Thursday, 18 February 2016

የሁሉም ጠላት ወያኔ ነው! – ከአንተነህ መርዕድ

ወያኔ የኦሮሞ ጠላት ነው
Woyaneመለስ ሲያጉረመርምበት ብርክ የሚይዘውና የሚሙለጨለጨው፣ ጓደኞቹን ደጋግሞ በፍርሃቱ የሸጠው አባይ ፀሃዬ ዞር ዞር ብሎ ሲመለከት ከሱ የተሻሉና የሚያስፈሩት ህወሃቶች የሌሉ መሆናቸውን በማረጋገጡ በየመድረኩ ብቅ እያለ መፎከርና መዘባረቅ የእለት ተእለት ሥራው ሆኗል። በተለይም በዋና ባለቤትነት የአዲስ አበባን መሬት ሸጦ ከጨረሰ በኋላ የአካባቢውን ገበሬዎች ከነመሬታቸው ሊቀራመት ያደባበት ተንኮል አልሠራ ሲል “ልክ እናስገባቸዋለን”ሲል ፎከረ።  አሁን ደግሞ ፉከራው የለኮሰውን እሳት ማዳፈን ተስኖት “ወያኔ የኦሮሞ ጠላት አይደለም”  የሚል የሽሽት ሽምጥ ሩጫ ይዟል። እሳቱ ግን እሱን ሳይለበልበው የሚመለስ አይደለም።
ወያኔ ወደ ምኒልክ ቤተመንግሥት ሲገሰግስ ኦነግን ከተኛበት ቀስቅሶ ያመጣው ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ብሎ ሳይሆን በኦነግ እጅ ኦሮሞውንና ሌሎችንም ለመሸንቆጥ ወይም ልክ አስገብቶ ለመግዛት መሆኑን ለማወቅ ቀናት አልወሰደም። ወያኔዎች እንኳን ለኦሮሞው፣ ቆመንለታል ላሉት የትግራይ ህዝም ቢሆን ገና ከመጀመርያው ጠላቱ እንደሆኑ ድርጊታቸው መስክሯል። ህወሃት ጠፍጥፎ የሠራውን ኦህዴድን ማንም ስለማያውቅና ስለማይቀበለው ኦነግን ለመሸጋገርያነት ማዘጋጀታቸውን የማያውቁት የጊዜው የኦነግ አመራሮች ብቻ ነበሩ። ኦነግ ሳይሆን በስሩ የተሰባሰበው ህዝብ የወያኔን ተንኮል ቀድሞ በመረዳቱ አልገዛም ሲላቸው ወያኔዎች ሰይፋቸውን የመዘዙት በጓደኞቻቸው የኦነግ አመራሮች ሳይሆን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ነው። አመራሮቹን ቀስ አድርገው ከአገር ከመሸኘታቸው በፊት “ሰራዊታችሁን ካምፕ ውስጥ አስገቡልን”  አሏቸው።  በአሜሪካና በሻዕብያ ዋስትና ሰጭነት ሰራዊቱን ከህዝቡ መሃል አስወጥተው ካምፕ አስገቡላቸው። የሚገርመው የተመረጡት ካምፖች ከወያኔ ሰራዊት በቅርብ እርቀት ላይ ተወስነው በቀላሉ የሚደርስባቸው እንዲሆኑ የተመቻቹ መሆናቸው ነው። በጊዜው ኦነግን ወክሎ ምርጫ ለማስፈፀም ደሴ ተመድቦ ከነበረው የኦነግ አመራር አባል ከሆነው ነገሪ ፈይሳ ጋር ለመገናኘትና ለመግባባት እድል አግኝቼ ነበርና  ካምፕ ማስገባቱም ሆነ የተመረጡት ቦታዎችን አደገኝነት፣ ሻዕብያና አሜሪካ ከኦነግ ይልቅ ወያኔን የኋላ ኋላ እንደሚደግፉ ሃስቤን ስሰነዝርለት የሁኔታውን አሳሳቢነት የተረዳ አልነበረም። ጉዳዩ  እንግዳ ቢሆንበትም ኋላ ላይ በከፋ ሁኔታም ቢሆን ሳይማር አይቀርም።  የሆነውም ይሄው ነው። ወዳጄ ነገሪ ፈይሳና እነ ሌንጮም ሰራዊቱን አስረው አስረክበው  እነሱ በቦሌ የመውጣት የቪዛ ሽልማት አገኙ። የገረመኝና እስከ አጥንቴ የሰበቀኝ ነገር፤ ያለምንም ፋታ ኦሮሞዎችን በመጨፍጨፍና በማሰቃዬት የተካነውን መለስ ዜናዊን እስትንፋሱ በሞት እስክታቆም ድረስ ሲገናኙት መኖራቸውን ሌንጮ ለታ ሲናገሩ የሰማሁ እለት ነው። በምን ተስፋ? በምን ውለታ? አቶ ሌንጮ!
በወቅቱ የወያኔን ሰራዊት የሚመራው  የመከላከያ ሚኒስትሩ ስዬ አብርሃ  በካምፑ ውስጥ ያሉትን  በመክበብ የሚገድለውን ገድሎ የተረፈውን እስር ቤት ውስጥ ሞላቸው። እስር ቤቶች ኦሮምኛ መናገር የጀመሩት ስዬ ከጓደኞቹ ተጣልቶ እስር ቤት በገባበት ወርቅት ሳይሆን እሱና ጓደኞቹ የኦሮሞን ልጆች እንደ አውሬ እያደኑ በገደሉና ባሰሩ ጊዜ ነበር። “የአይጥ ምስክሯ ዲንቢጥ”  እንዲሉ “እስር ቤቶች ኦሮምኛ ይናገራሉ አለ ስዬ” እየተባለ ሲጠቀስ ይገርመኛል። እውነቱ እውነት ቢሆንም የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ምስክርነት ግን የሚጠይቅ አይደለም። ወያኔ ገና ጫካ እያለ ያቀደውን ነው ተግባራዊ ያደረገው። ስዬ፣ ገብሩ፣ አዳነች ወዘተ እጃቸውን እንደጲላጦስ እየታጠቡ ከደሙ ንጹህ ለመሆናቸው ብዙ ሊሉን ይችላሉ። በድርጊታቸው እንጂ በአፋቸው የማይነግሩን እውነት ቢኖር ኢትዮጵያንና ህዝቧን የሚጠሉ መሆናቸውን ነው። በአባይ ፀሃዬና አሁን ባሉትም ሆነ በተገለሉት የህወሃት መስራቾች መካከል ምንም ልዩነት የለም ። ቢኖርማ አሁን በኦሮሞ፣ በጋምቤላው፣ በአማራው፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚሠራውን ግፍ ዝም ብለው አይመለከቱም ነበር። የትግራይ ህዝብ ተነካ ብለው አይደለም እንዴ መሳርያ ይዘው ጫካ የገቡት። ዛሬ ምነው አደባባይ ወጥተው አገር ልትፈራርስ ስትል ያልጮሁ?
ወያኔ የኦሮሞ ጠላት አለመሆኑን  ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ ተመልከቱና ፍረዱ። እስር ቤቶች በኦሮሞ የተሞሉ ብቻ ሳይሆኑ የግፉ ሁሉ መጨረሻ ዝግናኝ ኢሰብአዊ ድርጊት ሁሉ የሚፈጸምባቸው ቦታዎች ናቸው። ዝርዝሩን ለኦሮሞዎች የሚቆረቆር አካል ለቅሞ ያወጣው ቢሆንም እውነቱን አጉልቶ ያሳያልና በጥሞና ተመልከቱት። ከአምስት መቶ በላይ የሆኑ እስረኞችን ዝርዝር የያዘ ቢሆንም ሞትና የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸውን ሰማንያ ሰዎች ብቻ መርጨ ነው ያቀረብሁት። ከዚህ ዝርዝር በተጨማሪ ከየመን ተጠልፎ እስር ላይ የሚገኘውንና  የሞት ፍርድ የተፈረደበትን አንዳርጋቸው ጽጌን አትርሱ። በዚህም አያበቃም፤ ባይታሰሩም ብርሃኑ ነጋ፣ አበበ ገላው …..እያላችሁ በወያኔ እጅ ባይኖሩም እድሜልክና ሞት የተፈረደባቸውን ኢትዮጵያውያን በህሊናችሁ እያሰባችሁ ዝርዝሩን ማስፋት ትችላላችሁ። እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያውያን የትኛው ወንጀላቸው ነው ሞትና እድሜልክ የሚያስፈርድባቸው? ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን  የገደሉና እየገደሉ ያሉ ህወሃቶች ምን ሊፈረድባቸው ነው? ነፃውን ፍርድቤትም በህሊናችሁ ነፃነቱን ቃኙት።
እውነቱን ባይቀይረውም በዝርዝሩ ላይ ስህተት ካለ እታረማለሁ።

ተ.ቁ

የእስረኛው ስምፆታብሄርየተወነጀለበት ጉዳይ ፍርድ             እስር ቤት
1አበረ አሰፋ አበራወንድአማራሽብርሞትቃልቲ
2አህመድ እስማኤል ሙዳሙመድወንድኦሮሞሽብርና ለጦርነት ማነሳሳትሞትቃልቲ
3በያን አህመድ እስማኤልወንድኦሮሞሽብርና ለጦርነት ማነሳሳትሞትቃልቲ
4ዲሪቢ ኢታናገመቹሴትኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርሞትቃልቲ
5ኢብራሂም ሃሰን ናሊያወንድኦሮሞሽብርሞትቃልቲ
6ጀማል ሙስጠፋ አደምወንድኦሮሞሽብርና ለጦርነት ማነሳሳትሞትቃልቲ
7ጁሙአ ሩፋኤል አሚንወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርሞትቃልቲ
8ከዲር ሻኩር ሙሴወንድኦሮሞሽብርሞትቃልቲ
9ሊቨን ዋሪዮ ጉዮወንድኦሮሞሽብርሞትቃልቲ
10መላኩ ተፈራ ጥላሁንወንድኦማራሽብርሞትቃልቲ
11መስፍን አበበ አብዲሳወንድኦሮሞሽብርሞትቃልቲ
12ሙሃመድ አህመድ አብዱላሂወንድሶማሌሽብርሞትቃልቲ
13ሙሃመድ ሃሰን ሙሃመድወንድሶማሌሽብርሞትቃልቲ
14ታደሰ ሃይሌ መኮነንወንድአማራሽብርሞትቃልቲ
15ኡርጂ አበበ ቃበታሴትኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርሞትቃልቲ
16አብዱልራሺድ አብዱላሂምወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
17አብዱራህማን ሙሳ ኢቶሳወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
18አብዱራህማን ኢሳ ሚቴሶወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
19አብዱራሺድ ባሺር ሁሴንወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
20አበረ አሰፋ አበራወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
21አለሙ ጌትነት አባተወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
22አሊዩ ሙሚ ቦኮወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
23አማኑኤል ገመቹ ዱሬሳወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
24አመራር ባይካል ካሳወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
25አንዱዓለም አራጌወንድአማራህገመንግሥትን በሃይል መናድእድሜ ልክቃልቲ
26አሳምነው ፅጌወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
27ባካሪ ሙሃመድ አባሴናወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
28ባሺር አህመድ መክታልወንድኦሮሞለጦርነት መቀስቀስእድሜ ልክቃልቲ
30በላይ አበራ ጃቤናወንድኦሮሞሉአላዊነትን መፃረርእድሜ ልክቃልቲ
31ቦጋለ ጎንፋ ዋይሳወንድኦሮሞሉአላዊነትን መፃረርእድሜ ልክቃልቲ
32ቸርነት የማነ ታደለወንድአማራሽብርና ጦርነት መቀስቀስእድሜ ልክቃልቲ
33ዳኔል አያሌው ጮርቃወንድአማራሽብርና ጦርነት መቀስቀስእድሜ ልክቃልቲ
34ደምሰው አንተነህ ደመላሽወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
35ደርጉ ኢቴና ገመቹወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
36ዱላ ኦቲ ኦልጂራወንድኦሮሞህገመንግሥትን በሃይል መናድእድሜ ልክቃልቲ
37እማዋዪሽ ዓለሙ ወልደሚካኤልሴትአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
38ፋይራ ኪቲላ ሳንካሌወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
39ፋንታሁን ሙሃባ ሙፍቲወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
40ጌታቸው ብርሌ ደሴወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
41ገቱ ወርቁ ናደውወንድጉራጌሽብርእድሜ ልክቃልቲ
42ግርማ ረጋሳ ወይሳወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
43ጎበና በላይ አየለወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
44ጎዳና ዳዩወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
45ጎሽራድ ጸጋው አጋፋሪወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
46ሃሊማ አብዲ ሞሃመድሴትኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
47ሃሰን ሞሃመድ ሃሰንወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
48ሁሴን ኡስማን ሳፋወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
49ጃታኒ ኩኖ ቱንዳወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
50ካዲር ዝናቡ አባቡልጉወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
51ከበደ ግርማ ሁንዴወንድስልጤሽብርእድሜ ልክቃልቲ
52ከፍያለው አብዲሳ ዱፈራወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
53ክፍሌ ስንሻው ታደገወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
54ከፍያለው ተፈራ ደረሶወንድኦሮሞህገ መንግሥትን በሃል መናድእድሜ ልክቃልቲ
55ሊባን ዋሪዮ ጉዩወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
56መኮነን ወርቁ ዓለሙወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
57መንግስቱ አበበ አረጋዊወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
58መንግስቱ ሆርዶፋ ሙለታወንድኦሮሞሽብርና ጦርነት መቀስቀስእድሜ ልክቃልቲ
59መስፍን ኢታና ፉፋወንድኦሮሞሽብርና ጦርነት መቀስቀስእድሜ ልክቃልቲ
60ምስጋናው ተሰማ ተገኘወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
61ምስክር ካሳ ወንድምወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
62ምትኩ ተስፋ ፋፋወንድአማራሽብርና ጦርነት መቀስቀስእድሜ ልክቃልቲ
63ሞሃመድ ዳዲ ጃራወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
64ሞሃመድ ሁሴን ሞሃመድወንድኦሮሞሽብርና ጦርነት መቀስቀስእድሜ ልክቃልቲ
65ሙሳ ኡማር ዋዲያወንድኦሮሞሉአላዊነትን መፃረርእድሜ ልክቃልቲ
66ሰይድ ሃሳን በሺርወንድኦሮሞሉአላዊነትን መፃረርእድሜ ልክቃልቲ
67ሰለሞን አሻግሬ አምበርብርወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
68ጣሂር ሞሃመድ ኡስማንወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
69ተማም ኢድሪስ አንቾወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
70ተመስገን ባይለየኝ ጸጋውወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
71ተፈራ ማሞ ጨርቆስወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
72ተሻለ ሺፈራው ረጋሳወንድኦሮሞሉአላዊነትን በመፃረርእድሜ ልክቃልቲ
73ፅጌ ሃብተማርያም ጮማሳወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
74ዋለልኝ ሃጢሶወንድሲዳማሽብርእድሜ ልክቃልቲ
75ውድነህ ተመስገን ዓለሙወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
76ያሲን አዱኛ ዳባወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ
77የሺዋስ መንገሻ በየነወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
78የሺዋስ ምትኩ ቸኮልወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
79ይበልጣል ብርሃኑ ታፈረወንድአማራሽብርእድሜ ልክቃልቲ
80ዘይኑ አብዶ ተማምወንድኦሮሞሽብርእድሜ ልክቃልቲ

ከላይ የተዘረዘሩትን እስረኞች አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሌ ጉራጌ እያሉ ማስቀመጡ ተገቢ ባይሆንም ወያኔ በዘር ላይ አነጣጥሮ እንደሚዘምት ማሳያ ይሆናልና አስፍላጊ ሆነ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ እስረኞችና በአጥቃላይ አገሪቱ ውስጥ የሚሰቃዩት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቋንቋቸው፣ ሃይማኖታቸው፣ ፆታቸው፣ ሙያቸው የማንነታቸው መገለጫ አካል ቢሆንም ኢትዮጵያዊነታቸውን በልጦ የማንነት መታወቂያቸው ሊሆን አይችልም።
ወያኔዎቹ የህዝብ ጠላትነታቸው የሚታየው በማሰርና በመግደል ብቻ ሳይሆን በዘረፋም ነውና በዚህ መስክ ምን ያህል እንደተሰማሩ ትንሽ ማየት ያስፈልጋል።
የሃብት ዘረፋን በተመለከተ በተደጋጋሚ በብዙ ጸሃፊዎች፣ አክቲኢስቶችና ፖለቲከኞች ብዙ የተባለ በመሆኑ የዛሬ አጀንዳዬ አይደለም። መላ አገሪቷን የሚዘርፈው ወያኔ መሆኑን አዲስ አበባ ጥሩ ማሳያ ናት። ለኤርምያስ ለገሰ ምስጋና ይግባውና የምናውቀውን ተጨባጭ እውነት በአሃዝና በመረጃ እያስደገፈ በማቅረቡ የኢህአዴግን የፕሮፓጋንዳ ልሳን ሳይቀር እንዳይተነፍስ አድርጎታል። ወያኔዎች ከ1997 ዓ ም ምርጫ በኋላ በአዋጅ የአዲስ አበባን መሬት የቸበቸቡት  በሃይለስላሴ፣ በግርማፅዮን በርሄ፣ በሃይሌ ፍስሃና በነጋ በርሄ መሪነት ቢሆንም ከዚያ በፊት ገና እንደገቡ ጀምሮ የመሬት ዘረፋው ላይ ያልተሰማራ ትልልቅ ባለስልጣን የለም። ሙት ወቃሽ አያርገኝና ጄኔራል ሃየሎም አርአያ በጓደኞቹ በተቀናበረ ተንኮል ቢገደልም፣ ከገዳዩ ጀሚል ያሲን ጋር በመሬት ጉዳይ ጠብ እንደነበራቸው በጊዜው በሚድያ ላይ የምንሠራ ሰዎች የምናውቀው እውነት ነው። ሃየሎምና የህወሃት መሪዎች የአዲስ አበባን መሬት መቸብቸብ የጀመሩት ገና በማለዳው ነው። ስለሆነም አባይ ፀሃዬ ቢንፈራግጥ አይገርመንም።
አቶ ሮባ መሃመድ “እነሱ ከተማቸው ላይ ኢንዱስትሪ እየገነቡ ለእኛ የተቆረጠ ጡት የያዘ ሃውልት ይገነቡልናል” ያሉትን መራራ እውነት ወያኔዎች በምንም መልኩ የሚያስተባብሉት አይደለም። ዛሬ ትናንት አይደለም። በትዕግስት ሲመለከታቸው የነበረ ህዝብ ዕድሉን በእጁ ብቻ እንደሚያገኝ በማመኑ ለመታገል የፖለቲካ ድርጅቶችና የካድሬዎች መሪነት አላስፈለገውም። እስር ቤቶች ሞልተው መፍሰስ ጀምረዋል። ፌደራሎችና አጋዚዎች የልብ ልብ ተሰምቷቸው ሰው የሚግድሉበትና የሚያሰቃዩበት ቀን ወደ ማብቃቱ ነው። ህዝቡ ይፈራ ነበር። አሁን የሚፈሩት የስርዓቱ አቀንቃኞችና ደጋፊዎቻቸው ሆነዋል።
ወያኔ የትግራይ ህዝብም ጠላት ነው
የተወሰኑ የትግራይ ልጆች ተሰባስበው የመሰረቱት የህወሃት ዋና አላማ የትግራይን ህዝብ ከአማራ ብሄር ነፃ ማውጣትና የትግራይ ሪፐብሊክን መመስረት እንደነበር ከራሳቸው ከህወሃቶች ጭምር ሲነገረን የኖረ ስለሆነ ሁሉም ያውቀዋል። ከሚናገሩትና ከሚጽፉት  በላይ ግን የህወሃቶችን ድርጊት ላለፉት አርባ ዓመታት የተከታተለ ዓላማቸውን አጥርቶ ማወቅ ይችላል። ይህ ለትግራይ ህዝብ ጥቅም ቆሜአለሁ የሚለው ድርጅት እውነት ለትግራይ ህዝብ ቆሟል? ድርጊቱን እንመርምር።
ህወሃት ገና ጫካ ከመግባቱ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ሃሳባቸውን የገለፁትንና ድርጅቱ ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይዞ እንዲታገል የጠየቁትን ጓደኞቻቸውን የትግራይ ልጆች በግፍ ገድለዋል። አባረዋልም። መሃሪ ዳዊት ከአዲግራት፣ እቁበእግዚዕ በየነ ከአክሱም፣ አስበሃ ዳኘው ከአድዋ፣ መንገሻ በላይ ከሽሬ፣ ሙሉጌታ አብርሃም ከእንደርታ፣ አልማዝ አስፋው ከመቀሌ፣ ኪዳኔ ግርማ ከመቀሌ፣ ተክሉ ሃዋዝ ከአድዋ ምን እንደተፈጸመባቸው ህወሃቶች ደፍረው ይናገራሉ?
በ1977 ዓ ም በነበረው ድርቅ ለትግራይ ህዝብ የተላከን እርዳታ ዘጠና ከመቶውን መሳርያ መግዣና የአመራሮች የውጭ ባንክ አካውንት ማበልፀያ በማድረግ በርካታ የትግራይ ገበሬዎች በርሃብ ተቀጥፈዋል።
አገራቸውን ከጠላት ተከላክለው ያዳኗትን የዮሃንስን፣ የአሉላንና የቀሪውን ጀግና የትግራይ ህዝብ ታሪክ ተፃርሮ የአገርን አንድነት አደጋ ላይ ጥሏል። ዮሃንስ የሞቱለት ድንበር ሳይቀር ለሱዳኖች ለመስጠት በመስማማት ላይ ነው።
ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ጥቂት የትግራይ ልጆችን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ለይቶ በመጥቀም ምስኪኑ፣ ብዙሃኑና ድሃው የትግራይ ህዝብ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ እንደልዩ ተጠቃሚና የስርዓቱ ደጋፊ ሆኖ በጥርጣሬ ዐይን እንዲታይ ሆን ብሎም እንዲቃቃር ሌት ተቀን እየሰራ ነው።
ወፋፍራሞቹ የወያኔ ድመቶች የሃይል ሚዛኑ ዘንበል ካለ እንደመንግስቱ ኃይለማርያም የያዙትን ይዘው ለመፈርጠጥ ቋፍ ላይ ናቸው። ግን የትም አያመልጡም። የፈሰሰው ደምና የተዘረፈው የአገር ሃብት የትየለሌ ስለሆነ በየሄዱበት ታንቀው ይጠየቁበታል። ወየው በስህተትም ይሁን ለጥቅም ብለው ወያኔን ለሚደግፉ አድርባዮች! ታዝዘን ነው የሚለው ምክንያት የደርግ ባለስልጣናትን በእስር ከመበስበስ አላዳናቸውምና።
ወየው በስሙ ለተነገደበትና ከወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን እንዲቆራረጥ እየተገፋ ላለው የትግራይ ህዝብ!! ሻዕብያና ወያኔ አቅል ባጡበት ፍቅራቸውና ኋላም በጠባቸው ጊዜ በሰሩት ስህተት ምስኪኑ የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ መለያየት ብቻ ሳይሆን እስከአሁን ለአለበት ዳፋ እንደተዳረገው ወያኔዎች ለትግራይ ህዝብ ያዘጋጁት ይህንኑ ዕድል ነው።
ትዝብት ይሁን ድምፃቸውን ላጠፉት የትግራይ ምሁራን። አንድም የሚደርሳቸው የዘረፋ ጥፍጣፊ፣ አንድም አደባባይ ያላወጡት ዘረኝነት ተፈታትኗቸው አንደበታቸው ተዘግቷል። ከገብረመድህን አርዓያ፣ ከአብርሃ ደስታና ከአስገደ ግብረስላሴ ውጭ ሌሎች የት ገቡ? ወያኔ ኢትዮጵያን በተለይም የትግራይን ህዝብ ህልውና ሊያጠፋ ሉአላዊነቷና ዜጎቿ ላይ ሲነሳ፣ በህዝብ ደም እጁን ሲታጠብ የት ነበርን ሊሉ ነው? አፋቸውን በእጃቸው ከድነው ሲስቁ እየታዩኮ ነው!
ወያኔ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው!
  • ኢትዮጵያን ያለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ያለወደብ ያስቀረ፤
  • ከሰማንያ ሺህ በላይ ዜጎቿን በማይረባ ጦርነት ማግዶ ካስጨረሰም በኋላ ያለመፍትሄ ያስቀመጠ፤
  • ጋምቤላ፣ አሰቦት፣ አርባጉጉ፣ ወተር፣ ጎንደር አደባባይ ኢየሱስ፣ አሶሳ፣ አረካ ወላይታ፣ አዋሳ፣ አፋር፣ አዲስ አበባና አሁን ደግሞ በመላ ኦሮምያና ጎንደር ኢትዮጵያውያንን የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈ፤
  • አባቶቻችን በመስዋዕትነት ዳር ድንበሯን ያስጠበቋትን አገር ለሱዳን ለመስጠት ያልሳሳ፤
  • ድሃ ገበሬን እያፈናቀለ ለህንድ፣ ለአረብ፣ ለቻይና መሬት በነጻ ያደለ፤
  • የአገሪቱን ሃብት ጠቅልሎ በወያኔ ካምፓኒ ኤፈርት ቁጥጥር ስር ያዋለ፤
  • የአገሪቱን ወጣት ሴቶችን ለአረብ፣ ወታደሮችን ለአሜሪካ ቅጥረኝነት፣ ህፃናትን ለምዕራቡ ገበያ አውጥቶ የቸበቸበ፤
  • አገሪቱን ፍትህ አልባ አድርጎ ዜጎችን ሙሉ በሙሉ ወደ እስረኝነት የለወጠ፤
  • ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍሎ ለህልውናችን በአንድነት እንዳንቆም አድርጎ ለአለንበት ውድቀት የዳረገን፤
  • ሚሊዮኖች ተርበው “የተራበ የለም” የሚልና ሲጋለጥ ደግሞ በርሃቡ ላይ እንዳይተኮር ጠንክሮ የሚሠራ ጨካኝና ዘረኛ ቡድን መሆኑን ያልተሀነዘበ ኢትዮጵያዊ ካለ ጤነኛ አይደለም። የህወሃት ወፍራም ድመቶች አፋቸውም፣ እጃቸውም ደም በደም መሆኑን ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም አይቷል። መደበቂያ የላቸውም።
ሌሎችን በማጥፋት ራሱን ያገዘፈው ወያኔ ከሁሉም አቅጣጫ በህዝቡ በሚሰነዘር ጥቃት በመድማት ላይ ያለ የቆሰለ አውሬ ሆኗል። ደም አስክሮት እየተወራጨ ነው። መድማቱን የሚያቆምበት ፋታ አጥቷል። አለኝታ ያጣው ህዝብ በቃኝ ብሎ በመነሳት የሚወረውራት እያንዳንዷጥቃት የወያኔን ሞት እያፋጠነችው ነው። ከተመልካችነትና ከአሽሟጣጭነት ወጥቶ የህዝቡን ትግል መቀላቀል አሁን ነው። ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ስለሆነ የመውደቁ ድል የጋራ እንዲሆን ትግሉም የጋራ ሊሆን ይገባል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ!                                                                                                                                                                               by ሳተናው

No comments:

Post a Comment