ዛሬ መላው ዓለም ኢትዮጵያን እየተመለክተ ቅጥ ያጣውን የወያኔ አገዛዝ እየታዘበ ነው።የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ የወያኔ ድርጊቶችን አውግዞ ውሳኔ አውጥቷል። ወያኔ አርሶ አደሩ ንብረቱን አይቀማም ያሉ ተማሪዎችን ገድሏል። ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን እያሰረ እየገደለ ነው። ኢትዮጵያ ዛሬም የቀይ ሽብር አገር ናት።ወያኔ ያልተረጋጋች አገር ያደርጋታል የሚለው የዓለም ግምትም እያሳሰበ ነው።እኛ ኢትዮጵያውያን ከማንም በላይ ይህ ሁኔታ የሚያሳስበን በመሆኑ ልንወያይ፤ ልንመክርበት ጊዜው የግድ ይለናል።የህብረትም፤ እጅ ለጅ ተያይዞ ለትግል በአንድነት መነሻውም ጊዜ ዛሬ ነው።
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለስራ ጉዳይ ከኤርትራ መጥተው በመካከላችን ይገኛሉ። ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ የዋሽግቶን ዲ ሲ አካል ሊቀ መንበሩን አግኝታችሁ መወያየት እንድትችሉ በታላቅ አክብሮት ይጋብዛችኋል።

No comments:
Post a Comment