«ለአፍሪካዊያን ዲሞክራሲ ቅንጦት ነው፣ የሚገባቸው ዲሞክራሲ ሳይሆን መልካም አስተዳደር ነው።»

ግና ገና ከጅምሩ በፖለቲካው መክሸፍ ሲያበዛ እየታዘብን ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ የሚሰጣቸው አስተያየቶች በእዝላልነት ይሁን ወይም ፖለቲካውን ባለመረዳት አላውቅም ብዙውን ጊዜ ግራ የሚያጋቡ ናቸው። … ዲሞክራሲ በሌለበት አኳኋን መልካም አስተዳደርን እንዴት ማስፈን እንደሚቻል አይገባኝም! ኃይሌ ለፖለቲካዊ ነገሮች በጣም የፈጠነ ይመስለኛል፤ ሰከን ረጋ ብሎ ብዙ ጥናቶችን ቢያደርግ ብዙ ጥሩ ነገሮችን አውቆ ማሳወቅ በቻለ ነበር። ለጥናት የሚሆን በቂ ባጀት ባይኖረውም ቅሉsmile emoticon
ሌላውና ሁሌም ሳስበው የሚገርመኝ ነገር ደግሞ የልጆቹ አፈ ፈረንጅነት ነው። እስቲ አስቡት ኃይሌ ተወዳድሮ አሸንፎ የአገሪቱ መሪ ሲሆንና EBC ዶክመንተሪ ሲሰራለትና የልጆቹ ቃለ ምልልስ እየተተረጎመ ሲነገረን wink emoticon … ምናለ እንደው አማርኛው እንኳ ቢቀር ኣፋን ኦሮሚኛ ቢያስተምራቸው?? … እስከማውቀው ድረስ ልጆቹ ኦሮሚኛም አይችሉም።ግን! ሁሌም እንደምናከብርህ፣ ሁሌም እንደምንኮራብህ፣ ሁሌም እንደምንወድህና የምንጊዜም ጀግናችን እንደሆንክ ትላንትም መስክረናለን ዛሬም እንመሰክራለን ነገው ደግመን እንመሰክራለን።
ይቺን የፖለቲካ ነገር ግን እንደጫማህ ወዲያ ወደ ቆጡ ብትሰቅላትና ዝም ብለህ ቤተስኪያን እየሳምህ ብትኖር ደስ ይለኛል by ሳተናው
No comments:
Post a Comment