በወለጋ ቄለምና ባሎ ከተማ አመኑ ተረፈ፣ ገለታ ነገሮ፣ ቢሉሱማ አብዲሳ፣ ቶሌራ መርጋ እና አርገኔ የተባለች ሴት በሰቃቂ ሁኔታ በመግስት ሃይሎች ተገድለዋል።
በሃረርጌ በመቻራ በበደኖና፣ ጨለንቆ ሃሰን አብደላ፣ አሳድ ኢብራሂም እና ሮባ ማሞ የተባሉ ወጣቶች በጥይት ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።
በሃረርጌ በመቻራ በበደኖና፣ ጨለንቆ ሃሰን አብደላ፣ አሳድ ኢብራሂም እና ሮባ ማሞ የተባሉ ወጣቶች በጥይት ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።
በመቻራ ለተቃውሞ የወጡ ነዋሪዎች ደረቱ ላይ በጥይት ተመትቶ የተገደለ ሌላ ወጣት አስከሬን ተሸክመው ጎዳና ላይ ሲወጡ ታይተዋል።
በዚሁ ከተማ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ ከ20 በላይ ሰዎች ወደገለምሶ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ታውቋል።
በዚሁ ከተማ በጥይት ተመትተው የቆሰሉ ከ20 በላይ ሰዎች ወደገለምሶ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ታውቋል።
ተቃውሞ ከተነሳበት ህዳር 1, 2008 ጀምሮ ተቃውሞው የጸረ-ሰላም ሃይሎች ነው ከዚያም የመልካም አስተዳደር ቸግር ያመጣው ነው ሲል የተለያዩ መግለጫዎችን ያወጣው የመንግስት፣ በአርሲ-ሸሸማኔ የነበረውን ተቃውሞ ተከትሎ ጉዳዩ የጸረ-ሰላም ሃይሎችና አክራሪዎች ነው በማለት ንብረቶችን መውደማቸውን ገልጿል።ይሁን እንጂ የመከላከያ ሰራዊትና ፊዴራል ፖሊስ በወሰዱት የሃይል እርምጃ፣ ስለሞቱት ዜጎች ቁጥር እስካሁን አልተገለጸም።
ባለፉት 3 ወራት በተካሄደው ተቃውሞ ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ፣ ቁጥሩ በውል ያልተገመቱ ሰዎች የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ከ 5000 በላይ ዜጎች ለእስር ተዳርገዋል
ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008)
No comments:
Post a Comment