Saturday, 13 February 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ

በአማራ ክል ከዞን እስከ ወረዳ ድረስ የአመራር ሹም ሽር እየተካሄደ ነው፡፡ የሰሜን ጎንደር አስተዳደር ሹም ግዛት አብዩ ከመጀመሪያዎቹ ተባራሪዎች መካከል አንዱ ሆኗል፡፡
===================================================
በአማራ ክልል ከዞን እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ሰሞኑን በግምገማ የተጠመዱ ሲሆን በዚህ መካከልም ከሹመታቸው የተባረሩ በርካታ ባለስልጣናት እንዳሉ እየተነገረ ነው፡፡ ወደፊትም ብዙ ባለስልጣናት ከወንበራቸው እንደሚነሱ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ የላኩት መረጃ አረጋግጧል፡፡
የሰሜን ጎንደር አስተዳደር ሹም ግዛት አብዩ ስልጣኑን ተነጥቆ ለጊዜው የት እንደደረሰ ያልታወቀ ሲሆን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበረው ሙሉጌታ ወርቁ እሱም ከክልል ወደ ዞን አስተዳደር ዝቅ ብሎ በቦታው መተካቱ ተዘግቧል፡፡

No comments:

Post a Comment