ከኢትዮጵያ ሌላ መኩሪያና መመኪያ የሌላቸው ሀገር ውስጥ የሚገኙና በዓለም ዙሪያ የተበተኑ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት በወያኔ የግፍ ስቃይ ደርሶበት ጣር ላይ ለሚገኘው ለአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ – ለሀብታሙ አያሌው – እያዘኑ ይገኛሉ፤ በርግጥም ይህ ብዙ ሩጫ የሚቀረው ወጣት አንዳች የማይቀለበስ ዘላቂ ጉዳት የሚደርስበት ከሆነ የሁላችንም ፀፀትና ሀዘን ነው፡፡
ዜጎችን ከእስር ቤት በአእምሮ፣ በኅሊናና በአካል ገድሎ በማውጣት ተወዳዳሪ የማይገኝለት የወሮበላው የትግሬው ገዢ መደብ ሕወሓት ደግሞ በዚህ የአንድ ሰው የሚመስል ግን ሀገራዊ ይዘት ባለው የጋራችን ጉዳይ ትርፍ እንደሚዝቅበት የታወቀ ነው፡፡ ሰው በአንድ ሀብታሙ ሲንጫጫ ወያኔዎች የተወሰነ እፎይታ ያገኛሉ፡፡ ወያኔ ጭርታን እንደማይወድ ግልጽ ነው፤ በምንም ይሁን በምን ሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተብዬው ስለወያኔና በወያኔ ሰበብ ሲንጫጩ ደስ ይለዋል – ዕብዶቹ ወያኔዎች የሆነ ሥነ ልቦናዊ እርካታ የሚያገኙበት ይመስለኛል – “አለን፣ ገና አልሞትንም” የሚል መልእክት ለአባሎቻቸውና ለወዳጆቻቸው ለማስተላለፍ ሲሉ መሆን አለበት፡፡ ሰሞኑን እንኳን ቤት በማፍረስ ተግባር ተሠማርተው ይሄውና በክረምት – በማይሆን ወቅት – እባብና ዐይጥ እንኳን ተስማምተው በሚኖሩበት የዝናብ ወራት – ሕዝብን በገዛ ቀየው በጥይት እየቆሉ ናቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሁከትና ግርግር ትልቅ መዝናኛቸው ነው፡፡ ከሀዘን አምላኪዎች (ከሳዲስቶች) ከዚህ ሌላ አይጠበቅም፡፡
ሀብታሙ አያሌው አንዱ አቤል ነው – በወንድሙ ቃየል የተገደለ፡፡ ለሀገሩ መስዋዕት የሆነ ንጹሕ በግ፡፡ ከዳነልን እሰዬው እልል በቅምጤ ነው፡፡ ካልሆነልንም በፊትም ሲናገረው የነበረው ትንቢቱ ደርሷልና ይብላኝ አሣራቸውን እያበዙ ለሚገኙት ወያኔዎች እንጂ እርሱ አንዱን መንገድ መያዙ ቢያስቀና እንጂ ሊያስቆጭ አይገባም፤ እንኳንስ የርሱን የመሰለ የክብር ሞት ቀርቶ ሰው በትንታና በእንቅፋትም ይሞታል፡፡ የሚታዘንልን እንግዲያውስ ጉድ እያየን እዚሁ ወያኔ አፍንጫ ሥር ለተጎለትነው ለእኛ ነው፡፡ መስዋዕትነት በሀብታሙ አልተጀመረም፤ በርሱም አያልቅም፡፡
ፕሮፌሰር አሥራትን የቀረጠፈ የቀን ጅብ፣ መምህር አሰፋ ማሩን የቆረጠመ ጭራቅ፣ ተማሪ ፋንታሁን ወርቁን የጎረደመ የአጋንንት ሠራዊት፣ በአሥርና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሓን ዜጎችን ከርቸሌ አውርዶ እያማቀቀ የሚገኝ የሣጥናኤል ፈረስ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ደም ያፈሰሰና በደም ባሕር እየዋኘ ያለ የትግሬ ወያኔ ጭፍራ ይህን ወጣት ሰላማዊ ታጋይ ለህክምና ወደ ውጭ ይፈቅድለታል ብሎ ማሰብና በማንኛውም መንገድ ፈቃድ መጠየቅ ግን የወያኔን ባሕርይ ካለመረዳት የሚመነጭ የዋህነት ወይም “የበኩሌን አድርጌያለሁ” ከሚል መጠነኛ የሥነ ልቦና እርካታ የማያልፍ ከንቱ ሙከራ ነው፡፡ ጦርነት የገጠምከውን ባላጋራ “ጥይት አልቆብኛልና ካርታውን እስክሞላ ድረስ እባክህን ሳትተኩስ ጠብቀኝ” ብሎ ጠላትን እንደመለመን ነው – ይህ ደግሞ በትንሹ ሞኝነት ይመስለኛል – የበሬ እንትን ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል የዋለችውን ቀበሮ ዓይነት ሞኝነት፡፡ ቀድሞ ነገር ከእስር ቤት አኮለሻሽተው የሚያወጧቸው ለምን ሆነና ነው? ስንትና ስንት ነገር እያወቅን እንዴት ነው ወያኔዎችን ማሰብ እንደሚችሉ ሰዎች ቆጥረን ለትዝብት የሚዳርግ ነገር የምናደርገው? ሰይጣን ምን ምሕረት ያውቅና ነው በስለት የማያገኘውን ድንቅ ነገር ለማደናቀፍ ሀብታሙን ለህክምና ወደ ውጪ የሚፈቅድለት? ሬሣውንም አይፈቅድም፤ በፈቀዱና እኔ በቀለልኩ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ተዓምር ዕፁብ ድንቅ ነውና ባለበት ምሕረቱን እንዲልክለት ወደርሱ እንጸልይ፡፡ ወያኔን ማባበሉም ሆነ ለጌቶቹ አቤት ማለቱ ጉንጭን ማልፋት ነው፡፡ አማራንና በእግረ መንገድም የኢትዮጵያዊነትን ኩራትና ብሔራዊ ስሜት ድምጥማጡን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ወያኔን እደግ ተመንደግ ከማለት ውጪ አንድ ሀብታሙን ይቅርና ከሚሊዮን የሚበልጥ ዜጋ በጠራራ ፀሐይ በየቀኑ ቢጨፈጨፍ ደንታ የላቸውም፡፡ እነዚህ የብዔል ዘቡል አሽከሮች ከአፍሪካውያን ተላላኪዎቻቸው ጋር እየተመሣጠሩ የዓለምን ሕዝብ ቁጥር ከዕርቦ እጅግ ባነሰ ሁኔታ አውርደው የራሳቸውን አዲስ ሥርዓት ለማቋቋም ወደ ፍጻሜ ትንቢቱ እየተንደረደሩ ስለሆነ የኛን ጩኸት ቀርቶ የገዛ ሕዝቦቻቸውን ስቃይና ዋይታ እንኳ የሚሰማ ጆሮ የላቸውም – እናም ወደላይ እንጩኽ ግዴላችሁም፡፡ በቀል የእግዚአብሔር ናትና፡፡ የሀገራችን ችግር ደግሞ ውስብስብ በመሆኑ አንድዬ ካልተጨመረበት ትርፉ ውኃ መውቀጥ ነው፡፡ ሰው እንዲልክልን ፈጣሪን ከልብ እንለምን፡፡
ይልቁንስ ጉድ ልንገርህ ወገኔ፡፡ ወያኔ ዐማራው ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍና በደል ወደር የለውም፡፡ ሰሞኑን ወደ ገጠር ወጣ ብዬ የታዘብኩት ነገር ቅዠት እየሆነ አላስተኛ ብሎኛል፡፡ ለዚህ ነው የሞተ ተገላገለ የምለው፡፡ በዚህን ወቅት እንደኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኖር ይልቅ አንድ ሞት በፀጋ ተቀብሎ መገላገል ትልቅ ዕረፍት ነው፡፡ ግን የሚፈልጉት ነገር በቀላሉ አይገኝም፡፡ ወያኔን ማየትና ስለወያኔ መስማት ኅሊናችንን እየሰቀጠጠው አካላዊው ሳይሆን መንፈሳዊውና ኅሊናዊው ኑሮ የከበደን ሞልተናል፡፡ ሀገራዊ ጣራችን ካላሳጠረልን ብዙዎቻችን ክፉኛ እየተጎዳን ነን፡፡
ለወትሮው ጄኖሣይድ የሚባለው በተቀራራቢ ፍቺ በሆነ ምክንያት አንድን የሰው ዘር መፍጀት ማለት ነበር፡፡ ይህ ሰውን በጅምላ የማጥፋት ሂደት መንስኤው በኛይቷ ሀገር እንደምናየውና በሩዋንዳ እንደተፈጸመው ዘረኝነት ሊሆን ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አማራው አካባቢ በወያኔ እየተፈጸመ ያለው ጄኖሣይድ ግን የተለዬ ነው፤ ምናልባትም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ነው ብንል ከፈጠጠው እውነታ አኳያ ትክክል ነን፡፡ በነገራችን ላይ ጄኖሣይድና ኢትኒክ ክሊንሲንግ (genocide and ethnic cleansing) የሚባሉ አንድም ሁለትም የሚሆኑ ጽንሰ ሃሳቦች አሉ፡፡ በመናኛ ንባባዊ ግንዛቤየ ባጭሩ ብገልጥላችሁ የመጀመሪያው ይበልጡን በጭፍጨፋና ግድያ ላይ የሚያተኩር ሲሆን ሁለተኛው ግን ግድያንም ጨምሮ አንድን ጎሣ ወይም የሕዝብ አካል በማስፈራራትና በማሰቃየት፣ ማንነቱን በግድ እንዲለውጥና ራሱን እንዲጠየፍ በማድረግ፣ የሚኖርበትን አካባቢ በኃይል በመቀማት፣ ዘሩን በአስገድዶ መድፈር በግድ በመበረዝና በመከለስ የሚከናወን ሲሆን ዋና ዓላማውም መኖሪያ ሥፍራውንና መሬቱን ለወራሪው ጎሣና ባህል በማስለቀቅ ነባሩን ማውደም ነው – የሚታሰበው ለንዋይና ለመሬት እንጂ ሰው እንደአማራ ማለትም እንደዝምብ ነው የሚቆጠር፡፡ እነዚህ ሁለቱም በሀገራችን ምድር በወያኔ አማካይነት እየተፈጸሙ ያሉ ዘመን አመጣሽ ወረርሽኞች ናቸው፡፡ የኛን መጠፋፋትና ውስጣዊ ቅኝ ግዛት ከሌሎች ትንሽ ለየት የሚያደርገውና ነገሩ እስካሁንም ድረስ አልገባን ብሎ ዕንቆቅልሽ ያደረገብን የአሳዳጆችና የተሳዳጆች ማኅበረሰብኣዊ ሥነ ልቦና፣ ባህል፣ አመጋገብ፣ ሃይማኖት፣የዘር ግንድ፣ የቋንቋ መሠረት፣ አስተሳሰብ፣ ትውፊት ወዘተ. ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ መሆኑ ነው፡፡ የሌሎችን ስናይ እንደኛ ያለ ተመሳስሎ አይታይባቸውም፡፡ ለምሣሌ የሩዋንዳውያኑ ሁቱዎችና ቱትሲዎች በመልክም በቁመትም እንደሚለያዩ ይታወቃል – ቀጠን፣ ረዘም፣ አፍንጫው እንደፖል ካጋሜ ሰልከክ ብሎ ካየኸው ቱትሲ ለመሆኑ ተጨማሪ ማረጋገጫ ላያስፈልግህ ይችላል፡፡ አጠር፣ ወፈር፣ ደልደል፣ ጠንከር፣ የበላውን ቁርስ ደፍጠጥ ባለው የአፍንጫው ቀዳዳ የምታይ ከሆነ ደግሞ ሁቱ መሆኑን ትገምታለህ፡፡ በቋንቋና ሃይማኖት እስከዚህም እንደማይለያዩ ይነገርላቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ስትመጣ ግን የዐድዋውን ሐጎስ ከመራቤቴው ድፋባቸው ለመለየት ነጭና ጥቁር ክር ግምባራቸው ላይ ካልታሰረላቸው በስተቀር አትችልም – (በሶማሌ የጦፈ የጎሣ ግጭት ወቅት አንዱን ከአንዱ ለመለየት ተቸገሩና አንድኛው ጎሣ የሆነ የቀለም ኮድ መርጦ በጨርቅ ምልክት መግባባት ጀመረ አሉ፡፡ ያቺ ምሥጢር ትሾልክና ጠላት እጅ ትገባለች አሉ፡፡ እነዚያ ጎሣዎች ያን ጨርቅ ልክ እንደነሱው ያስሩና በዚያ መንደር ገብተው ተቀናቃኛቸውን ጎሣ ረፈረፉት አሉ፡፡ ደግ ለ“አሉ”፡፡ እጅግም መመሳሰል መጥፎ ነው፤ ያስጠቃል፡፡ የኛ ዋና ችግር እኮ ይሄው ነው!)
ከፍ ሲል የተገለጹትና በተለያዩ ጎሣዎች መካከል የሚፈጸሙ የጥፋት መንገዶች ዓለም የሚያውቃቸውና ሰለባዎቹም ባዘኔታ ከንፈር የሚመጠጥላቸው ናቸው፡፡ አሁን እያየነው ያለነው ወያኔ በአማራ ሕዝብ ላይ እያደረሰው የሚገኘው ውድመት ግን በየትኛውም የዓለም ታሪክ ያልተመዘገበ ስም እንኳን የማይገኝለት ነው፡፡
በገጠር አካባቢ አማራው ላይ የወደቀው ማይምነትና ድንቁርና የተለዬ ነው፡፡ ሕዝቡ ላይ የተጣለበት ድህነት ወደር አይገኝለትም፡፡ እነዲኬቲና ሜሪስቶፕስ የተሰኙ ሥነ ተዋልዶ ላይ የሚሠሩ መያዶች እንኳን በምዕራባውያን ጌቶቻቸው ይሁንታና በወያኔ ግፊት መሠረት እንደልባቸው የሚፈነጩትና ዜጎች ዘራቸውን እንዳይተኩ በአነራዊ መርፌ የሚያመክኑት በአማራው አካባቢ ነው – ለደደብነቴ ይቅርታ ይደረግልኝና ትግሬ ሴቶች ሲወልዱ የሚሸለሙ ይመስለኛል፡፡ የአማራው ከተሞች ከልማትና ከዘመናዊ የአስፋልት መንገድ የፀዱ ናቸው፡፡ ቤቶቹ ፈራርሰው እንዳይወድቁ በአጠናና በሐረግ ተይዘዋል፤ ቆርቆሮው ወንፊት ሆኖና በእርጅና ምክንያት በስብሶ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሣር ቤት የሚሩ ከተመኞች የሚታዩት በአማራው አካባቢ ብቻ ነው፡፡ የትግራይዋ ኩንስንስ ዋጃ ከተማ ከአማራው ቀብራራ ደብረ ማርቆስ ትበልጣለች – ምክንያቱም ከየቦታው እየዘረፈ እሷን የሚያከብር ሕወሓት የሚባል ወምበዴ ድርጅት አላት፡፡ እነደብረ ማርቆስና እነ ደብረ ታቦር ግን የእንጀራ ከተሞች ናቸው – ጥፋት የተደገሰላቸው፡፡ አንድን የሚጠሉትን ሕዝብ ሲቻል በጥይትና በበሽታ፣ ያ ባይቻል በተዘዋዋሪ በርሀብና በችጋር በመጥበስና በማይምነት በማደንቆር ቀጥቅጦ መግዛት የልብን እንደሚሞላ ወያኔዎች በተግባር እያሳዩ ናቸው፡፡ አለሁህ ባይ የሌለው ባይተዋሩ የአማራ ሕዝብ በየገጠሩ እየገፋው የሚገኘው መራር ሕይወት ይህን ይመስላል – በወፍ በረር ቅኝት፡፡
የአማራ ልሂቃን ተብዬዎችን ከሥር መሠረቱ ለማጥፋት የሚፈልቁበትን ሕዝብ በሥልት ማጥፋቱን ወያኔው ተያይዞታል – ባሕሩን እስከወዲያኛው በማድረቅ አንድም የአገዛዝ ተቀናቃኝ እንዳይፈጠር ለማድረግ በታለመ የጅሎች ፈሊጥ፡፡ የማን ምክር መሆኑ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡
ስለዚህም በአማራው አካባቢ እኔ ነኝ ያለ ዲግሪ ጭኖ ስሙን አስተካክሎ የማይጽፍ “ምሁር” ብታገኙ እንዳትደነቁ፡፡ በአማራው አካባቢ አስተሳሰቡ ከአፍ እስካፍንጫው የማይደርስ ምሁር በዲግሪና ዲፕሎማ ተምበሽብሾ ታገኛላችሁ፡፡ እንግሊዝኛን ቀርቶ አማርኛን በቅጡ መናገር የማይችል አማራን ማየት ዛሬ ዛሬ ያልተለመደ አይደለም፡፡ የወያኔ ሤራ ግቡን እየመታ ለመሆኑ የአማራን አካባቢ በመጎብኘት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ አገር ምድሩን በነፈዝ ዜጋ እየሞሉት ነው፡፡ ራሳቸው ኤቢሲዲን ሳይለዩ በሁለተኛ ደረጃ እንዲያስተምሩ የተመደቡ “መምህራን”ን አይቻለሁ፡፡ ተማሪው ፉዞ፣ መምህሩም ፉዞ፣ ርዕሰ መምህሩም ፉዞ፣ ሁሉም ዜሮና የፉዞ ፉዞ፡፡ ተዋርደናል ጎበዝ! …
የአማራን አካባቢዎች በግልጽና በሥውር እያስተዳደሩ የሚገኙት ትግሬዎች መሆናቸውን ደግሞ መርሳት የለባችሁም፡፡ ትግራይ ውስጥ በአንድም የመንግሥት መሥሪያ ቤት አማራ በኃላፊነት ቀርቶ – ይበልጡን ከቴክኒክ ሥራዎች ውጪ ማለት ነው – በተራ የቢሮ ሠራተኝነት እንደማይገኝ ሳንነጋገር የምንግባባ ይመስለኛል፡፡ በአማራው ክልል ግን ፈላጭ ቆራጩ ትግሬ ነው፤ ብአዴን ተብዬው ከኮንዶምነት አያልፍም – እንደኮንዶም የሚለጠጥ ሆዳም የላስቲክ ጓንት፡፡ በብዙ የአማራ አካባቢዎች ምርጥ ምርጡ የከተማና የእርሻ ቦታዎች ለትግሬዎች የሚሰጡ የቅኝ ገዢዎች አንጡራ ሀብት ናቸው፡፡ አማራው ሕዝብ የተረፈው በየከተሞቹ የሚደመጡ የትግርኛ ዘፈኖች ብቻ ናቸው – የከበሮ ድለቃ፤ እልፍ ሲልም ጥቂት የኮብልስቶን መንገዶች፡፡ በኖኅ የውኃ ጥፋት ዘመን ወያኔን መሰል የኃጢኣት ማኅደሮች የተራራና የትላልቅ ዛፍ ጫፎች ላይ ከነከበሯቸውና እምቢልታቸው በመውጣት በውኃው እስኪሰምጡ ድረስ እንደትግሬዎቹ ይደልቁ ነበር ይባላል – ታሪክ ራሱን ደግሞ አሁን ወያኔዎች በመላዋ ኢትዮጵያ መሬት ጠባቸው እየደለቁ ናቸው – መልካም ድለቃ፡፡ ልክ እንደ አዲስ አበባው ሁሉ በአማራው አካባቢም ይህንን ነው የታዘብኩት፡፡ “ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ” ይላል የተረት አባቱ አማራ፡፡ ለነገሩ ዱሮም በልጅነቴ “ትግሬ ጥጋብ አይችልም” ሲባል እሰማ ነበር – አሁንም እምብዝም ላልተለመደ ግልጽነቴ ይቅርታ፡፡ አሁን እኔም እንዳቅሚቲ “ጥጋቡን የሚቆጣጠር ብፁዕ ነው” ብዬ ብተርትስ? አዎ፣ ጥጋብን በልክ ማድረግ የፈጣሪን መንገድ እንድንከተል ከማስቻሉም በላይ ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ እንድንገነዘብ ያስችለናል፡፡ የተራበ መጥገቡ፣ የጠገብም መራቡ ያለና የነበረ ነው፡፡ ትናንትን ማየት የማይችል ስለነገም ዕውር ነው – ዛሬ የያዝነው የሚመስለን ነገር ነገ ይንሸራተትና ወደ ጎረቤታችን ሊሄድ ይችላል፡፡ ማንኛውም ዓይነት ዕውርነት ደግሞ ላልታሰበ አደጋ ይዳርጋልና የውስጥ ዐይናችንን ገልጠን ዙሪያ ገባችንን እንመልከት፤ ከወደቁ በኋላ ወዬው ከማለት ሳይወድቁ በፊት መጠንቀቅ ይቻላል፤ ይህ ደግሞ ተገቢና አስተዋይነትም ነው፡፡ አንጎልን ካደራበት የጥጋብና የዕብሪት ሞራ ነጻ ማውጣት በቅድሚያ የሚጠቅመው ራስን ነው፡፡
ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደሞከርኩት በዚህች መጣጥፍ መልእክቴ ባጭሩ አማራው በቁሙ ሞቷል እያልኩ ነው፡፡ የተማረ ዜጋ እንዳይኖረው፣ ተቆርቋሪ ዘጋ እንዳያፈራ፣ ተረካቢ ዜጋ እንዳይኖረው፣… ሆን ተብሎ በተጣለ የማይምነት ደዌ እየተለከፈ ያልተማረው ቀርቶ ተማረ የተባለው ሳይቀር ጠብደል ማይም እየሆነ ነው፡፡ መምህራንን አየሁ፤ ተማሪዎችን አየሁ – ሁሉም በሚያሳዝን ደረጃ በማይምነት ልምሻ ተመትተዋል፤ ትምህርት ቤቶች የፈራረሱና አንድም ግብኣት የሌላቸው ናቸው፤ የተተው ምድረ በዳዎች ሆነዋል፡፡ አንድን ሕዝብ ከዚህ በላይ መግደል አይቻልም፡፡ አማራው ክልል ውስጥ ተቀምጠህ ትግራይ ውስጥ ያለህ ያህል ይሰማሃል፤ ፍርሀትን አንግሠው፣ ጆሮ ጠቢን በሰው ልክ አሰማርተው፣ … አማራው ተጨብጦና ተኮራምቶ በርሀብና በርዛት እንዲያልቅ እያደረጉት ነው – ለወትሮው አማራው የሚፈናቀለው ከሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ነበር፤ አሁን ግን ከራሱ ቄ በትግሬዎች እየተፈናቀለ ነው – ለእነእንትና ቢመር ቢጎመዝዝም እውነትን አንሸፋፍን፡፡ የመጣ ይምጣ እንጂ እነእንትናን ለማስደሰት ብዬም እውነትን ከመግለጥ አላፈገፍግም፡፡
ይህ እንግዲህ ሰው የሚያውቅላቸውንና የማያውቅላቸውን በአማራው ላይ የሚፈጽሙትን ዘርን በመርፌ እስከማምከን የሚደርሰውን ወንላጀቸውን ሳይጨምር ነው፡፡ ሌላ ሌላውን ታሪክ፣ ታሪክ ራሱ ወደፊት ያወጣዋል፡፡ ትግራይ ከፍላ የማትጨርሰው ዕዳ ውስጥ እየተዘፈቀች እንዳለች በበኩሌ ይሰማኛል፤ አማሮችስ ተገላገሉ፡፡ አረረም መረረም ማመራቸውን ተወጡ፡፡ የማን ዕዳ መሆኑ ወደፊት የሚታይ(የሚጣራ) ሆኖ እነሱ ግን በምድርም በሰማይም ያልተፈጸመ ግፍና በደል በትግሬ ወያኔዎች እንደዶፍ ወረደባቸው፡፡ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ፈዘውና ደንግዛው ዝም ብለው ዋጧት፡፡ እናም ከአሁን በኋላ ጨለማውና ጭጋጉ እየገፈፈ እንደሚመጣላቸው መተንበይ እችላለሁ፡፡ ግን እነሱም ይወቁበት፡፡ እንደትግሬዎቹ በበቀልና በጥላቻ ተሞልተውና በዱባ ጥጋብ ታውረው በተመሳሳይ መንገድ የሚነጉዱ ከሆነ የነጻነታቸው ቀን ይርቃል – ከናካቴውም የነፃነት ቀን የሚባል ነገር ላይመጣ ይችላል፤ ወደፈጣሪ ተመልሰው የውስጣቸውንም የምቀኝትና የተንኮለኝነት ክርፋት በቅንነትና በደግነት ጠበል አጥበው ወደ እግዚአብሔር ከተማጠኑ ነፃነታቸው በደጅ ቆማለች – ወንድም በወንድሙ ላይ ማስተብተቡንና በደንቃራና በመተት አውጀምጅም መጠላለፉን፣ ጧት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ደጅ መጥናቱን፣ ከሰዓት በለጥሻቸው አድባር መፈናደሱን ትተን በትክክል ወደ አምላክ ከተመለስን አንድዬ ቅርብ ነው፡፡ አንዳንድ አክራሪዎች እንደሚሰብኩት አማሮች አማራነታቸውን የማወቅ ግዴታ የለባቸውም፡፡ በኢትዮጵያዊነታቸው ግን አንድ ሆነው እርስ በርስ ሳይናናቁና “አንተ ሸዌ፣ አንተ ጎንደሬ፤ አንተኛህ ጎጃም አንተኛህ ወሎ” ሳይባባሉ ባንድነት መታገል አለባቸው፤ የዓለም አቀፉ የጥቃት ጦር ዋና ዒላማ እነሱ ስለሆኑ ሌሎች ወንድምና እህቶቻቸውን አስተባብረው ከዚህ አገርን በቁም ከሚሸጥ የወያኔ ግሪሣ ራሳቸውንም ሀገራቸውንም ነፃ ለማውጣት መታገል ይገባቸዋል፡፡ ሀገረ ማርያምንም ወደ ቦታዋ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ኢአማኒ ጉድሽ! እንዲህ በል አለኝ፡፡ አልኩ፡፡
ስለዚህ አንድ ሀብታሙ ታመመ፣ ሞተ … የሚለው ነገር ከዚህ ታዝቤው ከመጣሁት ዘግናኝ እውነት አንጻር ሲታይ በርግጥም የምንገኝበት የታሪክ አንጓ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ጊዜ የለንም፡፡ ይህን ሕዝብ ለማዳን ዕድሉና አጋጣሚው ያላችሁ ሁሉ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ ከሰው የሚቻለውን አድርጉ እንጂ ቀሪውን የኢትዮጵያ አምላክ ይጨርሰዋል፡፡ አምላክ ኢትዮጵያን እስከወዲያኛው ትቷት አያውቅም፡፡ የአሁኑ ለየት አለ እንጂ ዱሮም ወደዚህ የሚጠጋ ችግርና የመከራ ወቅት ይከሰት ነበር፡፡ ስለሆነም እኛ ወደርሱ ስንመለስ እርሱም ወደኛ ይመለሳልና ከኛም እንዳይቀር የምንችለውን ሁሉ ከልብ እናድርግ፡፡ ሁሉን ለርሱ መጣል የማይቻል መሆኑን ለማጠየቅ ለአዳምና ለሔዋን የነገራቸው “ አዳም ሆይ፣ በላብህና በወዝህ ለፍተህ ደክመህ ብላ” የሚለው ቃል ኅያው ምሥክር ነው፡፡ ተዓምርን ብቻ አንጋጦ የሚጠብቅ ሕዝብ ደግሞ “ሰነፍና ሣይዋጋም የተሸነፈ ነው” እንደሚባል እንወቅ፡፡ በቃ፡፡Posted by: Zehabesha
No comments:
Post a Comment