Friday, 12 February 2016

ታማኝ ካድሬነት – የህወሓት ኣባላት ከህዝባቸውና ሃገራቸው ይልቅ ለድርጅታቸው ያላቸው ታማኝነት ይበልጥባቸዋል – አንዶም ገብረስላሴ

ህወሓትና ምርጫ ቦርድ የኣንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች መሆናቸው ይታወቃል። ከዚህ ጋር የተያያዘ በሑመራ ያጋጠመን ኣንድ ታማኝ የህወሓት ካድሬና የምርጫ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ትንሽ ላካፍላቹ።
በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ራውያን ቀበሌ ፅህፈት ቤት ከፍተን ታፔላና ባንዴራ ስንተክል ተገኝተን ” ከ5 በላይ ሰዎች ሁናቹ ተሰብስባቹ ስለተገኛቹ መታሰር ኣለባቹ”12646943_984252494999740_957581530124139659_nብለው ለ23 ሰዓታት ኣስረው ሲለቁን ጉዳዩ ለወረዳው ሃላፊዎች ለማስረዳት ወደ ወረዳው መስተዳድር ፅህፈት ቤት ስንሄድ ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ኣቶ ጌታቸው በየነ የሚባለው ሰውየ ኣስተናገደን።
ሰውየው የህወሓት ከፍተኛ ካድሬ ተብሎ የሰለጠነና የወረዳው ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሆኖ የተሾመ ነው።
ታድያ ይሄ ኣቶ ጌታቸው በየነ በምርጫ 2002ና በ2007 ዓ/ም የሑመራ ምርጫ ክልል ሃላፊ ሆኖ ያገለገለና ኣሁንም እየሰራ ያለው ታማኝ ካድሬ ነው። የምርጫው ውጤት 100% የሚያደርጉትም እነዚህ ታማኞች ናቸው።
ሰውየው ብንለው ብንለው ጉዳያችን በቀላሉ ሊረዳን ኣልቻለም ኣልያም ኣልፈለገም። እንደምንም ብሎ ለዞኖ ምርጫ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ስለህጉ ጠይቆ ማብራርያ ከተሰጠውና የህግ ክፍተት እንደሌለን ሲያውቅም ኣንገራግሮ ስህተቱ እንደሚያርሙ ገልፆልን ተለያየን።
እነዚ ታማኝ ካድሬዎች ለህዝቡና ለፓርቲዎች በገለልተኝነት ፍትሓዊ ኣገልግሎት ሊሰጡ ኣይፈልጉም ወይም ኣይችሉም።
ሰለማዊ ትግልና ምርጫ የሚባለው ከገዢው ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ ታዛቢዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚድያው በህወሓት ታማኝ ካድሬዎች የሚመሩ ኣድርጎ የይስሙላ መወዳደር ኣይደለም።
ኣቶ ጌታቸውና መሰሎቻቸው የህወሓት ታማኝ ካድሬዎች የሚመሩት ምርጫ ቦርድ “የሁለት ምክቶች ምክር ኣንታረድ ነው” እንደሚባለው ኣስቀድሞ የሚታወቅ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ በሰለማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ማምጣት የሚፈልግ ከሆነ እነዚህ ተቋማት ከኢህኣዴግ እጅ ፈልቅቆ ሊያወጣቸውና በገለልተኛ ሰዎች እንዲመሩ ማድረግ ይጠበቅበታል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።

                                                                                                                                                                                 #by_Zehabesha.com 

No comments:

Post a Comment