Thursday, 30 June 2016

የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (3)

.ነገስታቶቻችንን ከአማራነት መነጠል ምን ጉዳት ያመጣል?
******************************************************************
አንድ የአማራ “ተቆርቋሪ” ሰው በተደጋጋሚ አጼ ቴዎድሮስ “ቅማንት” ናቸው ብሎ ይናገራል፤ ኧረ እንዲያውም ይህንኑ ኑፋቁ በጥራዝ መልኩ ጸፎአል አሉ፡፡ ታዲያ አንዲት አማራ ትበሳጭና እስኪ ማስረጃ ትለዋለች፡ እርሱም እግዜርን ሳይፈራ ሰውንም ሳያፍር “የታንጉት ምስጢር” ላይ ነው ያነበብኩት ይላል፡፡ ይህ ሰው አጼ ቴዎድሮስን ቅማንት ለማድረግ የታንጉት ምስጢርን ምስክር መጥራቱ ብቻ አይደለም ችግሩ፡፡ ትልቁ ችግር ይህንን መጽሀፍ አለማንበቡ ነው፡፡ ሶስተኛው ችግር ደግሞ አጼ ቴዎድሮስን ቅማንት ናቸው ሲል አማራን እና ቅማንት አማራን አራርቆ ለማስቀመጥ መሞከሩ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ አጼ ቴዎድሮስ ቅማንት ናቸው የሚለው በራሱ ችግር አልነበረውም፡፡ ችግሩ ያለው በውስጡ ካዘለው ጸረ አማራ ፖለቲካዊ አጀንዳ ላይ ነው፡፡ እንጅማ ቅማንት አማራም ሆነ አማራ ያው አማራ ነው፡፡) ሌላኛው ችግር ደግሞ ለኢትዮጵያ ሲባል የአማራን ታሪክ ለማይፈልጉት ሁሉ መወርወር እና አማራን ታሪክ አልባ አድርጎ የማስቀረቱ ዘመን ያስቆጠረ ልማድ ቀጣይ ክፍል አራማጅ መሆኑ ነው፡፡ እግዜር ያሳያችሁ! ሌሎች ብሄሮችን ታሪክ እንዲሰሩ እና ከአማራ ጋር እንዲስተካከሉ ማድረግ ሲገባ የአማራን ዘርፎ አማራን ባዶ አድርጎ እነዛን ያልሰሩቱኑ ባለታሪክ ማድረግ! ይህንን የሚገልጽ አንድ ሌላ አማራዊ ገጠመኝ፡፡ በ1996 ዓ.ም. አማራ ከ8ኛ ክፍል በኋላ መማር የለበትም ተብሎ ፖሊሲ ወጥቶ ነበር፡፡ እስከ 8ኛ ክፍል ይማራሉ፤ ከዛ ወዲያ የራሳቸው ጉዳይ፡፡ ኦቦ አዲሱ ለገሰ ለምን እንዲህ ይደረጋል ተብሎ ተጠይቆ ሲመልስ “አማራ ከዚህ በፊት ስለተማረ ከሌሎች ጋር ለማስተካከል ነው” አይነት ንግግር ተናገረ፡፡ ገራሚ፡፡ ሌሎችን በማስተማር ከአማራ ጋር ማስተካከል ነው ወይስ አማራውን እንዳይማር ማድረግ ነው የሚገባው? ግን ቅንጅት መጥቶ የአማራን ወጣት ከዛ መከራ አተረፈው፡፡ ቅንጅት ለአማራ የዋለው ውለታ በዚህ ረገድ የሚረሳ አይደለም መቸም፡፡
ወደጥንተ ነገራችን እንመለስ፡፡ አንድ የብርሀኑ ዘርይሁን ጓደኛ የነበረ ሰው ብርሀኑ የታንጉት ምስጢርን እንዴት እንደጻፈው አጫውቶኝ ነበር፡፡ ብርሀኑ የታንጉት ምስጢርን ሲጽፍ የአዲስ ዘመን ስራ አስኪያጅ ነበር አለ፡፡ አንድ ጠረጴዛ ላይ በአንድ እጁ የታንጉት ምስጢርን ሲከትብ፤ በሌላ ወገን ተስተናጋጅ እና የስራ ባልደረቦች ስራ ሲሰጡት ደብተሩን እያጠፈ፤ እንደገና ስራና ሰው ቀለል ሲልለት ገልጦ እየጻፈ፤ እንደገና እየተዋከበ ነው የጻፈው አለ፡፡ ይህ ጓደኛየ ለብርሀኑ ዘሪሁን ያለውን አድናቆት ተናግሮ አይጠግብም፡፡ ብርሀኑ የታንጉት ምስጢርን በጻፈበት ውክቢያ ሁኔታ አይደለም መጽሀፍ የጋዜጣ አምድ ማዘጋጀት ፈታኝ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ለዚህ ጓደኛየ ብርሀኑ በቃ ብርቱ ሰው ነው፡፡ እና በዛ ወከባ ውስጥ ሆኖ የጻፈው መጽሀፍ እስከዛሬም ድንቅ ነው፡፡
ያው እንግዲህ መጽሀፉ ታሪካዊ ልቦለድ ነው፡፡ ታሪካዊ ልቦለድ በመሰረታዊ ጭብጥነት ታሪክ እና አፈ ታሪክ ላይ የሚመረኮዝ ቢሆንም በደራሲው ምናባዊ ተጽእኖ ስር ስለሚወድቅ ለታሪክ ማጣቀሻነት አይውልም፡፡ እንዲህ አይነቱ ድርሰት ደራሲው ተጨባጭ ታሪኮችን እና አፈ ታሪኮችን ልብ አንጠልጣይ በሆነ ሁኔታ የሚጽፍበት እንጅ የታሪክ ሰነድ አገላብጦ ማጣቀሻ አስቀምጦ እውነትን ብቻ የሚያስቀምጥበት አይደለም፡፡
ያም ሆኖ የታንጉት ምስጢር ውስጥ ላይ አጼ ቴዎድሮስ ቅማንት ናቸው የሚል አይገኝም፡፡ መጽሀፉ ራሱ የታንጉት ምስጢር የተባለበት ምክንያት የአጼ ቴዎድሮስ አባት ታንጉትን ከቅማንት አማራ መውለዳቸው እና በኋላም ይህችን ታንጉትን ወንድምዋ አጼ ቴዎድሮስ ለታማኛቸው ፊታውራሪ ገብርየ ሚስት አድርገው ማጋባታቸው እና በጋብቻውም ፍሬ ማፍራት ባለመቻላቸው አሁንም ቅድምም “ኧረ ባባጃሌው” የምትለዋ ወፍራም ሴትዮ (ስሟን ረስቸዋለሁ) ታንጉትን በመጀመሪያ ጭልጋ ወይኒ ኪዳነምህረት ጸበል መውሰድዋ (ይህ የወይኒ ኪዳነ ምህረቱ የጸበል ጉዳይ በአቤ ጉበኛ “አንድ ለእናቱ” መፅሀፍ ላይም በስፋት መገለጹ ይታወሳል)፤ በጸበል አልሳካ ሲል አምባ ጊዮርጊስ በሚስጢር ከአንድ የቆሎ ተማሪ ጋር እንድትተኛ ተደርጎ መጸነሱዋን እና ያንንም ወፍራሟ ሴት እና ታንጉት የገብርየ ልጅ ነው ብለው የማሳመናቸውንና የመሳሰለውን ውስብስብ የመንግስት ፖለቲካ ለማስረዳት ነው፡፡ የአጼ ቴዎድሮስ እህት ታንጉት በአንድ ወገን ከቅማንት አማራ ትወለዳለች፡፡ ነገር ግን አጼ ቴዎድሮስ እህቱ ቅማንት አማራ በመሆኑዋ ብቻ ቅማንት ነው ብለው የሚከራከሩ የአማራ “ተቆርቋሪዎች” ስናገኝ ያለንበት ዘመን እውነትም 8ኛው ሽህ መሆኑን በደምብ እንገነዘባለን፡፡ እዚሁ መጽሀፍ ላይ ፊታውራሪ ገልሞ የሚባል በጣም ጀግና ቅማንት አማራ ነበር፡፡ አጼ ቴዎድሮስ ይህንን ጀግና ሰው “ምነው ሁሉም ቅማንት እንዳንተ በሆነልኝ” እያሉ ያንቆለጳጵሱት እንደነበር ብርሀኑ ጸፎአል፡፡ የማንቆለጳጰሱ ነገር የደራሲው ምናብ ይሁን እውነታ ወደጎን እንተወው እና ፊታውራሪ ገልሞ የሚባል በጣም ጀግና ቅማንት አማራ ከአጼ ቴዎድሮስ ጎን ከእነ ራስ እንግዳ እና ፊታውራሪ ገብርየ ጋር ተሰልፎ እንደነበረ ግን በታሪክ የሚታወቅ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ እስካሁን ድረስ አንድም አማራ ራሱን በፌስቡክ ራስ እንግዳ ብሎ በማስታወሻነት አለመሰየሙ አሳዝኖኛል)፡፡ አጼ ቴዎድሮስን ሀበሻ በሙሉ ከድቶ ከንጉሱ ጎን እስከመጨረሻው በታማኝነት ከቆሙት 5000 ወታደሮች አንዱ እና በጦርነቱም ለሚወደው ንጉስ እና ለቆመለት አላማ የተሰዋ ጀግና ነውና…. ራስ እንግዳ፡፡ ባጭር አገላለጽ ቅማንት አማራ የተበታተነውን አማራ ለማሰባሰብ በተደረገው እልህ አስጨራሽ የጀግንነት ስራ ከአጼ ቴዎድሮስ ጎን ሆኖ በህዝብ ሰብሳቢነት እና አገር አንድ አድራጊነት ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡
እንግዲህ አማራ ላለፈው ግማሽ ክፍለዘመን DeAmharization Process ውስጥ ያለ ህዝብ ነው፡፡ አማራን በዚህ ኢ-አማራ ማድረግ ሂደት ውስጥ የተሳተፉት በሚያሳዝን ሁኔታ አማራ ያልሆኑቱ ብቻ አይደሉም፡፡ አማሮቹ ራሳቸው በስፋት ተሳትፈውበታል፤ አሁንም እየተሳተፉበት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያንን በስሜትም በግብርም እንደ አንድ ሰው አሳቢ እንደ አንድ ልብ መካሪ ለማድረግ የእያንዳንዱን ብሄራዊ ማንነት ማጥፋት መልካም ሊመስል ወይም ሊሆን ይችላል፡፡ ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ለጋዜጠኛ ዘነበ ወላ እንዳለው ፈረንሳዮች ኦምሌት ለመስራት እነቁላሉን መስበር ያስፈልጋል ይላሉ፤ አጼ ምኒልክም ኢትዮጵያን ለመፍጠር ወይም ኦምሌት ለመስራት እንቁላሉን መስበር ነበረባቸው፤ አጼ ምኒልክ እንቁላሉን ባይሰብሩት እና አማርኛን ባይሰጡን ኖሮ አንተ ከጋሞ እኔ ከትግራይ በምን እንግባባ ነበር ብለውት!
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሁሉም እንቁላሎች ተሰብረዋል ማለት አይቻልም፡፡ ሌሎች እንቁላሎች እንዳሉ ሆነው አማራ ብቻ ተሰብሮ በስብርባሪው ሌሎችን እንቁላሎች እንዲያጣብቅ ነው የተደረገው፡፡ አማራ ተሰብሮ ሌላው ሳይሰበር የተሰራውም ኦምሌት ዛሬ የሌሎች አለመሰበር ህልውና እየተላወሰ እያየን ነው፡፡ የእነሱ ህልውናም አማራውን ጨርሶ ለማጥፋት ደርሷል፡፡ አሁን የተያያዝነው ሌሎችን እስከህይወታቸው ለማቆየት የተሰበረውን እንቁላል፤ አማራን፤ እንደገና መጠገን እና በብዙ ድካም ወደነበረበት መመለስ ነው፡፡ ኢትዮጵያን እንደ አገር እንደገና ለማቆም አማራ ብዙ ጊዜ ሲጨፈለቅ እና ሲሰባበር ነው የቆየው፡፡ በኋላም አማራ ማንነቱን ረስቶ ለኢትዮጵያዊነት ሲለውጥ ሌሎች ግን ስላልተሰባበሩ በነበሩበት ቆዩ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያዊነት ፕሮጀክት ሲጀመርም ሁሉንም ማንነቱን አሳጥቶ አንድ የማድረግ ሂደትን ያልተከተለ ነበር፡፡ ውጤቱንም አሁን እያየነው ነው፡፡ ያለፉት መሪዎቻችን፤ ልሂቃን እና አሁን ያለው ልሂቅ አማራን ብቻ ማጥፋት ኢትዮጵያን ይገነባል ወይም አጣብቆ ያቆያል ብለው ያስባሉ፡፡ በጣም ስህተት፡፡ ይህ ግን በአማራ ሞት ላይ ለሌሎች ያልተሰበሩ እንቁላሎች ህይወት መስጠት ነው፡፡ አማራ እየተሰባበረ ሌላው ግን ሲፈለፈል ቆይቷል፡፡ ስለሆነም አንዲት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተደረገው ሂደት እና አሁንም እየቀጠለ ያለው ጥረት በአማራ ኪሳራ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፡፡ ለአማራ ጎጅ ነው፡፡ አማራ ብቻውን ለምን ይሰበር!?
ስለዚህ ሚዛናዊ ባልሆነው እንቁላል ሰበራ የተዳከመውን የአማራነት ስሜት ለማጠናከር እየጣርን ባለንበት በአሁኑ ሰአት የተዘረፈብን እና እየተዘረፍብን ያለውን ታሪክ አለምንም መታለል እና መዘናጋት ማስመለስ ወይም መመለስ አለብን፡፡ አማራነታችን ለሌሎች የመስዋእት በግ ሆኖ በነጻ እንደታደለው ሁሉ የአማራ የሆነው ነገር ሁሉ እንዲሁ በገፍ ተዘርፏል፡፡ ከላይ የኦቦ አዲሱ ለገሰ ምሳሌነት እንደሚያስረዳው አይነት ነገር ነው አማራ እና አማራነት እንዲሁም የአማራ የሆነው ሁሉ ላይ እየተካሄደ ያለው፡፡ በጣም በሚያናድድ መልኩ እኛም ራሳችን ሳናውቅ ወይም በግብዝነት ይህንን የአማራ የሆነውን ሁሉ ፍቆ የማጥፋት እና ለሌሎች የመሸለሙ ስራ ላይ በአጋዥነት ስንሰራ እንታያለን፡፡
ከላይ በአጼ ቴዎድሮስ ላይ የቀረበው የታንጉት ምስጢር አይነት ምስክር በአጼ ምኒልክና በአጼ ኃይለ ሥላሴ ላይ በስፋት ሲንጸባረቅ ይታያል፡፡ ለምሳሌ በመግቢያየ የጠቀስኩት የአማራ “ተቆርቋሪ” አጼ ምኒልክን እና አጼ ኃይለ ሥላሴን ከአማራነት ፍቆ ለሌላ አስረክቧል፡፡ ያው ማስረጃው መሰለኝና ደሳለኝ ቢሆንም ቅሉ! ማን ይሰማዋል! በተመሳሳይ እዚሁ ፌስቡክ ላይ በአማራ ብሄረተኝነት አምናለሁ የሚል ራሱን ካይማር ሠርፀ ድንግል ብሎ የሚጠራ ሰው አጼ ኃይለ ሥላሴን አማራ አይደሉም ብሏል፡፡ በጣም የሚገርመው ይህ ሰው ጉራጌን አማራ ነው ብሎ ያምናል፡፡ በዚህ ሰው አባባል ለምሳሌ በቅርቡ ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋየ ሀብተማርያም ጉራጌ አማራ ሲሆን ከወሎ የተወለደውን የሻእብያና ኦነግ መጠቀሚያ የነበረውን ዋለልኝ መኮንንን በበረራ ልዩ ሀይልነቱ መግደሉን አወድሶ ጽፎአል፡፡ ነገር ግን አጼ ሀይለስላሴ አማራ አይደሉም የሚባልበት ምክንያት አንዱ ጉራጌ ደም አላቸው የሚለው ነው፡፡ ጉራጌን አማራ ያለ ሰው ታዲያ ከጉራጌ እና አማራ ተወለደ የተባለን ንጉስ እንዴት ብሎ ነው አማራ አይደለም የሚለው!!!!? በነገራችን ላይ አጼ ኃይለ ሥላሴ የጉራጌ ደም አላቸው የሚለውን በቂ ማስረጃ የለኝም፡፡ እንደማስረጃ የምጠቅሰው የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌን “ነጻነትን የማያውቁ ነጻ አውጭዎች”ን ነው፡፡ ታጋይ አንዳርጋቸው እዛ ላይ ቃል በቃል “በአጼ ምኒልክና አጼ ኃይለ ሥላሴ የደም ቧንቧ ከሚፈሰው የአማራ ደም ይልቅ የኦሮሞና ጉራጌ ደም ይበልጣል” ብሏል፡፡ ከየት እንዳገኘው አላውቅም፡፡ ይሁንና ይህም አባባል የተጠቀሰው ኢ-አማራ የማድረጉ ሂደት (DeAmharization Process) አንዱ አካል ነው፡፡
እንግዲህ ጉራጌ፤ ሀድያ፤ ከምባታና አደሬ በኦሮሞ ወረራ ከጥፋት ከተረፉት የጥንት የአማራ ክፍሎች የሚጠቀሱ መሆናቸው አያከራክርም፡፡ አጼ ምኒልክም ሆኑ አጼ ሀይለ ሥላሴ የጉራጌ ደም ቢኖራቸው አማራነታቸው እንደተጠበቀ ነው፡፡ እንደዋዛ መታለፍ የሌለበት ግን እነዚህ ነገስታት የኦሮሞ ደም አላቸው የሚለው የክህደት ነገር ነው፡፡ አጼ ምኒልክ የኦሮሞ ደም አላቸው የሚለው ነጭ ውሸት ነው፡፡ የዘር ሀረጋቸውን የንጉሱ ጸሀፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ “ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ” በተሰኘው መጽሀፋቸው በተገቢው ዘርዝረው ጽፈውታል፡፡ እዛ ላይ መመልከት ነው፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ ኦሮሞ ደም አላቸው የሚለው በጥልቀት መታየት አለበት፡፡ እንደሚባለው በአያታቸው ከሀረር ኦሮሞ ይወለዳሉ ነው፡፡ መልካም፡፡ ነገር ግን ኦሮሞ በሁለት ይከፈላል፡፡ ኦሮምኛ ተናጋሪ አማራ እና ኦሮሞ ተብሎ (ቢያንስ ከዚህ ጽሁፍ አንጻር)፡፡ እንደሚታወቀው የሀረር ኦሮሞ ኦሮምኛን ለረዥም ጊዜ በመናገሩ ወደኦሮሞነት የተቀየረ የጥንት አማራ ነው፡፡ ይህንን መሰል ጉዳይ የጀነቲክስ (ዘረመል) ጥናቶች እያፍታቱት ነው፡፡ ለወደፊቱም ኦሮምኛ በመናገር ብቻ ኦሮሞ መስሎት የሚኖረውን የጥንት አማራ ወገናችንን በዚህ መሰል ሳይንሳዊ ዘዴ ነው ወደቀደመ አማራ ማንነቱ የምንሰበስበው፡፡ ይህም ማለት አጼ ኃይለ ሥላሴ በአያታቸው ኦሮሞ ናቸው ቢባል እንኳ በዚህ መንገድ ኦሮምኛ በመናገር ላይ ከሚገኝ ከጥንት አማራ የተወለዱ አማራ ናቸው ማለት ነው (He descends from a culturally Oromo but a genetically Amhara population)፡፡ ስለዚህ አጼ ኃይለ ሥላሴ አማራ ብቻ ናቸው፡፡
ቢባል ቢባል እና አጼ ኃይለ ሥላሴ ኦሮሞ ደም አላቸው ብንል እንኳ ሊሆኑ የሚችሉት በአንድ አያታቸው ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት 75% አማራ ናቸው ማለት ነው፡፡ በጀነቲክ ሳይንስ ደግሞ 25% is recessive while 75% is dominant gene. ይህ ማለት 25 ከመቶው ጅን በ75 ከመቶው የተሸፈነ ወይም ዋና ያልሆነ፤ የዘር ሀረግን በዋናነት ማስተላለፍ የማይችል፤ ለራሱ የተወሰነ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው 75 ከመቶው የወረሰበትን ወላጅ ዘር ሙሉ በሙሉ ይይዛል ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ግማሹ ወይም 50 ከመቶው አማራ ቢሆን እንኳ አማራ ነው እንኳን 75 ከመቶው! እንዳለመታደል ግን ለግማሽ ክፍለ ዘመን ከዘለቀው የኢ-አማራ ማድረግ ሂደት የተነሳ አማራን ኦሮሞ ለማድረግ 25 ከመቶ በቂ ነው፡፡ 75ን ለ25 በግድ እጁን ጠምዝዞ ማስረከብ! በእናንተ በራሳችሁ ክርክር እንኳ 75 ከመቶ የሆነን ሙሉ አማራ ለ25 ከመቶው አሳልፋችሁ ለመስጠት የምትንጦለጦሉ አማራ ተብየዎች ማፈር አለባችሁ፡፡ ያም አለ ይህ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከፍ ዝቅ የሌለባቸው አማራ ናቸው፡፡ እዚህ ጋር የተጠቀሰው ጀነቲክ ማብራሪያ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ደግሞ ንጉሱ በባህል ሙሉ በሙሉ አማራ ናቸው፡፡ ማለትም አንድን ህዝብ ከዘሩ በተጨማሪ አማራ የሚያደርገው ሳይንሳዊ የባህል ማብራሪያ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ፤ አንድም ሳያጓድሉ የያዙ ንጉስ ናቸው፡፡ ኧረ በበለጠ ሁኔታ፡፡
በነገራችን ላይ ካይማር እና አክናሁስ “አጼ ሀይለ ስላሴ በታሪክ ፊት ብላችሁ” ስለፓኪስታን ምናምን የምትዘባርቁትን ሀሜት አይቸዋለሁ፡፡ ያው ሀሜት ከሀሜትነቱ አይዘልም…ታውቃላችሁ ወይም ታውቃለህ፡፡ የፓኪስታኑ ጉዳይ አስጨንቆኝ ሳይሆን አንድ ምክር ለመለገስ ነው ያንን ትርኪ ምርኪ ሀሳባችሁን ያነሳሁት፡፡ ይህንን ሀሳብ የሚያራምዱትን ዋነኞቹን የጀርመን ፕሮፌሰሮች አውቃቸዋለሁ፡፡ እዛ ትግራይ አካባቢ ያስተምራሉ፤ ሪሰርች ይሰራሉ፡፡ ለአማራ ያላቸው ክፉ አመለካከት ግን ከአንድ የአድዋ ተወላጅ ወያኔ ቢብስ አንጅ አያንስም፡፡ አንዱ በተለይ ትግሬን ደግፎ እዚህች አገር ላይ ለደረሰው ችግር ሁሉ አማራን ተጠያቂ አድርጎ የሚከራከር ነው፡፡ ስለፓኪስታኑ ጉዳይ ሲያራግብ ማስረጃ አምጣ ስለው ንጉሰ ራሳቸው የጻፉት ጽሁፍ ላይ የሆነ ፎቶ አይቸ ምናምን ነው የሚለው፡፡ ሌላም የሚዘባርቀው ነገር አለ፡፡ ግን አላማው የወያኔን ጸረ አማራ ስራ ማገዝ ነው፡፡ ይህንን ስላችሁም ዝም ብየ አይደለም፡፡ የጀርመን ምሁራን ለኦነግ፤ ሻእብያና ወያኔ በትጥቅ ትግል ወቅት የፕሮፓጋዳ ድጋፍ ያደርጉ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ዘነበ ፈለቀ “ነበር” ብሎ በጻፈው መጽሀፍ ውስጥ ደርግ ሁለት የደህንነት ሰራተኞችን ወደምእራብ ጀርመን መላኩን፤ የደህንነቶችም ተልእኮ አንድ የሸማቂዎች ዋና ሰውን ለመግደል እንደነበረ፤ ነገር ግን አንደኛው ደህነነት ቦምቡን በመጽሀፍ መልክ ለማጥመድ እየሰራ በነበረበት ጊዜ ሌላኛው ደህንነት ውጭ ቆይቶ ድንገት ወደክፍላቸው ሲገባ ሳያስበው ቦምቡን ነክቶት መፈንዳቱን፤ ያንንም ተከትሎ ይህንን ከፍንዳታ የተረፈ ደህንነት የምእራብ ጀርመን የደህነነት ሰራተኛ አይኑን ደንቁሎ አውጠቶ ጥሎት ወደአዲስ አበባ መመለሱን እንደጻፈ ነገርኩት፡፡ ይህም ፕሮፌሰር “ደርግ የላካቸው እነዛ ደህንነቶች ማንን ለመግደል እንደነበር አውቃለሁ፤ ለተቃዋሚዎች የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ ያደርግ የነበረን ጓደኛየን ለመግደል ነበር” ብሎ ነገረኝ፡፡ እና ምን ማለት ፈልጌ ነው፡- አጼ ኃይለ ሥላሴን ኢ-አማራ ማድረግ ወይም አማራ ላይ መዝመት የዚህ አገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን አለማቀፍ ተልእኮም አካል ነው እያልኳችሁ ነው፡፡ ሀሜትን እንደማስረጃ በማቅረብ ወይም ማረጋገጥ የማትችሉትን ወሬ በማዛመት አማራነታችንን ከመጉዳት እንድትታቀቡ ለማሳሰብም እወዳለሁ፡፡
ከላይ በተጠቀሰው መልኩ እየተደረገ ያለው ነገስታቶቻችንን ኢ-አማራ ማድረግ ምን ጉዳት ያመጣል የሚለውን እንመልከት፡፡ አማራ የሆኑትን ነገስታቶቻችን አማራ አይደሉም ስንል ብዙ ነገር እናጣለን፡፡ ዋና ዋናዎቹም አምሐራ ነጻ ህዝብ ነው ስንል አማራ ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘመነ ቅኝ ግዛት ድረስ በማንም ተገዝቶ አያውቅም ማለታችን ነው፡፡ በአለም ደረጃ ቅኝ ያልተገዛች ኢትዮጵያ ሲባል የዚህ ድል ዋናው ተዋናይ አማራ ነው፡፡ የማእከሉ ማእከል ላይ ደግሞ አማራ ነገስታት ይገኛሉ፡፡ አጼ ቴዎድሮስ አማራን በማሰባሰባቸው በኋላ የመጡትን ወራሪዎች በአንድነት እንዲመክት እድል አመቻቹ፡፡ ይህንን አጼ ቴዎድሮስ የሰበሰቡትን እና በሀይለኛ ክንድ ደቁሰው አንድ ያደረጉትን አማራ በመጠቀም ዳግማዊ ምኒልክ የበለጠ በማጠናከር የመከላከያ ወረዳቸውን አስፋፉበት፤ የተወሰደውንም መሬት መለሱበት፡፡ የመከላከያ ወረዳ ማስፋት ምን ማለት ነው? ንጉሱ የጥንት ግዛታቸውን ከማስመለስ ባለፈ ዙሪያቸውን በስፋት ከያዙበት ምክንያቶች አንዱ ቅኝ ገዥዎች ምናልባት ወደመሀል እንምጣ ቢሉ እዛው በረዥም ዳርቻ ለመከላከል በማሰብ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ ከጅቡቲ ወይም ሀርጌሳ ተነስቶ የሚመጣ ሀይል መሀል ኢትዮጵያ ወይ አማራ ላይ ከመድረሱ በፊት መከላከል ይቻላል፡፡ በጋምቤላም በሩዶልፎ (ደቡብ፡ ኬንያም) እንዲሁ ነው፡፡ ይህን የተስፋፋ የመከላከያ ወረዳ በመጠቀም እና ሰፊው ግዛት የፈጠረውን አቅም በመጠቀም በወራሪዎች ላይ አለም አቀፍ ድል ተጎናጸፉ፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴም በበኩላቸው ከዚህ ታላቅ ንጉስ የተረከቡትን አገር እና ነጻነት ለማስጠበቅ በነፍጥ ተፋልመዋል፡፡ አልሆን ሲልም ወደ ውጭ ሄደዋል፡፡
እዚህ ላይ ንጉሱ ወደውጭ መሄዳቸውን እንደሽሽት የሚቆጥሩ አሉ፡፡ ይህ ግን ውሀ የማያነሳ ክርክር ነው፡፡ አምባሳደር ብርሀኑ ድንቁ “ቄሳርና አብዮት” በተሰኘች መጽሀፉ ይህንን ነገር በሚገባ አብራርቶታል፡፡ ብርሀኑ ድንቄ ለመከራከሪያነት ያቀረባቸው ጭብጦች የአጼ ኃየለ ሥላሴን ከአገር መውጣት እና የአጼ ቴዎድሮስን መቅደላ ላይ መሰዋት ነው፡፡ እንደ ብርሀኑ ድንቄ አባባል ለአንድ አይዲያሊስቲክ ኢትዮጵያዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ማይጨው ላይ ራሳቸውን ማጥፋት ነበረባቸው፤ ራሳቸውን ቢያጠፉ ትክክል ናቸው፡፡ በሌላ ጎኑ ለአንድ ፕራግማቲክ ሰው አጼ ኃይለ ሥላሴ ሁኔታው እንደማይሆን ሲያውቁ አገር ለቀው መሰደዳቸው ተቀባይነት አለው፡፡ እዚህ ጋር ክርክሩ በአይዲያሊስት እና ፕራግማቲስት ተቃርኖዎች ላይ ነው፡፡ ማለትም አንድ አይዲያሊስት የአጼ ኃይለ ሥላሴን ድርጊት ኮንኖ ሊከራከር ይችላል፡፡ በሌላ ወገን አንድ ፕራግማቲስት ግን የንጉሱን ድርጊት ደግፎ ሊከራከር ይችላል፡፡
በአጭር አገላለጽ ምን ማለት ነው፡- ንጉሱ መሰደዳቸው ተጨባጭ ለውጥ አምጥቶአል፡፡ ንጉሱ እዛው ላይ ሞተው ቢሆን እና ጣልያን ተቆጣጥሮን ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ወይም የአማራ ነጻ ህዝብነት ወይም አምሐራነት አከተመ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ንጉሱ በመሰደዳቸው የኢትዮጵያ ስልጣነ መንግስት አብሮ ተሰደደ ማለት ነው፡፡ ያ ማለት የኢትዮጵያ መንግስት ከአገሩ ተሰዶ በሌላ አገር በስደተኝነት ቀጥሎ ነበር ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ንጉሱ አገራቸውን እንጅ ስልጣናቸውን አልተቀሙም፡፡ ዙፋናችንም አልተወገደም፡፡ ንጉሱ በስደት መንግስታቸውን ይዘው በመሰደዳቸው ኢትዮጵያ በጣልያን ስር ሆናም የመንግስትዋ ህልውና አላከተመም ነበር፡፡ ይህ በራሱ ትልቅ ጥቅም አምጥቷል፡፡ ንጉሱ በስደት ሆነው ዲፕሎማሲያዊ ትግል በማድረግ የአላይድ ፓወርስ ድጋፍ ማግኘት ችለዋል፡፡ ያም ድጋፍ በኋላ ከአርበኞች ትግል ጋር ተደማምሮ በስደት የነበረውን መንግስት ተመልሶ በቦታው እንዲተከል አድርጎታል፡፡ አገር ውስጥ ይደረግ የነበረው የአርበኝነት ትግልም ይህንን የንጉሱን ዲፕሎማሲያዊ ትግል ለማገዝ ረድቶአል፡፡ እዚህ ላይ የንጉሱን ዲፕሎማሲያዊ ትግልና ያም ትግል ያስገኘውን አለማቀፍ ድጋፍ ለማሳነስ ሲል አርበኞች ነጻ ሊያወጡን ይችሉ ነበር ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ እኔ ግን የአርበኞች ትግል ብቻውን ነጻነታችንን ያጎናጽፈን ነበር ብየ ለማሰብ ይከብደኛል፡፡ በምንም መልኩ የአርበኞች ተጋድሎ ወደር የለሽ መሆኑ የታመነበት ነው፤ ይሁንና የንጉሱ ዲፕሎማሲያዊ ትግል የላቀውን ሚና ተጫውቷል ብየ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ Michela Wrong “I didn’t Do It For You” በተባለው መጽሀፏ ውስጥ የንጉሱ ቀኝ እጆች የነበሩት የሲልቪያ ፓንክረስት ቤተሰቦች በተለይም ሲልቪያ ፓንክረስት የነበራትን ተደማጭነት በመጠቀም በየአገሩ እየዞረች ለንጉሱ ድጋፍ ታሰባስብ ነበረች፡፡ የድጋፉም አይነት የዲፕሎማሲ እና የገንዘብ ነበር፡፡ በዚህም ብዙ እንግሊዛዊያንን እና ከዛም አልፎ ሌሎች አውሮፓዊያንን ከንጉሱ ጎን ማሰለፍ ችላለች፡፡ ግን ደርግ ንጉሱን ለማጥላላት ብዙ ሰርቷል፡፡ የዛም ክፉ ፕሮፓጋንዳ ቅሪት በወያኔ ህይወት ተዘርቶበት ወደራሳችን ወገኖችም ተጋብቶ እስከዛሬ ድረስ አለ፡፡
ስለዚህ የነገስታቶቻችን አማራነት ከጣልን አምሐራ ነጻ ህዝብ ነው የምንለውን አብረን መጣል አለብን፤ ኢትዮጵያ ወይም አማራ ቅኝ አልተገዙም የሚለውን መወርወር አለብን፤ የጥቁር ዘር አንጸባራቂ የሆነ አለማቀፍ ድል ሲያደርግ ዋነኛው ህዝብ አማራ እና መሪዎቹ አማራ ነገስታት መሆናቸውንም መጣል አለብን፤ እነደአማራነታችን የወረስነውን አኩሪ ገድል ሁሉ አብረን መጣል አለብን ማለት ነው፡፡ አንዱን የአማራነት አሻራ ስንጥል ሁሉንም እየጣልን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ በራሳችን ነገስታት ላይ ስንዘምት በራሳችን ላይ እየዘመትን መሆናችንን እንገንዘብ፡፡ አማራነታችንን ሌሎች የሚሸራርፉት እና የሚያጠፉት ይበቃል፡፡
መለክ ሐራ

የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (2)

ታሪክ በብሄረተኝነት መነጽር
*********************************************************
በተደጋጋሚ ከፋም ለማም የአማራ ታሪክ የአማራ ነው፤ ከሁለቱም በኩል ትምህርት ብቻ ነው መውሰድ ያለብን እያልን ለማስገንዘብ ስንሞክር ቆይተናል፡፡ አንድ ነገር በግድ መታወቅ አለበት፡፡ ታሪክን ለመናቆሪያነት መጠቀም ካሰብን ዘለአለም ስንጨቃጨቅ መኖር እንችላለን፡፡ ማለትም ላለመስማማት ከፈለግን መቸም አንስማማም፡፡ ይህም የሚሆነው በሶስት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛ ያለፈውን ታሪክ ሙሉ ስእል ማግኘት ስለማንችል እና የምንመረኮዝባቸው ሀቆች በሙሉ ሊደርሱን ስለማይችሉ፡፡ ሁለተኛ የአለፈን ጊዜ በአሁን ጊዜ መመንዘርና መፍረድ በአመዛኙ ስህተት በመሆኑ እና ብዙዎቻችን ለዚህ ሰለባ ስለምንሆን፡፡ ሶስተኛ በታሪክ ውስጥ ሆነ ተብሎም ይሁን ሳይተሳብበት የተሰሩ ስህተቶች የግድ አይቀሬ ስለሆኑ፤ ማለትም ታሪክን የሚሰሩት የሰው ልጆች በመሆናቸው ሰውን የሚያጋጥመው ውስንነትና ስህተት ታሪክ ላይም የግድ ስለሚንጸባረቅ፡፡ ስለሆነም ስለታሪክ ስንነጋር እነዚህን ነገሮች በቅድሚያ ግምት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅብናል፡፡ ይህም የአማራን ታሪክ እና አሁን ከጀመርነው የብሄረተኝነት እንቅስቃሴ ጋር አዋህደን ለማራመድ ይጠቅመናል፡፡ ይህ ጽሁፍ በአመዛኙ ሰሞኑን ፌቡ ላይ ሲንሸራሸሩ ለነበሩ ሚዛናዊ ያልሆኑ እይታዎች እንደመልስነት የታሰበ ነው፡፡
ከዚህ በፊት የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (1) ላይ የአማራ ማንነት ተገልጹዋል፡፡ የአማራ ታሪክ ተዋናዮች የሆነው ህዝብ በተለይም በታሪክ ላይ ሰፍረው የሚገኙት መሪዎችም ማንነታቸው ከዚሁ ከተጠቀሰው ሳይንሳዊ እሳቤ የሚወጡ አይደሉም፡፡ የአማራን ማንነት በቅጡ ካለመረዳታችን የተነሳ ይሄ ንጉስ አማራ አይደለም፤ ያ ንጉስ እትን ነው እያልን የራሳችንን ታሪክ ስንሸረሽር እንታያለን፡፡ መጀመሪያ አንድን ንጉስ ወይም ገዥ አማራ ነው ወይስ አይደለም ከማለታችን በፊት ስለአማራ ማንነት በጥቂቱም ቢሆን ማወቅ አለብን፡፡ የብሄረተኝነት እንቅስቃሴን እደግፋለሁ ወይም ቅርጽ እሰጠዋለሁ የሚል ሰው በመጠኑም ቢሆን ስለማንነት እንቅስቃሴዎችና መሰረቶች ማወቅ አለበት፡፡ ብሄረተኝነትን ለመቅረጽ መጀመሪያ ራስን ሰፋ አድርጎ መቅረጽ ያስፈልጋል፡፡ ይህ የተባለበት ምክንያት የብዙዎቹ ሰዎች ጽሁፎች ስህተት ወይም እውነት ናቸው ለማለት ሳይሆን የምንናገረው እውነትስ ሆነ ስህተት የተያያዝነውን የማንነት ፖለቲካ እንዴት ባለ መንገድ እና ሁኔታ እንደሚጠቅመው እና እንደሚጎዳው በደምብ እንዲታሰብበት ለማመላከት ነው፡፡
የብሄረተኝነት እንቅስቃሴ የወደፊት እቅድን የሚቀርጽ ሂደት ስለሆነ የወደፊቱን ለመቅረጽ የኋላ መነሻ ያስፈልገዋል፡፡ ብሄረተኝነት እንቅስቃሴዎች እንኳን ያለውን ታሪክ የሌለ አዲስ ነገር ይፈጥራሉ፡፡ የሰውን ቀልብ ማሰባሰብ እና ለአንድ አላማ አሰልፎ ግብን መጨበጥ የሚቻለው በሆነ አንኳር ወይም በሆኑ አንኳር ታሪካዊ ክስተቶች ዙሪያ ነው፡፡ ታሪክ በብሄረተኝነት እንቅስቀሴ ውስጥ እንደንብ አውራ (ንግስት) ነው፡፡ አውራው ወይም ንግስቲቷ የሌለችበት ንብ ይበተናል፡፡ ምክንያቱም አብሮ የሚያኖር ምክንያት ስለሌለው፡፡ እንደዚሁም የብሄረተኝነት እንቅስቃሴ አንድ ላይ አያይዞ ለአንድ ግብ የሚያሰልፍ ታሪክ ያስፈልገዋል፡፡ ከዚሁም በላይ የተጋጋለ ብሄረተኝነት ለማካሄድ የህዝቡን ያለፈ ታላቅነት መንገር የግድ ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ ያለበት ቦታ ላይ ሊወድቅ እንደማይገባው ደጋግሞ መንገር እና ያለፈው ትልቅነቱ እንዲናፍቀው ማድረግ ያሻል፡፡ ብሄረተኝነት የዛሬው ያለንበት ሁኔታ ውድቀት ነው ብሎ ነው የሚነሳው፡፡ ወደፊት ታላቅ ለመሆን መጀመሪያ ከታላቅነት መውደቅን ማመን ያስፈልጋል፡፡
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የሚወድ የእንትን ጠላት ነው ብለው የሚጽፉ ውስን ሰዎች አሉ፡፡ እንደአስተያየት ይከበርላቸዋል፡፡ ግን ነገርየው የማይጠቅም እና የእይታ ችግርን የሚያመለክት ነው፡፡ ንጉሱ እገሌን ግዛት በድለዋል ብሎ የሚያስብ ሰው እንደዛ ቢያስብ አይገርምም፡፡ በደል ከተባለ እንግዲህ ንጉሱ ላይ ሁሉም የሚነቅፍባቸው ይኖራል፡፡ እንግዲህ ዝም ተብሎ ሲታይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ነገስታት የሚጠቀስ ጉድለት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዛን ጉድለቶች ወይም አሉ የተባሉ ጉድለቶች ጠምዝዞ ለራስ አላማ ማዋል ግን ስህተት ነው፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የሚወድ የእንትን ጠላት ነው የሚለው ሀሳብ ግን እንደቀላል መታየት የሌለበት ነው፡፡ አንድ ሰው የአማራ ብሄረተኝነትን እደግፋለሁ ብሎ ሲያበቃ እንደገና ራሱን ከመላው አማራ ነጥሎ የተወሰነ አካባቢ ጠበቃ ካደረገ ጨዋታ ፈረሰ ማለት ነው፡፡ አንድ የአማራ ብሄረተኛ ስለራሱ ትውልድ ቦታ ብቻ የተለየ ስሜት ካለው እና ያንኑ ስሜቱን ሌሎቹም እንዲጋሩለት ከጠየቀ ይህ ሰው ትክክለኛ የአማራ ብሄረተኛ ነው ማለት አይቻልም፡፡ የሆነ አካባቢ ሰው ስለሆንኩ ብቻ ለአካባቢየ የተለየ ስሜት የሚሰማኝ ከሆነማ ሙሉ ኪሳራ ውስጥ ወደቅኩ ማለት ነው፡፡ አንድ የአማራ ብሄረተኛ የትም ይወለድ የትም አጀንዳው የግድ መላው አማራ ነው መሆን ያለበት፡፡ በአራቱ ግዛቶች፤ በሌላው ኢትዮጵያ እና በተቀረው አለም ተበትኖ የሚገኝ አማራ ሁሉ የእየለት ህይወቱ ሊያሳስበን እና በፍጹም አንድ እይታ ልንመለከተው ይገባል፡፡ አማራ ነኝ ስል የወሎም ሆነ የጎጃም ወይ የሸዋ አልያም የጎንደር ወይም በመላው አለም የተበተነው አማራ ህመም በእኩል ይሰማኛል ማለቴ ነው፡፡ በአማራ ብሄረተኝነት ውስጥ ሌላ ጭብጦ ይዞ መገኘት የብሄረተኝነቱ ነገር ያልገባው መሆንን ያመለክታል፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ክፍለ ሀገራዊ ስሜት ራሳቸውን ከየትኛውም ክፍለ ሀገር ጋር ማያያዝ የማይችሉትን የተበተኑ አማሮች ያገላል፡፡ ታዲያ አንዱን አማራ የበለጠ እያሰብኩለት ሌላውን ሆነ ብየ ከረሳሁት ምን ዋጋ አለው!
እንዲህ አይነት የአማራን ብሄረተኝነት ለራስ ትውልድ ቦታ እንዲያጎበድድ መጣር በንኡስ ብሄረተኝነት እንጅ በአማራ ብሄረተኝነት መነጽር ሊታይ የማይገባው ነው፡፡ አመክንዮው ራሱ የሚገርም ነው እኮ፡፡ ቀኃሥን መውደድ በምንም መንገድ ከአንድ አካባቢ ጠላትነት ጋር አይያዝም፡፡ አንድ ሰው ስለየትኛውም አካባቢ ችግር ምንም ሳያውቅ ንጉሱን ሊወድ ይችላል፡፡ ያ ማለት ሳያውቅ እንኳ በጠላትነት ሊያዝ ነው ማለት ነው፡፡ እንደዛማ ከሆነ በየቤቱ የቀኃሥ ፎቶ የሌለው የለም እና ንጉሱን እጅግ ብዙ አማራ ይወዳልና ንጉሱን መጥላት ስለማይቻል የአማራ ብሄረተኝነት ከነአካቴው መቅረት አለበት ማለት ሊሆን ነው እኮ፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ንኡስ ብሄረተኛነት ሌላ ንኡስ ብሄረተኝነትን ሊፈጥር እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እጅግ አጥብቄ የእኔ መንደር ባልኩ ቁጥር ሌላ የእኔስ መንደር የሚል ቡድን እየፈጠርኩ መሆኔን መረዳት ይገበኛል፡፡ በዛ ላይ ንጉሱ በጎም ሆኑ አልሆኑ ንጉሱ ላይ እጣት ከመቀሰር በፊት ንጉሱን እንዲህ ብል የእርሳቸው ደጋፊ ሊርቀኝ ይችላል፤ ብሄረተኝነቱም ሊጎዳ ይችላል ብሎ ማሰብም ያስፈልጋል፡፡
እንዲህ አይነቱ ንኡስ ብሄረተኝነት ጎጅ ነው፡፡ ምክንያቱም የብሄረተኝነት ዋና አላማው በማናቸውም ሰበብ ህዝቡን አንድ ላይ ማሰባሰብ እና አንድ አይነት ስሜት እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ እንዲህ አይነት የንኡስ ብሄረተኝነት አዝማሚያ ግን ህዝብን በአንድነት እንዳይቆም የመጋፋት አይነት ነገር ነው፡፡ በዛ ላይ ታሪክን ለመናቆሪያ መጠቀም የብሄረተኝነት ሌላው ተቃራኒ ጫፍ እንጅ ደጋፊ አይደለም፡፡ ከታሪክ ልንወስድ የሚገባው አንድነትን የሚያጎለብቱ እና የሚጠቅሙንን ብቻ ነው፡፡ ሌላውን በትምህርትነቱ እንይዘዋለን፡፡
ታሪክን በተመለከተ የአማራ ብሄረተኝነት በእውነት ላይ ብቻ መመስረት አለበት የሚለው አስተሳሰብ ስህተት ነው፡፡ በእርግጥ ብሄረተኝነት በእውነት ላይ ነው የሚገነባው፡፡ ያ ማለት ግን ብሄረተኝነት እንቅስቃሴ ፖለቲካ መሆኑን መርሳትን አያመለክትም፡፡ እውነት ብቻውን ፖለቲካዊ እቅስቃሴ ሊፈጥር አይችልም፡፡ እኛ የተያያዝነው የፍልስፍና ወይም የስነመለኮት ወይም የአካዳሚያዊ ታሪክ ትምህርት ክፍለጊዜን ማስፈን አይደለም፡፡ የአማራ ብሄረተኝነት ዋና አላማ ህዝብን በተገቢው ታሪካዊ ሀቆች ላይ በመመርኮዝ ለአንድ እጣ ፋንታ ማሰለፍ ነው፡፡ ታሪካዊ ጸጉር ስንጠቃውን ህዝባችን ነጻ ከወጣ በኋላ በመደበኛ የታሪክ ትምህርት ክፍለጊዜ እናስተምራለን፡፡ እውነትም ራሱ አንጻራዊ ነው እኮ፡፡ ቅንጭብ እውነት ይዘን የእውነት መጨረሻ ላይ የደረስንም ሊመስለን ይችላል፡፡ እውነትን ይዘን እንከራከር ብንል እንኳ እውነት በየደረስንበት የግንዛቤ ደረጃ ይወሰናልና እና ቋሚ መለኪያ አናገኝም፡፡ አንዱ እውነት ብሎ የያዘውን ሌላው በተጨማሪ እና ጥልቅ መረጃ ሊያፈርሰው ይችላል፡፡ ያም አለ ይህ የብሄረተኝነት አላማ እውነትና ሀሰት በሚል መነታረክ ሳይሆን ህዝብን በአንድነት ለተመሳሳይ አላማ ማቆም ነው፡፡ አማራ ህዝብ ትግል የህልውና መሆኑም መዘንጋት የለበትም፡፡
በአማራ ብሄረተኝነት ውስጥ የሞዐ አንበሣ አስተሳሰብ አያስፈልግም የሚል ደከም ያለ ነገርም ተጽፎ አይተናል፡፡ ቀኃሥን እንደሞዐ አንበሣ አድርጎ የማቅረብ ነገር ነው፡፡ ይን እንጅ ይህ የመረጃ እጥረት ነው፡፡ ቀኃሥ የሶሎሞናዊያን ስርዎ መንግሥት 225ኛ ንጉስ እንጅ ብቸኛ ንጉስ አይደለም፡፡ የሶሎሞናዊያን ስርወ መንግሥት ዋና አርማ ደግሞ ሞአ አንበሣ ነው፡፡ ስለዚህ ሞዓ አንበሳ በአርማነቱ የታሪካችን አካል እንጅ የአንድ ንጉስ ብቻ አሻራ አይደለም፡፡ ይሄንን ደግሞ መፋቅ አይቻልም፡፡
ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ የአማራ ጠላት ናቸው፡ አማራን ለማጥፋት ሰርተዋል የሚሉ ክሶችም ታይተዋል፡፡ እንግዲህ ቀኃሥ የአማራ ጠላት ናቸው፤ አማራን ሲያጠፉ ነው የኖሩ የሚለው ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው፡፡ እሳቸው እንደ አንድ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግስታዊ ሀላፊነቶችን ለሁሊም አካባቢ ለማዳረስ እና አገሪቷን ህዝቡ በአንድ ጥላነት እንዲቀበላት ጥረዋል፡፡ በተለየ ሁኔታ አማራን አጠፉ የሚለው አጉል ክስ ነው፡፡ በእርግጥ ተቀናቃኞቻቸውን አጥፍተዋል፡፡ ያ ደግሞ የፖለቲካው ባህርይ እንጅ የንጉሱ የተለየ አማራን የማጥፋት ፖሊሲ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፡፡ ደግሞም አማራን አጠፉ የሚለውን ቃል ለእኝ ንጉስ መስጠት ጨካኝነት ነው፡፡ የተወሰኑ ተቀናቃኞችን ማፈናቸው ወይም ማጥፋታቸው አማራን ማጥፋት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ በእርግጥ ስልጣናቸውን ለማማከል ወይም አሀዳዊ አገርን ለመፍጠር የየአውራጃና ጠቅላይ ግዛት ሹሞችን ሀይል አሳጥተው ማእከላዊ ጦር መስርተዋል፡፡ ይህ ሂደት እርሳቸው ያደረጉት ብቻ ሳይሆን ጣልያን በትልቁ አሻራውን ያሳረፈበት ነው፡፡ የየግዛት ሀይል ተዳክሞ በአንድ ማእከላዊ እዝ ስር የመውደቁ ሁኔታ ደግሞ የዘመኑ ሁኔታ ውጤት እንጅ የንጉሱ ብቻ መለኮት- መራሽ ስራ ውጤት አይደለም፡፡ እርሳቸውም እዛ ቦታ ላይ ባይሆኑ ሌላው ሊያደርገው የሚችለው ወይም በራሱ ጊዜ የሚሆን ክስተት ነው፡፡ የ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ በአማሮች የተከናወነ ነው፡፡ ያ ማለት ደግሞ ስልጣን ላይ አማሮች ነበሩ ማለት ነው፡፡ እንደጉድለት ከተቆጠረ ንጉሱ መኳንንትን ችላ በማለት ከተራው ህዝብ ወገን የሆኑ ሰዎችን ለወግ ለማእረግ አብቅተዋል፡፡ ግን አማራን ሆነ ብለው በደሉ የሚለው አያስኬድም፡፡
በመጨረሻም ነገስታቶቻችንን ከአማራ መነጠል ምን ጉዳት ያመጣል የሚለውን በቀጣይ የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (3) እንመለስበታለን፡፡
መለክ ሐራ

የአማራ ብሄርተኝነት በመለክ ሃራ (ሊነበብ የሚገባው)

ይህ ጽሁፍ የድንቁ ወንድማችን መለክ ሃራ ስጦታ ነው።እንግድህ ይሄን በትእግስ ማንበብ ፣መረዳት እና መተግበር የኛ ስራ ነው ። መልካም ንባብ
=======================================================
የአማራ ብሄረተኝነት መስመር.... (1)………ስለ አማራ ማንነት
**************************************************
የአማራ ብሄረተኝነት በአማራ ነገዳዊ ማንነት እና ፖለቲካዊ አካልነት ላይ ያጠነጥናል፡፡ ለዛሬ ነገዳዊ ወይም ብሄራዊ ማንነቱን ተንትነን በማየት ፖለቲካዊ ማንነቱን በይደር እናቆያለን፡፡
አማራ ስንል አማራ የሚባለውን ህዝብ ማለታችን ነው፡፡ ታዲያ አማራ መሆን እንደምንድነው ቢሉ በሁለት ይመደባል፡፡
አንደኛው በዝርያ አማራ የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ይመለከታል፡፡ ከጥንት የአማራ የዘር ሀረግ ያለው ህዝብ እና አማራ በመባል ሲጠራ የቆየው ህዝብ ማለት ነው፡፡ አማራ ስንል ሱዳን ያልሆነ፤ ጋምቤላ ወይም ጉምዝ ያልሆነ፤ ኦሮሞ ወይም ሱማሌ ያልሆነ፤ ትግሬ ወይም ኩናማ ያልሆነ ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ እና ከሌሎች አጎራባች ነገዶች አንጻር ሲታይ እነዚህን ያልሆነ ማለት ነው፡፡ በኢትዮጵያ 86 ብሄረሰቦች (ነገዶች) አሉ፡፡ 85ቱ አማራ አይደሉም፡፡ አማራ 85ቱን አይደለም፡፡ እነሱ አማራ አይደሉም፤ አማራም እነሱን አይደለም፡፡ ስለዚህ አማራ የብቻው የሆነ ነገዳዊ ማንነት አለው፡፡ ይህ ዘር ሀረጋዊ አማራነት “እኔ አማራ ነኝ” የሚል ገጽ ሲኖረው የዚህ “እኔ አማራ ነኝ” ሌላኛው ጎን ደግሞ “እሱ አማራ አይደለም” የሚል ገጽ ይፈጥራል፡፡ ይህም አማራ ከራሱ አንጻር የአማራን ማንነት ሲያመለክት፤ ከሌሎች አንጻርም እንደዛው አማራነቱን ያመለክታል፡፡ ለምሳሌ ዳንኤል ብርሀነ “እኔ ትግሬ” ነኝ ሲል በሌላ ገጹ “እኔ አማራ አይደለሁም” ወይም “እነ ተመስገን ደሳለኝ ትግሬ አይደሉም” ማለቱ ነው፡፡ ከትግሬ አንጻር ትግሬ ያልሆነ ሁሉ አማራ ነው፡፡ አዲስ አበባ ሲመጡ ነው ከአማራ ሌሎች ብሄረሰቦች እንዳሉ የሚያውቁት፡፡ በእነሱ አለም አለም የትግሬ እና የአማራ ተብላ በሁለት ትከፈላለች፡፡ ሌላውም ዘወር ዘወር ብሎ ሌሎችን እስካላየ ድረስ እንደዛ ነው የሚለው፡፡ ባጭሩ ትግሬ ያልሆነ ሁሉ አማራ ነው--ከትግሬ አንጻር፡፡ አማራ ደግሞ ትግሬዎችን ትግሬ እንጅ አማራ ናቸው ብሎ አይቆጥርም፡፡ ለአማራ ኦሮሞም ኦሮሞ ነው፡፡ ሱማሌም ሱማሌ ነው፡፡ ስለዚህ አማራ ራሱን አረጋግጦ የሚያቆምበት ነገዳዊ ቦታው አማራ ነው፡፡ ሌላው ትግሬ የሆነውን ያህል አማራም አማራ ነው፡፡ ይህ የዘር ሀረጋዊ አማራነት የስሜት ትስስርን አዳብሎ የያዘ ነው፡፡ “እኔ አማራ ነኝ” ሲል አንድ ሰው በአእምሮው የሚሳለው አማራ የተባለ አካል ነው፡፡ ያ አማራ የተባለ አካል አማራ የሆነበት እና ከሌሎች የሚለይበት ባህርያትን የያዘ ነው፡፡ አማራነቱን ሲያመለክት ወደአእምሮው የሚመጣ ቀድሞ የተሳለ ምስለ አማራ አለ፡፡ እኔ አማራ ነኝ ሲል ያንን ምስለ አማራ ማመልከቱ ነው፡፡ ይህም የዘር ሀረጋዊ እና የስሜት አማራነት ሌሎች ባህላዊ፤ ስነልቡናዊ፤ ስነልሳናዊ፤ ገጸ መሬታዊ እና ታሪካዊ እንዲሁም አኗኗራዊ መገለጫዎችን በውስጡ እንዳዘለ እንረዳለን፡፡
ሁለተኛው ባህላዊ አማራነት ነው፡፡ ከአማራ ህዝብ ጋር ለረዥም ጊዜ የኖሩ እና የአማራውን ስነልሳን፤ ስነልቡናና ባህርይ ሙሉ በሙሉ የወረሱ እናም ከአማራነት ውጭ በሆነ ሌላ መንገድ ራሳቸውን ሊገልጹ የማይችሉ ናቸው፡፡ እነዚህ በአመዛኙ የቅርብ ጊዜ ማለትም ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ በኋላ የመጡ ክስተቶች ናቸው፡፡ ያም ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ በተሰባጠረ መልኩ ከዳር እስከዳር ተንቀሳቅሶ መስራት እና የውትድርና አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የሌላ ብሄረሰብ አባላትም ወደአማራ አገር መጥተው መኖር እንደጀመሩ የሚታወቅ ነው፡፡ የእነዛ ሰዎች ልጆች እና የልጅ ልጆች አማራዊ ባህርይ የተላበሱ በመሆናቸው በራሳቸው ጊዜ አማራነትን ወስደዋል፡፡ ነገር ግን በቁጥር ደረጃ ከዋናው ከዘር ሀረጋዊው አማራ ጋር ሲነጻጸሩ እዚህ ግባ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ከአማራ አገር ውጭ በሆኑ ከተማ አካባቢዎች የተወለዱ እና በአማራው ባህላዊ መሰረት ታንጸው ያደጉ እና የአማራነትን ማንነት በራሳቸው ጊዜ የደረቡም አይጠፉም፡፡ የእነዚህ ቁጥር ግን ከ1983 ወዲህ ግልባጭ መልክ ይዞ ከአማራነት ሸሽተው ወደማለቁ ናቸው፡፡ ለምን ቢባል አማራ መሆን ጉዳት እንጅ ጥቅም እንደማያመጣላቸው ሲያውቁ በአማራነት የቀየሩትን የአያትና ወላጅ ማንነት እንደገና አንስተዋል ማለት ነው፡፡ በአማራ አገር ውስጥ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጀምረው የኖሩትም ከዚህ 1983 ወዲህ የአያት ቅድመ አያት ማንነታቸውን በመሻት አማራነትን ለጥቅም ሲሉ ለውጠዋል፡፡ ይህም እሳቤ ወደአንድ መደምደሚያ ያደርሰናል፡፡ እርሱም ዛሬ አማራ ነኝ ብሎ የሚኖረው ህዝብ ከሞላ ጎደል ዋናው የዘር ሀረጋዊ አማራ መሆኑ ነው፡፡ የባህል አማራዎች ሲሸሹት ማምለጫ የሌለው እውነተኛው አማራ በአማራነቱ ጸንቶ ተገኘ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን አማራ ስንል በዋነኝነት የአማራ ዘር (ስነፍጥረታዊ ህልውና) ማለታችን መሆኑ ከትክክልነትም ከፍ ያለ ነው፡፡
አማራነትን በሳንሳዊ መስፈርት መመዘን ይቻላልን?
አወ፡፡ በሚገባ እንጅ፡፡ አማራነት ዘር ሀረጋዊም ሆነ ባህላዊ ህልውና እንደሚኖረው ከላይ አይተናል፡፡ ባህላዊ አማሮች እየጠፉ ዘር ሀረጋዊ አማሮች ብቻ በአማራነታቸው መቅረታቸውንም አይተናል፡፡ አንድን ብሄር ብሄር የሚያደርገው ታዲያ ምንድነው ብልን ስንጠይቅ የሚከተለውን መስፈርት እናገኛለን፡፡
በታሪክ
አማራ በአማራነቱ እንደህዝብ የሚወክለው ታሪክ አለው፡፡ አማራ ለብቻው የሰራቸው እና ሌሎች ብሄሮች የማይጋሩት ታሪካዊ ሂደቶችና ስኬቶች አሉት፡፡ አማራ ራሱ ብቻውን በተዋናይነት የነበረበት ታሪክ ለረዥም ጊዜ ነበረ፡፡ ያ ታሪክ አማራን አንድ አይነት ምስል ይፈጥርለታል፡፡ ስለታሪክ ባወሳን እና ባሰብን ቁጥር የሆነ ምስለ አማራ በእዝነልቡናችን ይመጣል፡፡ ታሪክን ብቻውን ነጥለን ስንወስድ የሆነ የአማራ ምስል እናገኛለን ማለት ነው፡፡ ይህም በስነሰብ የሳይንስ ዘርፍ አንድን ብሄር ወይም ነገድ በነገድነት ከሚገልጹት ነገሮች አንዱ የጋራ የሆነ ታሪካዊ ሁነት ሲኖር ነው የሚለውን መስፈርት ያሟላል፡፡ የአማራን ታሪካዊ ሂደቶች፤ ድል እና ውድቀትም ጭምር ጨምቀን በመውሰድ አንዳች የአማራ ምስል እንፈጥራለን፡፡ ያ ታሪካዊ ሂደትም አማራን እንደህዝብ በአንድ አሃድ ይገልጸዋል ማለት ነው፡፡
በስነልቡናዊ-ማህበረሰባዊ ባህርይ
አማራ የራሱ የሆነ የጋራ ስነልቡናዊ ባህርይ አለው፡፡ ከሸዋ ሮቢት እስከ ገላባት፤ ከወልቃይት እስከ ባሌ ድረስ ብንሄድ አማራ አንድ አይነት ስነልቡናዊ ባህርይ ተላብሶ እናገኘዋለን፡፡ ይህም አንድ አይነት ስነልቡባዊ ባህርይ ከአማራነት የተወረሰ እና በትውልዶች መካከል ሲቀጥል የቆየ እና የሚቀጥል ነው፡፡ በርካታ ስነልቡናዊ ባህርያትን በመዘርዘር የአንዱ አካባቢ አማራ ከሌላው አካባቢ አማራ ፈጽሞ አንድ እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡ ይህም በስነሰብ የሳይንስ ዘርፍ አንድን ብሄር አንድ ከሚያደርጉት እና በብሄርነት ከሚገልጹት ነገሮች አንዱ የጋራ የሆነ ስነልቡናዊ-ማህበራዊ ባህርይ ነው የሚለውን ያሟላል፡፡ እንግሊዝኛው Common psychosocial makeup ነው የሚለው፡፡ ይህም ያ አንድ አይነት ስነልቡና የሚያጎናጽፈው አንድ አይነት ማህበራዊ ባህርይን የሚያመለክት ነው ማለት ነው፡፡ ከተመሳሳይ ስነልቡናዊ ባህርይ ተመሳሳይ ማህበራዊ ባህርይ ይፈጠርና ሁለቱ ተዳብለው አንድን ህዝብ ገላጭ አሀዶች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አማራ አንድ አይነት ስነልቡናዊ-ማህበረሰባዊ ህልውና አለው ማለት ነው፡፡ ይህንን አሀድ ነጥለን በመውሰድ ብቻ የአማራን አንጻራዊ ምስል መከሰት እንችላለን፡፡
በቋንቋ (ስነልሳን)
አማራ የራሱ የሆነ አንድ ቋንቋ አለው፡፡ እረሱም አማርኛ ነው፡፡ ስለዚህ በሳይንሱ አንድ አይነት ቋንቋ የሚናገር ህዝብ የራሱ የሆነ የብሄርነት ወይም የነገድነት ህልውና አለው የሚለውን ይህ አማርኛ ቋንቋ ይገልጸዋል፡፡ እዚህ ላይ በአማራ አገር ውስጥ ታዲያ ሌላ ቋንቋዎች አሉ እና እንዴት ነው ማብራራት የሚቻለው ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ አወ፡፡ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ አማሮች አሉ፡፡ ነገር ግን ሌሎች ቋንቋዎች በግንዱ አማራነት ውስጥ ንኡስ ቋንቋዊ ማንነትን ብቻ ይፈጥራሉ እንጅ በአጠቃላይ አማራነት ላይ ተጽእኖ አያመጡም፡፡ በሳይንሱ Dominant Culture and Subculture የሚባል ነገር አለ፡፡ ይህም ጽንሰ ሀሳብ የሚገልጸው በአንድ ግንድ ባህል ውስጥ ንኡሳን ባህላዊ እሴቶችም ሊኖሩ መቻላቸውን ነው፡፡ በእኛ ጉዳይ ግንዱ አማርኛ ቋንቋ ሲሆን ንኡስ ቋንቋዎች ደግሞ አማርኛ ያልሆኑቱ ናቸው፡፡ አማርኛ ለምን ግንድ ባህል ሆነ ተብሎ ቢጠየቅ ሁሉም ከአማርኛ ውጭ የሚናገሩ ሰዎች አማርኛን ይናገሩታል ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት በአማራ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ አንድ አይነት የጋራ ቋንቋ አለው ማለት ነው፡፡ ይህንንም ሳይንሱ እንደሚያስረግጠው አንድ ህዝብ የጋራ የሆነ አንድ ቋንቋ ካለው የብሄርነት ህልውናው የተረጋገጠ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በአማራ አገር ውስጥ ያለን ህዝብ በሞላ አማርኛ በጋራ ቋንቋነት ይገልጸዋል ማለት ነው፡፡ ይሄ ምናልባት በአማራ አገር ውስጥ ላሉ ንኡስ (መንደርተኛ) ፖለቲከኞች ላይዋጥ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ከአማራ ወጥቶ ወደኦሮሞ ወይም ወደትግሬ ወይም ወደሱማሌ ቢሄድ ያለ አንዳች ጥርጥር አማራ መሆኑ በእነዛ በእግዳ ሰዎች ይታወቃል፡፡ አንድ አማራ ወደእነዚህ ቦታዎች ሄዶ “እኔ እኮ አማራ አይደለሁም….እንትን ቋንቋ ተናጋሪ ነኝ” ቢል የሚያምነው የለም፡፡ “አንተ አማራ ነህ” ነው የሚባለው፡፡ ንኡስ ባህል ወይም ቋንቋ እዛው አማራ አገር ውስጥ ልዩነት ለመፍጠር ያገለግላል እንጅ ከአማራ አገር ሲወጣ ዜሮ ምስል ነው ያለው፡፡ ያ ሰው ከአማራ አገር ሲወጣ አጠቃላዩን የአማራ ምስል ይዞ ነው የሚወጣው፡፡ ስለዚህ የአማራ አገር ህዝብ አንድ የሆነ ቋንቋዊ ማንነት አለው ማለት ነው፡፡
በምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታና መንግስታዊ አመራር
አማራ እንደህዝብ በግብርና ላይ የተመሰረተ ኑሮ የሚኖር ህዝብ ነው፡፡ በአማራ ውስጥ ትላልቅ ቦታ ያላቸው ግብርናና መንግስታዊ አመራር ናቸው፡፡ በአማራ እዝነልቡና ከእያንዳንዱ ሰው በላይ መንግስት አለ፡፡ ህዝብን ያለመንግስት ማሰብ አይቻልም፡፡ ህግና ስርአት ከመንግስት ይመነጫል ብሎ ያምናል፡፡ በመሬት ላይ የተመሰረተውን ኑሮውን የሚቆጣጠርለትም ይሄው መንግስት ነው፡፡ አማራን ከመንግስትነት እና መሬት ጋር ካለው ልዩ ቁርኝት ተነስተን አንድ አይነት ምስለ አማራ ልንከስትለት እችላለን፡፡
በገጸ መሬታዊ አሰፋፈር
አማራ አንድ ወጥ እና ቅርጽ ያለው አሰፋፈር ያለው ህዝብ ነው-- የዛሬውን አሰፋፈሩን ስንመለከት፡፡ በታሪክ የራሱ የነበሩት እና በወራሪዎች የተዘረፉበትን ስንጨምርም ከሞላ ጎደል Compact የመሬት ገጽ ላይ የሰፈረ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አማራ በተለየ አንድ ላይ ይኖር የነበረ እና አንድ አይነት ብቻ አሰፋፈራዊ እጣ ፋንታ የነበረው ህዝብ ነው፡፡ ለምሳሌ ትግሬ በሁለት አገሮች ውስጥ ይገኛል፡፡ አፋርም በሶስት አገሮች ውስጥ ይገኛል፡፡ ኦሮሞ ከአራት በላይ በሆኑ አገሮች ውስጥ ይገኛል፡፡ ጋምቤላም በሁለት አገሮች ውስጥ ይገኛል፡፡ አማራ ግን በኢትዮጵያ ብቻ እንጅ በሌላ በየትም አገር አይገኝም፡፡ ይህም ማለት ለረጅም ዘመናት አንድ ላይ ሰፍሮ የኖረ ህዝብ ነው ማለት ነው፡፡ ለረጅም ዘመናት አንድ ላይ በመኖሩም ከላይ የተዘረዘሩትን የጋራ የሆኑ ታሪካዊ ሁነት፤ ስነልቡናዊ-ማህበራዊ ባህርይ፤ እና ስነልሳናዊ እሴት በጋራ አበልጽጎ ኖረ፤ በእነሱም በአንድ ወጥ ህዝብነት ይገለጻል እንላለን፡፡ በዚህም አመክንዮአዊ መስመር ስንሄድ የአማራ አንድነት ከአሰፋፈር ሁኔታውም ጋር የተያያዘ ነው እና ይህ አሰፋሩ ለሌሎች ምስለ አማራ ከሳች መለያዎች መሰረት ነው ልንል እንችላለን፡፡
መለክ ሐራ
===================================================
የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (2: ታሪክ በብሄረተኝነት መነጽር*********************************************************

በተደጋጋሚ ከፋም ለማም የአማራ ታሪክ የአማራ ነው፤ ከሁለቱም በኩል ትምህርት ብቻ ነው መውሰድ ያለብን እያልን ለማስገንዘብ ስንሞክር ቆይተናል፡፡ አንድ ነገር በግድ መታወቅ አለበት፡፡ ታሪክን ለመናቆሪያነት መጠቀም ካሰብን ዘለአለም ስንጨቃጨቅ መኖር እንችላለን፡፡ ማለትም ላለመስማማት ከፈለግን መቸም አንስማማም፡፡ ይህም የሚሆነው በሶስት ምክንያቶች ነው፡፡ አንደኛ ያለፈውን ታሪክ ሙሉ ስእል ማግኘት ስለማንችል እና የምንመረኮዝባቸው ሀቆች በሙሉ ሊደርሱን ስለማይችሉ፡፡ ሁለተኛ የአለፈን ጊዜ በአሁን ጊዜ መመንዘርና መፍረድ በአመዛኙ ስህተት በመሆኑ እና ብዙዎቻችን ለዚህ ሰለባ ስለምንሆን፡፡ ሶስተኛ በታሪክ ውስጥ ሆነ ተብሎም ይሁን ሳይተሳብበት የተሰሩ ስህተቶች የግድ አይቀሬ ስለሆኑ፤ ማለትም ታሪክን የሚሰሩት የሰው ልጆች በመሆናቸው ሰውን የሚያጋጥመው ውስንነትና ስህተት ታሪክ ላይም የግድ ስለሚንጸባረቅ፡፡ ስለሆነም ስለታሪክ ስንነጋር እነዚህን ነገሮች በቅድሚያ ግምት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅብናል፡፡ ይህም የአማራን ታሪክ እና አሁን ከጀመርነው የብሄረተኝነት እንቅስቃሴ ጋር አዋህደን ለማራመድ ይጠቅመናል፡፡ ይህ ጽሁፍ በአመዛኙ ሰሞኑን ፌቡ ላይ ሲንሸራሸሩ ለነበሩ ሚዛናዊ ያልሆኑ እይታዎች እንደመልስነት የታሰበ ነው፡፡
ከዚህ በፊት የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (1) ላይ የአማራ ማንነት ተገልጹዋል፡፡ የአማራ ታሪክ ተዋናዮች የሆነው ህዝብ በተለይም በታሪክ ላይ ሰፍረው የሚገኙት መሪዎችም ማንነታቸው ከዚሁ ከተጠቀሰው ሳይንሳዊ እሳቤ የሚወጡ አይደሉም፡፡ የአማራን ማንነት በቅጡ ካለመረዳታችን የተነሳ ይሄ ንጉስ አማራ አይደለም፤ ያ ንጉስ እትን ነው እያልን የራሳችንን ታሪክ ስንሸረሽር እንታያለን፡፡ መጀመሪያ አንድን ንጉስ ወይም ገዥ አማራ ነው ወይስ አይደለም ከማለታችን በፊት ስለአማራ ማንነት በጥቂቱም ቢሆን ማወቅ አለብን፡፡ የብሄረተኝነት እንቅስቃሴን እደግፋለሁ ወይም ቅርጽ እሰጠዋለሁ የሚል ሰው በመጠኑም ቢሆን ስለማንነት እንቅስቃሴዎችና መሰረቶች ማወቅ አለበት፡፡ ብሄረተኝነትን ለመቅረጽ መጀመሪያ ራስን ሰፋ አድርጎ መቅረጽ ያስፈልጋል፡፡ ይህ የተባለበት ምክንያት የብዙዎቹ ሰዎች ጽሁፎች ስህተት ወይም እውነት ናቸው ለማለት ሳይሆን የምንናገረው እውነትስ ሆነ ስህተት የተያያዝነውን የማንነት ፖለቲካ እንዴት ባለ መንገድ እና ሁኔታ እንደሚጠቅመው እና እንደሚጎዳው በደምብ እንዲታሰብበት ለማመላከት ነው፡፡
የብሄረተኝነት እንቅስቃሴ የወደፊት እቅድን የሚቀርጽ ሂደት ስለሆነ የወደፊቱን ለመቅረጽ የኋላ መነሻ ያስፈልገዋል፡፡ ብሄረተኝነት እንቅስቃሴዎች እንኳን ያለውን ታሪክ የሌለ አዲስ ነገር ይፈጥራሉ፡፡ የሰውን ቀልብ ማሰባሰብ እና ለአንድ አላማ አሰልፎ ግብን መጨበጥ የሚቻለው በሆነ አንኳር ወይም በሆኑ አንኳር ታሪካዊ ክስተቶች ዙሪያ ነው፡፡ ታሪክ በብሄረተኝነት እንቅስቀሴ ውስጥ እንደንብ አውራ (ንግስት) ነው፡፡ አውራው ወይም ንግስቲቷ የሌለችበት ንብ ይበተናል፡፡ ምክንያቱም አብሮ የሚያኖር ምክንያት ስለሌለው፡፡ እንደዚሁም የብሄረተኝነት እንቅስቃሴ አንድ ላይ አያይዞ ለአንድ ግብ የሚያሰልፍ ታሪክ ያስፈልገዋል፡፡ ከዚሁም በላይ የተጋጋለ ብሄረተኝነት ለማካሄድ የህዝቡን ያለፈ ታላቅነት መንገር የግድ ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ ያለበት ቦታ ላይ ሊወድቅ እንደማይገባው ደጋግሞ መንገር እና ያለፈው ትልቅነቱ እንዲናፍቀው ማድረግ ያሻል፡፡ ብሄረተኝነት የዛሬው ያለንበት ሁኔታ ውድቀት ነው ብሎ ነው የሚነሳው፡፡ ወደፊት ታላቅ ለመሆን መጀመሪያ ከታላቅነት መውደቅን ማመን ያስፈልጋል፡፡
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የሚወድ የእንትን ጠላት ነው ብለው የሚጽፉ ውስን ሰዎች አሉ፡፡ እንደአስተያየት ይከበርላቸዋል፡፡ ግን ነገርየው የማይጠቅም እና የእይታ ችግርን የሚያመለክት ነው፡፡ ንጉሱ እገሌን ግዛት በድለዋል ብሎ የሚያስብ ሰው እንደዛ ቢያስብ አይገርምም፡፡ በደል ከተባለ እንግዲህ ንጉሱ ላይ ሁሉም የሚነቅፍባቸው ይኖራል፡፡ እንግዲህ ዝም ተብሎ ሲታይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ነገስታት የሚጠቀስ ጉድለት ይኖርባቸዋል፡፡ እነዛን ጉድለቶች ወይም አሉ የተባሉ ጉድለቶች ጠምዝዞ ለራስ አላማ ማዋል ግን ስህተት ነው፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የሚወድ የእንትን ጠላት ነው የሚለው ሀሳብ ግን እንደቀላል መታየት የሌለበት ነው፡፡ አንድ ሰው የአማራ ብሄረተኝነትን እደግፋለሁ ብሎ ሲያበቃ እንደገና ራሱን ከመላው አማራ ነጥሎ የተወሰነ አካባቢ ጠበቃ ካደረገ ጨዋታ ፈረሰ ማለት ነው፡፡ አንድ የአማራ ብሄረተኛ ስለራሱ ትውልድ ቦታ ብቻ የተለየ ስሜት ካለው እና ያንኑ ስሜቱን ሌሎቹም እንዲጋሩለት ከጠየቀ ይህ ሰው ትክክለኛ የአማራ ብሄረተኛ ነው ማለት አይቻልም፡፡ የሆነ አካባቢ ሰው ስለሆንኩ ብቻ ለአካባቢየ የተለየ ስሜት የሚሰማኝ ከሆነማ ሙሉ ኪሳራ ውስጥ ወደቅኩ ማለት ነው፡፡ አንድ የአማራ ብሄረተኛ የትም ይወለድ የትም አጀንዳው የግድ መላው አማራ ነው መሆን ያለበት፡፡ በአራቱ ግዛቶች፤ በሌላው ኢትዮጵያ እና በተቀረው አለም ተበትኖ የሚገኝ አማራ ሁሉ የእየለት ህይወቱ ሊያሳስበን እና በፍጹም አንድ እይታ ልንመለከተው ይገባል፡፡ አማራ ነኝ ስል የወሎም ሆነ የጎጃም ወይ የሸዋ አልያም የጎንደር ወይም በመላው አለም የተበተነው አማራ ህመም በእኩል ይሰማኛል ማለቴ ነው፡፡ በአማራ ብሄረተኝነት ውስጥ ሌላ ጭብጦ ይዞ መገኘት የብሄረተኝነቱ ነገር ያልገባው መሆንን ያመለክታል፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ክፍለ ሀገራዊ ስሜት ራሳቸውን ከየትኛውም ክፍለ ሀገር ጋር ማያያዝ የማይችሉትን የተበተኑ አማሮች ያገላል፡፡ ታዲያ አንዱን አማራ የበለጠ እያሰብኩለት ሌላውን ሆነ ብየ ከረሳሁት ምን ዋጋ አለው!
እንዲህ አይነት የአማራን ብሄረተኝነት ለራስ ትውልድ ቦታ እንዲያጎበድድ መጣር በንኡስ ብሄረተኝነት እንጅ በአማራ ብሄረተኝነት መነጽር ሊታይ የማይገባው ነው፡፡ አመክንዮው ራሱ የሚገርም ነው እኮ፡፡ ቀኃሥን መውደድ በምንም መንገድ ከአንድ አካባቢ ጠላትነት ጋር አይያዝም፡፡ አንድ ሰው ስለየትኛውም አካባቢ ችግር ምንም ሳያውቅ ንጉሱን ሊወድ ይችላል፡፡ ያ ማለት ሳያውቅ እንኳ በጠላትነት ሊያዝ ነው ማለት ነው፡፡ እንደዛማ ከሆነ በየቤቱ የቀኃሥ ፎቶ የሌለው የለም እና ንጉሱን እጅግ ብዙ አማራ ይወዳልና ንጉሱን መጥላት ስለማይቻል የአማራ ብሄረተኝነት ከነአካቴው መቅረት አለበት ማለት ሊሆን ነው እኮ፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ንኡስ ብሄረተኛነት ሌላ ንኡስ ብሄረተኝነትን ሊፈጥር እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ እጅግ አጥብቄ የእኔ መንደር ባልኩ ቁጥር ሌላ የእኔስ መንደር የሚል ቡድን እየፈጠርኩ መሆኔን መረዳት ይገበኛል፡፡ በዛ ላይ ንጉሱ በጎም ሆኑ አልሆኑ ንጉሱ ላይ እጣት ከመቀሰር በፊት ንጉሱን እንዲህ ብል የእርሳቸው ደጋፊ ሊርቀኝ ይችላል፤ ብሄረተኝነቱም ሊጎዳ ይችላል ብሎ ማሰብም ያስፈልጋል፡፡
እንዲህ አይነቱ ንኡስ ብሄረተኝነት ጎጅ ነው፡፡ ምክንያቱም የብሄረተኝነት ዋና አላማው በማናቸውም ሰበብ ህዝቡን አንድ ላይ ማሰባሰብ እና አንድ አይነት ስሜት እንዲኖረው ማድረግ ነው፡፡ እንዲህ አይነት የንኡስ ብሄረተኝነት አዝማሚያ ግን ህዝብን በአንድነት እንዳይቆም የመጋፋት አይነት ነገር ነው፡፡ በዛ ላይ ታሪክን ለመናቆሪያ መጠቀም የብሄረተኝነት ሌላው ተቃራኒ ጫፍ እንጅ ደጋፊ አይደለም፡፡ ከታሪክ ልንወስድ የሚገባው አንድነትን የሚያጎለብቱ እና የሚጠቅሙንን ብቻ ነው፡፡ ሌላውን በትምህርትነቱ እንይዘዋለን፡፡
ታሪክን በተመለከተ የአማራ ብሄረተኝነት በእውነት ላይ ብቻ መመስረት አለበት የሚለው አስተሳሰብ ስህተት ነው፡፡ በእርግጥ ብሄረተኝነት በእውነት ላይ ነው የሚገነባው፡፡ ያ ማለት ግን ብሄረተኝነት እንቅስቃሴ ፖለቲካ መሆኑን መርሳትን አያመለክትም፡፡ እውነት ብቻውን ፖለቲካዊ እቅስቃሴ ሊፈጥር አይችልም፡፡ እኛ የተያያዝነው የፍልስፍና ወይም የስነመለኮት ወይም የአካዳሚያዊ ታሪክ ትምህርት ክፍለጊዜን ማስፈን አይደለም፡፡ የአማራ ብሄረተኝነት ዋና አላማ ህዝብን በተገቢው ታሪካዊ ሀቆች ላይ በመመርኮዝ ለአንድ እጣ ፋንታ ማሰለፍ ነው፡፡ ታሪካዊ ጸጉር ስንጠቃውን ህዝባችን ነጻ ከወጣ በኋላ በመደበኛ የታሪክ ትምህርት ክፍለጊዜ እናስተምራለን፡፡ እውነትም ራሱ አንጻራዊ ነው እኮ፡፡ ቅንጭብ እውነት ይዘን የእውነት መጨረሻ ላይ የደረስንም ሊመስለን ይችላል፡፡ እውነትን ይዘን እንከራከር ብንል እንኳ እውነት በየደረስንበት የግንዛቤ ደረጃ ይወሰናልና እና ቋሚ መለኪያ አናገኝም፡፡ አንዱ እውነት ብሎ የያዘውን ሌላው በተጨማሪ እና ጥልቅ መረጃ ሊያፈርሰው ይችላል፡፡ ያም አለ ይህ የብሄረተኝነት አላማ እውነትና ሀሰት በሚል መነታረክ ሳይሆን ህዝብን በአንድነት ለተመሳሳይ አላማ ማቆም ነው፡፡ አማራ ህዝብ ትግል የህልውና መሆኑም መዘንጋት የለበትም፡፡
በአማራ ብሄረተኝነት ውስጥ የሞዐ አንበሣ አስተሳሰብ አያስፈልግም የሚል ደከም ያለ ነገርም ተጽፎ አይተናል፡፡ ቀኃሥን እንደሞዐ አንበሣ አድርጎ የማቅረብ ነገር ነው፡፡ ይን እንጅ ይህ የመረጃ እጥረት ነው፡፡ ቀኃሥ የሶሎሞናዊያን ስርዎ መንግሥት 225ኛ ንጉስ እንጅ ብቸኛ ንጉስ አይደለም፡፡ የሶሎሞናዊያን ስርወ መንግሥት ዋና አርማ ደግሞ ሞአ አንበሣ ነው፡፡ ስለዚህ ሞዓ አንበሳ በአርማነቱ የታሪካችን አካል እንጅ የአንድ ንጉስ ብቻ አሻራ አይደለም፡፡ ይሄንን ደግሞ መፋቅ አይቻልም፡፡
ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ የአማራ ጠላት ናቸው፡ አማራን ለማጥፋት ሰርተዋል የሚሉ ክሶችም ታይተዋል፡፡ እንግዲህ ቀኃሥ የአማራ ጠላት ናቸው፤ አማራን ሲያጠፉ ነው የኖሩ የሚለው ውንጀላ መሰረተ ቢስ ነው፡፡ እሳቸው እንደ አንድ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግስታዊ ሀላፊነቶችን ለሁሊም አካባቢ ለማዳረስ እና አገሪቷን ህዝቡ በአንድ ጥላነት እንዲቀበላት ጥረዋል፡፡ በተለየ ሁኔታ አማራን አጠፉ የሚለው አጉል ክስ ነው፡፡ በእርግጥ ተቀናቃኞቻቸውን አጥፍተዋል፡፡ ያ ደግሞ የፖለቲካው ባህርይ እንጅ የንጉሱ የተለየ አማራን የማጥፋት ፖሊሲ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፡፡ ደግሞም አማራን አጠፉ የሚለውን ቃል ለእኝ ንጉስ መስጠት ጨካኝነት ነው፡፡ የተወሰኑ ተቀናቃኞችን ማፈናቸው ወይም ማጥፋታቸው አማራን ማጥፋት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡ በእርግጥ ስልጣናቸውን ለማማከል ወይም አሀዳዊ አገርን ለመፍጠር የየአውራጃና ጠቅላይ ግዛት ሹሞችን ሀይል አሳጥተው ማእከላዊ ጦር መስርተዋል፡፡ ይህ ሂደት እርሳቸው ያደረጉት ብቻ ሳይሆን ጣልያን በትልቁ አሻራውን ያሳረፈበት ነው፡፡ የየግዛት ሀይል ተዳክሞ በአንድ ማእከላዊ እዝ ስር የመውደቁ ሁኔታ ደግሞ የዘመኑ ሁኔታ ውጤት እንጅ የንጉሱ ብቻ መለኮት- መራሽ ስራ ውጤት አይደለም፡፡ እርሳቸውም እዛ ቦታ ላይ ባይሆኑ ሌላው ሊያደርገው የሚችለው ወይም በራሱ ጊዜ የሚሆን ክስተት ነው፡፡ የ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ በአማሮች የተከናወነ ነው፡፡ ያ ማለት ደግሞ ስልጣን ላይ አማሮች ነበሩ ማለት ነው፡፡ እንደጉድለት ከተቆጠረ ንጉሱ መኳንንትን ችላ በማለት ከተራው ህዝብ ወገን የሆኑ ሰዎችን ለወግ ለማእረግ አብቅተዋል፡፡ ግን አማራን ሆነ ብለው በደሉ የሚለው አያስኬድም፡፡
በመጨረሻም ነገስታቶቻችንን ከአማራ መነጠል ምን ጉዳት ያመጣል የሚለውን በቀጣይ የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (3) እንመለስበታለን፡፡
መለክ ሐራ
===================================================
የአማራ ብሄረተኝነት መስመር (3): ነገስታቶቻችንን ከአማራነት መነጠል ምን ጉዳት ያመጣል?
******************************************************************

አንድ የአማራ “ተቆርቋሪ” ሰው በተደጋጋሚ አጼ ቴዎድሮስ “ቅማንት” ናቸው ብሎ ይናገራል፤ ኧረ እንዲያውም ይህንኑ ኑፋቁ በጥራዝ መልኩ ጸፎአል አሉ፡፡ ታዲያ አንዲት አማራ ትበሳጭና እስኪ ማስረጃ ትለዋለች፡ እርሱም እግዜርን ሳይፈራ ሰውንም ሳያፍር “የታንጉት ምስጢር” ላይ ነው ያነበብኩት ይላል፡፡ ይህ ሰው አጼ ቴዎድሮስን ቅማንት ለማድረግ የታንጉት ምስጢርን ምስክር መጥራቱ ብቻ አይደለም ችግሩ፡፡ ትልቁ ችግር ይህንን መጽሀፍ አለማንበቡ ነው፡፡ ሶስተኛው ችግር ደግሞ አጼ ቴዎድሮስን ቅማንት ናቸው ሲል አማራን እና ቅማንት አማራን አራርቆ ለማስቀመጥ መሞከሩ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ አጼ ቴዎድሮስ ቅማንት ናቸው የሚለው በራሱ ችግር አልነበረውም፡፡ ችግሩ ያለው በውስጡ ካዘለው ጸረ አማራ ፖለቲካዊ አጀንዳ ላይ ነው፡፡ እንጅማ ቅማንት አማራም ሆነ አማራ ያው አማራ ነው፡፡) ሌላኛው ችግር ደግሞ ለኢትዮጵያ ሲባል የአማራን ታሪክ ለማይፈልጉት ሁሉ መወርወር እና አማራን ታሪክ አልባ አድርጎ የማስቀረቱ ዘመን ያስቆጠረ ልማድ ቀጣይ ክፍል አራማጅ መሆኑ ነው፡፡ እግዜር ያሳያችሁ! ሌሎች ብሄሮችን ታሪክ እንዲሰሩ እና ከአማራ ጋር እንዲስተካከሉ ማድረግ ሲገባ የአማራን ዘርፎ አማራን ባዶ አድርጎ እነዛን ያልሰሩቱኑ ባለታሪክ ማድረግ! ይህንን የሚገልጽ አንድ ሌላ አማራዊ ገጠመኝ፡፡ በ1996 ዓ.ም. አማራ ከ8ኛ ክፍል በኋላ መማር የለበትም ተብሎ ፖሊሲ ወጥቶ ነበር፡፡ እስከ 8ኛ ክፍል ይማራሉ፤ ከዛ ወዲያ የራሳቸው ጉዳይ፡፡ ኦቦ አዲሱ ለገሰ ለምን እንዲህ ይደረጋል ተብሎ ተጠይቆ ሲመልስ “አማራ ከዚህ በፊት ስለተማረ ከሌሎች ጋር ለማስተካከል ነው” አይነት ንግግር ተናገረ፡፡ ገራሚ፡፡ ሌሎችን በማስተማር ከአማራ ጋር ማስተካከል ነው ወይስ አማራውን እንዳይማር ማድረግ ነው የሚገባው? ግን ቅንጅት መጥቶ የአማራን ወጣት ከዛ መከራ አተረፈው፡፡ ቅንጅት ለአማራ የዋለው ውለታ በዚህ ረገድ የሚረሳ አይደለም መቸም፡፡
ወደጥንተ ነገራችን እንመለስ፡፡ አንድ የብርሀኑ ዘርይሁን ጓደኛ የነበረ ሰው ብርሀኑ የታንጉት ምስጢርን እንዴት እንደጻፈው አጫውቶኝ ነበር፡፡ ብርሀኑ የታንጉት ምስጢርን ሲጽፍ የአዲስ ዘመን ስራ አስኪያጅ ነበር አለ፡፡ አንድ ጠረጴዛ ላይ በአንድ እጁ የታንጉት ምስጢርን ሲከትብ፤ በሌላ ወገን ተስተናጋጅ እና የስራ ባልደረቦች ስራ ሲሰጡት ደብተሩን እያጠፈ፤ እንደገና ስራና ሰው ቀለል ሲልለት ገልጦ እየጻፈ፤ እንደገና እየተዋከበ ነው የጻፈው አለ፡፡ ይህ ጓደኛየ ለብርሀኑ ዘሪሁን ያለውን አድናቆት ተናግሮ አይጠግብም፡፡ ብርሀኑ የታንጉት ምስጢርን በጻፈበት ውክቢያ ሁኔታ አይደለም መጽሀፍ የጋዜጣ አምድ ማዘጋጀት ፈታኝ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡ ለዚህ ጓደኛየ ብርሀኑ በቃ ብርቱ ሰው ነው፡፡ እና በዛ ወከባ ውስጥ ሆኖ የጻፈው መጽሀፍ እስከዛሬም ድንቅ ነው፡፡
ያው እንግዲህ መጽሀፉ ታሪካዊ ልቦለድ ነው፡፡ ታሪካዊ ልቦለድ በመሰረታዊ ጭብጥነት ታሪክ እና አፈ ታሪክ ላይ የሚመረኮዝ ቢሆንም በደራሲው ምናባዊ ተጽእኖ ስር ስለሚወድቅ ለታሪክ ማጣቀሻነት አይውልም፡፡ እንዲህ አይነቱ ድርሰት ደራሲው ተጨባጭ ታሪኮችን እና አፈ ታሪኮችን ልብ አንጠልጣይ በሆነ ሁኔታ የሚጽፍበት እንጅ የታሪክ ሰነድ አገላብጦ ማጣቀሻ አስቀምጦ እውነትን ብቻ የሚያስቀምጥበት አይደለም፡፡
ያም ሆኖ የታንጉት ምስጢር ውስጥ ላይ አጼ ቴዎድሮስ ቅማንት ናቸው የሚል አይገኝም፡፡ መጽሀፉ ራሱ የታንጉት ምስጢር የተባለበት ምክንያት የአጼ ቴዎድሮስ አባት ታንጉትን ከቅማንት አማራ መውለዳቸው እና በኋላም ይህችን ታንጉትን ወንድምዋ አጼ ቴዎድሮስ ለታማኛቸው ፊታውራሪ ገብርየ ሚስት አድርገው ማጋባታቸው እና በጋብቻውም ፍሬ ማፍራት ባለመቻላቸው አሁንም ቅድምም “ኧረ ባባጃሌው” የምትለዋ ወፍራም ሴትዮ (ስሟን ረስቸዋለሁ) ታንጉትን በመጀመሪያ ጭልጋ ወይኒ ኪዳነምህረት ጸበል መውሰድዋ (ይህ የወይኒ ኪዳነ ምህረቱ የጸበል ጉዳይ በአቤ ጉበኛ “አንድ ለእናቱ” መፅሀፍ ላይም በስፋት መገለጹ ይታወሳል)፤ በጸበል አልሳካ ሲል አምባ ጊዮርጊስ በሚስጢር ከአንድ የቆሎ ተማሪ ጋር እንድትተኛ ተደርጎ መጸነሱዋን እና ያንንም ወፍራሟ ሴት እና ታንጉት የገብርየ ልጅ ነው ብለው የማሳመናቸውንና የመሳሰለውን ውስብስብ የመንግስት ፖለቲካ ለማስረዳት ነው፡፡ የአጼ ቴዎድሮስ እህት ታንጉት በአንድ ወገን ከቅማንት አማራ ትወለዳለች፡፡ ነገር ግን አጼ ቴዎድሮስ እህቱ ቅማንት አማራ በመሆኑዋ ብቻ ቅማንት ነው ብለው የሚከራከሩ የአማራ “ተቆርቋሪዎች” ስናገኝ ያለንበት ዘመን እውነትም 8ኛው ሽህ መሆኑን በደምብ እንገነዘባለን፡፡ እዚሁ መጽሀፍ ላይ ፊታውራሪ ገልሞ የሚባል በጣም ጀግና ቅማንት አማራ ነበር፡፡ አጼ ቴዎድሮስ ይህንን ጀግና ሰው “ምነው ሁሉም ቅማንት እንዳንተ በሆነልኝ” እያሉ ያንቆለጳጵሱት እንደነበር ብርሀኑ ጸፎአል፡፡ የማንቆለጳጰሱ ነገር የደራሲው ምናብ ይሁን እውነታ ወደጎን እንተወው እና ፊታውራሪ ገልሞ የሚባል በጣም ጀግና ቅማንት አማራ ከአጼ ቴዎድሮስ ጎን ከእነ ራስ እንግዳ እና ፊታውራሪ ገብርየ ጋር ተሰልፎ እንደነበረ ግን በታሪክ የሚታወቅ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ እስካሁን ድረስ አንድም አማራ ራሱን በፌስቡክ ራስ እንግዳ ብሎ በማስታወሻነት አለመሰየሙ አሳዝኖኛል)፡፡ አጼ ቴዎድሮስን ሀበሻ በሙሉ ከድቶ ከንጉሱ ጎን እስከመጨረሻው በታማኝነት ከቆሙት 5000 ወታደሮች አንዱ እና በጦርነቱም ለሚወደው ንጉስ እና ለቆመለት አላማ የተሰዋ ጀግና ነውና…. ራስ እንግዳ፡፡ ባጭር አገላለጽ ቅማንት አማራ የተበታተነውን አማራ ለማሰባሰብ በተደረገው እልህ አስጨራሽ የጀግንነት ስራ ከአጼ ቴዎድሮስ ጎን ሆኖ በህዝብ ሰብሳቢነት እና አገር አንድ አድራጊነት ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡
እንግዲህ አማራ ላለፈው ግማሽ ክፍለዘመን DeAmharization Process ውስጥ ያለ ህዝብ ነው፡፡ አማራን በዚህ ኢ-አማራ ማድረግ ሂደት ውስጥ የተሳተፉት በሚያሳዝን ሁኔታ አማራ ያልሆኑቱ ብቻ አይደሉም፡፡ አማሮቹ ራሳቸው በስፋት ተሳትፈውበታል፤ አሁንም እየተሳተፉበት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊያንን በስሜትም በግብርም እንደ አንድ ሰው አሳቢ እንደ አንድ ልብ መካሪ ለማድረግ የእያንዳንዱን ብሄራዊ ማንነት ማጥፋት መልካም ሊመስል ወይም ሊሆን ይችላል፡፡ ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ለጋዜጠኛ ዘነበ ወላ እንዳለው ፈረንሳዮች ኦምሌት ለመስራት እነቁላሉን መስበር ያስፈልጋል ይላሉ፤ አጼ ምኒልክም ኢትዮጵያን ለመፍጠር ወይም ኦምሌት ለመስራት እንቁላሉን መስበር ነበረባቸው፤ አጼ ምኒልክ እንቁላሉን ባይሰብሩት እና አማርኛን ባይሰጡን ኖሮ አንተ ከጋሞ እኔ ከትግራይ በምን እንግባባ ነበር ብለውት!
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሁሉም እንቁላሎች ተሰብረዋል ማለት አይቻልም፡፡ ሌሎች እንቁላሎች እንዳሉ ሆነው አማራ ብቻ ተሰብሮ በስብርባሪው ሌሎችን እንቁላሎች እንዲያጣብቅ ነው የተደረገው፡፡ አማራ ተሰብሮ ሌላው ሳይሰበር የተሰራውም ኦምሌት ዛሬ የሌሎች አለመሰበር ህልውና እየተላወሰ እያየን ነው፡፡ የእነሱ ህልውናም አማራውን ጨርሶ ለማጥፋት ደርሷል፡፡ አሁን የተያያዝነው ሌሎችን እስከህይወታቸው ለማቆየት የተሰበረውን እንቁላል፤ አማራን፤ እንደገና መጠገን እና በብዙ ድካም ወደነበረበት መመለስ ነው፡፡ ኢትዮጵያን እንደ አገር እንደገና ለማቆም አማራ ብዙ ጊዜ ሲጨፈለቅ እና ሲሰባበር ነው የቆየው፡፡ በኋላም አማራ ማንነቱን ረስቶ ለኢትዮጵያዊነት ሲለውጥ ሌሎች ግን ስላልተሰባበሩ በነበሩበት ቆዩ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያዊነት ፕሮጀክት ሲጀመርም ሁሉንም ማንነቱን አሳጥቶ አንድ የማድረግ ሂደትን ያልተከተለ ነበር፡፡ ውጤቱንም አሁን እያየነው ነው፡፡ ያለፉት መሪዎቻችን፤ ልሂቃን እና አሁን ያለው ልሂቅ አማራን ብቻ ማጥፋት ኢትዮጵያን ይገነባል ወይም አጣብቆ ያቆያል ብለው ያስባሉ፡፡ በጣም ስህተት፡፡ ይህ ግን በአማራ ሞት ላይ ለሌሎች ያልተሰበሩ እንቁላሎች ህይወት መስጠት ነው፡፡ አማራ እየተሰባበረ ሌላው ግን ሲፈለፈል ቆይቷል፡፡ ስለሆነም አንዲት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የተደረገው ሂደት እና አሁንም እየቀጠለ ያለው ጥረት በአማራ ኪሳራ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፡፡ ለአማራ ጎጅ ነው፡፡ አማራ ብቻውን ለምን ይሰበር!?
ስለዚህ ሚዛናዊ ባልሆነው እንቁላል ሰበራ የተዳከመውን የአማራነት ስሜት ለማጠናከር እየጣርን ባለንበት በአሁኑ ሰአት የተዘረፈብን እና እየተዘረፍብን ያለውን ታሪክ አለምንም መታለል እና መዘናጋት ማስመለስ ወይም መመለስ አለብን፡፡ አማራነታችን ለሌሎች የመስዋእት በግ ሆኖ በነጻ እንደታደለው ሁሉ የአማራ የሆነው ነገር ሁሉ እንዲሁ በገፍ ተዘርፏል፡፡ ከላይ የኦቦ አዲሱ ለገሰ ምሳሌነት እንደሚያስረዳው አይነት ነገር ነው አማራ እና አማራነት እንዲሁም የአማራ የሆነው ሁሉ ላይ እየተካሄደ ያለው፡፡ በጣም በሚያናድድ መልኩ እኛም ራሳችን ሳናውቅ ወይም በግብዝነት ይህንን የአማራ የሆነውን ሁሉ ፍቆ የማጥፋት እና ለሌሎች የመሸለሙ ስራ ላይ በአጋዥነት ስንሰራ እንታያለን፡፡
ከላይ በአጼ ቴዎድሮስ ላይ የቀረበው የታንጉት ምስጢር አይነት ምስክር በአጼ ምኒልክና በአጼ ኃይለ ሥላሴ ላይ በስፋት ሲንጸባረቅ ይታያል፡፡ ለምሳሌ በመግቢያየ የጠቀስኩት የአማራ “ተቆርቋሪ” አጼ ምኒልክን እና አጼ ኃይለ ሥላሴን ከአማራነት ፍቆ ለሌላ አስረክቧል፡፡ ያው ማስረጃው መሰለኝና ደሳለኝ ቢሆንም ቅሉ! ማን ይሰማዋል! በተመሳሳይ እዚሁ ፌስቡክ ላይ በአማራ ብሄረተኝነት አምናለሁ የሚል ራሱን ካይማር ሠርፀ ድንግል ብሎ የሚጠራ ሰው አጼ ኃይለ ሥላሴን አማራ አይደሉም ብሏል፡፡ በጣም የሚገርመው ይህ ሰው ጉራጌን አማራ ነው ብሎ ያምናል፡፡ በዚህ ሰው አባባል ለምሳሌ በቅርቡ ብርጋዴር ጀኔራል ተስፋየ ሀብተማርያም ጉራጌ አማራ ሲሆን ከወሎ የተወለደውን የሻእብያና ኦነግ መጠቀሚያ የነበረውን ዋለልኝ መኮንንን በበረራ ልዩ ሀይልነቱ መግደሉን አወድሶ ጽፎአል፡፡ ነገር ግን አጼ ሀይለስላሴ አማራ አይደሉም የሚባልበት ምክንያት አንዱ ጉራጌ ደም አላቸው የሚለው ነው፡፡ ጉራጌን አማራ ያለ ሰው ታዲያ ከጉራጌ እና አማራ ተወለደ የተባለን ንጉስ እንዴት ብሎ ነው አማራ አይደለም የሚለው!!!!? በነገራችን ላይ አጼ ኃይለ ሥላሴ የጉራጌ ደም አላቸው የሚለውን በቂ ማስረጃ የለኝም፡፡ እንደማስረጃ የምጠቅሰው የታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌን “ነጻነትን የማያውቁ ነጻ አውጭዎች”ን ነው፡፡ ታጋይ አንዳርጋቸው እዛ ላይ ቃል በቃል “በአጼ ምኒልክና አጼ ኃይለ ሥላሴ የደም ቧንቧ ከሚፈሰው የአማራ ደም ይልቅ የኦሮሞና ጉራጌ ደም ይበልጣል” ብሏል፡፡ ከየት እንዳገኘው አላውቅም፡፡ ይሁንና ይህም አባባል የተጠቀሰው ኢ-አማራ የማድረጉ ሂደት (DeAmharization Process) አንዱ አካል ነው፡፡
እንግዲህ ጉራጌ፤ ሀድያ፤ ከምባታና አደሬ በኦሮሞ ወረራ ከጥፋት ከተረፉት የጥንት የአማራ ክፍሎች የሚጠቀሱ መሆናቸው አያከራክርም፡፡ አጼ ምኒልክም ሆኑ አጼ ሀይለ ሥላሴ የጉራጌ ደም ቢኖራቸው አማራነታቸው እንደተጠበቀ ነው፡፡ እንደዋዛ መታለፍ የሌለበት ግን እነዚህ ነገስታት የኦሮሞ ደም አላቸው የሚለው የክህደት ነገር ነው፡፡ አጼ ምኒልክ የኦሮሞ ደም አላቸው የሚለው ነጭ ውሸት ነው፡፡ የዘር ሀረጋቸውን የንጉሱ ጸሀፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ “ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ” በተሰኘው መጽሀፋቸው በተገቢው ዘርዝረው ጽፈውታል፡፡ እዛ ላይ መመልከት ነው፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ ኦሮሞ ደም አላቸው የሚለው በጥልቀት መታየት አለበት፡፡ እንደሚባለው በአያታቸው ከሀረር ኦሮሞ ይወለዳሉ ነው፡፡ መልካም፡፡ ነገር ግን ኦሮሞ በሁለት ይከፈላል፡፡ ኦሮምኛ ተናጋሪ አማራ እና ኦሮሞ ተብሎ (ቢያንስ ከዚህ ጽሁፍ አንጻር)፡፡ እንደሚታወቀው የሀረር ኦሮሞ ኦሮምኛን ለረዥም ጊዜ በመናገሩ ወደኦሮሞነት የተቀየረ የጥንት አማራ ነው፡፡ ይህንን መሰል ጉዳይ የጀነቲክስ (ዘረመል) ጥናቶች እያፍታቱት ነው፡፡ ለወደፊቱም ኦሮምኛ በመናገር ብቻ ኦሮሞ መስሎት የሚኖረውን የጥንት አማራ ወገናችንን በዚህ መሰል ሳይንሳዊ ዘዴ ነው ወደቀደመ አማራ ማንነቱ የምንሰበስበው፡፡ ይህም ማለት አጼ ኃይለ ሥላሴ በአያታቸው ኦሮሞ ናቸው ቢባል እንኳ በዚህ መንገድ ኦሮምኛ በመናገር ላይ ከሚገኝ ከጥንት አማራ የተወለዱ አማራ ናቸው ማለት ነው (He descends from a culturally Oromo but a genetically Amhara population)፡፡ ስለዚህ አጼ ኃይለ ሥላሴ አማራ ብቻ ናቸው፡፡
ቢባል ቢባል እና አጼ ኃይለ ሥላሴ ኦሮሞ ደም አላቸው ብንል እንኳ ሊሆኑ የሚችሉት በአንድ አያታቸው ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት 75% አማራ ናቸው ማለት ነው፡፡ በጀነቲክ ሳይንስ ደግሞ 25% is recessive while 75% is dominant gene. ይህ ማለት 25 ከመቶው ጅን በ75 ከመቶው የተሸፈነ ወይም ዋና ያልሆነ፤ የዘር ሀረግን በዋናነት ማስተላለፍ የማይችል፤ ለራሱ የተወሰነ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው 75 ከመቶው የወረሰበትን ወላጅ ዘር ሙሉ በሙሉ ይይዛል ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ግማሹ ወይም 50 ከመቶው አማራ ቢሆን እንኳ አማራ ነው እንኳን 75 ከመቶው! እንዳለመታደል ግን ለግማሽ ክፍለ ዘመን ከዘለቀው የኢ-አማራ ማድረግ ሂደት የተነሳ አማራን ኦሮሞ ለማድረግ 25 ከመቶ በቂ ነው፡፡ 75ን ለ25 በግድ እጁን ጠምዝዞ ማስረከብ! በእናንተ በራሳችሁ ክርክር እንኳ 75 ከመቶ የሆነን ሙሉ አማራ ለ25 ከመቶው አሳልፋችሁ ለመስጠት የምትንጦለጦሉ አማራ ተብየዎች ማፈር አለባችሁ፡፡ ያም አለ ይህ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከፍ ዝቅ የሌለባቸው አማራ ናቸው፡፡ እዚህ ጋር የተጠቀሰው ጀነቲክ ማብራሪያ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ደግሞ ንጉሱ በባህል ሙሉ በሙሉ አማራ ናቸው፡፡ ማለትም አንድን ህዝብ ከዘሩ በተጨማሪ አማራ የሚያደርገው ሳይንሳዊ የባህል ማብራሪያ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ፤ አንድም ሳያጓድሉ የያዙ ንጉስ ናቸው፡፡ ኧረ በበለጠ ሁኔታ፡፡
በነገራችን ላይ ካይማር እና አክናሁስ “አጼ ሀይለ ስላሴ በታሪክ ፊት ብላችሁ” ስለፓኪስታን ምናምን የምትዘባርቁትን ሀሜት አይቸዋለሁ፡፡ ያው ሀሜት ከሀሜትነቱ አይዘልም…ታውቃላችሁ ወይም ታውቃለህ፡፡ የፓኪስታኑ ጉዳይ አስጨንቆኝ ሳይሆን አንድ ምክር ለመለገስ ነው ያንን ትርኪ ምርኪ ሀሳባችሁን ያነሳሁት፡፡ ይህንን ሀሳብ የሚያራምዱትን ዋነኞቹን የጀርመን ፕሮፌሰሮች አውቃቸዋለሁ፡፡ እዛ ትግራይ አካባቢ ያስተምራሉ፤ ሪሰርች ይሰራሉ፡፡ ለአማራ ያላቸው ክፉ አመለካከት ግን ከአንድ የአድዋ ተወላጅ ወያኔ ቢብስ አንጅ አያንስም፡፡ አንዱ በተለይ ትግሬን ደግፎ እዚህች አገር ላይ ለደረሰው ችግር ሁሉ አማራን ተጠያቂ አድርጎ የሚከራከር ነው፡፡ ስለፓኪስታኑ ጉዳይ ሲያራግብ ማስረጃ አምጣ ስለው ንጉሰ ራሳቸው የጻፉት ጽሁፍ ላይ የሆነ ፎቶ አይቸ ምናምን ነው የሚለው፡፡ ሌላም የሚዘባርቀው ነገር አለ፡፡ ግን አላማው የወያኔን ጸረ አማራ ስራ ማገዝ ነው፡፡ ይህንን ስላችሁም ዝም ብየ አይደለም፡፡ የጀርመን ምሁራን ለኦነግ፤ ሻእብያና ወያኔ በትጥቅ ትግል ወቅት የፕሮፓጋዳ ድጋፍ ያደርጉ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ዘነበ ፈለቀ “ነበር” ብሎ በጻፈው መጽሀፍ ውስጥ ደርግ ሁለት የደህንነት ሰራተኞችን ወደምእራብ ጀርመን መላኩን፤ የደህንነቶችም ተልእኮ አንድ የሸማቂዎች ዋና ሰውን ለመግደል እንደነበረ፤ ነገር ግን አንደኛው ደህነነት ቦምቡን በመጽሀፍ መልክ ለማጥመድ እየሰራ በነበረበት ጊዜ ሌላኛው ደህንነት ውጭ ቆይቶ ድንገት ወደክፍላቸው ሲገባ ሳያስበው ቦምቡን ነክቶት መፈንዳቱን፤ ያንንም ተከትሎ ይህንን ከፍንዳታ የተረፈ ደህንነት የምእራብ ጀርመን የደህነነት ሰራተኛ አይኑን ደንቁሎ አውጠቶ ጥሎት ወደአዲስ አበባ መመለሱን እንደጻፈ ነገርኩት፡፡ ይህም ፕሮፌሰር “ደርግ የላካቸው እነዛ ደህንነቶች ማንን ለመግደል እንደነበር አውቃለሁ፤ ለተቃዋሚዎች የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ ያደርግ የነበረን ጓደኛየን ለመግደል ነበር” ብሎ ነገረኝ፡፡ እና ምን ማለት ፈልጌ ነው፡- አጼ ኃይለ ሥላሴን ኢ-አማራ ማድረግ ወይም አማራ ላይ መዝመት የዚህ አገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን አለማቀፍ ተልእኮም አካል ነው እያልኳችሁ ነው፡፡ ሀሜትን እንደማስረጃ በማቅረብ ወይም ማረጋገጥ የማትችሉትን ወሬ በማዛመት አማራነታችንን ከመጉዳት እንድትታቀቡ ለማሳሰብም እወዳለሁ፡፡
ከላይ በተጠቀሰው መልኩ እየተደረገ ያለው ነገስታቶቻችንን ኢ-አማራ ማድረግ ምን ጉዳት ያመጣል የሚለውን እንመልከት፡፡ አማራ የሆኑትን ነገስታቶቻችን አማራ አይደሉም ስንል ብዙ ነገር እናጣለን፡፡ ዋና ዋናዎቹም አምሐራ ነጻ ህዝብ ነው ስንል አማራ ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘመነ ቅኝ ግዛት ድረስ በማንም ተገዝቶ አያውቅም ማለታችን ነው፡፡ በአለም ደረጃ ቅኝ ያልተገዛች ኢትዮጵያ ሲባል የዚህ ድል ዋናው ተዋናይ አማራ ነው፡፡ የማእከሉ ማእከል ላይ ደግሞ አማራ ነገስታት ይገኛሉ፡፡ አጼ ቴዎድሮስ አማራን በማሰባሰባቸው በኋላ የመጡትን ወራሪዎች በአንድነት እንዲመክት እድል አመቻቹ፡፡ ይህንን አጼ ቴዎድሮስ የሰበሰቡትን እና በሀይለኛ ክንድ ደቁሰው አንድ ያደረጉትን አማራ በመጠቀም ዳግማዊ ምኒልክ የበለጠ በማጠናከር የመከላከያ ወረዳቸውን አስፋፉበት፤ የተወሰደውንም መሬት መለሱበት፡፡ የመከላከያ ወረዳ ማስፋት ምን ማለት ነው? ንጉሱ የጥንት ግዛታቸውን ከማስመለስ ባለፈ ዙሪያቸውን በስፋት ከያዙበት ምክንያቶች አንዱ ቅኝ ገዥዎች ምናልባት ወደመሀል እንምጣ ቢሉ እዛው በረዥም ዳርቻ ለመከላከል በማሰብ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ ከጅቡቲ ወይም ሀርጌሳ ተነስቶ የሚመጣ ሀይል መሀል ኢትዮጵያ ወይ አማራ ላይ ከመድረሱ በፊት መከላከል ይቻላል፡፡ በጋምቤላም በሩዶልፎ (ደቡብ፡ ኬንያም) እንዲሁ ነው፡፡ ይህን የተስፋፋ የመከላከያ ወረዳ በመጠቀም እና ሰፊው ግዛት የፈጠረውን አቅም በመጠቀም በወራሪዎች ላይ አለም አቀፍ ድል ተጎናጸፉ፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴም በበኩላቸው ከዚህ ታላቅ ንጉስ የተረከቡትን አገር እና ነጻነት ለማስጠበቅ በነፍጥ ተፋልመዋል፡፡ አልሆን ሲልም ወደ ውጭ ሄደዋል፡፡
እዚህ ላይ ንጉሱ ወደውጭ መሄዳቸውን እንደሽሽት የሚቆጥሩ አሉ፡፡ ይህ ግን ውሀ የማያነሳ ክርክር ነው፡፡ አምባሳደር ብርሀኑ ድንቁ “ቄሳርና አብዮት” በተሰኘች መጽሀፉ ይህንን ነገር በሚገባ አብራርቶታል፡፡ ብርሀኑ ድንቄ ለመከራከሪያነት ያቀረባቸው ጭብጦች የአጼ ኃየለ ሥላሴን ከአገር መውጣት እና የአጼ ቴዎድሮስን መቅደላ ላይ መሰዋት ነው፡፡ እንደ ብርሀኑ ድንቄ አባባል ለአንድ አይዲያሊስቲክ ኢትዮጵያዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ማይጨው ላይ ራሳቸውን ማጥፋት ነበረባቸው፤ ራሳቸውን ቢያጠፉ ትክክል ናቸው፡፡ በሌላ ጎኑ ለአንድ ፕራግማቲክ ሰው አጼ ኃይለ ሥላሴ ሁኔታው እንደማይሆን ሲያውቁ አገር ለቀው መሰደዳቸው ተቀባይነት አለው፡፡ እዚህ ጋር ክርክሩ በአይዲያሊስት እና ፕራግማቲስት ተቃርኖዎች ላይ ነው፡፡ ማለትም አንድ አይዲያሊስት የአጼ ኃይለ ሥላሴን ድርጊት ኮንኖ ሊከራከር ይችላል፡፡ በሌላ ወገን አንድ ፕራግማቲስት ግን የንጉሱን ድርጊት ደግፎ ሊከራከር ይችላል፡፡
በአጭር አገላለጽ ምን ማለት ነው፡- ንጉሱ መሰደዳቸው ተጨባጭ ለውጥ አምጥቶአል፡፡ ንጉሱ እዛው ላይ ሞተው ቢሆን እና ጣልያን ተቆጣጥሮን ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ወይም የአማራ ነጻ ህዝብነት ወይም አምሐራነት አከተመ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ንጉሱ በመሰደዳቸው የኢትዮጵያ ስልጣነ መንግስት አብሮ ተሰደደ ማለት ነው፡፡ ያ ማለት የኢትዮጵያ መንግስት ከአገሩ ተሰዶ በሌላ አገር በስደተኝነት ቀጥሎ ነበር ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ንጉሱ አገራቸውን እንጅ ስልጣናቸውን አልተቀሙም፡፡ ዙፋናችንም አልተወገደም፡፡ ንጉሱ በስደት መንግስታቸውን ይዘው በመሰደዳቸው ኢትዮጵያ በጣልያን ስር ሆናም የመንግስትዋ ህልውና አላከተመም ነበር፡፡ ይህ በራሱ ትልቅ ጥቅም አምጥቷል፡፡ ንጉሱ በስደት ሆነው ዲፕሎማሲያዊ ትግል በማድረግ የአላይድ ፓወርስ ድጋፍ ማግኘት ችለዋል፡፡ ያም ድጋፍ በኋላ ከአርበኞች ትግል ጋር ተደማምሮ በስደት የነበረውን መንግስት ተመልሶ በቦታው እንዲተከል አድርጎታል፡፡ አገር ውስጥ ይደረግ የነበረው የአርበኝነት ትግልም ይህንን የንጉሱን ዲፕሎማሲያዊ ትግል ለማገዝ ረድቶአል፡፡ እዚህ ላይ የንጉሱን ዲፕሎማሲያዊ ትግልና ያም ትግል ያስገኘውን አለማቀፍ ድጋፍ ለማሳነስ ሲል አርበኞች ነጻ ሊያወጡን ይችሉ ነበር ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ እኔ ግን የአርበኞች ትግል ብቻውን ነጻነታችንን ያጎናጽፈን ነበር ብየ ለማሰብ ይከብደኛል፡፡ በምንም መልኩ የአርበኞች ተጋድሎ ወደር የለሽ መሆኑ የታመነበት ነው፤ ይሁንና የንጉሱ ዲፕሎማሲያዊ ትግል የላቀውን ሚና ተጫውቷል ብየ አስባለሁ፡፡ ለምሳሌ Michela Wrong “I didn’t Do It For You” በተባለው መጽሀፏ ውስጥ የንጉሱ ቀኝ እጆች የነበሩት የሲልቪያ ፓንክረስት ቤተሰቦች በተለይም ሲልቪያ ፓንክረስት የነበራትን ተደማጭነት በመጠቀም በየአገሩ እየዞረች ለንጉሱ ድጋፍ ታሰባስብ ነበረች፡፡ የድጋፉም አይነት የዲፕሎማሲ እና የገንዘብ ነበር፡፡ በዚህም ብዙ እንግሊዛዊያንን እና ከዛም አልፎ ሌሎች አውሮፓዊያንን ከንጉሱ ጎን ማሰለፍ ችላለች፡፡ ግን ደርግ ንጉሱን ለማጥላላት ብዙ ሰርቷል፡፡ የዛም ክፉ ፕሮፓጋንዳ ቅሪት በወያኔ ህይወት ተዘርቶበት ወደራሳችን ወገኖችም ተጋብቶ እስከዛሬ ድረስ አለ፡፡
ስለዚህ የነገስታቶቻችን አማራነት ከጣልን አምሐራ ነጻ ህዝብ ነው የምንለውን አብረን መጣል አለብን፤ ኢትዮጵያ ወይም አማራ ቅኝ አልተገዙም የሚለውን መወርወር አለብን፤ የጥቁር ዘር አንጸባራቂ የሆነ አለማቀፍ ድል ሲያደርግ ዋነኛው ህዝብ አማራ እና መሪዎቹ አማራ ነገስታት መሆናቸውንም መጣል አለብን፤ እነደአማራነታችን የወረስነውን አኩሪ ገድል ሁሉ አብረን መጣል አለብን ማለት ነው፡፡ አንዱን የአማራነት አሻራ ስንጥል ሁሉንም እየጣልን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ በራሳችን ነገስታት ላይ ስንዘምት በራሳችን ላይ እየዘመትን መሆናችንን እንገንዘብ፡፡ አማራነታችንን ሌሎች የሚሸራርፉት እና የሚያጠፉት ይበቃል፡፡post Amhara rise
መለክ ሐራ [Melek Hara] Thank you the Enlightened

Saturday, 25 June 2016

አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” የህወሃት ነፍጠኞች

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት

ogaden 4
የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡
ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል)
“በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላogaden 1 የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ ከተናገረችው፡፡
የሚዲና የዕርዳታ ሥራዎችን የሚያካሂዱ ሁሉ ወደ ኦጋዴን እንዳይገቡ በህወሃት ትዕዛዝ ተደርጎባቸው ባለበት ባሁኑ ወቅት በኦጋዴን የሚካሄደው ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፤ እስር፣ እንግልት፣ ወከባ፣ … በድብቅ ቀጥሏል ይላል ጋዜጠኛ ግራሃም፡፡
ዘጋቢ ፊልሙን ለመሥራት መረጃው የተሰበሰበው ከሚሊታሪው የኮበለሉና ሌሎች ለህይወታቸው ያልሳሱ ደፋሮች በሰጡት ምስክርነት ነው፡፡ በተለይም ከኢትዮጵያ ኮብለለው በቅርቡ ኬኒያ ልትዘጋው ወደ ወሰነችው የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ሦስት ሴቶች የህወሃት ሠራዊት ስላደረሰባቸው መከራ፣ ሥቃይና አስገድዶ መድፈር ተግባራት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ወደ ዳዳብ በግንቦት 2006ዓም የመጣችው ሚሪያም ለሁለት ዓመት ተኩል እንዴት እንደተሰቃየች፣ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ እንዴት እንደተፈጸመባት ትናግራለች፤
“እንደ ማሰቃያ ይሆን ዘንድ እስኪደክመኝ ድረስ ሬሣ አቅፌ እንድቆም ተደርጌአለሁ፤ ከዚያም ሚጥሚጣ የሞላበት ላስቲክ በራሴ ላይ አስረውብኛል፤ ገመዱን ሲያስሩት አጥብቀው ከአንገቴ ጋር በማሰራቸው ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር፡፡ ከዚያ ለብዙ ሆነ እየተፈራረቁ አስገድደው ደፈሩኝ …”ogaden 10
“ኦጋዴን በሚገኘው እስርቤት 1097 የምንሆን ነበርን፤ ቁጥሩን በትክክል አውቀዋለሁ ምክንያቱም በየቀኑ ማለዳ ላይ እያሰለፉ ከቆጠሩን በኋላ በቡድን በቡድን እያደረጉ ይከፋፍሉን ነበር፤ …
“(የተያዝን ጊዜ) እህቴን ጉሮሮዋን አንቀው መረጃ አምጪ አሏት፤ ምንም እንደማታውቅ ብትነግራቸውም አልሰሟትም፤ ከሌሎቻችን ጋር ተቀላቅላ እንድትቀመጥ አደረጓት ከዚያም ሁላችን እያየን አራት ቤቶቻችን አቃጠሏቸው፤ ቤቱን እያቃጠሉ እህቴን ከመካከል ነጥለው ግምባሯ ላይ በጥይት መቷት፤ እህቴን እስከሞት ስትደማ አየኋት፤ ከእርሷ አጠገብ ሌላ ሴት ልጅ በድብደባ ብዛት ሞታ ነበር፤ ከዚያም እኔን ሬሣ ባለበት ጉድጓድ ውስጥ ጣሉኝ፤ በዚያ ጉድጓድ ውስጥ አራት ቀንና አራት ምሽት አሳለፍኩ፤ ጥፋተኛ መሆኔን እንድናዘዝ ምርመራ ይካሄድብኝ ነበር፤ አለበለዚያ መጨረሻዬ እንደ ሬሣው እንደሚሆን ይነግሩኝ ነበር፤ እኔም ምንም የምናዘዘው የለኝም የምታርዱኝ ከሆነ እረዱኝ አልኳቸው፤ (ጉድጓድ ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ) ከሬሣው መካከል አንዱ ጉሮሮው ታርዶ፤ አንገቱም በዱልዱም ነገር ተቆርጦ ጭንቅላቱ እዚያው የቀረው አካሉ ጎን ነበር፤…”
በመስከረም 2007ዓም ወደ ዳዳብ ካምፕ የመጣቸው አናብ ደግሞ “የኢትዮጵያ ሠራዊት በጅምላ ከገደሉ በኋላ በጅምላ የሚቀብሩበትን ቦታ በመደበቅ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ አንዳንዶቹ መቼም አይገኙም፤ አንዳንዶቹ ግን በቁሻሻ ጉድጓዶች ውስጥ ተገኝተዋል” ትላለች፡፡
በእርሷ ላይ የደረሰውን በተመለከተ ስትናገር አናብ እንዲህ ትላለች፤ “ወደ እስር ቤት ተወስጄ በሽቦ ታነቅሁኝ፤ ይህ ዓይነቱን ተግባር በተደጋጋሚ ሲፈጽሙ ቆይተው በኋላ እስርቤት ተዉኝ፤ በተያዝኩ ጊዜ ከፊት፥ ከኋላና ጭኔ ላይ በጎማ ጠፍር ገርፈውናል፤ ከእኔ ጋር የተያዙ አምስት ልጃገረዶች ነበሩ፤ ከተያዙት ውስጥ ትልቋ 19ዓመቷ አካባቢ ነበር፤ ትንሽዋ ደግሞ ወደ 15ዓመት አካባቢ ነበረች፤ በተያዝንበት ወቅት ልጆቹን ክፉኛ ሲደበድቧቸውና በሰደፍ ሲመቷቸው አይቻለሁ፤ ልብሳቸውንም ቀዳድደውባቸው ብጣቂ እራፊ አድርገው ተመልሰዋል፤ ይህንን በየጊዜው የሚያደርጉት ተግባር ነው፤ …Ogaden 11
“መረጃ እንድንሰጣቸው በየጊዜው ይመረምሩን ነበር፤ ሴቶችን ‘አስገድደን እንደፍራችኋለን’ እያሉ ያስፈራራሉ፤ ‘አንደፈርም’ ብለው አሻፈረን የሚሉትን ደግሞ ያንቋቸዋል፤ ሴቶቹ ራሳቸውን ስተው ባሉበት ወቅት እንኳን ይደፍሯቸዋል … እኔ የታሰርኩበት ትንሽ ክፍል ውስጥ ሰባት ሴቶች ነበሩ፤ ከዚያ ክፍል ነጻ የተለቀቀ የለም ማለት ይቻላል፤ ከእኛ በፊት እዚያ ክፍል የነበሩት ታርደዋል፤ ሌሎቹም በረሃብ እንዲሞቱ ተደርገዋል፤ ሬሣቸውንም በየጉድጓዱ ወርውረውታል፤ እኛ የነበርንበት ክፍል ሬሣ ነበር፤ የክፍሉን ሁኔታ ማንም ሊገምት የሚችል አይደልም (መግለጽ አይቻልም)፤ በክፍሉ የነበረው ሬሣ ባብዛኛው የወጣት ወንዶች ነው፤ እስከ አራት ቀናት ሬሣው በክፍሉ እንዲቆይ ይደረጋል፤ ከዚያ አውጥተው በየቦታው፤ በየመንገዱ ይወረውሩታል፤ …”
እንደ ሚሪያም በግንቦት 2006 ዓም ወደ ዳዳብ የመጣችው ፋጡማ “ወታደሮቹ እናንተ የኦጋዴንን ሰዎች እናጠፋችኋለን፤ ምንም ዓይነት ነዋሪ እዚህ አካባቢ አንፈልግም፤ እንጨርሳችኋለን” ይሉናል፡፡ “እስርቤት ሳለሁ አንቀውኝ ነበር፤ በሳንጃም ወግተውኛል፤ በየጊዜው መላ አካላቴን ደብድበውኛል፤ ጭንቅላቴን በኤሌትሪክ ጠብሰውታል፤ የማያደርጉት ዓይነት ስቃይ የለም …” በማለት ምሬት እና ሰቆቃ በተሞላበት ድምጽ ምስክርነቷን ስትሰጥ ትደመጣለች፡፡ ኦብነግ በአካባቢው እንዳለ እና ሠራዊቱ አንድ መቀመጫ ቦታ እንደሌለው፤ በተገኘው አጋጣሚ ወደ ሰፈር እንደሚመጡ እና የሚፈልጉትን እንደሚያገኙ ፋጡማ ትናገራለች፡፡Ogaden 12
ህወሃት በበረሃ በነበረበት ጊዜ ተጋዳላዮቹ በየምሽቱና በየሌሊቱ ወደ መንደራቸውና ሰፈራቸው በሚመጡበት ጊዜ የትግራይ እናቶች ልጆቻቸውን ምግብና መጠጥ እያሲያዙ፤ ስንቅ እንየቋጠሩ ይልኩ ነበር አቶ ስዬ አብርሃ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ እንዲያውም የራሳቸውን እናት ጠቅሰው ብዙዎችን ይመግቡ እንደነበርና ለበርካታ ተጋዳላዮች “እናት” እንደነበሩ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በህወሃት አዛዥነት ወደ ሥፍራው የተላከው ሠራዊት አስገድዶ መድፈር አንዱ የጥቃት መሣሪያው ነው፡፡ በወታደራዊ ሠፈሮች ውስጥ ሴቶች ለወሲብ መገልገያ ሆነዋል፤ ከሚደርስባቸው ሰቆቃ በተጨማሪ በተደጋጋሚ በበርካታዎች ይደፈራሉ በሚለው የግራሃም የቪዲዮ ዘገባ ላይ የስቃይ እንባ የምታፈሰውን ሚሪያም “በተደጋጋሚ ተደፍሬአለሁ፤ ድርጊቱ መደበኛ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳ ተቀበልነው” ስትል ያሳያል፡፡ “ብዙዎች በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፤ አንዳንዶችም የሚጥል በሽታ ይዟቸዋል ሌሎችም እውር ሆነዋል፤ እኔም ራሴ ከደረሰብኝ ስቃይና ድብደባ የተነሳ አሁን እየተሻለኝ ቢሆንም የጡንቻ መኮማተርና የሚጥል በሽታ ይዞኛል፡፡”
የኦጋዴን ጭፍጨፋ መሃንዲሱና ጀማሪው ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ነው፡፡ የሙት ውርስ እንጠብቃለን የሚሉት አወዳሾቹም በሙት መንፈስ እየተመሩ ግፉን ቀጥለውበታል፡፡Ogaden 13
የኢትዮጵያን ስም ይዞ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የዘመተው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሠራዊት ኦጋዴን በደረሰበት ጊዜ የፈጸመውን እማኞቹ በግልጽ ያስረዳሉ፡፡ “የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ይሁኑ ወይም ልዩ ፖሊስ እኔ አላውቅም” የምትለው ፋጡማ ሰፈሮቻቸው በወራሪው ሠራዊት ከተከበበ በኋላ ከብቶቻቸው፤ ግመሎቻቸው፤ … በአጠቃላይ ንብረታቸው እንደተዘረፈ ትናገራለች፡፡ ከሁለቱ ሴቶች ጋር በመስማማትም ወንዶች እየተነጠሉ እንደተገደሉ ታስረዳለች፡፡ በተለይ የተማሩ የሚባሉ የኦጋዴን ወጣቶችን እየለዩ እንደገደሉ የሟች ቤተሰብ የሆኑት እነዚህ እህቶች በቃለምልልሱ ላይ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ሁልጊዜ የሚባሉትም “አንዳችሁንም አናስተርፍም፤ እንጨርሳችኋልን” መሆኑን ግፍ፤ እልህና ሲቃ በሞላው ድምጽ ይናገራሉ፡፡ ዘጋቢ ፊልሙ ላይ በተሰጠው መረጃ መሠረት ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ግዢው ህወሃት በልዩ ሁኔታ ያሰለጠናቸው በትምህርት ያልታነጹ፤ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የሌላቸውና ከወሮበላ የማይተናነስ ባህርይ ያላቸው ጨካኝ ፓራሚሊታሪዎች እንደሆኑ ያስረዳል፡፡
ህወሃትንና ሹሞቹን በዚህ የኦጋዴን ዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ በሚፈጸም ወንጀል ማስከሰስ፤ ለፍርድ ማቅረብ የኦጋዴን ወገኖችንና የመላ ኢትዮጵያ ልጆችን ትብብር ይጠይቃል፡፡ ስቃይ፣ መከራ፣ ሰቆቃ፣ … ካላስተባበረን ሌላ ምን ሊያስተባብረን ይችላል? ሰዎች ደስታን እንደመሰላቸው ሊተረጉሙት ይችላሉ፤ ግፍ ግን ቋንቋውና ስሜቱ አንድ ዓይነት ነው – እስከ አጥንት ይዘልቃል፤ መቅኔን ይቆጠቁጣል፡፡
Ogaden 15ከአዘጋጆቹ፤ ምንም እንኳን በጋዜጠኛነት ተግባር ላይ የምንገኝ ቢሆንም የእነዚህ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን መከራና ስቃይ ያመናል፤ ያስለቅሰናል፡፡ ከአንዲት እናት የተወለድን ሰብዓዊ ፍጡር እንደመሆናችን የሴቶች ስቃይ ከምንም በላይ ልባችንን ያሳምማል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊ ይህንን ስቃይ ማቅረብ ሌላውን ዜና የመዘገብ ያህል ቀላል አይደለም፡፡ ድርጊቱ አሁን የተፈጸመ ያህል እየተሰማቸው አሁንም ትኩስ እንባ እያፈሰሱ ስቃያቸውን የገለጹት እህቶቻችን ህመም የማያመውና የማያስለቅሰው ህወሃትና በድንቁርና ጭለማ ውስጥ የገቡት ጀሌዎቹ ናቸው፡፡ ህወሃት ይህንን ዓይነቱን ግፍ ሲደርግ ኖሯል፤ አሁንም እያደረገ ነው፤ ኢትዮጵያ ግን አሁንም ከእናንተ የኦጋዴን ግፉአን ጋር ታለቅሳለች፡፡
ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የተወሰደ

Tuesday, 21 June 2016

የወያኔ ሰልፍ በፍራንክፈርት እና ግንቦት 7 ! (በልጅግ ዓሊ)

ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በፍራንክፈርት የዶክተር ብርሃኑ ነጋን መምጣት አስመልክቶ በተጠራ ስብሰባ ላይ ለመካፈል ወደ ቦታው አምርቼ ነበር። የስብሰባው ቦታ ከወትሮ በተለየ በፖሊስ ተከቦ ከሩቅ ተመለከትኩና ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ ወደ ቦታው ጠጋ አልኩ። ጥቂት ግለሰቦችም ከወዲህ ወዲያ ይራወጣሉ፣ ግርግር ይስተዋላል። ይበልጥ እየተጠጋሁ ሲሄድ አንዳንድ የማውቃቸውን የወያኔ ደጋፊዎችን ለመለየት ቻልኩ። እውነቱን ለመናገር በመጀመሪያ የወያኔ አባላት የዶክተር ብርሃኑ ስብሰባ ለመቃወም ያዘጋጁት ስልፍ ነው ብዬ  ለማመን አልቻልኩም ነበር። እንዲያውም ስብሰባውን አትካፈሉም ተብለው የተከለከሉ ሰዎች ተቃውሞ መስሎኝ ነበር።TPLF protest in Frankfurt
ፍራንክፈርት ኢትዮጵያዊነት ጎልቶ ሲቀነቀንባት የነበረች ከተማ፣ አያሌ ታላላቅ የተቃዋሚዎች ስብሰባ የተካሄደባት ከተማ ፣ የወያኔ አባላት አንገታቸውን ደፍተው የኖሩባት ከተማ፣ ዛሬ ወያኔ የልብ ልብ አግኝቶ፣ አፉን ከፍቶ፣ ለይቶለት አደባባይ ወጥቶ የተቃውሞ ስልፍ ያካሂድባታል ተብሎ ፈጽሞ አይታሰብም ነበር። አንድ ቀን ልንደፈር እንችላለን ብሎ የጠረጠረ ተቃዋሚ ከቶ ኖሮስ ያውቅ ይሆን? ወያኔ ሰርጓጅ ጦሩን ወደ ጀርመን አስርጎ ቅኝ ግዛቱን ያስፋፋል ብሎስ ማን አሰቦ ያውቅ ይሆን? እነዚህ የጎጠኞች ማዕድ ፍርፋሪ የሚለቅሙ፣ ሳይጠሩ አስቀድመው በወያኔ ደጀሰላም በራፍ ላይ ለዳረጎት የሚኮለኮሉ፣ በሚገባቸው አባባል፣ የልማት አጋር ኢንቨስተሮች፣ እንዲህ በድፍረት ለተቃውሞ ይወጣሉ ብሎ ማንስ አስቦ ያውቅ ይሆን? https://www.youtube.com/watch?v=ywugKQfWVn4

(ይህ ቪዲዮ ወያኔ ከለጠፈው የተገኘ ነው ። ለፕሮፖጋንዳ ሲባል ብዙ ተቆርጧል።)
ያም ሆነ ይህ ያልነበረው ታዬ! ያልተደፈረው ተደፈረ፣ ያልተደረገው ተደረገ፣ … ከውስጥም ከውጭም ሁሉም ይጮሃል። የትላንቱ አባራሪ ዛሬ በተባራሪነት ይጫወታል። ትላንት ወያኔ ሌባ! … ወያኔ ዘረኛ! .. ወያኔ አምባገነን የነበር መፈክር፣ ዛሬ ቅኝቱ ተለውጦ “ግንቦት7 ሌባ! …ግንቦት7 አሸባሪ! ብረሃኑ ሌባ! ተራራውን ያንቀጠቀጠው ትውልድ ያሸንፋል፣ ደርጋዊነት ይወድማል ወ.ዘ.ተ“ በሚል ተቀይሯል። በዚህ ተለዋዋጭ ዓለም የማይቻለው ፣የማይታሰበው መፈጸም ከጀመረ ሰንብቷል።
ለእኔ የሰለፈኞቹን ማንና ምንነት  ለመለየት ብዙም አላዳገተኝም። ገና ወያኔ የትግራይ ክልል ሰንደቅ ዓላማ የሚለውን አንድ ባልቴት ተሸክማው ሳይ ነው እነማን መሆናቸውን ያወቅሁት። መቼም በጥቅምና በዘረኝነት ያበደ ካልሆነ ይህንን የዘረኝነት ምልክት በአደባባይ ይዞ የሚወጣ አይኖርም። በዚህ በወያኔ ግርግር ላይ አለፍ’ አለፍ እያለ “የኢትዮጵያ”(ባለ ሃምባሻው)፣ እንዲሁም የጀርመን ሰንደቅ ዓላማዎች ነበሩ።
ወደ ቦታው ጠጋ አልኩ። ከመሃል አንዱ እዚሁ ፍራንክፈርት አካባቢ የሚኖር ወያኔ ስለለየኝ፣ ወዲያውም “አምሃራይ” ብሎ ጮኸ። የከበቡት ሁሉ እሱን ተከትለው “ አምሃራይ ሌባ ፣ ግንቦት 7 ሌባ ! ደርግ ሌባ ! ብርሃኑ ሌባ !“ እያሉ አዋከቡኝ። እንደ ልማዳቸው ብዙ ፎቶም አነሱኝ። በመካከላችን የጀርመን ፖሊሶች ጣልቃ ገቡ። ቆሜ በደንብ ለመስማት ፍላጎት ቢኖረኝም ፖሊሶቹ አዋክበው ወደ ስብሰባው አዳራሽ አስገቡኝ። እንኳን ፌደራል አልሆነ ፣ እንኳን አጋዕዚ አልሆነ . . .!…  እንኳንም ቃሊቲ አልኖረ ፣ እንኳንም በነፃው ዓለም በጀርመን ሃገር ሆነ! . . .  ባይሆን ኖሮ እንደ ቀይ ሽብሩ ዘመን “ አምሃራይ “ ብሎ ያጋለጠኝ ሶለግ …..! ሳይቦጫጭቀኝ መች ይቀር ነበር። ያችስ ብትሆን. . .  ድምጽዋ እስከሚዘጋ በሰሜን ቅላጼ ጀርመንኛ የምትሞክረው ባልቴት እኔን ለመንከስ አለያም አስቀፍድዳ ለማስገረፍ ወደ ኋላ መች ትል ነበር። ይሁን እስኪ “ማምሻም እድሜ ነው” . . . እዚሁ አብረን ስለምንኖር እንተዋወቃለን።
ለነገሩ የተጮኸብኝ ስለማይመለከተኝ አልገረመኝም። የግንቦት 7 አባል አይደለሁምና፣ ደርግም አይደለሁም፣ ብርሃኑም አይደለሁም። ወያኔዎቹ ግን ጥላቻቸው ከሁላችንም ጋር እንደሆነ አውቃለሁ። ወያኔ የወንጀለኞች ቁንጮ፣ የዘረኝነት ሁሉ የበላይ፣ የሕዝብ ጠላት መሆኑን አውቃለሁ። በሃገሬ ያጣሁትን ነጻነት በጀርመን ሃገር ሊያሳጡኝ መሞከራቸውም ከቶ አልገረመኝም ። ቢቻላቸው ከዛም በላይ ይሞክራሉ። ከእነዚህ ዓይን ከማይሞሉ ህዳጣን፣ የያዙትን መፈክር እንኳ አስተካክለው ማንበብ ከማይችሉ ማይማን ሌላ አይጠበቅም። ከእነዚህ በዘር ልጓም ተሸብበው ዞሮ ማያ አንገት የሌላቸው ሆዳሞች፣ ሌላ ምን ሊጠበቅ ይችላል?   አብረን እዚሁ ፍራንክፈርት ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ የኖርን ሰለሆንን እንተዋወቃለን። እንኳን የጀርመንን ሕግ፣ ዴሞክራሲና ሥነ ስርዓት ሊረዱ ይቅረና ስማቸውን አስተካክለው እንደማይጽፉ አውቀዋለሁ። በተለይ ደግሞ “አምሃራይ” ብሎ ሌሎቹ እንዲጮኹብኝ የቀሰቀሰውን አስለኳሽ ጋሻ ጃግሬ አብረን የኖርን ስለሆንን ድፍን ቅልነቱን እረዳዋለሁ። እርሱ ይረሳው እንደሆን እንጂ ከ20ዓመታት በፊት ይህ ማይም ከሻብዕያ አባላት ጋር ሆኖ ያደርግ  የነበረው የምዘነጋው አይደለም።
ወያኔዎቹ እንዳለሙት፣ የወያኔ ቆንስላ እንደተለመው፣ ብዙዎቻችንን በምንም ሊያስፈራሩን አይችሉም። ማስፈራራት የሚችሉት መሬትና ኮንደሚኒየም ይሰጠናል ብለው ማንነታቸውን ሸጠው እጅ የሚነሱላቸውን ባንዳዎችን ብቻ ነው። እነርሱ ደግሞ ስብሰባ አይመጡም።  ማስፈራራት የሚችሉት በሁለት እጃቸው የሚጨብጧቸውን የዘመኑ ሆዳም “ኢንቨስተሮችን“ ብቻ ነው። ልማታዊ ካድሬዎቻቸውን። ሌሎቻችንማ ደረታችንን ገልብጠን፣ ኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል! እያልን ፣ ዘረኝነት ይወድማል! እያልን ፣ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! እያልን ወደ ስብሰባው አዳራሽ ገብተናል።
አዳራሹ ውስጥ ስገባ የግንቦት ሰባት አባላትና ደጋፊዎች መሪያቸውን ዶክተር ብርሃኑን ከበው መፈክር ያሰማሉ። ተናጋሪው “ ዛሬ ትግላችን ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋገረ” ብሎ በድምጽ ማጉያው ይናገራል። ውስጥ ያለው ሁኔታ በብዛትም በጩኸትም ከውጭው በጣም ይበልጣል ። ለጥቂት ደቂቃዎች የውስጡን ከውጩ እያወዳደርኩ ተቀመጥኩ። የሃገሬ የወደፊት ዕጣ ምን ሊሆን እንደሚችል በማጤን ለትንሽ ጊዜ ቆዘምኩ። በአዕምሮዬ አንድ ሃሳብ ፣ አንድ ጥያቄ እየተመላለሰ አወከኝ።
ውነት ዛሬ ወያኔ በፍራንክፈርት ተቃውሞ የወጣው ስለደከመ ነው? ወይስ ስለጠነከረ ?
ይህ ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ነው ። በእውነቱ ከሆነ ወያኔ በአሁኑ ወቅት በብዙ ቅራኔ የተወጠረበት ወቅት ነው ። ደክሟል ! በውስጥ ክፍፍል ተጎድቷል፣ በስልጣን ሽኩቻ ጉልበቱ ዝሏል ፣ ጉድጓዱ የተማሰ ነው፤ ፍራሃትም አለበት ። ትንንሹንም ችግር ቢሆን እንደ ቀልድ አይመለከተውም ። እርምጃ መውስድ ይሞክራል ። ዶክተር ብርሃኑ ስብሰባው ላይ እንደተነተነው የተቃውሞ ግርግሩን ከዚህ አንጻር ሊታይ ይቻል ይሆናል።  የግንቦት ሰባት ከኤርትራው መሪ ኢሳያስ ጋር መግጠም ሊያስፈራው ይችላል። ነገር ግን ግንቦት ሰባት ከኢሳያስ ጋር መግጠሙ ዛሬ የመጀመሪያው ቀን አይደለም። ወያኔ ከደከመ ሰነባብቷል። ለምን ታዲያ ወያኔዎች ዛሬ ሰልፍ ለመውጣት ደፈሩ? ብለን መጠየቅ ደግሞ ብልህነት ነው።
እንደኔ ከሆነ ፍርሃት ብቻ አይመስለኝም ። ወያኔ ፍራንክፈርት አካባቢ ብዙ ሥራ ሰራሁበት፣ ብዙ አባላት 5 ለ 1 ጠረነፍኩበት የሚለው ክልሉ ነው። እዚሁ ፍራንክፈርት ውስጥ ባለፉት ሁለት አስር ዓመትት ወያኔ መሬትና ኮንደሚኒየም ለመደለያ በመስጠት አያሌ ዜጎቻችንን ከፋፍሏል። ቀንደኛ የወያኔ ተቃዋሚ ነን ይሉ የነበሩ ግለሰቦቸች ሳይቀሩ የወያኔ ደጅ ጠኝ ሆነዋል። ብዙ ጠንካራ ዜጎቻችንን በተቃዋሚዎች መካከል ያለውን ክፍፍል ስላስጠላቸው ከትግሉ ገለል ብለዋል፣ ወያኔ በትምህርት ስም ብዙ ወጣት ደጋፊዎቹን አምጥቷል፣ በስደተኛ ስም ብዙ አባሎቹን አስርጓል ። በዚህ ክልሌ ነው በሚለው ፍራንክፈርት የልብ ልብ የበላይነት ይሰማዋል ። ቀደም ሲል ጠንካራ የነበሩት ተቃዋሚዎች እነ መድህን ፣ እነ መኢአድ ፣ እነ ኢሕአፓ ዛሬ የሉም፣ በእነርሱ ቦታ በኮንደሚንየም ፣ በመሬት ጥቅም ምክንያት 5 ለ 1 የተጠረነፉ ሆዳሞች ቦታውን ሞልተውታል ። ለእኔ ወያኔን የልብ ልብ የሰጠው ይህ የሆዳምነት፣ የመከፋፈል፣ ከትግል የመሸሽ አዝማሚያ ብዙዎቻችንን በመልከፉ ሳቢያ ይመስለኛል ።
በሌላ በኩል ደግሞ በተቃዋሚዎች መካካል ወደሚያስማማን ሳይሆን ወደሚያለያየን የሚደረገው ጉዞ እንደቀጠለ መሆኑ ለወያኔዎች የልብ ልብ ሰጥቶታል። በተለይ የኤርትራ ጉዳይ በተመለከተ በሕዝብ መሃል የተፈጠረውን የአቋም ክፍፍል ወያኔ በውል ያጤነው ጉዳይ ነው። የኤርትራ መንግስት በነ ተስፋዬ ገብረ እባብ የተነደፈለትን ኢትዮጵያን የመከፋፈል ፖሊስ ቀረጾ ፕሮፖጋንዳውን ማጧጧፉ ለማንም ድብቅ አይደለም። ይህንን ወያኔም ይገነዘበዋል። ወያኔ እኔ ከሌለሁ አማራጫችሁ ተስፋዬ ገብረ እባብ፣ ጃዋር እና መሰሎቹ ናቸው ብሎ መቀስቀስ ከጀመረ ሰነበተ። ሁኔታውን ሲያጤኑት ደግሞ ጉዞው ወደ መሳፍንት ዘመን ይመስላል። እንደተለመደው ወያኔም ይህችንን የአቋም ክፍተት መጠቀም መፈለጉ ግልጽ ነው። በዘር እንደነገደ፣ በዓባይ ግድብ እንደነገደ፣ ዛሬም በኤርትራ፣ ዛሬ ጽንፈኛ ሆኖ  በጽንፈኞች፣ ዘረኛ ሆኖ እሱን እንስከጠቀመ ድረስ  ዘረኞች አውግዞ ሊነግድ ይሞክራል።
በሰልፉ ላይ ደርግና ደርጋዊነት ሲኮነኑ ነበር። በተለይም ደግሞ የደርግ ባለስልጣናት የነበሩ በተቃውሞው የትግል መድረክ ላይ ወጣ ወጣ እያሉ በመምጣታቸው ወያኔ ይህን እንደ በጎ አጋጣሚ ሊጠቀምበት መፈለጉ ከወያኔ ሰልፍ መፈክር መረዳት ይቻላል። የደርግን ፋሽሽትነትን ለማመልከት የገባችው መፈክር የማንን  ልብ ለማማለል እነደሆነ አስቀድማ ትሸተናለች። በእውነት ቢሆንማ ኖሮ ከወያኔ ከራሱ ጋር ዛሬም ድረስ የሚሰሩ ብዙ የደርግ ባለስልጣናት ባልኖሩ ነበር ።
በፍራንክፈርቱ የወያኔ ሰልፍ የተገነዘብኩት ሌላው ጉዳይ ደግሞ፣ እየተስለመለመ ባለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የደም ደብዳቤ በማረቀቅ ላይ የሚገኘው ወያኔ፣ በቀቢፀ ተስፋ የጎሳ እንጉርጉሮ እያዜሙ የሚጓዙ አጋር ድርጅቶቹና ወዶገብ አባላቱ የኢትዮጵያዊነትን ህዋስ ከውስጣችን አሟጦ ለማስወጣት እየተሄደበት ያለው እርቀት ምን ያህል እንደሆነ ከወያኔ የተቃውሞ ሰልፍ መገመት አያዳግትም። በሰልፉ ላይ አብዛኛዎቹ የትግራይ  ሰዎች እንደነበሩ ቢታወቅም፣ በዶክተር ብርሃኑ ስብሰባ ውስጥም የትግራይ ልጆችንም በብዛት እንደነበሩ እዚህ ፍራንክፈርት ለኖርነው ግልጽ ነው። ይህ የፍራንክፈርቱን የተቃውሞ ሰልፍ ከአንድ ዘር አቅጣጫ ለማያያዝ የሚከብደውም ለዚሁ ነው። ይህንን የወያኔን ሰልፍ ከወያኔ አቅጣጫ ብቻ ነው ማያያዝ ያለብን የሚል እምነት አለኝ።
የፍራንክፈርት ነዋሪ የሆንን ሁሉ በውል ልናጤነው የሚገባ አንድ ነገር አለ። አሱም እነዚህ ዛሬ የወያኔ ደጋፊ ሆነው ስብሰባ ለማደናቀፍ የሞከሩ፣ በስብሰባው ላይ የተገኘነውን ፎቶ አንስተው ለወያኔ ለማስተላለፍ የሞከሩትን ዝም ብለን ማለፍ የለብንም። በተቻለን መጠን ለጀርመን መንግስት በወያኔ ስለሚደርስብን ማስፈራራት (erpressung) ማሳወቅ ይኖርብናል። በሃገር ውስጥ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን መከራና ስቃይ አልበቃ ብሎ ዛሬ እዚህ እኛን በጀርመን ሃገር ለማሰቃየት መሞከራቸውን ዝም ብለን ማለፍ የለብንም። ፍራንክፈርት ወያኔ ቆንስላ ዛሬ የዲፐሎማቲክ ስራውን ትቶ የስለላና የማስፈራራት ተግባር መጀመሩ የሚያስፈራ ወንጀል ነው። ሊጠየቅ ይገባል። በስደተኛነት ስም ተቀምጠው የስለላ ስራ የሚሰሩትንም ዝም ብለን ማየት ከቶ የለብንም። የጀርመን መንግስት ለእኛ ለስደተኞች በሃገሩ በነጻነት እንድንኖር እንዲያደርግ ጥያቄችንን ማቅረብ አለብን።
በሌላ በኩል የግንቦት 7 መሪዎችም ከዚህ ስልፍ መማር የሚችሉት ወያኔን ለመጣል የኤርትራ ድጋፍ ማግኘቱ ብቻ  በቂ አለመሆኑን ነው። በውጭ አፋቸውን ለማዘጋት እቤታቸው ድረስ እየመጣ ያለውን ተቃውሞ ለመቋቋም መዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን መረዳት ያሻል። ያን ለማድረግ ደግሞ የሕዝብን ልብ ማማለል መቻል ይጠይቃል። ደጋፊዎቻቸውን ብቻ ሳይሆን ከተቃዋሚዎቻቸውም የሚያነሱትን ጥያቄ ለምን እንደሆነና መፍትሄው ምን እንደሆነ በግልጽ ወጥተው መናገር አለባቸው። ለጊዜያዊ ፖለቲካ ጥቅም ሲባል ከነተስፋዬ ገብረ-እባብና ከእነ ጀዋር መሀመድ ጎን መሰለፍ፣ ድጋፍ ሊያሳጣ እንደሚችልም ከወዲሁ መገንዘብ ትልቅ ሒሳብ ስሌት አይደለም። አሁንም በግንቦት ሰባት ሊመለሱ የሚችሉ ጥያቄዎች እንዳሉ በስብሰባው ውስጥ በጥያቄና መልሱ ወቅት በጉልህ የታየ ጉዳይ ነው ። የሰጎን ፖለቲካ የሚያዋጣ አይሆንም ። አንገትን አሸዋ ውስጥ ደብቆ አካላት እንዳሪ ሆኖ መደበቅ አይቻልም። እነ ተስፋዬ ገብረ-እባብ የሚቀሰቅሱትን አማራን ለማጥፋት የሚደረግ መጠነ ሰፊ የተቀነባበረ ዘመቻ የኤርትራ መንግስት የለበትም የሚለው ማሳመኛ ነጥብ ውሃ አይቋጥርም።
የፍራንክፈርቱ የወያኔ ሰልፍ ሁለት ገፅታዎች አሉት። አንዱ ግንቦት ሰባት እና ኢሳት እንደሚነግሩን የትግላችን ጥንካሬን ምን ያህል ወደፊት እየተወነጨፈ እንዳለ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ አጉልቶ የሚያሳየን የድክመታችንን ፣ የሸንፈታችንን፣ የክፍፍላችንን ጥልቀት ጭምር ስለሆነ በዚህ ላይ የቤት ሥራው እየከበደ ነው ማለት ነው። ለእኔ ዛሬ የወያኔ ትግል ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የተሸጋገረበት ነው። ይህ ደግሞ በቀላል ለማስቆም የሚቻል ነው። በሁሉም አቅጣጫ በቅንጅት ከፍተኛ ሥራ ካልተሰራ ወያኔ አሁንም ዳግም ፈልፍሎ ቀዳዳ ማግኘቱ የማይቀር ነው። ቀባሪ የሌለው ሞት እንዳንሞት ማስተዋል ያስፈልጋል።by: ecadforum
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ፍራንክፈርት

የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።

የህዝብን ትግል ለማስጠበቅ የሕዝብን ነጻነት ለማረጋገጥ የጋራ አንድነታችንን ማጠናከር ግድ የሚልበት እና ሃገራዊ/ህዝባዊ ሃላፊነታችንን በመወጣት ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችንን አውቀን የትግል ቃልኪዳናችንን በማጥበቅ ህዝባዊ ድሎችን ማረጋገጥ ሃገራዊ ግዴታችን እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል::ባሳለፍነው የትግል አመታት ውስጥ የተቃዋሚዎች እርስ በ እርስ መፈራረጅ መወነጃጀል መናናቅ ለስልጣን ጥመኝነት መሮጥ እንዲሁም ለስም እና ለዝና መትጋት ያለመደማመጥ እና ያለመከባበር ፖለቲካ ተቀራርቦ ያለመነጋገር እና ያለመመካከር ፖለቲካ ሃገራኢ ሆደሰፊነት እና መቻቻልን ያላዘለ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተረፈው ነገር ቢኖር ከጭቆን ወደ ጭቆና ማቅ ውስጥ ከመዘፈቅ ውጪ ምንም የናፈቀውን የነጻነት አየር እንዲተነፍስ አላደረግነውም። የተቃዋሚ ሃይሎች ጥንካሬ እንዲጎለብት በየድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እንከኖች በማጥራት በጋራ እና በተመቻቸ የሃሳብ መግባባት ተቻችሉ እና ተግባብቶ የትግል ስትራቴጂን ግብ ለማድረስ ለአንድ ወጥ ህዝባዊ እና ሃገራዊ አጀንዳ ተግቶ መስራት ይጠበቅብናል።
ወያኔ የተቃዋሚዎችን እና የለውጥ ሃይሎችን እርስ በእርስ መፈነካከት በማየት አርጩሜውን ተስፋ በሚጣልባቸው ግለሰቦች እና ፓርቲዎች ላይ እያወናጨፈ ባለበት እንዲሁም የውስጥ አሰራራቸውን በመሰለል በትግሉ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲኮላሽ በመስራት የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመጠቀም እርስ በርስ እንዲፋጁ እና ተቃዋሚዎች እንዲከስሙ ጥንካሪያቸውን እንዳያገኙ ሲሰራ ይህንን እንዴት አድርገን በማሻሻል የወያኔን ሴራ ማክሸፍ አለብን የሚል አመኔታ የሚያስገኝ ሕዝባዊ ስራዎችን በመስራት ጥንካሬን ማግነት እንዲሁም ሕዝባዊ ድጋፎችን ማግኘት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ መሆናቸውን ተቃዋሚዎች ሊያውቁት ይገባል::ተቃዋሚዎች ካለፈው ድክመቶቻችን ተምረን ከዘለፋ እና ከስድብ እንዲሁም ከመፈራረጅ የሴራ ፖለቲካ በመውጣት ጥንካሬዎቻችንን የምናሳይበት ለውጥ የምናመጣበት አመት እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን። አንድነት ሃይል ነው የሚለው ብሂል ለሃገራዊ አጀንዳ መተግበር ትልቅ አስታውጾ አለው::ከኛ በላይ ላሳር ከኛ በላይ አዋቂ የለም የሚል አመለካከት ይዞ ከመክነፍ የህዝብን ጥያቄ መሰረት አድርጎ ተቀራርቦ በመነጋገር እና በመወያየት ሃገራጂ ማኒፌስቶ በማምጣት የጋራ ሃገራዊ አጀንዳ በመቅረጽ ለለውጥ መትጋት ግዴታ ነው::
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ሳይታለም የተፈታ እና የሁሉም የነጻነት ፈላጊ ሃይሎች ጥያቄ ነው። በሃገር ውስጥ ያሉትን ፓርቲዎች መዋቅሮቻቸውን በማጠናከር የውስጥ ድክመቶቻቸውን በመቅረፍ እንዲጠነክሩ የማድረግ ግዴታ ከለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ይጠበቃል። መመካከር መተራረም ግድ ይላል። በውጪው አለም የሚገኙ የነጻነት እና የለውጥ ሃይሎች እንዲጠናከሩ እና ከጥልፍልፎሽ ፖለቲካ ወተው ጠንካራ ሃይል እንዲሆኑ የዲያስፖራው ሃይል ከበፊቱ በበለጠ መልኩ ሊሰራ ግድ ይለዋል። የወያኔ የጎን ውጋት እና የራስ ምታት የሆነው ዲያስፖራው የጀመረውን የትግል ስልት እና ትጋት በማስፋት ሚዲያዎችን በማጠናከር እና የነጻ አውጪ ፓርቲዎችን በመርዳት በማግባባት ጠንካራ ሰንሰለት ከሃገር ቤት ጋር በመፍጠር ሕዝብን ከጨቋኞች ነጻ ማውጣት አለበት።ዲያስፖራው በየቀኑ ወያኔ የሚፈጥረውን ተራ የቤት ስራ እና የማደናገሪያ ማዘናጊያ አሉባልታ ፊት ሳይሰጠው በለውጡ ጉዳይ ላይ በማተኮር በሃገር ቤት ያለው ሃይል እንዲስማማ የፖለቲካ ጡዘቶች ክፍተት እንዳይኖር ተቀራርቦ እንዲሰራ ትልቁን ሚና መጫወት አለበት::by minilik salsawi

የኢትዮጵያ-ኤርትራ የጦርነት ጨዋታዎች፣

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ይህን አስቂ ኝ (አስለቃሽ) ትአይንት  (ትያትር)  ፊልም ከዚህ ቀደም አላየነውምን?
Wargames Amharicእ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 ዘ-ህወሀት የሕዝብን ስሜት ለማስቀየስ (ለማወናበድ ) ስለሚያካሂደው የጦርነት ጨዋታ  ትችት በጽሁፍ አቅርቤ ነበር፡፡
ዘ-ህወሀት ማለት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አገዛዝ በዓለም አቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ስም ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተመዝግቦ የሚገኝ አሸባሪ ድርጅት ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 አሁን በህይወት የሌለው የዘ-ህወሀት መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመለኮስ እና ከግብጽ ጋር ደግሞ የውኃ ጦርነት ለማካሄድ የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ስለጦርነት አይቀሬነት ድምጹን ከፍ አድርጎ በማጉላት የወሬ ክኩን ይሰልቅ ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ይኸው በአሁኑ ጊዜ እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 ወደለመድነው የጦርነት አረንቋ ተመልሰን ለመዘፈቅ አሀዱ/አንድ በማለት ጀምረናል፡፡
ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደገና በድጋሜ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ስለ”ጦርነት” ሰበካ፣ ስለጦርነት ሟርት እና ስለጦርነት ከበሮ ድለቃ ሌት ከቀን እየተለፈፈልን ሳንወድ በግድ እንድናዳምጥ በመደረግ ላይ እንገኛለን፡፡
እናም ይህንን የሕዝብ ስሜት/ቀልብ ማስቀየሻ ጦርነት እንደገና መመልከት ይኖርብናልን?
የዘ-ህወሀት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ጌታቸው “አፈ ጮሌው” ረዳ እንዲህ በሏል፣ “በሁለቱም ወገኖች በኩል ከፍተኛ የሆነ እልቂት ተፈጽሟል፣ በይበልጥ ደግሞ በኤርትራ በኩል ያለው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ስንወስድ ቆይተናል፡፡ ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ እስከ አሁን ድረስ ስንወስዳቸው ከቆዩት እርምጃዎች በዓይነቱ እና በመጠኑ ከፍ ያለ እርምጃ መውሰድ በጣም ጠቃሚ ነገር ስለሆነ አስተማሪ የሆነ እርምጃ ወስደናል፡፡“
ኤርትራ በበኩሏ 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በመግደል ከ300 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ቁስለኛ አድርጊያለሁ የሚል መግለጫ ይፋ አድርጋለች፡፡
የካሊፎርኒያ ግዛት የዩኤስ አሜሪካ ታዋቂ የምክር ቤት አባል/ሴናተር የሆኑት ሂራም ጆሀንሰን ከብዙ ጊዜ በፊት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ጦርነት በሚመጣበት ጊዜ የመጀመሪያው የጥቃት ሰለባ የሚሆነው “እውነት” ነው፡፡“
ሁለት የጦርነት ተፋላሚ ቡድኖች በአንድ ዓይነት “እውነት” ላይ የጋራ ስምምነት ሲያደርጉ የምመለከት ከሆነ “እውነት” የመጀመሪያ እና ብቸኛ የጥቃት ሰለባ ሆኖ ስለመቆየቱ መገረም የምጀምር ይሆናል፡፡
እንደዚሁም ሁሉ የጠነባን ዓይጥ ማሽተት እጀምራለሁ፡፡ የጠነባን ዓይጥ ገና ከ10 ሺ ሜትሮች ርቀት ላይ ማሽተት እችላለሁ፡፡ ያ ሽታም  በኢትዮጵያ-ኤርትራን ጦርነት በሚባለው ላይ ተንሳፎ ይገኛል! (እፍ እፍ እፍ!!!)
በእርግጥ የጆሀንሰን ቁም ነገር የጦርነት ሰለባ መርህ አነጋገር  በጦርነት ተጫዋቾች ላይ አይሰራም፡፡
ለበርካታ ዓመታት ሳስተውለው እንደቆየሁት የዘ-ህወሀት አመራሮች ከሕዝብ ጋር መጥፎ የሆነ የግንኙነት አባዜ ላይ እንደወደቁ አድርገው እራሳቸውን በሚቆጥሩበት ጊዜ ለዚያ ማስቀየሻ ዘዴ ጦርነትን ያውጃሉ፡፡
ዘ-ህወሀት በህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ሰብአዊ ወንጀል፣ ሙስና፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀም እና ሰላማዊ ዜጎችን መጨቆንን ለመደበቅ ሲያስብ የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ስሜት ለማስቀየስ የሚያጋልጡትን መጥፎ ዜናዎችን ማፈን እና የሕዝብን ስሜት የማስቀየስ መንገድ እንደሚጠቀም እገምታለሁ፡፡
ያለፉት ጥቂት ሳምንታት ለዘ-ህወሀት መጥፎ ዜናዎች እንደነበሩ ምንም ዓይነት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡
ባለፈው ሳምንት የዩኤስ አሜሪካ የቦንድ እና የአክሲዮን ልውውጥ ኮሚሽን ዘ-ህወሀት ህገወጥ ወንጀለኛ በሆነ መልኩ ከደጋፊዎቹ እና ጥቅም አገኛለሁ ብለው ለቦንድ ግዥ ክፍያ ሲፈጽሙ ከቆዩት ኢትዮ-አሜሪካውያን 6.5 ሚሊዮን ዶላር በህገወጥ መልክ ዘርፎ በመገኘቱ ያወናበደዉን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲመልስ ቅጣት ጥሎበታል፡፡ ዘ-ህወሀቶች ኮሚሽኑ ለሚያቋቁመው አስተዳዳሪ እ.ኤ.አ ሀምሌ 8/2016 ከማለፉ በፊት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
ይህ ድርጊት ለዘ-ህወሀት ትልቅ ውርደት እና የኢትዮጵያውያንን እና የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያንን ኪስ በማራቆት በአፍሪካ ታላቅ ግድብ እሰራለሁ በማለት መቋጫ የሌለው ዲስኩሩን ሲያሰማ በነበረው እና አሁን በህይወት በሌለው በወሮበላ ዘራፊው መሪ በአምባገነኑ መላስ ትውስታ ላይ ታላቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ነገር ነው፡፡
ባልተመዘገበ እና ህገወጥ በሆነ የቦንድ ሽያጭ በማጭበርበር ግዙፍ የሆነ ግድብ በአፍሪካ እገነባለሁ ማለትን እስቲ አስቡት ጎበዝ! ቦንድ የማጭበርበር እኩይ ምግባሩን መከላከያ ዘዴ መሆኗ ነውን?
በዩኤስ አሜሪካ ሕግ መሰረት ያልተመዘገበ ቦንድ መሸጥ ሕገ ወጥ ነው በማለት ከሶስት ዓመታት ገደማ በፊት የተናገርኩ ሲሆን ከተናገርኩ ከሶስት ዓመታት በኋላ የዘ-ህወሀት መሪዎች የማጭበርበር አባዜ የተጠናወታቸው በመሆኑ ከማሰሮው ውስጥ እጃቸውን እንዳስገቡ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ማሰብ እችላለሁ፡፡
የሚሰማ ጆሮ እና የሚያስተውል አእምሮ የላቸውም እንጅ እ.ኤ.አ ግንቦት 8/2013 ፊት ለፊት እና በቀጥታ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ይህንን ነገር አታድርጉ! ያልተመዘገበ ቦንድ አትሽጡ! በዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል እና የአካባቢ መንግስታት ሕግ መሰረት ወንጀል ነው ብዬ ነግሪያቸው ነበር፡፡ ወንጀልን አትስሩ፣ ከጊዜ በኋላ አደጋው የሚያንዣብብ እና የሚያስጠይቃችሁ ይሆናል በማለት በግልጽ ተናግሬ ነበር፡፡
እንደተናገርኩት ከሶስት ዓመታት በኋላ ያልተመዘገበ ቦንድ ሽያጭ (ወንጀል ነው፣ የ1933 የቦንድ ድንጋጌ ክፍል 20 (b)ን ይመልከቱ) ወንጀል ስለሆነ ማጅራታችዉን ተያዙ፡፡
ሆኖም ግን የዘ-ህወሀት ያልተመዘገበ ቦንድ ዋና ሻጮች የወንጀል ቅጣቱን በማጭበርበር አንደተለመደው ሊያልፉት አልቻሉም፡፡
በእርግጥ አላለፉትምን?
የዘ-ህወሀት መሪዎች ለበርካታ ዓመታት ያህል ሰብአዊ መብቶችን እየደፈጠጡ ምንም ዓይነት ተጠያቂ ሳይሆኑ ደረታቸውን ነፍተው ተቀምጠው እንደሚገኙት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሜሪካ ሕጎች ላይም አፍንጫቸውን በመንፋት ከወንጀል ተጠያቂነት የሚያመልጡ መስሎ ታይቷቸዋል፡፡
በምንም ዓይነት መልኩ ሊሆንላቸው አልቻለም፡፡
ጉዳዩ በኮሚሽኑ (SEC) ግልጽ እና ይፋ ከሆነ በኋላ የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂዩማን ራይትስ ዎች (ሂራዎ)/Human Rights Watch (HRW) “ጭካኔ የተመላበት እርምጃ፡ ለኢትዮጵያ ኦሮሞዎች ተቃውሞ የተሰጠ የግድያ እና እስራት ምላሽ“ በሚል ርዕስ ትልቅ ዘገባ አቅርቧል፡፡
ያ ዘገባ “ከመጠን ያለፈ እና አላስፈላጊ የሆነ የጥላቻ ኃይል መጠቀም እና ዜጎችን በጅምላ በቁጥጥር ስር የማዋል፣ መጥፎ የእስር ቤት አያያዝ፣ የሰላማዊ አመጽ እንቅስቃሴውን ለማኮላሸት የመረጃ ምንጮችን መቆጣጠር“ በማለት ዝርዝሩን አቅርቧል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት የሂራዎ/HRW የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክር የሆኑት ሌዝሊ ሌፍኮው እንዲህ ብለው ነበር፣ “የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የሰው ልጆችን ህይወት ከቁብ ሳይቆጥሩ የጭካኔ ተኩስ በመክፈት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን፣ አርሶ አደሮችን እና ሌሎችን ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል፡፡“
ለሰው ልጆች ህይወት ምንም ዓይነት ቁብ ሳይሰጡ በሰላማዊ ተቃዋሚ ስብስብ ላይ የጭካኔ ተኩስ መክፈት በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ሰብአዊ ወንጀል ነው፡፡ ይህንን የምለው ለታሪክ ምዝገባ ብዬ ነው፡፡
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 የዘ-ህወሀት ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በአመጹ ላይ የተገደሉት ሕዝቦች “ሁከት እና ብጥብጥን ዓላማ ያደረገ የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል በመፍጠር ሞዴል አርሰ አደሮችን፣ የህዝብ መሪዎችን እና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩትን የጎሳ ቡድኖች መግደል በመጀመራቸው ነበር” ብሏል፡፡
የሚገርም ነገር እኮ ነው ጎበዝ! በመንገድ ላይ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ የሁለተኛ ደረጃ እምቦቃቅላ ተማሪዎች እና የኮሌጅ ተማሪዎች በምን መስፈርት እና መለኪያ ነው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሊባሉ የሚችሉት? ወያኔ በእራሱ የፍርሀት ምዕናብ እየፈጠረ በህዝብ ላይ የሚነዛው ሽብር ካልሆነ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?
ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ የተባለው ድራጎን (ዘንዶ)፣ ሳንዲ እየተባለች የምትጠራውን ተንቀሳቃሽ ሲኒማ ልጃገረድ ውሸት እና ቅጥፈት ወደሚነገርባት ምድር የወሰደበትን ታሪክ  አስታወሰኝ፡፡ ሳንዲ እዚያ ከደረሰች በኋላ በሬ ወለደ እያለ የሚናገረውን ፕናክዮንን አገኘችው፡፡
ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት ምድር ፑፍ እና ሳንዲ ማንም አይቷቸው የማያውቅ ቀይ እና ሰማያዊ ላም እንዲሁም ቀይ እና ነጭ ዝሆንም አዩ፡፡
13 ወራት ሙሉ ውሸት እና ቅጥፈት በሚነገርባት በዘ-ህወሀት ቁጥጥር ስር ባለችው ኢትዮጵያ የትምህርት ቤት ልጆች እና የኮሌጅ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር እንደተዘጋጀ ቡድን ተቆጥረው “የተደራጀ እና የታጠቀ አሸባሪ ኃይል” ሆነው ይታያሉ፡፡
ኢትዮጵያ 13 ወራት ሙሉ የፀሐይ ብርሀን የሚፈነጥቅባት ሀገር መሆኗን ነበር እኔ የማስታውሰው፡፡
በነገራችን ላይ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ሌሎች እ.ኤ.አ በ2007 በኬንያ ተደርጎ በነበረው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ወቅት ተከስቶ በነበረው ውዝግብ ወደ 2000 ገደማ በሚሆኑ ሰላማዊ ኬንያውያን ዜጎች እልቂት ላይ እጃቸው አለበት በሚል የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት እ.ኤአ. በ2012 ክስ መስርቶባቸው ነበር፡፡
ሂራዎ/HRW በኦሮሞ ሰላማዊ አመጸኛ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው እልቂት እንዲጣራ ነጻ የሆነ አጣሪ አካል እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ሆኖም ግን ዘ-ህወሀት እንደተለመደው የዝሆን ጆሮ (የጅብ ሆድስ አለኝ) ይስጠኝ በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፡፡
ዘ-ህወሀት ወደ 20 ሚሊዮን ገደማ የሚሆነውን ህዝብ እያሰቃየ ያለውን የረሀብ ሁኔታ አያያዝ በሚመለከት እያደረገ ስላለው ፍጹም የሆነ ብቃትየለሽነት እና ይኸ አውዳሚ የሆነ ረሀብ በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እይታ ደብቆ ለማቆየት እያደረገ ባለው አሳፋሪ ጥረት የህዝብ ግንኙነት ስራው በመጥፎ ሁኔታ ተበላሽቶበታል፡፡
ከዩኤስኤአይዲ/USAID እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የድህነት ወትዋች አቃጣሪዎች መጥፎ ሸፍጥ ጋር በመተባበር ዘ-ህወሀት ድርቁ ካጠቃቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት መረጃ እንዳይወጣ በማድረጉ እና ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ እውነታውን ለእራሳቸው እና ለህዝቡ ፈልፍለው እንዳያወጡ በመከልከሉ ደባ ተሳክቶላቸዋል፡፡
እስከ አሁን ድረስ ዘ-ህወሀት ስለረሀቡ ሁኔታ ስለጠቅላላ ተጠያቂነቱ እና ግዴለሽነቱ፣ ለብቃትየለሽነቱ እና ወንጀለኛነቱ ምንም ነገር ባለመሆኑ ስኬታማ ሆኗል፡፡ (ለዩኤስኤአይዲ/USAID አስተዳዳሪ ለጋይሌ ኢ. ስሚዝ የጻፍኩትን ደብዳቤ ይመልከቱ፡፡)
ዘ-ህወሀት ሁሉንም መጥፎ ዜናዎች ሁሉ ፍጹም በሆነ መልኩ ለምን እንደሚያፍን ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡
ዘ-ህወሀት የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ መጥፎ ዜናዎችን በማፈን የጦርነት ወሬዎችን ከማምረት እና የጦርነት ነጋሪት ከመጎሰም የተሻለ ምን የተሻለ ስልት ሊኖረው ይችላል?
በዘ-ህወሀት እና በስተሰሜን በኩል ባሉት ጠላቶቹ መካከል የሚካሄደው ጦርነት በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው የጽጌረዳ ጦርነት ዓይነት ነው፡፡ የተለያዩ አባላት በሆኑት በአንድ ቤተሰብ መካከል የሚደረግ ጦርነት የውስጥ ጦርነት ነው፡፡
ዘ-ህወሀት እና ጠላቶቼ ናቸው እያለ የሚወነጅላቸው ኃይሎች በወንድማማችነት በአንድ ላይ ሆነው ለበርካታ ዓመታት በመዋጋት ወታደራዊውን አገዛዝ በማስወገድ ስልጣንን ተቆጣጠሩ፡፡ በወታደራዊ ኦፕሬሽን እና በህዝብ ግንኙት ስራ በአንድ ላይ ሆነው በመረዳዳት በወታደራዊ ጓደኝነት ሲታገሉ ቆይተው ነበር፡፡
በርካታ የዘ-ህወሀት አመራሮች ከጠላቶቻቸው ጋር የቤተሰብ እና የስጋ ዝምድና ትስስር እንዳላቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ ነው፡፡
ዘ-ህወሀት እ.ኤ.አ በ1991 ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ አሁን እየከሰሷቸው ካሉት ጋር አስቂኝ በሆነ የመድረክ ላይ ተውኔት በደስታ ስልጣንን ተካፍለው እንደ አበደ ውሻ ጭራቸውን በመቆለፍ ቆዩ፡፡ ያ ሁኑታ ግን እ.ኤ.አ በ1993-94 ላይ ተቋረጠ፡፡
እ.ኤ.አ ከ1998-2000 ባለው ጊዜ ውስጥ ሁለቱ የጦር ጓደኛሞች በድንበር ጦርነት ተጠመዱ፡፡ ኤርትራውያን የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት በመጣስ የኢትዮጵያን ግዛት ተቆጣጠሩ፡፡ ሆኖም ግን በግጭቱ ከ70 እስከ 120 ሺ የሚገመት የወታደሮች እና የሲቪል ዜጎች ህይወት ከተገበረ በኋላ ተቆጣጥረውት ከነበረው ግዛት በኃይል ተባረሩ፡፡
አሁን በህይወት የሌለው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስቡ አለቃ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወዲያውኑ የድል ዜናን አወጀ፣ እናም በዓለም አቀፍ የሽምግልና እርቅ ሰበብ በተሰላ የፖለቲካ የሸፍጥ ስሌት እና በሀገር ክዳት ወረውት የነበረውን የሀገሪቱን አንጡራ ግዛት ተመልሶ ኤርትራውያኖች እንዲወስዱት በመፍቀድ የተንበርካኪነቱን የመድረክ ላይ ተውኔት አከናወነ፡፡
አምባገነኑ መለስ ጠንካራ የሕግ መከላከል ጥረትን ማድረግ ሲችል የሽምግልና የዕርቅ ስምምነቱ የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ አያወጣም በማለት የሀገርን ጉዳይ እንደተራ ነገር በመቁጠር ጉዳዩን አጣጣለው፡፡
በአሁኑ ጊዜ የቀድሞ የጦር ጓደኛሞች በጦርነት ላይ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ የሌባ ጣቶቻቸውን አንዳቸው በአንዳቸው ላይ በመቀሰር የተለመደ ተራ ቅጥፈታቸውን በማራመድ ላይ ናቸው፡፡
ሆኖም ግን እነዚህ ውሸት እንጅ እውነት በአፋቸው የማይገባ ኃይሎች በእርግጠኝነት ጦርነት ያካሂዳሉ ወይስ ደግሞ የጦርነት ጨዋታ በመጫወት ላይ ነው የሚገኙት?
ሆኖም ግን ለምን እርስ በእርሳቸው እንደሚዋጉ ትክክለኛውን ነገር አይናገሩም፡፡
አንድ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን እንዳቀረበው ውንጀላ ከሆነ የኤርትራ መሪዎች በሰው ልጆች ላይ የመብት ረገጣ ማለትም ማሰቃየትን፣ ግድያ እና በባርነት መያዝን ጨምሮ የሰብአዊ መብትን ይደፈጥጣሉ የሚል ዘገባ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የምታቀርበው ኢትዮጵያ ናት የሚለው የመድረክ ላይ ትወና የተተወነው በኢትዮጵያ ነው በማለት በኢትዮጵያ ከምስክሮች የሚሰበሰበው መረጃ እንዳትረጋጋ ለማደረግ ጥረት ለምታደርገው ሀገር ለኤርትራ ጥሩ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ እንድታገኝ አስችሏታል፡፡
የተመድ ዘገባ ለጦርነቱ መንስኤ መሆን ችሏልን?
“ሀገሮች ለምን እንደሚዋጉ“ በሚል ርዕስ ሪቻርድ ኔድ ሌቦው በ2010 በጻፉት መጽሐፋቸው ላይ አራት ታሪካዊ ዓላማዎች፡ ፍርሀት፣ ፍላጎት፣ ዝና እና በቀል በሚል መንግስታት ጦርነትን እንዲቀሰቅሱ ይመሯቸዋል በማለት የክርክር ጭብጣቸውን አቅርበዋል፡፡ አብዛኞቹ ጦርነቶች ለዝና እና ቀደም ሲል አንዱ መንግስት በጠላቱ ላይ ድልን በመቀዳጀት ግዛቱን ያስለቀቀው ከሆነ ያንን ለመበቀል ሲባል የሚደረጉ ናቸው በማለት ይሞግታሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ዝና፣ በቀል እና ግዛትን ለመያዝ ሲባል በሁለቱ መንግስታት መካከል ለጦርነት መንስኤ ሊሆን ይችላልን?
እኔ የማደርጋቸው የአምባገነንነት እና ጦርነት ጥናቶች በእነዚህ ነገሮች የሚቀሰቀስ ሌላ የተለዋጭ ገለጸ ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡
“የጦርነትን ካርድ” ማውጣት በአምባገነኖች የእጅ መጽሐፍ ውስጥ ያለ አሮጌው የማጭበርበር ዘዴ ነው፡፡
የእጅ መጽሐፉ እንዲህ ይላል፣ “የህዝብ ጥላቻ ሲመጣ ጦርነትን አውጅ፡፡ እውነተኛ ወይም ደግሞ የውሸት የማስመሰያ ጦርነት አውጅ፡፡ ምንም ዓይነት ችግር የለውም፡፡ ስለጦርነት አውራ፡፡ የጦርነት ቅስቀሳን ሆን ብለህ አሰራጭ፡፡ የጦርነት ከበሮ ምታ፡፡ የጦርነት ጨዋታዎችን ተጫወት፡፡“
ግን ለምን ጦርነት?
ምክንያቱም ጦርነት የተረጋገጠ እና በተግባር የተፈተነ የህዝብ ስሜት ማስቀዬሻ ፍቱን ዘዴ ነው!
ከሮማ ነገስታት ጀምሮ እስከ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ የጦርነት ጌቶች እና ትናንሽ አምላኮች የጦርነት ካርድን ተጫውተዋል፣ እናም በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት የግዛት ዘመናቸውን ለማስቀጠል ሲሉ በህዝቡ ልብ ውስጥ የአርበኝነት ትኩሳትን ይቀሰቅሳሉ፡፡
በምዕተ ዓመታት የጦርነት ቴክኖሎጂው ሊቀየር ይችላል ሆኖም ግን የማታለል ማሽኑ፣ ማጭበርበሩ፣ ሸፍጡ እና የጦርነት ናፋቂዎች የከበሮ ድለቃ ዜማ እና አፈጻጸም እስከ አሁንም ድረስ ያው ነው፡፡
አምባገነኖች ሁልጊዜ በጦርነት ቃላት ይጀምራሉ፣ እናም ህዝቦቻቸውን በጦርነት ውሸት ፕሮፓጋንዳዎች፣ ፍብረካዎች እና ስለጦርነት ዝርዝር መረጃዎች የሌለው እና አሳሳች መረጃዎችን በማቅረብ በፕሮፓጋንዳ ጎርፍ እንዲጥለቀለቅ ድርጋሉ፡፡
አምባገነኖች በጦርነት መጀመሪያ አካባቢ ሊተነበይ የሚችል የአካሄድ ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለጦርነቱ አስፈላጊነት ግዙፍ የሆነ መግለጫ ለህዝብ ያቀርባሉ፣ እንደዚሁም ሁሉ በሀገር ውስጥ ታላቅ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ተስፋን በመሰነቅ በጠላታቸው ላይ ግዙፍ የሆነ ጥላሸት የመቀባት ዕኩይ ምግባርን ያራምዳሉ፡፡
ታምራዊ በሆነ መልኩ የእናት ሀገር ፍቅርን ከመቅጽበት ይለብሳሉ፣ በሰንደቅ ዓላማዎቻቸው ውስጥ ይጠቀለላሉ እናም ኃያል አርበኞች ይሆናሉ፡፡ አርበኝነትን ለማነሳሳት በመሞከር የተወሰዱ ግዛቶችንም እናስመልሳለን በማለት ቃል ይገባሉ፡፡
አምባገነኖች የህዝቡን ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ዓይን ባወጣ መልኩ በሀገር ወዳድ ብሄራዊነት እና የትምክህት እንቅስቃሴዎችን ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡ ስለማይቀረው የጦርነት ጥቃት፣ ስለማይታዩ ጠላቶች፣ ሳይታሰብ ስለሚመጡ አሸባሪዎች፣ ስለሀገር ሉዓላዊነት መደፈር እና ስለሌሎች ነገሮችም ሁሉ ገደብ የሌለው ፕሮፓጋንዳ እና ቅስቀሳ በማካሄድ በህዝቡ ዘንድ ፍርሀት እንዲነግስ ያደርጋሉ፡፡
በሚያገኙት በማንኛውም አጋጣሚ ሁሉ ህዝቡ ስሜታዊ ሆኖ በጠላቶቻቸው ላይ በቁጣ እንዲነሳ በመቀስቀስ የህዝብን ድጋፍ ለማግኘት አሳፋሪ እና የሌለ ታሪክ በመፍጠር እነርሱ አገር ወዳድ አርበኛ የእነርሱ ተቃዋሚዎች እና ጠላቶች ደግሞ ምንም ዓይነት የሀገር ወዳድነት አርበኛነት የሌላቸው አድርገው ይፈርጃሉ፡፡
ሁሉም ነገር ሲከሽፍ እና ሲወድቅ አምባገነኖች በህዝቡ ላይ ፍርሀት እና ስሜታዊነት እንዲነግሱ በማድረግ የህዝብን ስሜት በማስቀየስ እነርሱ ከተዘፈቁበት ሰብአዊ ወንጀል እና አምባገነናዊ አገዛዝ ለማምለጥ ጥረት ያደርጋሉ፡፡
አብዛኛውን ጊዜ የጦርነት ቃላት ስለአርበኝነት እና ስሜታዊነት በመቀስቀስ ከመክሰስ እና ጥላሸት ከመቀባት የበለጠ ኃይል የላቸውም፡፡ ወደ ሌላ ወደየትም ፈቀቅ ሳይሉ ስም በማጥፋት እና ጥላሸት በመቀባት ላይ ብቻ ተወስነው ይቀራሉ፡፡
ሆኖም ግን አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በጦር ሜዳ አውድ ውስጥ የጥይት ጭሆት ካቆመም በህዋላ ስለጦርነት ማውራት እና የጦርነት ነጋሪት መጎሰምን አጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡
ሆኖም ግን ጦርነት ለአምባገነኖች የማታለያ ሀሳብ ነው፡፡
የአምባገነኖች የመኖር ህልውና በጀመሩት ጦርነት የማሸነፍ ዝንባሌ የሚወሰን ይሆናል፡፡
በጦርነት የአምባገነኖች መሸነፍ ማለት የህልውናቸው ፍጻሜ ማለት ነው፡፡
የተሸነፉ አምባገነኖች አብዛኛውን ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት ወይም ደግሞ በሌሎች ህዝባዊ አመጾች ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ አምባገነኖች በሚሸነፉበት በእያንዳንዱ ጦርነት የመሰደድ፣ የመታሰር እና የመሞት ዕድላቸው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
ጥቂት የአፍሪካ አምባገነኖች ዓይን ባወጣ መልኩ ያለምንም ተጨባጭነት ሁኔታ በለኮሱት ጦርነት ቢሸነፉም ቅሉ ለበርካታ ጊዚያት በስልጣን ላይ ተጣብቀው ቆይተዋል፡፡ በእርግጥ ሽንፈታቸውን ለምክንያት እና ለይቅርታ በመጠቀም ህዝቦቻቸውን ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ለመግዛት ይጠቀሙበታል፡፡ ጠላቶቻቸውን እንደ ጭራቅ በመቁጠር በእራሳቸው ህዝቦች ላይ እንደማስፈራሪያ በመጠቀም ህዝቡ ለጥ ገጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ይጠቀሙበታል ፡፡
አምባገነኖች ስለሚጭሩት የጦርነት እሳት እውነታነት የሂትለር ቀኝ እጅ ከነበረው ከኸርማን ጎሪንግ የበለጠ እውነታውን ያረጋገጠ በዚህ ዓለም ላይ የለም፡፡ ኸርማን እ.ኤ.አ በ1945 ኑረምበርግ በተሰየመው የዓለም አቀፍ ችሎት ላይ ቆሞ ሲጠየቅ እንዲህ በማለት ተናግሮ ነበር፡
“በተፈጥሮ ተራው ህዝብ ጦርነትን አይፈልግም፡፡ ይኸ ነገር ግንዛቤ የተወሰደበት ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከሁሉም በላይ የሀገሪቱ መሪዎች ናቸው ፖሊሲውን የሚወስኑት እናም በዚያ አቅጣጫ ህዝቡን የሚስቡት… ድምጽ ወይስ ድምጽ አልባ [ዴሞክራሲያዊ ወይስ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ያልሆነ መንግስት] ህዝቡ ምንጊዜም ቢሆን መሪዎች በሚያስቡት ነገር ላይ ሊመጣ ይችላል፡፡ ያ ቀላል ነገር ነው፡፡ ሁላችሁም ልትሰሩት የምትችሉት ነገር ቢኖር ጥቃት እየደረሰባቸው መሆናቸውን ንገሯቸው፣ እናም የአርበኝነት ጉዳይን ቸል በማለት ሀገሪቱን ለከፍተኛ አደጋ በሚጥሉት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ውግዘት አካሂዱ፡፡ ይህ ጉዳይ በእያንዳንዱ ሀገር ሙሉ በሙሉ ይሰራል፡፡“
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 አሁን በህይወት የሌለው የወሮበላ ዘራፊው ሀዋሃት መሪ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የጎሪንግን አባባል እንዳለ በመውሰድ እንዲህ በማለት የገደል ማሚቶውን አሰምቶ ነበር፡
“አሁን በቅርቡ ኤርትራ አልሸባብን እና በሀገር ውስጥ የበቀሉትን አውዳሚ ኃይሎች በማሰልጠን በሀገራችን ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ ሆኖም ግን ግብጽ ለዚህ የሽብር ድርጊት በዋናነት ከጀርባ ቆማለች፡፡ እስከ አሁን ድረስ የነበረን ስልት ልማታችንን በማፋጠን የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ዝም ብለን በቸልታ ቆመን ምንም ዓይነት መከላከል ሳናደርግ የምናይበት ሁኔታ የለም፡፡ ዝም ብሎ መከላከል የሌለው ድርጊትን እያራመድን መቆየትን እንደ ብቸኛ አማራጭ አድርገን ለመቀጠል አንችልም፡፡ ስለዚህ የኤርትራ ህዝብ አምባገነኑን አገዛዝ ለማስወገድ የሚያደርገው ትግል እንዲፋጠን መንገድ መቀየስ አለብን፡፡ ይህንን ስንል እንዲሁ ዘው ብለን በሀገራቸው ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ እንገባለን ማለት አይደለም፣ ሆኖም ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነውን እጃችንን ረዘም አድርገን ወደዚያ መላክ ይኖርብናል፡፡ የኤርትራ መንግስት በእኛ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚሞክር ከሆነ እኛም ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ እንሰጣለን“ ነበር ያለው አፈር ይቅለለውና፡፡
እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረትን ከሶማሊያ ለማስወጣት እና አልሻባብን ለማጥፋት 843 ቀናት ያህል ጦሩን እዚያ ካቆየ በኋላ ስኬታማ ሳይሆን ሀፍረቱን ተከናንቦ ሰራዊቱን ከሶማሊያ በሚያስወጣበት ወቅት በተመሳሳይ መልኩ እንዲህ በማለት ነበር የጦርነት አመክንዮውን የገለጸው፡
“አካላዊ ጉዳትን በሚመለከት ወይም ደግሞ የወረራው አካላዊ ሁኔታን በሚመለከት ካለፈው የክረምት ወቅት ጀምሮ ምን እንደተደረገ ለመግለጽ የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የታጠቁ ኃይሎችን በማሰልጠን፣ በማስታጠቅ እና ሰርገው እንዲገቡ በማድረግ ላይ ቆይቷል፡፡ እነዚህ ኃይሎች በኢትዮጵያ ውስጥ መረጋጋት እንዳይኖር ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩት እነዚህ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው በመግባት ከደህንነት ኃይሎች ጋር ግብግብ በመግጠም ላይ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህልም የእስልምና ፍርድ ቤቶች ህብረት እነዚህን ሰርጎ ገብ ኃይሎች  አሰልጥኗል፣ አስታጥቋል፣ እስከ ድንበሩ ድረስ ለሰርጎ ገቦቹ የመጠለያ እና የትራንስፖርት አገልግሎትም አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ ላይ የጥቃት እርምጃ ለመውሰድ ቀጥተኛ በሆነ መንገድ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ድርጊት ካለፈው የክረምት ወቅት ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ እስከ አሁንም ድረስ ቀጥሏል፡፡“ 
እ.ኤ.አ በ2009 ጭራውን በእግሮቹ መካከል በመወተፍ ከሶማሊያ ሲወጣ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የፈላስፋ ሸፍጡን በመያዝ እንዲህ በማለት ጉራውን ቸረቸረ፣ “ለኢትዮጵያ አዎንታዊ አመላካከት የሌለው የሶማሊያ ህዝብ መንግስት ቢኖርም እንኳ በአሁኑ ጊዜ ያለው ሁኔታ የተሻለ ነው፡፡ በሶማሊያ ውስጥ የተረጋጋ መንግስት እንዲኖር ማድረግ ብሄራዊ ፍላጎታችን ነው፡፡“        
ይኸው አምባገነን ሰው እ.ኤ.አ ታህሳስ 2006 አሸባሪዎችን ከሶማሊያ ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድል በማድረግ አባርረን እንመለሳለን ብሎ ነበር፡፡
አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የሰራው ነገር ቢኖር በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪል ሶማሊያውያን ሞትና እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ የጅምላ ተፈናቃይ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡
በሶማሊያ ውስጥ ሄደው የሞቱ የመለስ ዜናዊ የጦር ወታደሮች ብዛት ስንት ነው?
እ.ኤ.አ በ2009 አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከይስሙላው ፓርላማ ፊት በመቅረብ እንዲህ በማለት ተናገረ፣ “በሶማሊያ ውስጥ ስንት ወታደሮች እንደሞቱ ፓርላማው ማወቅ አስፈላጊው አይደለም፡፡“
አምባገነኖች ህዝቦቻቸውን የጦርነት እራት እንዲሆኑ በማድረግ በጦርነቱ ምን ያህል ወታደሮች እንደሞቱ ማወቅ የእናንተ ስራ አይደለም በማለት መናገር ይችላሉ፡፡
እንደዚሁም ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ዘ-ሀወሀት እና ኤርትራ የጦርነት ከበሮ በመደለቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በጦርነት ከበሮው የድምጽ ቅላጼ በመደነስ ላይ ይገኛሉ፡፡
በእርግጥ አስገዳጁ የጦርነት ማስጠንቀቂያ ሁልጊዜ ከሚጠበቁት ሲመጣ የቆየ ነው፡፡
የዩኤስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ጥላቻው በአስቸኳይ እንዲቆም” እና “ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሁለቱም መረጋጋትን ለማስፈን እንዲተባበሩ እና በቀጣናው ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ” በማለት የተለመደ የተዕማጽኖ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ ባንኪሙን ኢትዮጵያ እና ኤርትራ “ከሰባት ዓመታት በፊት የድንበር ውዝግባቸውን በሰላም እንዲፈቱ የቋጨውን ሕግ በማክበር ከማንኛውም ጠብ አጫሪነትን ከሚቀሰቅሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል“ የሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዋና ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት ጉዳይ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለው ጦርነት ነው ወይስ ደግሞ የጦርነት ጨዋታዎች ናቸው የሚለው ነው፡፡
እኔ የማውቀው ነገር የለኝም!
ለእኔ የጦርነት ጨዋታዎችን እያካሄዱ ይመስለኛል፡፡
ሁለቱም ወገኖች በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ገደልን አቆሰልን እያሉ በመለፍለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
ለእኔ ሁሉም ነገር አጠራጣሪ ነው፡፡
እኔ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር ቢኖር ይህንን የሰርከስ ተውኔት ቀደም ሲል የተመለከትኩት መሆኑን ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 ዘ-ህወሀት ሲፈጽም የነበረውን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ፣ ሙስና፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀምን እና ሌሎችንም ዕኩይ ድርጊቶች መፈጸሙን በማስመልከት ለመደበቅ እና የኢትዮጵያን ህዝብ እና የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ስሜት በማስቀየስ ላይ ዒላማ ያደረገ ባለሶስት ዙር የፖለቲካ ጦርነቶችን የፕሮፓጋንዳ ሰርከስ ተመልክቻለሁ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉም ስለጦርነቱ እየተደረገ ያለው ንግግር እና የጦርነት ነጋሪት ጉሰማ ዘ-ህወሀትን ጥልቅ በሆነ መንገድ ሊያስወግድ የሚችል ድብቅ የህልውና ጦርነት ነውን?
በእኔ አስተያየት ግብታዊ በሆነ ህዝባዊ አመጽ ምክንያት ዘ-ህወሀት አእምሮው በማይቀረው ስልጣኑን እና ቁጥጥሩን የማጣት አባዜ ውስጥ ተዘፍቆ ስለሚገኝ የማስመሰያ የፍርሀት ጋጋታ ጨዋታ ነው፡፡ ሁሉም የጦርነት ዲስኩሮች በድብቅ አእምሮ ውስጥ ተሸብቦ ለሚገኘው አገዛዝ ጥልቅ ፍርሀት እና መሰረታዊ የሆነ የፖለቲካ ብስጭትን የሚገልጹ ናቸው፡፡
ፕሬዚዳንት ኬኔዲ በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “ቀደም ሲል  በቂልነት በነብር ጀርባ ላይ ሆነው መጋለብን ይፈልጉ የነበሩ ሰዎች መጨረሻቸው በነብሩ ሆድ ውስጥ ሆነው መገኘት ነው፡፡“
ወደፊት በተቆጣ እና በተራበ የነብር ሆድ ውስጥ ሆኖ የመገኘት ዕድል የዘ-ህወሀትን አመራሮች እና ደጋፊዎች ሌት ቀን እንቅልፍ ነስቶ ሁሉንም ቀናት የጦርነት ነጋሪትን በመጎሰም እንዲቆዩ አስገድዷቸዋል፡፡
ዘ-ህወሀት ስለጦርነት በጥልቅ በማሰብ ላይ ይገኛል፣ ሆኖም ግን ከኤርትራ ጋር ስለሚያካሂደው ጦርነት አይደለም፡፡
እያሳሰበው እና ሌት ቀን ረፍት ነስቶ እያሰጨነቀው ያለው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ነው፡፡
እኔ ስለዘ-ህወሀት እውነቱን በመናገር ላይ ነው ያለሁት ምክንያቱም የዘ-ህወሀት አባላት እያንዳንዳቸው ሁልጊዜ እየተነጋገሩ ያሉበት ጉዳይ ስለሆነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ ቢያድርግ ምን…? በማለት ብርክ ይዟቸዋል፡፡
እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 የጦርነት ማቆሚያ ስለመሆኑ ወይም ደግሞ ቀደም ሲል ጀምሮ የሚተዋወቁት ወንድማማች ቡድኖች የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ ሲሉ የጦርነት ጨዋታዎችን ሲያካሂዱ ለማየት ስለመቻሌ በእርግጠኝነት የማውቀው ነገር የለም፡፡
በአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ላይ ያሉ ባሉ ቡድኖች መካከል ጦርነት ሊካሄድ ይችላልን? በማህጸን ውስጥ ያሉ አንድ ዓይነት መንትዮች በህይወት ለመቆየት የአንዱ መኖር ለሌላው ህልውና አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱ አሸባሪ ቡድኖች በስልጣናቸው ላይ ለመቆየት እያንዳንዳቸው እርስ በእርስ ይፈላለጋሉ፡፡ ያላንዱ ህልውና የሌላው ህልውና ሊቆይ እንደማይችል ያውቃሉና፡፡
በአሁኑ ጊዜ ጦርነት ማናቸውም ቢሆኑ የማይፈልጉት ነገር ነው፣ እናም ይህንን በሚገባ ያውቁታል፡፡
እ.ኤ.አ ጥቅምት 2015 የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ተግባራዊ እንዲሆን አጽድቋል፡፡ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ የተጣለበት ሀገር ጦርነትን አካሂዶ ስለማሸነፉ ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው፡፡
ጨካኝ እና አረመኔ የነበረው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔቪል ቻምበርላይን በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፣ “በጦርነት ጊዜ የትኛውም ወገን እራሱን አሸናፊ ነኝ በማለት ሊጠራ ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን አሸናፊ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ሁለቱም ወገኖች ተሸናፊዎች ናቸው፡፡“
በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ማን ነው ተሸናፊ ሊሆን የሚችለው?
ስለጦርነት ሁለት ዝሆኖች በሚገጥሙ ጊዜ የሚጎዳው ሳሩ ነው የሚል የተለመደ አባባል አለ፡፡
በዝሆኖች መካከል በሚደረገው ጦርነት ሳሩ አሸናፊ ሆኖ ሊወጣ የማይችለው ለምንድን ነው?
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 እንዲህ በማለት ጽፌ ነበር፣ “ከኤርትራ ጋር ጦርነት ወይም ደግሞ ጣልቃገብነት ለማድረግ ስለመሞከሩ እና ከግብጽ ጋር የውኃ ጦርነት ስለመደረጉ ወደፊት ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል… ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በዚያ ዕጣ ፈንታ ላይ ማንም ቢሆን ዓይኑን ለአንድ አፍታም ቢሆን አይነቅልም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሊደረግ የሚችለው ብቸኛው የዜናዊ ጦርነት የህዝብን ስሜት የማስቀየስ ጦርነት ብቻ ነው“ ብዬ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ሚያዝ 2011 “የኤርትራ ህዝብ አምባገነኑን አገዛዝ ለማስወገድ ፈጣን መንገድ መከተል አለበት“ በማለት ዜናዊ አስፈራርቶ ነበር፡፡
ያለፉት አምስት ዓመታት እውነታ ለእራሳቸው ይናገራሉ፡፡
ምንም የማታውቅ ሞኝ ነህ ብላችሁ ጥሩኝ፡፡ ከዚህም በላይ ስለጅኦ ፖለቲካ ምንም ዓይነት ግንዛቤ የሌለኝ ትላንት እንደተወለድኩ አድርጎ መናገር ይቻላል፡፡
ምንም የማላውቅ እና ትላንት እንደተወለድኩ አድርጎ ማየቱ እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ትላንት ማታ አልተወለድኩም!
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2011 የተናገርኩትን እንደገና እ.ኤ.አ ሰኔ 2016ም እደግመዋለሁ፡፡ “የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የህዝብን ስሜት ለማስቀየስ የተደረገ የጦርነት ጨዋታ ነው፡፡”Posted in Amharic Translations By almariam
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  
ሰኔ 13 ቀን 2008 ዓ.ም