Wednesday, 24 February 2016

ህወሃት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች እንዲታሰሩ ወሰነ ህወሃት የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች እንዲታሰሩ ወሰነ

ልኡል አለም
የወልቃይት ጠገዴ ማንነት አጣሪ ኮሚቴዎች ከያሉበት ተለቅመዉ እንዲታሰሩ የወያኔ ብሔራዊ መረጃን ተንተርሶ የትግራዩ ነጻ አዉጭ ቡድን ስራ አስፈጻሚዎች በትናንትናዉ እለት ወስነዋል።
የወልቃይት ህዝብ ሙሉ ለሙሉ በትግሬነቱ አምኖ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥትዋል! በማለት ሪፖርት ለብሔራዊ መረጃ ያቀረበዉ የትግራዩ መስተዳድር ደህንነት ክፍል… የህዝቦችን የእርስ በእርስ መጨራረስ በሚፈልጉ የአርበኞች ግንቦት 7 እና መሰል የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ሴራ ምክንያት የተሰማሩ ቀንደኛ ተቀናቃኞች! ይላቸዋል… የወልቃይት ጠገዴን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች።
ወልቃይት ጠገዼ ላይ የሰፈሩ ወራሪዎቹ የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ደጋፊዎች እንዲሁም ከትግራይ ክልል ይተወሰዱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ወልቃይቶች ትግሬዎች ነን ብለዋልና ወልቃይት አማራ ነዉ በሚል የሚንቀሳቀስ ማንኛዉም ሐይል ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የመረጃ ዉሳኔዉ ተላልፏል ።
በመላዉ ሐገሪቱ ላይ በተለይም በኦሮሚያ የተነሳዉን ህዝባዊ እንቢተኝነት ምክንያት ባደረገ መልኩ በተለያዩ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ወደ ቅርብ ከተማ ክልል እንዲሸጋገሩ የተላለፈዉን ዉስጣዊ ትእዛዝ ተከትሎ አዲስ አበባና መሰል ከተማዎች የፈለሱ የትግሬ ተወላጆችን እያስተናገዱ ሲሆን በየእለቱ በልዩ ወጪ ወደ ሁለት መለስተኛ አዉሮፕላኖች እና የእረጅም እረቀት ተጓዥ ባሶች ተዘጋጅተዉ ወደ ትግራይ ሽሽቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል..ሆኖም መረጃዎቻችን እንደሚገልጹት ወልቃይትን ከትግራይ መስፋፋት አናጻር የመጠቅለሉ ሂደት ግድ ይላል በሚል የሞት ሽረቱ ተጀምሯል!!
በመላዉ ኢትዮጵያ የምትገኙ ወገኖቻችን በሙሉ በሐገራችን ላይ የትግራይ ነጻ አዉጭ የተባለ ወራሪ ሐይል እንዳሻዉ እየገደለና እየዘረፈ መሬትህን እየነጠቀ እየወሰደና ለለሎች ሐገሮች እየሸጠ ክብርህን እንዳሻዉ እየዋረደ ሊቀጠቅጥህ የተሰየመዉን ጠላትህን ህወሃት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተባብረህ ታንበረክከዉ ዘንድ ጊዜዉ አሁን ነዉ!!
ወርደት ወይም ነጻነት ! !
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !                                                                                                                            by: ecadforum

No comments:

Post a Comment