Sunday, 7 February 2016

ይህ ካርታ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አንድ ማስታወቂያ ላይ መታየቱ እየተነገረ ነው። በእርግጥ በህወሀት መንግስት የውስጥ ሰነዶች የሚገኘው ይህ ካርታ ነው። የአማራውን ወሰን ሙሉ በሙሉ ከድንበር እንዲሸሽና በፊት ከሱዳን ጋር ስንዝር መሬት የማይዋሰነው የትግራይ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን ከሱዳን ጋር ይጋራል። ካርታው እንደምርጫ ቦርድ ባሉ መስሪያ ቤቶች እንደሚገኝም ተረጋግጧል። በትግራይ በአንድ የማስተማሪያ መጽሀፍ ላይ ዳሽን ተራራ ከአማራ ክልል ወጥቶ በትግራይ መጠቃለሉን ኢሳት ዘግቦ እንደነበረ ይታወሳል። ሶስት ነገሮችን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ህወሀት
1. በጉልበት ወልቃይትን ከማንነት ጭምር ወስዷል።
2. ከሱዳን ጋር ድንበሩን ከኢትዮጵያ ህዝብ ተደብቆ ማካለሉን ከጫፍ አድርሶታል።
3. በቅማንትና በአማራ ማህበረሰቦች መሃል ክብሪት ጭሯል። አማራን ከሌሎችም ጋር በእርስ እርስ ግጭት ለመጥመድ እየተዘጋጀ እንደሆነ መረጃዎች ይፈነጥቃሉ።
እነዚህን በድል ካጠናቀቀ በጓሮ የሚጠቀማትን ይህቺን ካርታ አደባባይ ያወጣታል። ደደቢት የጠነሰሳትን ህልሙን ለማሳካት ጥርጊያ መንገድ ይከፍትለታል።

No comments:

Post a Comment