በስያሜ ቢሆን ኖሮ ብዙ ስፍራዎች አሁን ባሉበት ክልል ባልቀጠሉ ነበር፡፡ለምሳሌ ወልቂጤ (የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ),ጉራ ፈርዳ(ቤንች ማጂ),ቡታ ጅራ(ጉራጌ ዞን), ጉባ ላፍቶ(ሰሜን ወሎ),ቦረና (ደቡብ ወሎ),ቡሬ(ጎጃም) እና የመሳሰሉት የኦሮምኛ ስያሜዎች ናቸዉ፡፡ከተሞቹ ግን የኦሮሞ መኖሪያ አይደሉም፡፡
የአማርኛ ስያሜዎችንም እንመልከት አርባ ምንጭ(ደቡብ),ሀገረ ማርያም(ኦሮምያ),ደብረዘይት(ኦሮሚያ), አዲስዓለም(ኦሮሚያ) እና የመሳሰሉት የአማርኛ ስያሜዎች ናቸዉ፡፡ስፍራዎቹ ግን የአማራ መኖሪያዎች አይደሉም፡፡
የአማርኛ ስያሜዎችንም እንመልከት አርባ ምንጭ(ደቡብ),ሀገረ ማርያም(ኦሮምያ),ደብረዘይት(ኦሮሚያ), አዲስዓለም(ኦሮሚያ) እና የመሳሰሉት የአማርኛ ስያሜዎች ናቸዉ፡፡ስፍራዎቹ ግን የአማራ መኖሪያዎች አይደሉም፡፡
ስያሜዎች በአብዛኛው የሚያመላክቱት የሕዝቦችን አብሮ መኖር እንጂ ባለቤትነትን አይደለም፡፡ለምሳሌ በጎንደር በኩል ከሱዳን ጋር በምንዋሰንባቸዉ ቦታዎች ላይ የሱዳንኛ ስያሜ ያላቸው መሬቶች አሉን፡፡ሉገዲ,አቦጢር,ገላሉባን,ከረደም,ስናር,መንደካና የመሳሰሉት መሬቶቻችን ስያሜዎች አማርኛ አይደሉም፡፡
የሰዎችም ስም ቢሆን እንዲሁ ነዉ፡፡ብዙ ኦሮሞዎች የአማርኛ ስሞችን ይጠቀማሉ፡፡ቁጥራቸዉ ቢያንስም አማራዎችም የኦሮምኛ ስሞችን ይጠቀማሉ፡፡ትግርኛም እንዲሁ ነዉ፡፡ለምሳሌ የወልቃይት የአማራ ማንነት አንቀሳቃሽ ኮሚቴዎች ዉስጥ ብዙ የትግርኛ ስም ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡
የሰዎችም ስም ቢሆን እንዲሁ ነዉ፡፡ብዙ ኦሮሞዎች የአማርኛ ስሞችን ይጠቀማሉ፡፡ቁጥራቸዉ ቢያንስም አማራዎችም የኦሮምኛ ስሞችን ይጠቀማሉ፡፡ትግርኛም እንዲሁ ነዉ፡፡ለምሳሌ የወልቃይት የአማራ ማንነት አንቀሳቃሽ ኮሚቴዎች ዉስጥ ብዙ የትግርኛ ስም ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡
ወያኔዎች መሬታቸዉ ላይ ማረስ ስለማይችሉ ብቻ የጎንደርን መሬት በመዉሰድ በግድ ትግሬ ናችሁ ብሎ ከሚጨፈልቋቸዉ እባካችሁ መሬታችን ለእርሻ ስለማይመች መጥተን እንረስ ቢሉ የወልቃይት ሕዝብ ይተባበራቸዉ ነበር፡፡አሁን ግን በማንነቱ መጡበት፡፡
ቀልድ ቢጤ ልጨምርና ልጨርስ
ቀልድ ቢጤ ልጨምርና ልጨርስ
አንድ የፌደራል ፖሊስ አንዲትን በግ ይይዝና “ፍየል ነሽ” እያለ ይገርፋታል፡፡በጊቱም ድብደባዉ አድክሟት ስትልፈሰፈስ ወደ ባልደረባዉ አምጥቶ “ይቻት ፍየሏ” ይለዋል፡፡ባልደረባዉም “ይቺ እኮ በግ ነች ፍየል አይደለችም” ሲለዉ ፌደራል ፖሊሱም በመናደድ “ፍየል ነች ፍየል ነኝ ብላ አምናለች” ብሎ መለሰለት አሉ፡፡
አሁንም ወያኔ የወልቃይት አማራዎችን ላለፉት 25 ዓመታት በግድ ትግሬ ናችሁ እያለ ቀጥቅጦ እየገዛ “እኛ ትግሬ ነን ብለዋል፡፡” እያለ የጅል ቀልዱን ይቀልዳል፡፡
(Bethel Moges Aragaw) by ሳተናው
አሁንም ወያኔ የወልቃይት አማራዎችን ላለፉት 25 ዓመታት በግድ ትግሬ ናችሁ እያለ ቀጥቅጦ እየገዛ “እኛ ትግሬ ነን ብለዋል፡፡” እያለ የጅል ቀልዱን ይቀልዳል፡፡
(Bethel Moges Aragaw) by ሳተናው
No comments:
Post a Comment