት ሙሉ ሳያቋርጡ ድሀን ማስለቀስ የማያቋርጥ የአብዮተኞች እንቅስቃሴ ነው። ለነሱ ድሀውን በማያቋርጥ ግርግር ካላዋከቡት ለከት የለሽ የዘረፋ ጥማቸው አይረካም። ስለሆነም በህግ ዳኝነት ሳይሆን በግርግር ይመነጥሩታል ፣ በወከባ ያስለቅሱታል ፣ በጥይት እሩምታ ይረፈርፉታል – ያንንም አብዮት ነው ይሉታል… የማያቋርጥ እንቅስቃሴ ፣ የማያቋርጥ እንባ ፣ የማያቋርጥ የጥይት እሩምታ… አዲስ አበባ ፣ ጋምቤላ ፣ ኦሮሚያ…
ወያኔ የዲሞክረሲ ለምድ የለበሰ ተኩላ መሆኑን አፍቃሪ የሆኑ ምዕራባውያን ጭምር የሚስቱት አይደለም። ተኩላው ለምድ የለበሰው እነሱን ለማደናገር መሆኑም ጠፍቷቸው አይመስለኝም። ከወቅቱ አለም አቀፍ ቀውስ አንፃር የምዕራባውያንን ብሔራዊ ጥቅም ለመጠበቅ ተኩላም ቢሆን ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ይታገሱታል… ተኩላው ቀን የጎደለበት ቀን ግን ተኩላውን አያድርገኝ… በመዝገብ ቤታቸው ያከማቹትን የሰብአዊ መብት ረገጣ ታሪክ ፣ የታዘቡትን ፣ የመከሩትን ሁሉ አደባባይ ያወጡታል… ስንት ጉድ እንሰማ ይሆን?
በቅርቡ ይፋ በሆነ ሰነድ የዞን 9 ጦማሪዎች ያጠናቀሩት የእስረኞች ሰቆቃ ጥናታዊ ሰነድ (ከዞን ዘጠኝ ወይንም ጎልጉል ድረ-ገፅ ላይ ታገኙታላችሁ) ከብዙ በጥቂቱ እንደሚያሳየው የወያኔ የማሰቃያ ተቋማት በየዕለቱ የሚፈፅሙት ግፍ ለጆሮ ይቀፋል። ከትግራይ መንደሮች ተመልምለው የመጡ ፍየል እረኞች መርማሪ ሆነው የነገሱበትን የማዕከላዊ እስር ቤት ምርመራ በጨረፍታ ያሳየናል።
ከትግራይ መንደሮች ተመልምለው በመርማሪነት የሰለጠኑት ሰቆቃ ፈፃሚዎች አንድን ዜጋ (በነሱ እምነት የአብዮታዊ ዲሞክረሲ ጠላት) አሰቃይቶ እንዴት ያልዋለበትን ፣ ያልፈፀመውን ሁሉ እንዲያምን ማድረግ መቻል እንዳለባቸው ያምናሉ። የመርማሪዎቹ አብዮታዊነት የሚለካው ወያኔ ጠላት ብሎ በፈረጀው ዜጋ ላይ በሚያወርዱት አበሳ ነው ፤ እርግጫው ፣ ጥፊው ፣ ስየሉ ፣ ጋጠ ወጥ ስድቡ… እዚህ ለመጥቀስ እጅግ አሳፋሪ የሆኑ ድርጊቶችን በእህቶቻችን እና ለጋ ወጣቶች ላይ የሚያደርሱት… አረ ስንቱ።
እንዳልኩት እነኝህ የማዕከላዊ መርማሪዎች ፣ የወህኒ ዘበኞች እና አዛዦቻቸው… ሁሉም አንዳችም የበቃ የትምህርት ብቃት ሳይኖራቸው ያው እንደ ሚኒስትሮቹ ፣ መምሪያ ሀላፊዎቹ ፣ ኮርፐሬሽን አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ በድርጅታዊ ታማኝነት መለኪያ ብቻ የተቀጠሩ ወያኔዎች ናቸው። ህወሃት ለተዋጊነት ይመለምላቸው የነበሩ ፍየል እረኞች ዛሬ ለመርማሪነት ሰልጥነው ክቡር የሆነውን ሰብአዊ ፍጡር እንደ አውሬ ሲዘለዝሉት ማየት ያሳዝናል።
እነኝህ የወያኔ መርማሪዎች ‘በሰማዕታት መስዋዕትነት’ የተጎናፀፉትን ከፍየል እረኝነት ወደ መርማሪነት ያሸጋገራቸውን ስራቸውን ሊያጡና ወደ ፍየል እረኝነት ሊመለሱ የሚችሉት በሁለት ምክንያት ብቻ መሆኑን ያውቃሉ – አንድ ወያኔ ባስቀመጠው የጥራት ደረጃ ስራቸውን ማከናወን ካልቻሉ ፤ ማለትም ማናቸውንም አይነት የማሰቃያ ስልት ተጠቅመው እስረኛው ያልፈፀመውን ፣ ያልዋለበትን ሁሉ ማድረጉን አምኖ እንዲፈርም ማድረግ ካልቻሉ። የህወሃት መርማሪዎች ግምገማ አልፈው በመርማሪነት ስራ ለመቆየት ግፍ መፈፀም አለባቸው – የስራ ዋስትናቸው ሰቆቃ መፈፀም ብቻ ነው – ሌላ ዋስትና የላቸውም። አጋዚ የሚሾመው የሚሸለመው ለወያኔ ስልጣን ሲል ንፁሀን ዜጎችን በጭካኔ ለመግደል የማያመነታ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ብቻ እንደሆነ ሁሉ…
ሁለተኛው ስራቸውን የሚያሳጣ ሰበብ ወያኔ ከስልጣን ከተወገደ ብቻ ይሆናል። ይኼ ሁለተኛ ሰበብ የመርማሪነት ስራ ከማጣታቸውም በላይ ሌላ መዘዝ አለው ፣ ተጠያቂነት።
ከፍ ብዬ የጠቀስኩትን የዞን ዘጠኝ ጥናታዊ ሰነድ በቅጡ ካነበባችሁት የምትገነዘቡት ነገር አለ…. ባልተለመደ ሁኔታ አንድ እስረኛ ለምርመራ ሲጠራ አይኑ ይታሰራል። መርማሪዎቹ ሲደበድቡት ፣ ሲያዳፉት ፣ ቃሉን ሲቀበሉ ወይንም ሲያስፈርሙት ሁልጊዜም አይኑ ጥፍር ተደርጎ ታስሮ ነው። በዚህ ላይ መርመሪዎቹ ስማቸው እንዳይታወቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ ፤ ልክ አለቆቻቸው የታጋይ ስም እንዳላቸው ሁሉ የወያኔ መርማሪዎች የመርማሪ ስም ለራሳቸው ያወጣሉ። የትግል ስም የመርማሪ ስም… ይኼ ለምን ሆነ ብላችሁ እንደኔ ታሰላስሉ ይሆናል። መልሱ አጭር ነው – ይኸውም የወያኔ መርማሪዎች ለፈፀሙት ሰቆቃ ሁሉ አንድ ቀን ተጠያቂነት መኖሩ የማይቀር መሆኑን በደመ ነብስ ይገምታሉ።
አይን በማሰር እና ስማቸውን በመቀየር በነሱ ቤት የዛሬ ሰቆቃ ተቀባይ ነገ አንድ ቁጥር መስካሪ ሆኖ ዳኛ ፊት ሊመሰክርባቸው የሚችልበትን ዕድል ማጥበባቸው ነው። ስም በመደበቅ እና አይን አስሮ በመግረፍ ከህግ ፊት ማምለጥ ይቻል እንደሆነ ግን ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።
እንቅስቃሴው የማያቋርጠው የወያኔ አብዮት አንቀላፍቶ አያውቅም – መንደሮቸን ያተራምሳል፣ ድሀ ዜጎችን ያፈናቅላል ፣ ቱጃሮችን ባንድ ጀምበር ይፈጥራል… ይተክላል (ቱጃሮቹን ታወቋቸዋላችሁ) ፣ ባንኮችን ያራቁታል ፣ መሬቶችን ይወራል ፣ የፀሀፊዎችን ብእር ብቻ ሳይሆን ጣት ይቆርጣል ፤ ደግሞ ህግ አለ ይላል ወዲህም አብዮት የማያቃርጥ እንቅስቃሴ ነው ይ። ዳኞችንም ይሾማል ፣ በአብዮታዊ ዲሞክረሲ አቅጣጫ ይበይናል። በህግ አምላክ ለማለት የከጀላቸውን ዳኞች በብቃት ማነስ ያባርራል ፣ ግፍ እና ሰቆቃ መፈፀም ያልቻሉ መርማሪዎችንም ያሰናብታል…
ሰቆቃ ፈፃሚ መርማሪዎች የሚታደጉበት ፣ ፍትህ አዛብተው የሚበይኑ ዳኞች ሸንጎውን የተቆጣጠሩበት ፣ በሙስና የተዘፈቁ ሹማምንት ትከሻ የደነደነበት ድህነትን ሳይሆን ድሆችን እየጠራረገ በመራመድ ላይ ነው… የወያኔ አብዮታዊ ዲሞክረሲ… የማያቋርጥ እንቅስቃሴ…

Saturday, 9 July 2016

ምነው ምን በደል ደጉ ያገሬ ሰው? ለባዴራው ክብር ለሰደቅ አላማው ፣ ላገር የወደቀው ለወገኑ የደማው፣
ምነው ምን በደል ደጉ ያገሬ ሰው?
እረ የሰው ያለ - እረ ሰው እረ ሰው
እረ ሰው እረ ሰው እረ ሰው፣
እሳት ቢቀላፋ ገለባ ጎበኝተው፣
ዘመን አረጀ እና እሄ ቀን አገኘው፣
ከባህር ይሰፋል አማራ ማለት፣
ያንድነት ሐረግ ነው ኢትዮጵያዊነት።
ጠላት በመከተ ሀገሩን ባቀና፣
ዳር ደምበር ጠብቆ አንድነት ባፀና፣
እምነት በገነባ ፊደል ባስተማረ፣
በገዛ ወንድሙ በወገኑ አፈረ።
ለባዴራው ክብር ለሰደቅ አላማው ፣
ላገር የወደቀው ለወገኑ የደማው፣
ፍቅር እየራበው ሠላም እየጠማው፣
ምን በደለ አማራ መብቱን የተቀማው?
አማራን ከኢትዮጵያ ነጥሎ ማየት፣
ሁለቱንም ማጥፋት ዘበት ነው ዘበት፣
በፍቅር ነው እና አማራ ፈጥረቱ፣
ከኢትዮጵያ ጋር ነው ሞት እና ሽረቱ።
ቴዎድሮስ ሚኒልክ ኢትዮጵያን ሲመሩ፣
አፍሪካን ያቀኑ ጃንሆይ ነበሩ።
ሁሉ አለፈ እንጂ ሐገር እያደሰ፣
የትኛው አማራ ሐገሩን ቆረሰ?
ሐገር አቀና እንጂ ደሙን እየዘራ፣
አፈርሷት አያውቅም ኢትዮጵያን አማራ።
የሙሴ ጽላቱ አይመነዘር፣
አትለያይው ማሪያም የኢትዮጵያን ዘር፣
አትለይውም ማሪያም የኢትዮጵያን ዘር ።                                                                                                                    

Friday, 8 July 2016

አርቲስት ማዲንጎ መልካም ጅምር ነውና እናመሰግናለን ********************************

የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋርም ይሁን አባላት ጋር መታየት የሰቀቀን ምንጭና የስጋት መንሰኤ በሆነባት በሃገራችን ኢትዮጵያ እስካሁን አርቲስቶች ከህዝብ ልጆች /ፖለቲከኞች/ጋር ያላችው የእለት ተእለት ማህበራዊ ትስስርና ቀረቤታ ምን አልባትም ከሰው እይታ አልያም ከካሜራ ውጭ ካልሆነ በቀር የተለመደ ክስተት አይደልም።ዛሬ ግን ይህን አመለካከት የሰበረ ክስተት ስመለከት የነገ ተስፋ በውስጤ አጫረ ። ሀብታሙ የህዝብ ልጅ ነው ።አርቲስቶቻችንም ከዚህ ህዝብ ውጪ ሌላ ህዝብ የላቸውምና ቢያንስ በማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የነቃ ተሳትፎዋችሁ ከፍርሃት በጸዳ ሁኔታ ቢቀጥል ? አርቲስት ማዲንጎን ያሳየህን መልካም ጅምር ነውና እናመሰግናለን።