የጎንደር ሕብረት ዛሬም እንደ አለፉት መግለጫዎቻችን፤ በጎንደር ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን የግፍ ተግባሮች አደባባይ በማውጣት፤ አገር አድን ብሔራዊ ትግላችንን የምናጠናክርበትን ስልት የማጠናከሩን ዓላማ ግብ ለማድረስ ነው። ይህ ሲባል ግን፤ በጦርነት ተወልዶ፤ በጦርነት እያረጀ ያለው፤ አገር አጥፊው የወያኔ ቡድን፤ በወረቀት ብቻ ይወድቃል ብለን ማመናችን አይደለም። መግለጫ፤ ጠላትን ያጋልጣል። ባንፃሩም ወገንን ያሥተባብራል፤ ያደራጃል፤ ያሥታጥቃል፤ በመጨረሻም ጠላቱን ይደመሥሳል።

ባለፉት 25 ዓመታት የጎንደር ሕዝብ የተፈጸመበትን ሰቆቃና ግፍ ለመዘርዘር በየጊዜው በምናወጣቸው ጥቂት ገጾች ላይ ብቻ ተዘርዝሮ የሚያበቃ ሳይሆን ሙሉ መጽሐፍ እንኳ አይበቃውም። ወያኔዎች ዛሬም እንደ ትናንቱ በሕዝባችን ላይ አረመኒያዊ ጭፍጫፋ ለማካሄድ ኃይላቸዉን አጠናክረዉ ወደ መተማና ቋራ የግዛት መረባቸውን ለመዘርጋት ልዩ ቅልብ ጦር አሰማርተዋል ። ይህ ቅልብ ሰራዊት በወያኔ ካድሬነት ለፖለቲካ ተግባር ተሰማርቶ የሁለቱን ማህበረሰብ ለማጋጨጥ ለቅማንት ወገኖቻችን ከናንተ ጋር ነን አይዟችሁ ሲሉ፤ ለአማራዉ ማህበረሰብ ደግሞ ከናንተ ጎን ሁነን ቅማንትን ድራሹን እናጠፋለን እንደሚሉ ከመሬት ላይ በነጋዴ ባህር፤ በዳንጉራ እና በዳዋ የተረጋገጠ መረጃ ደርሶናል። ይህ አገርን ለማጥፋት ትዉልድን በጥላቻ የመበከል በሽታን እያጋብን ያለን መሰሪ ኃይል፤ የዘር ጎራ ሳንለይ በህብረት ጠንክረን መዋጋት እና ራሳችንን ነፃ ማውጣት፤ ታሪካዊ እና አገራዎ ግዴታችን ነው። ምንጭ ECADF news
No comments:
Post a Comment